Minor Prophets Habakkuk

Habakkuk's Prophecy

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Salvation Habakkuk 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 701 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ሳምንንት የታናናሽ ነቢያት ጥናታችንን ብቻ ሳይሆን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ የብሉይ ኪዳን ጥናት ሕይወት ቀያሪ ነው ፡፡ በታናናሽ ነቢያት ዉስጥ እስካሁን ሆሴዕን፣ ኢዩኤል፣ አሞጽን፣ አብድዩን፣ ዮናስን፣ ሚክያስን እና ናሆምን አጥንተናል ፤ ስምንንተኛዉ ታናናሽ ነቢያት ዕንባቆም ነው ፡፡

የዕንባቆም መጽሐፍ በፀኃፊዉ የተሰየመ ሲሆን የስሙ ትርጓሜም “ የሚይዝ/የሚገናኝ “ ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በትንቢቱ መጨረሻ ላይ ምንም እንኳን ለሕዝቡ ስለ እግዚአብሔር እቅድ ግራ መጋባት ቢኖርም ይህ ስም ነቢዩ ከእግዚአብሔር ጋር ሲገናኝ ተገቢ እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ ስለ ነቢዩ በመጽኃፉ ዉስጥ ካሰጠዉ/ካስቀመጠው ነገር ዉጪ ምንም ነገር አይታወቅም ፡፡ ምንም እንኳን መረጃዎች በጥቂቱ የተሰጡ ቢሆኑም አንዳንድ ምሁራን በወቅቱ ዕባቆብ በጣም የታወቀ ስለ ነበር ተጨማሪ መረጃ እንዳላስፈለገዉ ያመለክታሉ ፡፡ ዕንባቆም የኤርምያስ፣ የሕዝቅኤል፣ የዳንኤል እና የሶፎንያስ ዘመን ሰዉ ሲሆን መልዕክቱም ለደቡቡ መንግስት ለይሁዳ ነበር ፡፡ ዕን (1፡ 6) ከክርስቶስ ልደት በፊት ከሰባተኛዉ ክፍለ ዘመን በኋላ የተፃፈበትን ቀን የሚያመለክት ከለዳዉያንን (ባቢሎናዊያንን) ይጠቅሳቸዋል ፡፡ ማክአርቱር ይህ “ በአጭሩ ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት ናቡከደነጾር በነነዌ ላይ ወታደራዊ ዘመቻን ከመጀመሩ በፊት “ እና “ የዕንባቆም መራር ኃዘን (ዕን 1፡ 2-4) ምናልባትም ከክርስቶስ ልደት 609 በፊት ከንጉስ ኢዮስያስ ሞት በኋል እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የነበረዉ የንጉሱ ታሀድሶ (2 ነገስት 23) በተተኪዉ ኢዩአቄም በፍጥነት ተቀይሮ በነበረበት ጊዜ ኤር( 22፡ 13-19) በአጭሩ ጊዜዉን መሆኑን እንደሚያንፀባርቅ “ ይገልፃል ፡፡ ስለዚህም ዕንባቆም ይህን የአለም ኃያልነት ለዉጥ ከአሶር ወደ ባቢሎን ሸፍኗል ፡፡

ዕንባቆም በአሶር ግዛት ማብቂያ እና በባቢሎን አገዛዝ መጀመሪያ ላይ ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ እነዚህ እና ሌሎች የአለም ኃያላን ሁሉም በእግዚአብሔር መንግስት ፊት ይወድቃሉ ፡፡ የባቢሎናዊያን ግዛት በንጉስ ናቦፖላስር እና በልጁም በናቡከደነፆር ስር አሶርን በማጥቃት ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት ዋና ከተማቸዉን ነነዌ በማጥፋት በመጨረሻም ከክርስቶስ ልደት 605 በፊት በካርሜሽ አሸነፏቸው ፡፡ የግብፃዉያን ንጉስ ኒኮአሶርን ለመርዳት በይሁዳ በኩል በመጓዝ በንጉስ ኢዮስያስ እና በንጉሱ ሰራዊት ላይ መጣ ፤ በጦርነቱም ንጉስ ኢዮስያስ ተገደለ ፡፡ ንጉስ ኢዮስያስ በቤተ መቅደሱ የሕጉ የተልዕኮ መጽሐፍ የተገኘበትን ተሀድሶ መርቶ ነበር ፤ በሕጉ ኢዮስያስ ከክርስቶስ ልደት 622 በፊት ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸዉን ኪዳን እንዲያድሱ መራቸው ፡፡ ይሁን እንጂ በልጁ አስተዳደር ስር ይሁዳ ከእግዚአብሔር ርቆ በመሄድ ወደ ጣዖት አምልኮ እና አማልዕክት ወደ ማምለክ ተመለሱ ፡፡

ቃላችን ለዕንባቆም ኢየሱስን ልናይበት የምንችለዉ የሚመጣዉ ድነት የሚል ነው ፡፡ ይህ በዕን (2፡ 3) እና (3፡ 18) ሊታይ ይችላል ፤ (ዕብ 10፡ 37) ፡፡

  • ዕን (2፡ 3)፡ “ ራእዩ ገና እስከ ተወሰነዉ ጊዜ ነው ወደ ፍጻሜዉም ይቸኩላል እርሱም አይዋሽም ፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሰው ፤ እርሱ አይዘገይም “ ፡፡
  • ዕን (3፡ 18)፡ “ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል ፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሴት አደርጋለሁ “ ፡፡

ትምህርት

ዕንባቆም (1፡ 1-17)፡ ዕንባቆም ስለሚመጣው የእግዚአብሔርን ራዕይ አይቶ እንደ ነበር(ቁጥር 1) እና ወደ ፀሎቱ እግዚአብሔር ለምን እያዳመጣ እንዳልነበር እንደጠየቀ ገለፀ (ቁጥር 1-4) ፡፡ እግዚአብሔር ዕንባቆምን በአለም ላይ በሚሆነዉ ነገር በመጨረሻ እንደሚደነቅ መለሰለት (ቁጥር 5-8) ፡፡ እግዚአብሔር የራሱን ሕዝቡን በኃይል ለመዉሰድ ባቢሎናዊያንን እያስነሳ ነበር (ቁጥር 9 -11) ፡፡ ከዚያም ዕንባቆም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ (ቁጥር 12-17) ፤ ዕንባቆም ባቢሎናዊያን አይሁዳዊያንን ወደ መረባቸዉ በመሳብም በጣም ክፉዎች እንደ ነበሩ ተናገረ ፡፡

ዕንባቆም (2፡ 1-5)፡ ዕንባቆም ከእግዚአብሔር እስኪሰማ ድረስ በመጠበቂያዉ ላይ እንደሚቆም ተናገረ (ቁጥር 1) ፤ እግዚአብሔር በቁጥር (2-5) በመመለስ ዕንባቆምን ሁሉም ማየት እንዲችሉት ምላሹን እንዲጽፍ ነገረው ፡፡ ማክአርቱር “ ዕንባቆም ራዕዩን ለመጪዉ ትዉልድ ስለሚመዘግበው የሚያነበዉ ሁሉም የመፈፀሙን እርግጠኝነት እንደሚያዉቁ “ ፅፏል ፡፡ ይህ ስለ መጨረሻዉ ዘመን የሚመሰክር ራዕይ ነበር (ቁጥር 3) ፤ በእግዚአብሔር ጊዜ ይሆናል (ቁጥር 3) ፡፡ በቁጥር 4 እግዚአብሔር ባቢሎንን በጻድቁ የምትያዝ ያለምንም ኃቀኝነት የተወጠረ አመለካከት እንዳላት ገለፃት (ሮሜ 1፡ 17, ገላ 3፡ 11, ዕብ 10፡ 37-38) ፡፡ ከአለም ሳንወጣ ልክ እንደ ፃድቅ እንኖራለን ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ትዕቢተኛ ሰው በፍፁም አይረካም ሁልጊዜም ለራሱ ብዙ ነገርን ይፈልጋል (ቁጥር 5) ፡፡

ዕንባቆም (2፡ 6-20)፡ በቁጥር 6 እግዚአብሔር ትዕቢተኛ ሰዉ የሚገጥመዉን አምስት ኃዘኖችን አሳይቷል፡

መጀመሪያ፡- በቋሚነት የእርሱ የማያሆንን ታላቅ የሆነ ኃብት/ብልፅግና የሚኖረዉ ትዕቢተኛ ያዝናል ፡፡ ይህ የሌሎች የሆነን ነገር በመዉሰድም እንኳን በሌሎች ሕዝቦች ላይ የባቢሎንን የጉልበተኝነትን መልክ ይቀጥላል ፡፡ ቁጥር 7 እነዚህን አንድ ቀን በባቢሎን ላይ የሚሰበሰቡ የባቢሎን “እንደ ፈጣሪ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ባቢሎን ይዛቸዉ በነበረቻቸዉ ሁሉም ሕዝቦች ትወድቃለች (ቁጥር 8) ፡፡

ሁለተኛ፡- ኃብቱ እንደሚያድነዉ የሚያስብ ግፈኛ/ከኃዲ ሰዉ ያዝናል (ቁጥር 9) ፡፡ አለመታመኑ በግንቡ ዉስጥ በድንጋዩ እና በዉቅሩ ዉስጥ በአዉራጁ ይጮኻል (ቁጥር 10-11) ፡፡

ሰዎስተኛ፡- በደም ከተማን ለሚገነቡ ጥረታቸዉም ምንም ነገር የማያመጣዉ ያዝናሉ (ቁጥር 12-14) ፡፡ የሺዉ አመት መንግስት ብቻ ወደ አለም የእግዚአብሔርን ክብር መልሶ ያመጣዋል ፡፡

አራተኛ፡- በባልንጀራዉ ላይ ጥቅምን መዉሰድ እንዲችል ባልንጀራዉን የሚያሰክር ያዝናል (ቁጥር 15-17)፡፡

አምስተኛ፡- ከእንጨት ወይም ከብረት ምንም ኃይል የሌላቸዉን እና መናገር የማይችሉትን የሚቀርፅ/የሚሰራ ያዝበናል (ቁጥር 18-19) ፡፡

ቁጥር 20 “ እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ ፤ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡ እዚህ ጋር “ ዝም “ የሚለዉን ቃል ጥቅም ማክአርቱር፡ “ ከጣኦታት፣ ሕይወት ካለዉ ነገር ዝምታ በተቃራኒ የአለም ሉዓላዊዉ ገዢ ምድር ሁሉ በእርሱ ፊት ፀጥ እንድትል እንደሚጠራቸው ፤ ማንም ከእርሱ ዉጪ እንደሆነ ማረጋገጥ እንደማይችል፣ ምድር ሁሉ በተዋረደ መታዘዝ እንደሚያመልኩት (መዝ 46፡ 20, ኢሳ 53፡ 15) “ ይገልፃል ፡፡

ዕንባቆም (3፡ 2-16)፡ በምዕራፍ 3 ዕንባቆም ሌላ ፀሎትን አቀረበ ፡፡ በዚህን ጊዜ ስራዉን እንዲያስብ እግዚአብሔርን ጠየቀው (ቁጥር 2) ፤ ዕንባቆም የእግዚአብሔርን ዉበት በምስጋናዉ ሰማይን እና ምድርን ሁሉ እንደ ሞላ ገለፀ ፤ ተራሮችም እንኳን በእርሱ ፊት እንደሚንቀጠቀጡ እና ፀኃይ እና ጨረቃም አሁንም በፊቱ ይቆማሉ (ቁጥር 3-15) ፡፡ ዕንባቆም በምስጋና በወረሯቸው ላይ “ የሚያስጨንቅ ቀን በእነርሱ ላይ እስኪመጣ ድረስ ዝም ብሎ እንደሚጠብቅ “ ፍቃደኝነቱን ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 16) ፡፡

መደምደሚያ

ያ ለሁላችንም ጥያቄን ይፈጥራል ፡፡ በዚህን እግዚአብሔርን በመጠበቂያ ጊዜ በትዕግስት እንጠብቃለን ? በእግዚአብሔር ላይ እየጠበቅን ጥያቄን እናነሳለን ? እግዚአብሔርስ እየመጣ እንደሆነ እናምናለን ? ዕንባቆም ምንም እንኳን ባቢሎናዊያን በመንገዳቸዉ ላይ ቢሆኑም እግዚአብሔር ይገለጥ እንደ ነበር አምኗል ፡፡ ዕንባቆም በዚህ የመታመን ንግግር በእነዚህ ቃላቶች አጠቃለለ (ዕን 3፡ 19)፡ “ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል “ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1028.

  2. MacArthur, p. 1028.

  3. MacArthur, p. 1028.

  4. MacArthur, p. 1028.

  5. MacArthur, p. 1031.

  6. MacArthur, p. 1031.

ጥያቄዎች

  1. ዕን (1፡ 3) “ በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ፣ ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ ? “ በማለት ጠየቀ ፤ በእግዚአብሔር ላይ ልክ እንደዚህ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በአለም ላይ ክፋትን እና ኃጢዓትን ለማስቆም ለምን ምንም ነገር እንደማያደርግ አስደንቋችሁ/አስገርሟችሁ ያውቃል ?
  2. ዕን (1፡ 5) “ እናንተ የምትንቁ ሆይ አንድ ቢተርክላችሁ ስንኳ የማታምኑትን ስራ በዘመናችሁ እሰራለሁና እዩ! ተመልከቱ ! ተደነቁ ! “ እዚህ ጋር ማን እያወራ ነበር ማንንስ እየጠቀሰ/እያመለከተ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
  3. እግዚአብሔር ዕንባቆምን በአይሁዶች ላይ ፍርድን ለማምጣት ከለዳዉያንን እያስነሳ እንደ ነበር ነገረው ፤ በመጽሃፍ ላይ እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ለመቅጣት ክፉ ሕዝቦችን የተጠቀመባቸዉን ስፍራዎች ጥቀሱ (መሳ 3፡ 1-4, ኤር 21፡ 12) ፤ በአሁኑ ጊዜም ይህን እንደሚያደርግ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ይህ የሆነበትን ሁኔታ ወይም ጊዜን ጥቀሱ ፡፡
  4. በአሁኑ ጊዜ እንደ ጣዖት ሊታይ የሚችል በራሳችን እጅ ያደረግነው ነገር ምንድን ነው ? ልትጥሉ የሚያስፈልጋችሁ ጣዖት እና በህይወታችሁ ደስተኛ የሚያደር የምትደገፉበት ነገር ምንድን ነው ? (ዕብ 2፡ 18)
  5. ዕን (3፡ 3) “ እግዚአብሔር ከቴማን ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል ፡፡ ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል ምስጋናዉም ምድርን ሞልቶአል “ በማለት ይናገራል ፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያደረገ ከሆነ እና ከምንም ነገር የማይመጣ ከሆነ ቴማን እና ፋራን ተራራ ምን ማለት እና ምንን እንደሚያመለክት ምን ታስባላችሁ ?
  6. ዕን (3፡ 13) “ ሕዝብህን ለመታደግ የቀባኸዉንም ለማዳን ወጣህ ፤ የኃጢዓተኛዉን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ ፤ መሰረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ “ በማለት ይናገራል ፤ ይህ ጥቅስ እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ?
  7. በዕንባቆም (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Habakkuk 3:18–19

“Yet I will triumph in Yahweh; I will rejoice in the God of my salvation! Yahweh my LORD is my strength; He makes my feet like those of a deer and enables me to walk on mountain heights!”

ነቢዩ ዕንባቆም በዓለም ስላለው በደልና ግፍ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰ፡፡ ዕንባቆም የእግዚአብሔርን መንገድ ለማወቅ ግራ በመጋባት መንታ መንገድ ላይ ቆሞ “አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም? ከዳተኞችን ለምን ትታገሳለህ ? ብሎ ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም ከመለሰለት በኋላ፣ ዕንባቆም ባይገባውም እንኳ እግዚአብሔርን ተስፋ አደረገ፡፡ በፈተና ውስጥ ሆኖ በእግዚአብሔር ታመነ፡፡ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ በእግዚአብሔር ተስፋ አደረገ፡፡ እንዴት ? በእምነት ዕንባቆም በደህንነቱ አምላክ አመነ፡፡

እንድያሳይህ የጠየከውን መንገድ እግዚአብሔር በማያሳይህ ጊዜ ምንድን ነው የምታደርገው ? በዙሪያህ ያለውን በደል ግፍ መረዳት ሲያቅትህ ምንድን ነው የምታደርገው ? አዎን ለእግዚአብሔር ጥያቄዎች አሉህ፡፡ ነገር ግን አሁን፣ ዛሬ ለደቂቃ ቆም በል፡፡ በእምነት እንድህ በል፡- “እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል!” በችግሩ ላይ ከማትኮር ይልቅ፣ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ አድርግ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰህ፣ አመስግነው፡፡ በግራ መጋባት ውስጥ ሆነህ እንኳ እርሱን ማመንን መደገፍን ምረጥ፡፡ ሁልጊዜ ደስይበልህ፡፡

“እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።”

  • ዕንባቆም 3፡18-19

ተጨማሪ ጥቅስ

ዕንባቆም 1:2–3 — “አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም።በደልንስ ስለ ምን አሳየኸኝ? ጠማምነትንስ ስለ ምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፤ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።”

ፊልጵስዩስ 4:6–7 — “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”

ዕብራውያን 4:16 — “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።”