The Burden Bearer
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Burden Bearer Nahum 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እንደ እኔ ከሆናችሁ ከዚህ በፊት በሚገባ ናሆምን አላጠናችሁም ፡፡ መጽሐፉ ለነነዌ ማስጠንቀቂያ በወሰደዉ በነቢዩ ናሆም የተሰየመ ነው ፡፡ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ መሄድ ስላልፈለገ ኮበለለ/ሸሸ ፤ ይሁን እንጂ በመጨረሻም ዮናስ በመታዘዝ የእግዚአብሔርን መልዕክት ባደረሰ ጊዜ ሕዝቡ ንስኃ በመግባት ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፡፡ ናሆም ከአመታት በፊት የእግዚአብሔር ፍርድ እየመጣ እንደ ነበርና ሊቀር እንደማይችል መልዕክትን አምጥቷል ፡፡ ናሆም የሚለዉ ስም “ ምቾት ወይም መጽናኛ “ ማለት ሲሆን የነህምያ አጭር ስያሜም ነበር ፡፡ ናሆ (1፡ 15) ምን ይመጣ እንደ ነበር ስዕልን ይሰጣል፡ “ አጥፊዉ ፈጽሞ ጠፍቶአልና ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍም “ ፡፡
ናሆም በዉልደት ወይም ደግሞ በአገልግሎት ኤልቆሻዊ ነበር ፡፡ ማክአርቱር የኤልቆሻዊ ትክክለኛ መገኛ እንደማይታወቅ ነገር ግን “ ሰበሰሜን ኢራቅ (ናሆም ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት ወደ አሶር በምርኮ የተወሰዱት ዘር ይሆናል) ቅፍርናሆም አልቋሽን ጨምሮ ሊገኝ እንደሚችል “ ይናገራል ፡፡ የመጽሐፉ ቀን የተረጋገጠ አይደለም ፡፡ ነነዌ እንደ አለም ኃያል ስትጠቀሰ ናሆም ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት ከመዉደቋ በፊት እና ምናልባትም ከክርስቶስ ልደት በ626 በፊት አሹባኒል ከመሞቱ በፊት ሕዝቡ ከእርሱ ሞት በኋላ ኃላቸዉን ስላጡ ይህን ጽፎታል ፡፡ ናሆም ስለ ኖአሞን ወይም ቴቤስ ከጠቀሰ ምናልባትም “ በምናሴ ዘመን ጊዜ በሰባተኞዉ ክፍለ ዘመን መካከል ላይ (ከክርስቶስ ልደት 695-642 በፊት የተፃፈ ሊሆን ይችላል “ ፡፡
ነነዌ ንስኃ ከገባች ከመቶ አመታት በኋላ “ ወደ ጣዖት አምልኮ፣ ወደ አመጽ እና ትዕቢት ተመለሰች ፤ በኃል ከፍታም ላይ ነበረች “ ፡፡ በጊዜው እግዚአብሔር ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት በአሶር/በነነዌ ላይ ዉድቀትን ለማምጣት በንጉስ ናቦፖላስር እና በልጁ በናቡከደነጾር ስር የባቢሎንን ሰራዉት ተጠቀመ ፡፡
በመሰረቱ የናሆም መጽሐፍ የዮናስ መጽሐፍ ተከታይ ነው ፤ በዚህ ዉስጥ ለወንጌላዊያን ትምህርት አለ ፡፡ ሕዝቡ በትክክል በዮናስ ስር ንስኃ ገብተዋል ነገር ግን የኋላዉ ትዉልድ ግን አልገባም ፡፡ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መምራት እንችላለን ነገር ግን በእግዚአብሔር እዉነተኛ ምልልስ እንዲኖራቸዉ ማድረግ አንችልም ፡፡
ማክአርቱር “ ነነዌ በማይበገር ዝነኛ ከተማዋ ተኩራርታ እንደ ነበር ቅጥሮቿ 100 ጫማ ከፍታ እንደሚደርሱ እና 150 ጫማ ጫማ ስፋት እና 60 ጫማ ጥልቀት የዉኃ ቦይ እንደ ነበራት “ ይገልፃል ፤ ይሁን እንጂ ናሆ (1፡ 8) በሚያጥለቀልቅ ጎር እንደምትጠፋና ይናገራል በተጨማሪም በናሆ (3፡ 11) መሰረት ከተማዋም ከእይታ የጠፋች ትሆናለች ፡፡ “ ከክርስቶስ ልደት 612 በፊት ከመጥፋቷ በፊት ከክርስቶስ ሞት 1842 በኋላ ስፍራዉ እንደ ገና ደግሞ አልተገኘም “ ፡፡
ትምህርት
ናሆም (1፡ 2-6)፡ ናሆም እግዚአብሔርን እንደ ቀናተኛ፣ ተበቃይ እና በቁጣዉ እንደሚባላ እሳት ገልፆታል ፡፡ በእግዚአብሔር ኃይል ዳመናት ከእግሩ ስር ናቸው ፤ ባህሩን መገሰፀ ይችላል ይደርቅማል ሁሉንም ወንዞች ደረቅ ማድረግ ይችላል ፡፡ የሊባኖስ ታላላቅ ዛፎች (አበባዎች) እንኳን ይጠወልጋሉ፣ ተራሮች ይናወጣሉ ኮረብቶችም በፊቱ ይቀልጣሉ (ቁጥር 2-6) ፡፡
ናሆም (1፡ 7-13)፡ በናሆም መጽሐፍ ዉስጥ ኢየሱስ እንዴት እንደታዬ ቃላችን ሸክም ተሸካሚ ሲሆን በቁጥር 7 ላይም የሚገኝ ነዉ -“ …በመከራ ቀንም ነሸሸጊያ ነው በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል “ (መዝ 46፡ 1, ኢሳ 33፡ 2-4, 37፡ 3-7, 29-38) ፡፡ እግዚአብሔር ነነዌን ያጠፋታል እንደ ገና አትነሳም (ቁጥር 8-10) ፡፡ በቁጥር 11 “ ክፉ መካሪዎቹ “ ምናልባትም ከክርስቶስ ልደት 701 በፊት ይሁዳን የወረረዉን እና ኢሳይያስ በተመሳሳይ ቋንቋ የተናገረለትን (ኢሳ 10፡ 7) ሰናክሬምን “ እንደ አሶርን ንጉስ በመለየት በመሪነት ሰይጣናዊ ተፅዕኖን አመለከቱ “ ፤ ታላቅ ኃይል እና ግዙፍ ሰራዊት ቢኖራቸዉም አሶር ይሁዳን አያስጨንቅም አያስርምም (ቁጥር 12-13) ፡፡ ኢየሱስ የሰዎችን ሸክም በመዉሰድ ይህን ተመሳሳይ መልክን አሳይቷል (ኢሳይያስ 61፣ ማቴ 11፡ 28-30, ሉቃ 4፡ 18, 2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ክርስቶስ ለእኛ የነበረዉን የኃጢዓትን ሸክም በመዉሰድ ተሸከመው ፡፡
ናሆም (1፡ 14-15)፡ ናሆም የአሚመጣዉን የእግዚአብሔርን ፍርድ ገልፆታል ፡፡ መጀመሪያ የንጉሱን እና የሕዝቡ ስም የሚቀርበት ማንም ሰዉ የሚቀር ሰዉ አይኖርም ፤ ሁለተኛ የተቀረጹ ጣዖቶች እና የአሶራዊያን አማልዕክት ምስሎች ይጠፋሉ ፤ ሰዎስተኛ ንጉሱ የሚሞት ይሆናል (ቁጥር 14) ፤ ይሁን እንጂ መልካም ዜና የሚያመጣ እና ሰላምን የሚያዉጅ የሚመጣ ነበር (ቁጥር 15) ፡፡ ይህ መልካም ዜና/መጥፎ ዜና ትንቢት ነበር ፤ መጥፎዉ ዜና አሶራዊያን ከምድር ላይ እንደሚጠረጉ ነበር ፤ መልካሙ ዜና ደግሞ ይሁዳ ከአሶራዊያን እስራት ነፃ በመዉጣት ሰላም እንደሚሰጠው ነበር ፡፡ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚያስደነግጠው ይህን የሚተገብሩት እና የእግዚአብሔር ሕዝብ ከአሶራዊያን ነፃ የሚያወጡት ባቢሎናዊያን መሆናቸዉ ነው ፤ በሚያናድድ ሁኔታ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደ ገና በባቢሎናዊያን ምርኮኝነት ይገጥማቸዋል ፡፡
ናሆም (2፡ 1-13)፡ እግዚአብሔር ብዙ ወንጀሎችን ፈጽማ ስለ ነበር በነነዌ መጥፋት ልክ እንደ ነበር ገለፀ ፡፡
ናሆም (3፡ 1-19)፡ እግዚአብሔር የከተማዋን ዉስጣዊ ሁኔታ እና የከተማዋን ዉጫዊ ሁኔታ ገለፀ ፡፡ ባሪያዎችን ይሸጡ ነበር፣ ያለምንም መጨረሻ ሰዎችን ይጣሉና ይገሉ ነበር በተጨማሪም በምንዝርና፣ በጥንቆላ እና በድግምት ስራ እየተሳተፉ እና እያደረጉ ነበር ፡፡ በቴብስ ዉድቀት የሆነዉ በአሶር ላይም ይሆናል ፤ ለእነርሱ ማስተካከያ አይኖራቸዉም ፡፡ ማክጊ የዮናስን እና የናሆምን መልዕክት በዚህ መንገድ ያወዳድራል ፤ የዮናስ መልዕክት “ እግዚአብሔር ዛሬ ያድናል “ የሚል እንደ ነበርና የናሆም መልዕክት “ እግዚአብሔር ነገ ያጠፋል “ የሚል ነበር ፡፡ ማክጊ “ ሰዉ በሚያደርገዉ እግዚአብሔር አይቀየርም “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሔር ሕዝቡን ባዓላታቸዉን እንዲያከብሩ እና የኪዳን ስለታቸዉን እንዲፈፅሙ ነገራቸው ፤ በሌላ አነጋገር ከእርሱ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት እንዲመላለሱ ነገራቸው ፡፡ በእግዚአብሔር ብቻ መምጣት ስለሚችለዉ ሰላም ያዉጃሉ እንዲሁም መልካሙን ዜና የሚያመጣዉን ይጠብቃሉ ፡፡ ስለዚህ ነገር በአዲስ ኪዳንም ማስረጃ አለ፡
ማቴ (28፡ 18-20)፡ “ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ፡- ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ “ ፡፡
ሮሜ (10፡ 15)፡ “ መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ! ተብሎ እንደተፃፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? “
ኤፌ (2፡ 17)፡ “ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን ቀርበዉ ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ “
ኤፌ (6፡ 15)፡ “ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተውቁሙ “ ፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራዉ ስራ የተነሳ ሸክማችን ተሸካሚያችን ሲሆን ሰላምም አለን ፡፡
10 McGee
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1022.
MacArthur, p. 1022.
MacArthur, p. 1022.
MacArthur, p. 1022.
MacArthur, p. 1022.
MacArthur, p. 1023-1024.
MacArthur, p. 1023.
MacArthur, p. 1024.
J. Vernon McGee, “Outline of Nahum,” available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/nahum/nahum-outline.cfm.
ጥያቄዎች
-
የናሆም መፅኃፍ ለማን ነበር የተፃፈው ከዮናስ መጽኃፍም ጋር በምን የጋራ ይሆናል ?
-
ከነቢዩ ዮናስ በተቃራኒ ከ100 አመታት በፊት በነነዌ መንገዶች ላይ ማን ሰበከ ነቢዩ ናሆም ምን እንዲያደርግ/እንዲሰብክ ነበር የተላከው ?
-
ናሆ (2፡ 8) ከነነዌ ጋር በምን ይወዳደራል ? ነነዌን ወደ ቀድሞዋ መንገዷ እንድትመለስ ምን አደረጋት ?
-
ናሆም 3 ስለ ነነዌ የእግዚአብሔር ፍርድ ምን ይላል ? ነነዌ እያደረገቻቸዉ የነበሩትን አንዳንድ ክፉ ነገሮች በዚህ አለም ላይ ከሚሆኑት አንዳንድ ክፉ ነገሮች ጋር እንዴት ይነፃጸራሉ ? የእግዚአብሔርን ቁጣ እንፈራለን?
-
በናሆም (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nahum 1:7–8
“The LORD is good, a stronghold in a day of distress; He cares for those who take refuge in Him. But He will completely destroy Nineveh with an overwhelming flood, and He will chase His enemies into darkness.”
ነቢዩ ናሆም ለእስራኤላውያን የመጽናናት መልዕክትን አመጣ ደግሞም እንዲሁ በነነዌ እና በአሶር ላይ ስለሚመጣው ፍርድ ተነበየ፡፡ ናሆም እግዚአብሔር መልካም በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ጋሻ እንደሆነ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ የሚሸሸጉትን እነርሱን ይጠብቃቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ስለጥፋት መንገዳቸው አሶራውያንን ፈጽሞ እንደሚያጠፋቸው ይናገራል፡፡ እግዚአብሔርም ቀንበሩን ስለሚሰብር እስራቱንም ስለሚበጥስ እስራኤላውያን ከእንግድህ ወዲያ በአሶር ባርነት ውስጥ አይወድቁም፡፡ እግዚአብሔር ነጻ ያወጣቸዋል፤ አንድ ቀንም መልካሙን ዜና የሚናገሩ ሰላምንም የሚያውጁ እግሮች ይመጣሉ፡፡
በህይወታችሁ ውስጥ ምንም አይነት ጥፋት ይኑር፤ በጭንቅ ቀናቶቻችሁ ውስጥ እግዚአብሔር መሸሸጊያ ጋሻችሁ ነው፡፡ ሸክማችሁን ወደ ሚሸከመው ወደ ኢየሱስ ተመልከቱ፡፡ ዛሬ የገጠማችሁ ምንም ይሁን፡፡ ምንም ያህል ነገሩ ይክበዳችሁ ፤ ነገር ግን በከበዳችሁ ነገር ውስጥ እግዚአብሄርን መፈለግ እንዳትዘነጉ፡፡ እርሱ ሸክማችሁን ያቀለዋል፡፡ እርሱ ነጻ ያወጣችኋል፡፡ ሰላምን ይሰጣችኋል፡፡ ከዚህ በኋላ አትታሰሩም፡፡ በክርስቶስ ነጻና ፍጹማን ተደርጋችኋል፡፡ እግዚአብሔር ለደረሰው ጥፋት ካሳን ያደርጋል፡፡ አሁን ሂዱ በነጻነት ተራመዱ በዙሪያችሁ ካሉት ጋርም ሰላምን ተካፈሉ፡፡
“እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።”
- ናሆም 1፡7-8
ተጨማሪ ጥቅስ
ናሆም 1:13 — “አሁንም ቀንበሩን ከአንተ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ።”
ናሆም 1:15 — “እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።”
ማቴዎስ 11:30 — “ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።