The Day Of The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Mighty Warrior Zephaniah 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ አዲስ መጽኃፍ እንጀምራለን ! ትልቅም አይደለም ፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያገኙት አስቸጋሪ ጊዜ አላቸው ፡፡ እነዚህ ትንንሽ መጽሐፍቶች ታናናሽ ነቢያት ተብለዉ ይጠራሉ ምክንያቱም በጣም አጭር ስለሆኑ ፡፡ መጠን/ብዛት በታላላቅ እና በታናናሽ ነቢያት መካከል ያለዉ ብቸኛዉ ልዩነት ነው ፡፡ በሶፎንያስ ዘመን ጊዜ መንግስቱ ተከፍሎ እንደ ነበር ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፤ ሶፎንያስ በደቡቡ መንግስት አገለገለ ትንቢትንም ተናገረ ፡፡
በእያንዳንዳቸዉ 12 ታናናሽ ነቢያት የትንቢቱ መጽኃፍ የፀኃፊዉን ስም ተሸክመዋል ፡፡ ስለ ሶፎንያስ ትንሽ ይታወቃል ፤ የስሙም ትርጉም “ እግዚአብሔር ይሸሽጋል “ ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ነቢዩ ራሱ መልዕክቱን በኢዮስያስ ዘመን (ከክርስቶስ ልደት 630-609) በፊት ጊዜ እንደፃፈው ፤ በመፅኃፉ ዉስጥ ያሉት ስነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ዝርዝሮች (ሶፎ 1፡ 4-6, 3፡ 1-7) ትንቢቱ ይሁዳ በጣዖት አምልኮ እየተመላለስ/እየኖረ በነበረ ጊዜ ከኢዮስያስ ተሀድሶ ቀድሞ የተቀመጠ እንደሚመስል “ ይናገራል ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል ኢዮስያስ መሰዊያዎቹን በማፈራረስ የሐሰተኛ ነቢያቱን አጥንቶች በማቃጠል የተቀረጹትን ጣዖቶች ሰባበራቸው (ከክርስቶስ ልደት 628 በፊት አካባቢ) ፡፡ ዋይርስቤ ይህ ብዙዎች ሶፎንያስ እንደ ኤርምያስ በተመሳሳይ ጊዜ ከክርስቶስ ልደት (635-625በፊት) አካባቢ ትንቢትን እንደተናረ እንዲያምኑ እንደሚመራቸዉ ያመለክታል ፡፡ በዚህን ስፍራ በጊዜዉ እስራኤላዊያን ተስፋ እንዳልነበራቸዉ እንድናዉቅ ጊዜያቱ አስፈላጊዎች ናቸው ፡፡
በዚህን ጊዜ ፖለቲካሊይ የአለም ኃያልነት ከአሶር ወደ ባቢሎን ሄዶ ነበር ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ ይሁዳ አሶር ኃይሉን ማጣት በመጀመሩ እና ባቢሎን መጠንከር በመጀመሩ በአካባቢዉ ካለዉ የፖለቲካ ለዉጥ ተጠቅሟል ፤ በእርግጥ የባቢሎን ኃይለኛ ማስፈራራት በአሶር ላይ አሶርን በይሁዳ ላይ ያለዉን ይዞታ እንዲያጣ ምክንያት ሆነው “ በ50 አመታት ዉስጥም ለይሁዳ ለመጀመሪያ ጊዜ የነፃነትን ባህሪይን ያመጣላቸዋል ፤ በመንፈሳዊነት ደግሞ የሕዝቅያስ ልጅ የምናሴ ዘመን ከአስር አራት አመታት በላይ ተራዘመ የልጅ ልጁም አሞን ሁለት አመታቶችን ብቻ ቆዬ በክህደት እና በክፋት የተለዩ ነበሩ (2ነገስት 21, 2ዜና መዋዕል 33) “ ፡፡ ከኢዮስያስ ታሐድሶ በፊት ምድሪቱ በግፍ/በክፋት የታወቀች ነበረች ፤ የሕጉ መጽሐፍ ከተገኘም በኋላ ኢዮስያስ ተሐድሶዉን በመጀመር እንደ ገና ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዲያመልክ እና እንደፈልጉ መራቸው ፡፡
የሶፎንያስ መልዕክት ከኢዮስያስ ተሐድሶ በፊት ተስፋ በሌለ እና በክፉ ወቅት ጊዜ መጣ ፤ የሶፎንያስ መልዕክት በእዉነት ስለ እግዚአብሔር ቀን ያተኮረ ነው ፡፡ ለእስራኤላዊያን የመጨረሻዉ ቀን ቅርብ ነበር ፤ ፍርዳችሁ በባቢሎን ንጉስ በንጉስ ናቡከደነፆር እጅ እየመጣ ነበር (ከክርስቶስ ልደት 605-586 በፊት) ፡፡ ማክአርቱር የሶፎንያስ መልዕክት “ ከዳንኤል አስራ ሰባተኛዉ ሳምንት ፍርድ በሩቅ በይበልጥ በመብለጥ መፈፀምን እንደሚመስል (ሶፎ 1፡ 18, 3፡ 8) “ ይገልፃል ፡፡ መልዕክቱ አዎ ጨለማ ጊዜ እየመጣ ነዉ የሚል ነበር ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት እግዚአብሔርን ፈልጉ ፡፡ በሶፎንያስ ዉስጥ ኢየሱስን ያየንበት ሐረጋችን/ቃላችን ኃይለኛ ተዋጊ የሚል ነው ፡፡
ትምህርት
ሶፎንያስ (1፡ 1-6)፡ ሶፎንያስ ወደ ንጉስ ሕዝቅያስ በሚመልሱ ሁሉም መንገዶች የዘር ግንዱን ወደ ኋላ አራት ትዉልዶችን ሳለ ፡፡ ከነገስታት ዘር የመጣ ብቸኛዉ ነቢይ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ሶፎንያስ በምድር ሁሉ ላይ ፍርድ እንደሚሆን ፅፏል ፤ አለም ትጠፋለች (ቁጥር 2-3) ከዘፍጥረት ጎርፍ/የዉኃ ጥፋት ጋር ግልፅ ንጽጽር ነው (ዘፍ 6፡ 9, 7፡ 23) ፡፡ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻዉ ዘመን ድረስ እንደ ገና አለምን የሚያጠፋ ነገር እንደማይሆን ቃል እንደገባ እናስታውሳለን ፤ እግዚአብሔር በሰዉ ልጅ ሁሉ ላይ እስኪፈርድ ድረስ በምድር ላይ ህያዉ የሆኑ ነገሮችን ማስወገዱን ይቀጥላል ፡፡ በቁጥር አራት መጀመሪያ ላይ ሶፎንያስ ፍርድን በይሁዳ ላይ ተናገረ ፡፡ ዋይርስቤ ሶፎንያስ “ የእግዚአብሔርን ቀን ከአይሁዶች እና ከአሕዛብ ከሁለቱም ጋር እንዳገናኘዉ ይናገራል “ ፡፡
ሶፎንያስ (1፡ 7)፡ በቁጥር 7 ሶፎንያስ ስለ ይሁዳ የእግዚአብሔር መስዋዕት እንደሚሆን አወራ ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ የይሁዳ መስዋዕት ሲሆን የእግዚአብሔርን ፍርድ ለማድረስ እየመጣ የነበረዉ እንግዳ ደግሞ የባቢሎን ሰራዊት ነበር ፡፡ የእግዚአብሔር ቀን በራዕይ ላይ በዮሐንስ የተነገረዉን ከሰባት አመቱ በኋላ ያለዉን መከራ ያመለክታል ፡፡ እስራኤላዊያን ልክ ዛሬ እንደምናደርገው ስለ እግዚአብሔር ቀን ስዕል/ምስል አልነበራቸው ፡፡
ሶፎንያስ (1፡ 8-10)፡ “ የእንግዳ ልብስ የለበሱት ሁሉ “ የሚለዉ ንግግር በኃሰተኛ አማልክት እና በኃሰተኛ ነገሮች ላይ አትኩረዉ የነበሩትን ያመለክታል ፤ እንደማይኖሩ በማስመሰል መንገድ ዉሸጽን የለበሱ ነበሩ ፡፡
ሶፎንያስ (1፡ 11)፡ ዋይርስቤ “ የከተማዋን አቀማመጥ ለማወቁ ሶፎንያስ የኢየሩሳሌም ነዋሪ መሆን እንዳለበት “ ይናገራል ፡፡ ስለ ከተማዋ በተወሰኑ ዝርዝር ነገሮች ላይ ብቻ ሄዷል/አልፏል ፡፡ በሶፎንያስ የነጋዴዎች መጥቀስ ላይ ማክአርቱር “ ያልተገባን በማግኘት ኃብትን/ብልፅግናን ያደረጉ ነጋዴዎች የሚመጣዉ ፍርድን ጭንቀት ለመግለፅ ያሳዩ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡
ሶፎንያስ (1፡ 12)፡ ይህ በጣም የሚያስደንቅ አቋም ነው ፡፡ ለዚህ ዘመን “ ተረጋግቶ የተቀመጠን ሰው “ መግለጫ ትተገብሩ ከነበር ይህ ደስተኛ የሆነን አማኝ ያመለክታል ፡፡
ሶፎንያስ (1፡ 14-18)፡ ሶፎንያስ ለይሁዳ የእግዚአብሔር ቀንን ገለፀ በተጨማሪም ደግሞ ከሰባት አመቱ መጨረሻ ላይ ታላቁንም መከራ ገለፀ ፡፡ የእግዚአብሔር ቀን ለእስራኤላዊያን እየመጣላቸዉ ነበር ነገር ግን ለእኛም የሚመጣ ነው ፡፡ ማክጊ የእግዚአብሔርን ቀን “ እንደ ፍርኃት ቀን “ ይገልፀዋል ፡፡ ለመደበቅ ታላቅ ጊዜ እንደሚመስል እንድንረሳዉ አልፈልግም ፤ የትም ስፍራ ብትሆኑ ማምለጥ ወይም መደበቅ አትችሉም ፡፡ ለይሁዳ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰዉም የሚያስፈራዉን መጨረሻ ያያል/ይቀምሳል ፡፡
ሶፎንያስ 2፡ ሶፎንያስ እስራኤላዊያንን ከዚህ መከራ እንዲተርፉ/እንዲያመልጡ እንዲጸልዩ አሳሰባቸው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ፣ ፅድቅን እንዲፈልጉ እና ትህትናን እንዲፈልጉ አበረታታቸዉ ፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ይደብቃችኋል ፡፡ እኛ ሁላችንም ከእግዚአብሔር የመከራ ቀን የእግዚአብሔር ጥበቃ ያስፈልገናል ፤ በምድር ላይ ሲዖል ይሆናል ፡፡ ሶፎንያስ በይሁዳ ላይ ፍርድን ከመናገር ወደ መላዉ ሕዝብ ላይ ዞረ ፤ ፍርድም በኢትዮጲያ እና ከዚያም በአሶር ላይ ይመጣል ፡፡ የይሁዳ ሕብም እግዚአብሔር መልካምም ክፉም እንደማያደርግ በማመን የተደላደለ/የተመቸዉ ሆኖ ነበር ፤ እንደዚያ አይነት በራስ ደስተኛ የመሆን ቁመናን በምናይ ጊዜ እግዚአብሔር ጥፋትን ሲያመጣ እናያለን ፡፡ በራሳችን አቋም/ሁኔታ የተደሰትን መሆን የለብንም ፤ በማንኛዉም ጊዜ ለኢየሱስ ተመልሶ መምጣት የተዘጋጀን መሆን ያስፈልገናል ፡፡
ሶፎንያስ 3፡ ሶፎንያስ ኢየሩሳሌምን ስለሚገባት ስለሚመጣዉ ፍርድ ተናገረ ፡፡ በአለም ላይ ተመሳሳይ ፍርድ የሚገባቸዉ ብዙ ከተሞችን ማየት ትችላላችሁ ፡፡ እንደ ገና የአርማጌድዮን አስተሳሰብን እናያለን ፤ ማክጊ “ በክርስቶስ ወደ ምድር መመለስ የሚያበቃዉ ይህ አርማጌድዮን ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡ ለሕዝቡ የእግዚአብሔር ፍቅር ኃያል/ታላቅ ነው፣ ለሕዝቡ ቅንዓቱ ታላቅ ነው እንዲሁም በጦርነት በፊታቸዉ በሚሄድባቸዉ ሌሎች ሕዝቦች ላይ ቁጣዉ እጅግ ታላቅ ነው ፡፡
መደምደሚያ
የአርማጌድዮን ጦርነት ሁሉንም ሌሎች ሕዝቦች የሚያጠፋበት ጊዜ ነው ፡፡ በሶፎንያስ ኢየሱስን የሚያመለክተዉ ሐረግ/ቃል ኃይለኛ ተዋጊ ነው ፤ ሕዝቡን ለማዳን ተመልሶ የሚመጣዉ ኢየሱስ ነው ፤ ስለ እኛ ይዋጋል እንዲሁም ደግሞ ይወደናል ፡፡
9 McGee.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1036.
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Isaiah–Malachi (Colorado Spring: David C. Cook, 2002), p. 425.
MacArthur, p. 1036.
MacArthur, p. 1036-1037.
Wiersbe, p. 42.
Wiersbe, p. 427.
MacArthur, p. 1038.
J. Vernon McGee, “Notes for Zephaniah”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/zephaniah/zephaniah-outline.cfm.
ጥያቄዎች
-
በሶፎ (1፡ 1) ሰፎንያስ የዘር ሀረጉን በዚህ መልኩ በዝርዝር ለምን አስቀመጠ ?
-
በሶፎ (1፡ 14-18) ሶፎንያስ ያለፈዉን ወይስ የወደፊቱን እየጠቀሰ ነበር ?
-
ከሶፎ (1፡ 10) “ የአሳዉ በር “ እና “ ሁለተኛዉ ክፍል “ ምን እንደ ነበሩ ምን ታስባላችሁ ?
-
እንደ ሶፎንያስ እና ሌሎች የብሉይ ኪዳን ነቢያት አገላለፅ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ማንኛዉንም ነገር ከሚያመጡ የራሱን ሕዝብ በተለያዬ መንገድ እንዴት አድርጎ ይቀጣል ? ይህ ሌላ ሰው ልጆቻችንን ሊቀጣቸዉ፣ ሊጎዳቸዉ ወይም ሊያጠቃቸዉ በሚሞክር ጊዜ እንዴት እንደሚሰማን በምናወዳድር ጊዜ ልጆቻችንን የምንቀጣበት መንገድ እንዴት ይመስላል ?
-
የእስራኤል ሕዝብ ከነቢያት መስጠንቀቂያዎችን ከሰሙ በኋላ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን እንደ ማይቀበሉ ምን ታስባላችሁ (ሶፎ 3፡ 7) ? ዛሬስ እኛ እንዴት እንመስላለን ?
-
በሶፎንያስ (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Zephaniah 3:16–17
“On that day it will be said to Jerusalem: ‘Do not fear; Zion, do not let your hands grow weak. Yahweh your God is among you, a warrior who saves. He will rejoice over you with gladness. He will bring you quietness with His love. He will delight in you with shouts of joy.’”
ነቢዩ ሰፎንያስ ለኢየሩሳሌም፣ ለይሁዳ፣ ለአህዛብ ደግሞም እስከ ምድር ዳርቻ ሁሉ ፍርድ እንደሚመጣ ተናገረ፡፡ ሶፈንያስ የእግዚአብሔር ቀን፣ የመጨረሻው ቀን እንደቀረበ አወጀ፡፡ ሰፎንያስ ከዚህ ጋር አያይዞም እግዚአብሔር በሚያስደንቅ ጸጋው ቅሬታዎችን እንደሚሰበስብና ደግሞም በእነዚህ ክፋትን በሚሹት ላይ ቁጣውን እንደሚገልጥ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፣ ያድንም ዘንድ እርሱ ብርቱ ነው፡፡ እግዚአብሔርም በህዝቡ ደስ ይለዋል በእልልታቸውም ድምጽ ሀሴት ያደርጋል፡፡ እርሱ በመካከላቸውም አለ ከክፋትም ያድናቸዋል፡፡
ጓደኞቼ እግዚአብሔር በጥፋትና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሰላምን ይሰጣችኋል፡፡ እስኪ ራሳችሁን በሰልፍ ውስጥ እንዳላችሁ አስበ…… እና ከዚያ ወደ አድማሱ ስትመለከቱ፣ በሌሎች መካከል የቆመን ተዋጊ ታያላችሁ እናም ይህ ተዋጊ በአሸናፊነት ወደ እናንተ ይገሰግሳል፡፡ እናም ይህን ተዋጊ ስታዩት እናንተን ለመታደግ እየመጣ እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ እርሱም እናንተ ጋር ሲደርስ ከእናንተ ጋር በደስታ ሀሴትን ያደርጋል፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ሰላም እረፍት ይጨነቃል፣ ያድናችኋልም፡፡ ይህ ያያችሁት ምስል የሰማዩ አባታችሁ ፍቅር ምሳሌ ነው፡፡ በውጊያው በሰልፉ ውስጥ ሆናችሁ ተመልከቱ፡፡ ተመልከቱና እግዚአብሔርን ብቻ ፈልጉ፡፡ እርሱ በመካከላችሁ አለ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋል ያድናችኋልም፡፡ እርሱ በእልልታ በእናንተ ደስ ይለዋል፡፡ በደስታም በእናንተ ሀሴት ያደርጋል፡፡ እንዳትፈሩ፡፡ ጌታ ቅርብ ነው፡፡
“በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።”
- ሰፎንያስ 3፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 7:21 — “አምላክህ እግዚአብሔር፥ ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ፥ በመካከልህ ነውና ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጥ።”
መዝሙር 9:10 — “ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።”
ሶፎንያስ 2:3 — “እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፤ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።