Judgment And Restoration
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Shepherd Micah 6-7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ታናናሽ ነቢያቶች ትልቅ መልዕክት አላቸዉ ነገር ግን ስለ መልዕክቶቹ ለማዉራት ብዙ ቀናትን አይወስዱም ፡፡ መጽኃፎቻቸው ከታላላቅ ነቢያቶች በጣም ያነሱ ናቸው ነገር ግን አሁንም መልዕክታቸዉ አስፈላጊና ትልልቆች ናቸው፡፡ “ ሚክያስ “ የሚክይያስ ወይም የሚልክይያስ ያጠረ ስም ነው ፡፡ ሚክያስ ለእስራኤል ለደቡቡ ነገድ (ለይሁዳ) ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ ከዛሬዉ ምዕራፍ አንዱ ፍሬ ነገር የተዋሀደዉ መንግስት መታደስ ነዉ የሚሆነው ፡፡ ሚክያስ ስለ ሰሜኑ መንግስት ጥፋት ትንቢትን የተናገረ ቢሆንም በይበልጥ የእግዚአብሄር ፍርድ እንደሚደርስባቸዉ የደቡቡንም መንግስት አስጠንቅቋል ፡፡
ትምህርት
ሚክያስ (6፡ 1-16)፡ የሚክያስ ቋንቋ የዳኛን ይመስላል ፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ፊት የሚያመጣው “ ክስ “ እና “ ክርክር “ እንደ ነበረዉ ፅፏል (ቁጥር 2) ፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ክርክር በሚኖረዉ ጊዜ ነገሮች በመልካም አይሄዱም ፤ የእግዚአብሄር ክርክር በሕዝቡ ላይራሱ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለሚከራከር በጣም አስፈላጊ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ እግዚአብሔር “ እንዴት እንዳደከመኋችሁ ? “ (ቁጥር 3) ለመናገር ክርክራቸዉን በእርሱ ላይ እንዲያመጡ ሕዝቡን ሞገታቸው ፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ተቤዥቷቸዉ እንደ ነበርና ሕዝቡን እንዳይረግም እንዴት ለበለዓም እንዳልፈቀደለት አስታወሳቸው (ቁጥር 5) ፡፡
በመቀጠልም እግዚአብሔር አሳይቷቸዉ ለነበረዉ ቸርነት ምን መመለሰ እንዳለባቸው ጠየቃቸው ፤ ሕዝቡ ለእነርሱ ካሳየው ቸርነት የተነሳ በምላሹ ሊያመጧቸዉ የሚችሉአቸዉን የተለያዩ መስዋዕቶችን ዘረዘረ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ከመስዋዕት ወይም ከዉጫዊዉ ኃይማኖታዊ ስርዓት/እንቅስቃሴ ይልቅ እግዚአብሔር ሕዝቡ “ ፍርድን ያደርጉ ዘንድ ምሕረትን ይወድዱ ዘንድ በአምላካቸዉ በትሕትና ይመላለሱ ዘንድ “ (ቁጥር 8) ፈለገ ፡፡
እግዚአብሔር ከሚያደርጓቸዉ ድርጊቶች ይበልጥ በሕዝቡ የልብ ሁኔታ ላይ በደንብ ያተኮረ ነበር ፡፡ ማቴ (7፡ 21-23) “ በሰማያት ያለዉን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም ፡፡ በዚያ ቀን ብዙዎች ፡- ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስአጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራት አላደረግንምን ? ይሉኛል ፡፡ የዚያን ጊዜ ፡- ከቶ አላወቀኋችሁም ፤ እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ ! “ በማለት ይናገራል ፡፡
እግዚአብሔር የሰዎችን የኃይማኖት እና የክፋት መልክን ተመለከተ ፤ ጄ.ቬርኖን ማክጊ እግዚአብሔር “ አለመታመንን፣ ጥፋትን/አመጽን፣ ጠማማነትን፣ ዉሸትን እና ማታለልን ችላ ማለት እንደማይችል “ ጽፏል (ቁጥር 9-12) ፡፡ ከይሁዳ ኃጢዓት የተነሳ የእግዚአብሔር ፍርድ እየመጣ ነበር (ቁጥር 13-16) ፤ የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሄርን ፍርድ የቀመሱትን አባት እና ልጅ የነበሩትን ሁለቱን ነገስታቶች የዘንበሪን እና የአክዓብን መንገድ ተከትለዉ ነበር ፡፡
ሚክያስ (7፡ 1-4)፡ ሚክያስ በራሱ ሕዝብ ላይ ፍርድን በማወጁ ደስታን አልወሰደም/አላገኘም ፤ “ ወዮልኝ ! “ በማለት አወጀ (ቁጥር 1) ፤ ይህ ኃዘን በነቢያት መካከል የተለመደ ነበር ፡፡
ኤርምያስ “ ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ዉኃ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ “ (ኤር 9፡ 1) ፡፡
ኢሳይያስ “ እኔም ፡- ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ ከንፈሮቻቸዉም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሱን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ ! አልሁ “ (ኢሳ 6፡ 5) ፡፡
በማንኛዉም ህዝብ መካከል ብንኖርም በመጀመሪያ ደረጃ ስለ መንግስታችን ሁኔታ መጨነቅ የለብንም ፤ ይልቁንም በሕዝባችን ዉስጥ ስላሉ ወንዶችና ሴቶች ሁኔታ መጨነቅ/ማሰብ አለብን ፡፡
ሚክያስ “ ደግ ሰዉ ከምድር ጠፍቷል “ በማለት ተናገረ (ቁጥር 2) ፤ ይልቁንም ሁሉም ጥፋትን ለመፈፀም፣ ክፋትን ለማድረግ፣ ጉቦን ለመቀበል እና ለክፉ አላማ በአንድ ላይ ለማሴር የጓጉ ነበሩ (ቁጥር 2-3) ፡፡ ከእነዚህ ነገሮች የተነሳ የእግዚአብሔር ፍርድ በፍጥነት ይመጣል ፡፡ ዋይርስቤ “ በዚህን ጊዜ ሰዎች የነቁ መሆን እንደሚያስፈልጋቸው “ ፅፏል፡፡
ሚክያስ (7፡ 5-7)፡ ሚክያስ ሰዎቹን የቅር ወዳጆቻቸዉን ማመን እንደማይችሉ መከራቸው ፡፡ ነገሮች “ በክንድ ላይ ከምትተኛ ሴት “ እንኳን ማመን እስከ ማይቻል ድረስ ነገሮች በጣም መጥፎ ይሆናል ፡፡ ቤተሰብ የተሸላ አይሆንም፡ “ የሰው ጠላቶቹ የቤቱ ሰዎች ናቸውና “ (ቁጥር 6) ፤ ኢየሱስ ይህን ስዕል በማቴዎስ 10 ተጠቅሞበታል፡ “ ሰዉን ከአባቱ ሴት ልጅንም ከእናትዋ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና ፤ ለሰዉም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶቹ ይሆኑበታል “ (ማቴ 10፡ 35-36) ፡፡ ሚክያስ ሰዉ የራሱን ቤተሰብ ማመን እንዳይችል ነገሮች መጥፎ እንዲሚሆኑ ሲያስጠነቅቅ ኢየሱስ በእርሱ ስንመላለስ ተመሳሳይ ነገር እንደሚገጥመን አስጠንቅቋል ፡፡
በሚክያስ ዙሪያ ነገሮች ምንም ያክል መጥፎ ቢሆኑም ችግር አልነበረውም “ ወደ እግዚአብሄር በመመልከት “ እና “ የመድኃኒቱን አምላክ በመጠበቅ “ (ቁጥር 7) ፈታቸው ፡፡ ዳዊት ተመሳሳይ አመለካከትን ገልፆአል፡ “ በማለዳ ድምጼን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም “ (መዝ 5፡ 3) ፡፡ ሚክያስ በባህሉ ዉስጥ እና በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል በሚያየዉ ነገር ተጨንቆ ነበር ፤ ሚክያስ ማድረግ የቻላቸዉ ሁሉ የራሱ ትኩት በእግዚአብሄር ላይ እንደ ነበር እርግጠኛ የሚያደርጉ ነበሩ ፡፡ ማክአርቱር “ በኃይለኛ ሁኔታዎች ዉስጥም ቢሆን እንደ ጉበኛ ሚክያስ እግዚአብሄር በራሱ ቀን እና ጊዜ እንደሚያደርግ በማመን የእግዚአብሄር ስራ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንደሚመለከት “ ይናገራል ፡፡
ሚክያስ (7፡ 8-13)፡ በቁጥር 8 መጀመሪያ ላይ እስራኤል ተናገረች ፤ በቁጥር (8-10) እስራኤል ስለ ኃጢዓቷ መናዘዝ እና ንስኃ መግባት ጀመረች ፡፡ እስራኤል እግዚአብሄር ክርክሩን በእነርሱ ላይ ካመጣ በኋላ ፍትሕን እንደሚያመጣላቸዉ ስታምን እንደ ገና የሕግ ቋንቋ ተነሳ (ቁጥር 9) ፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅሬታዎች ወደ እስራኤል የሚመለሱበት ቀን ይመጣል (ቁጥር 10-13) ፡፡
ሚክያስ (7፡ 14-20)፡ እግዚአብሔር የሕዝቡን ቅሬታዎች እንደሚሰበስብ ቃል ገባ ፡፡ “ ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳያቸዋለሁ “ (ቁጥር 15) በማለት ቃል ገባ ፡፡ የሕዝቡም ጠላቶች “ ፈርተውም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ ስለ አንተም ይፈራሉ (ቁጥር 17) ፡፡
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከእርሱ የተመለሱ ቢሆኑም እንኳን ሁሉንም ኃጢዓታቸዉን ይቅር እንደሚል /እንደሚረሳ እና ታምነዉ በተቀመጡት ቅሬታዎች እንደሚደሰት ቃል ገባ ፡፡ ተስፋ አይለወጥም ፤ የእስራኤል ኃጢዓት ለአብርኃም ቃል ገብቶት የነበረዉን ተስፋ ከማድረግ እግዚአብሔርን አያስቆመዉም (ቁጥር 20) ፡፡ መዝ (89፡ 33) “ ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም በእዉነቴም አልበድልም “ ይላል ፡፡ የእግዚአብሔር የመጨረሻ እድሳት እና ከአብርኃም ጋር ላደረገዉ ኪዳን የመጨረሻ ሙላት በሺዉ አመት ይመጣል ፡፡
መደምደሚያ
በታናናሽ እና በታላላቅ ነቢያቶች ዉስጥ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያድስ/እንደሚመልስ ቃል የገባባቸዉ 13 ስፍራዎች አሉ ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ምድራቸዉ እንደሚመልሳቸዉ እና ወደ መጨረሻ እረኛቸዉ ወደ ኢየሱስ እንደሚመልሳቸው ቃል ገብቷል ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Micah, pp. 1–4; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/micah.pdf.
J. Vernon McGee, “Outline for Micah”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/micah/micah-outline.cfm.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 400.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 1021.
ጥያቄዎች
-
በሚክ (6፡ 8) መሰረት እግዚአብሔር ከእናንተ ምንን ይፈልጋል ?
-
በሚክ (6፡ 1-7) እግዚአብሔር እስራኤል ንስኃ እንዲገቡ ሲለምን ምንን እንዲተዉ አሳሰባቸው ?
-
ሚክያስ በምድር ላይ ትክክለኛ ሰዉ ማግኘት አልቻለም (ሚክ 7፡ 1-4) ፤ ይህን ከዛሬ ጋር እንዴት ይወዳደራል ? እምነታችንን የማናስቀምጥበት ማን ሊሆን ይችላል ? ማንስ ለማስቀመጥ ይመስላል ?
-
በሚክያስ (6-7) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Micah 6:8
“Mankind, He has told you what is good and what it is the LORD requires of you: to act justly, to love faithfulness, and to walk humbly with your God.”
ነቢዩ ሚክያስ ማስጠንቀቂያ ደግሞም ተስፋ ያለውን የእግዚአብሔርን መልዕክት ለእግዚአብሔር ህዝቦች ለእስራኤላውያን መናገሩን ቀጠለ፡፡ ሚክያስ እነርሱ የሚያቀርቡትን መስዋዕት ጭምር እንዴት ለታይታ እንደሚያደርጉትና እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንደሚሞክሩ ተናገረ፡፡ ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር ከልባቸው የሚመነጨውን መስዋዕት ይሻ ነበር፡፡ ሚክያስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ምን እንደሚፈልግ ተናግሯል ይህም፡- ፍርድን ያደርጉ ዘንድ፣ ምህረትን ይወድዱ ዘንድ እናም ከእርሱ ጋር በትህትና ይሄዱ ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አካሄዳቸውን አይቶ በእነርሱ ላይ ቅጣትን አመጣ ፡፡ ቀጥሎም ሚክያስ ለእግዚአብሔር ህዝብ ተስፋን በመናገርና ደግሞም ስለ እግዚአብሔር ባህሪና እርሱ ስለተናገረው ተስፋ ለእነርሱ በማስታወስ አጠቃለለ፡፡
ዛሬ አምላካችሁ እግዚአብሔር ኋጢአታችሁን መሻር ዓመጻችሁንም ይቅር ማለት እንደሚችል ይህን እመኑ፡፡ እርሱ ምህረትን ይወድዳልና ለዘላለም አይቆጣም፡፡ እርሱ ለእናንተ ያለው ርህራሄው አያልቅም፡፡ እርሱ በደላችሁን ወደ ባህር ጥልቅ እንደሚጥለው ይናገራል፡፡ እርሱ ታማኝነቱን ሊያሳያችሁ ለእናንተ ለሰጠውም ተስፋ እንደሚታመን ይናገራል፡፡ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስትሹ እርሱ ከእናንተ ይህንን ይፈልጋል ፡- ፍርድን እንድታደርጉ፣ ምህረትን እንድትወድዱ እና ከእርሱ ከአምላካችሁ ጋር በትህትና እንድትሄዱ ነው፡፡ እርሱ የልባችሁን መስዋዕትና መሰጠት ይፈልጋል፡፡
“ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?”
- ሚክያስ 6፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 89:33–34 — “ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፥ በእውነቴም አልበድልም፤ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም።”
ሚክያስ 7:7 — “እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል።”
ሚክያስ 7:18–20 — “በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።