Minor Prophets Micah

From Defeated Ruler to Conquering King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Shepherd Micah 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 698 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ታናናሽ ነቢያቶች አጭር መፅኃፍት ናቸዉ ነገር ግን ብዙ ሸክምን ይዘዋል ፡፡ በሚክያስ የኢየሱስ መልክ እረኛዉ ነው፡፡ የሚክያስ መጽሐፍ ሰዎስት የማስጠንቀቂያ ሸክሞች አሉት ፤ ሰዎስተኛዉ በሚክያስ 3 ላይ ሲሆን ስለ ሀገሪቱ መሪዎች ያወራል ፡፡ ሚክ (3፡ 1-4) ስለ አለቆች ኃጢዓት ያወራል ፤ ሚክ (3፡ 5-8) ስለ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ኃጢዓት እና ስለሚገጥማቸዉ ፍርድ ያወራል ፡፡ በሚክ (3፡ 9-12) ከሕዝቡ ኃጢዓት የተነሳ የኢየሩሳሌም ጥፋትን ሸፍኗል ፡፡

ትምህርት

ሚክያስ (4፡ 1-13)፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ ሚክያስ 4 “ ኢየሩሳሌምን የአምልኮ እና የመንግስቱ ማዕከል በማድረግ የሺዉ አመት መንግስት መልክ እንደሆነ ፤ በዚያም ጊዜ ሰይፍ ወደ ማረሻነት እንደሚቀጠቀጥ (ቁጥር 3) “ ያጠቃልለዋል ፤ ይህ ማለት ጦርነት እንደማይሆን እና የሰላም እና የብልጽግና ጊዜ ይሆናል ማለት ነው ፡፡ ኢዩ (3፡ 9-10) እንደ ቅዱስ ጦርነት ይገልፀዋል ፡፡ ሕዝቡ በራሳቸዉ የወይን መጥመቂያ እና አትክልት ዉስጥ ሰላምን እና ደህንነትን ያገኛሉ (ቁጥር 4-5) (ዘካ 3፡ 10) ፤ እረኛዉ ኢየሱስ የተበተኑትን ሕዝቦች ወደ መንግስቱ ይሰበስባቸዋል (ቁጥር 7-8) (ዮሐ 10፡ 10) ፡፡

በቁጥር 9 በሚክ (5፡ 1) የወደፊት ምርኮኝነታቸዉ ታወጀ/ተነግሯል ፡፡ ኮንስታብል “ እስራኤላዊያን በምጥ እንዳለች ሴት ኢየሩሳሌምን እንደሚለቅቁ “ ይገልፃል ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር እነርሱን በባቢሎን በመታደግ ከምርኮ ነፃ ያወጣቸዋል (ቁጥር 10) ፡፡ ቁጥር (11-13) በአርማጌድዮን የሚመጣዉን ዉጊያ መልክ ይሰጣል ፡፡

ሚክያስ (5፡ 1-9)፡ ሚክያስ 5 እንደ ሚክያስ 4 ተመሳሳይ የጊዜ ሰሌዳን ይዟል ፡፡ በመሰረቱ ቁጥር 1 በምዕራፍ 4 ይካተታል ፤ ቁጥር 1 “ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በባቢሎን እጅ የንጉስ ሴዴቅያስን መያዝ የሚያመለክት ነዉ “ የሚመስለው (2ነገስት 24-25) ፡፡ ቁጥር 2 ስለ ኢየሱስ ትንቢታዊ ጥቅስ ነው፡ “ አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል “ ፤ ይህ የመጀመሪያዉን የክርስቶስ መምጣትን ይገልፃል ፡፡ በማቴ (2፡ 1-2) አስተዋይ ሰው የሚክያስ (5፡ 2) ትንቢት ያውቀዋል ፤ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ ይጠብቃሉ እንደ ንጉስ እንደሚመጣም ያውቃሉ ፡፡ ማክጊ “ ክርስቶስ በሰዋዊነቱ ክርስቶስ ከቤተ ልሔም እንደ መጣ ፤ በአምላክነቱ ደግሞ ከዘላለም እንደ መጣ “ ይገልፃል (ማቴ 2፡ 5-6) ፡፡

ቁጥር 3 አሁን ያለንበትን ጊዜ ያመለክታል - ኢየሱስ በመጀመሪያዉ ምጽዓቱ የተወለደበትን ነገር ግን ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሶ ያልመጣበትን ጊዜ ፡፡ ማክአርቱር ይህ “ እስራኤል ክርስቶስን ባለመቀበል እና በጣላት ተጽዕኖ ስር የሆነችበት እንደ አሕዛብ ጊዜ “ ይገልፀዋል ፡፡ ሁለተኛዉ ምጽዓት “ የቀሩትም ወንድሞች ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ “ በሚለዉ ፅኁፍ/ንግግር ዉስጥ የተጠቀሰ ነው ፡፡ ክርስቶስ በአምላኩም በእግዚአብሄር ስም ግርማ ወንድሞቹን ሊጠብቅ እና ሊሰበስብ ተመልሶ ይመጣል (ቁጥር 4) ፤ ይህ የክርስቶስን የሺዉ አመት አስተዳደርን ያመለክታል ፡፡ በቁጥር 5 የኢሳ (9፡ 6) መልክ ያስተጋባል - “ ሰላማቸዉ ይሆናል “ ፡፡

ማክአርቱር በቁጥር (7-9) ያለዉን ዉጥረት “ በብዙ ሕዝቦች መካከል የእስራኤል መገኘት ለአንዳንዶች የበረከት ምንጭ እንደሚሆን፣ ለአንዳንዶች ደግሞ የፍራት እና የጥፋት ምንጭ እንደሚሆን ልክ እንደ አንበሳ እንደሆነ “ ይገልፀዋል ፡፡ የያዕቆብ ቅሬታ በእዉነት የታበረከ ሲሆን ጠላቶቹ ደግሞ ይጠፋሉ ፡፡

ሚክያስ (5፡ 10-15)፡ ኮንስታብል ቁጥር (10-15) “ እንደ ፂዎን መንፃት “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ኮንስታብል “ በሚመጡት የወደፊት ዘመን ቀናቶች እግዚአብሄር በፈረሶች፣ በሰረገላዎች፣ በከተሞች እና በምሽጎች ሁልጊዜ እስራኤላዊያንን ፈትነዉ የነበሩትን ከንቱ የደህንነት ምንጮችን ለማስወገድ ቃል እንደ ገባ “ ይገልፃል ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር የሐሰተኛ አማልዕክት መሰዊያዎችን፣ የተቀረጹ ምስሎችን እና የአሼር አምዶችን፣ አስማተኞችን እና ሞራ ገላጮችንም ያስወግዳቸዋል (ቁጥር 10-14) ፡፡ እግዚአብሄር እርሱን አክብረዉት ባልነበሩት ሕዝቦችም ላይ በቀልን እንደሚያደርግ ቃል ገባ ፡፡

መደምደሚያ

በመጨረሻም ከሚክያስ 4 እና ከሚክያስ 5 ማብቂያ በኋል የሚያስደንቅ የተስፋ መልዕክት አለን ፡፡ ሚክያስ 4 የሺዉ አመት መንግስት ምን እንደሚመስል መልኩን ይስላል ፤ ሚክያስ 5 በዚያ መግለጫ ላይ መልክን እና ዝርዝርን ይጨምራል ፡፡ ለሁለቱም ምዕራፍ መልዕክቱ መሲሁ ኢየሱስ ስለሚመጣ መዘጋጀት የሚል ነው ፡፡

ለአሕዛብ መልዕክቱ መሲሁን ኢየሱስን እንዲይዙት ነው ፡፡

ለአይሁዶች መልዕክቱ ተመሳሳይ ቢሆን ተጨማሪ ነገርን ግን ያካትታል ፡፡ መጽሐፍ ሁሉም አሕዛብ ስለ ኢየሱስ የመስማት እድል እስኪኖራቸዉ ድረስ በአይሁዶች መካከል በከፊል ድንዛዜ እንደ ሆነባቸዉ ይናገራል ፡፡ በአሁኑ ስዓት ስለ ኢየሱስ ያልሰሙ 196 ሀገራት ናቸው ፤ ወንጌል የመጨረሻዉ ዘመን እንቅስቃሴ የተቀመጠ ከመሆኑ በፊት ወደ እነዚህ ምድሮች መሄድ አለበት ፡፡ ከዚያም አለም ብቻ ታላቁ መከራ ይደርስባታል ፤ በዚያ ሂደት ዉስጥ አንዳንድ ስፍራ የአይሁድ ሰዎች ኢየሱስን እንደ መሲሀቸዉ ለመቀበል የተዘጋጁ ይሆናሉ ፡፡

2ጴጥ (3፡ 10-13)፡

“ የጌታዉ ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል ፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምጽ ያልፋሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይቀልጣል ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል ፡፡ ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኮላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል ? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይፈታል ፤ ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን “ ፡፡

4 McGee, np..

  1. J. Vernon McGee, “Outline for Micah”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/micah/micah-outline.cfm.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: Micah, p. 43; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/micah.pdf.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1019.

  4. MacArthur, p. 1019.

  5. MacArthur, p. 1019.

  6. Constable, p. 52.

  7. Constable, p. 52.

ጥያቄዎች

  1. ሚክ (4፡ 1-8) መቼ እና ስለ ምን ነበር የተነገረው ? (ኢሳ 2፡ 3-5, ሐዋ 1፡ 6-8, ራዕይ 21)
  2. ሚክ (5፡ 2) ስለማን እያወራ ነበር (ሉቃስ 2፡ 11) ? ኢየሱስ እንደ ሰዉ ለመኖር በምድር ላይ እንደሚመጣ ትንቢት ተናግረዉ የነበሩት አንዳንድ ነቢያቶች እነማን ነበሩ ? (ኢሳይያስ 53, ኤር 30፡ 21-22, 33፡ 14-16, ዘካ 9፡ 9)
  3. ሚክ (5፡ 5-15) በእስራኤል ጠላቶች ላይ ስለሚመጣዉ ፍርድ ይናገራል ፤ በእስራኤል ላይ ምን ያክል ሀገራት ጀርባቸዉን እንዳዞሩባት ስታስቡ ይህ ያስፈራችኋል ?
  4. በሚክያስ (4-5) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Micah 5:4–5a

“He will stand and shepherd them in the strength of Yahweh, in the majestic name of Yahweh His God. They will live securely, for then His greatness will extend to the ends of the earth. He will be their peace.”

ከባቢሎን ግዞት በኋላ እግዚአብሔር ህዝቡን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመልስ ተስፋን ሰጠ፡፡ ሚክያስ በትንቢት እስራኤልን ለመግዝት ከይሁዳ ነገድ ስለሚመጣው ንጉሥ ገዥ ተናገረ፡፡ በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ በቤተልሄም ይወለዳል እስራኤልንም ይጠብቃል፡፡ እናም ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በያህዌ ኃይል በአምላኩም በአግዚአብሔር ስም ግርማ ተመልሶ ይመጣል፡፡ ስሙን የሚጠሩ ሁሉ እስከ ምድር ዳር ድረስ በታላቅነቱ ተጠብቀው በሰላም ይኖራሉ፡፡ አዎን ኢየሱስ ለሰው ልጅ ሁሉ ሰላም ይሆናል፡፡ እርሱም ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘላለም ይነግሳል፡፡

ኢየሱስ ታላቅ እረኛ የነገሥታትም ንጉሥ ነው፡፡ እርሱም የተወለደው ዓለምን ሁሉ ይዋጅ ዘንድ ደግሞም ለራሱ ህዝብ ተስፋንና መመለስን ያደርግ ዘንድ ነው፡፡ እርሱ ሰላማችሁ፣ ኃይላችሁና ጠባቂያችሁ ነው፡፡ አይኖቻችሁ ያተኮሩት በዓለም ሀሰተኛ አማልክት ላይ፣ ሌላ ጠባቂ ላይ፣ ውድ በሆኑ ምድራዊ ሀብቶች ላይ ወይስ በምግብና በመጠጥ ብዛት ላይ ነው ? እግዚአብሔር ልክ በእስራኤላውያን ላይ እንዳደረገው ሁሉ ከእናንተም ህይወት ውስጥ ራዕያችሁን የሚያበላሹና አይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ የማድረግ አቅማችሁን የሚጎዱ ነገሮችን ከህይወታችሁ እንደሚያስወግድ ይናገራል፡፡ እርሱ ብቸኛው ሰላም ነው፡፡ እርሱ ብቸኛው ዕረፍት ነው፡፡ ዛሬ ለዓለም ስለተሰጠው ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ስለሆነው ወንድ ልጅ መወለድ አመስግኑ፡፡

“እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና። ይህም ለሰላም ይሆናል፡፡”

  • ሚክያስ 4–5a

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 9:6 — “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”

ሚክያስ 5:2 — “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።”

ማቴዎስ 2:4–6 — “የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።”