Minor Prophets Micah

God's Word Was Rejected

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Shepherd Micah 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 697 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በታናናሽ ነቢያት ዉይይታችን ዉስጥ ባለፈዉ ሳምንት ሆሴዕ፣ ኢዩኤልን እና የአሞጽ ክፍል ሸፍነናል ፤ በዚህ ሳምንት የአሞጽን መፅኃፍ አብድዩን እና ዮናስን ጨርሰናል ፡፡ ዛሬ ጥናታችንን በሚክያስ መፅኃፍ እንቀጥላለን ፡፡ ለሚክያስ የሜንዲ ስዕል ከምወዳቸዉ ዉስጥ አንዱ ነው ፡፡ ከሚክ (5፡ 4) በዚህ መፅኃፍ ዉስጥ ኢየሱስን የሚገልፅ አንድ ቃል እናገኛለን፡ የሚገዛዉ እረኛ ፡፡ የሚክያስ ስም ትርጉሙ “ እግዚአብሄርን ማን ይመስላል ? “ ማለት ነው ፤ ሚክያስ ሚክያስ ወይም ሚልክያስ የሚለዉ ስም አጭር ክፍል ነው ፡፡ በመሰረታዊነት ሚክያስ ከእግዚአብሄር ቃልን በመቀበል እንዲያዉጀዉ የተላከ ነበር ፤ በሚክያስ 2 ስለ ይሁዳ ኃጢዓት ያወራል ፡፡ በፊት የነቢያት መልዕክት በእነርሱ ላይ ከሸክም፣ ከኃዘን እና ከፍርድ የተነሳ በሕዝቡ በሚገባ ተቀባይነት ያገኛ ስላልነበረዉ እዉነት አዉርተናል ፤ ከዚያም ይህ የቀረበ ትንሽ ተስፋ ነበር ፡፡

በሚክያስ (1፡ 1) መሰረት ሚክያስ ሞሬታዊ ነበር ፡፡ ስለ ቤተሰቦቹ ምንም አናዉቅም ፡፡ በፍልስጤም ከጋዛ አጠገብ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ 25 ማይል ርቀት በይሁዳ ኮረብቶች ስር ከምትገኝ ከሞሬታ ነበር ፡፡ በሚክያስ አገልግሎት ጊዜ የሰሜኑ መንግስት በአሶር ስር ይወድቃል ፤ የሚክያስ የአገልግሎት ቀን በክስተቶች ላይ የይሁዳ ነገስታትን እየጠቀሰ ቢሆንም ቃሉ ለእስራኤል (ለሰሜኑ መንግስት) ነበር ፤ ነገር ግን እንደ አጠቃላይ የመጀመሪያ ትኩረቱ የሚኖርበት የደቡቡ መንግስት ይሁዳ ነበር ፡፡ በታሪካዊነት እነዚህ ቀኖች የኢኮኖሚ ብልፅግና እና ግጭት ስለ ነበሩ ነገሮች መልካም ነበሩ ፤ ነገር ግን ነገሮች መንሸራተት እየጀመሩ ነበር ፡፡ ሶሪያ እና እስራኤል ይሁዳን በመዉረር በጊዜአዊነት ክፉዉን አካዝ በምርኮ ወሰዱት ፡፡ አሶር ሶሪያን እና እስራኤልን ካስወገዳቸዉ በኋላ የይሁዳ ጥሩዉ ንጉስ ሕዝቅያስ ከአሶር ጋር ካለዉ ጥምረት ወጣ ፤ ይህም ከክርስቶስ ልደት 701 በፊት ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን ለማጥቃት ምክንያት ሆነው ፡፡ በ 1ዜና (32፡ 21) እግዚአብሄር ይሁዳን እንዲያድኑ መለዓክቱን ላከ ፤ በመቀጠልም እግዚአብሄር ይሁዳን እግዚአብሄርን ወደ ማምለክ ለመመለስ ለመምራት ሕዝቅያስን ተጠቀመበት ፡፡ ማክአርቱር “ ከክርስቶስ ልደት 739 በፊት ከሞተዉ ከዖዝያን የብልፅግና ዘመን በኋላ ልጁ ኢዮአታም ተመሳሳይ ፖሊሲ እንደ ተከተለ ነገር ግን የጣኦት መስገጃ ማዕከላትን እንዳላስወገደ ይገልፃል “ ፡፡ የይሁዳ ዉጫዊ ብልፅግና የዉሸት ሆነ፣ ከባዖል ጋር ያላቸዉ የጣዖት አምልኮ፣ የከነዓናዊያን የምርታማነት አማልዕክት ከብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓታቸዉ ጋር ተዋህደዉ ነበር ፡፡ ከዚህም የተነሳ አሞጽ ወደ በእስራኤል ላይ ተናግሮት እንደ ነበረው ሚክያስም በይሁዳ ላይ መናገር ጀመረ ፡፡

ሚክያስ ያለሟቋረጥ ክፉን በሚከታተሉት ሰዎች ላይ የፍርድን መልዕክት ማወጅን ጀመረ ፡፡ በሚክያስ (1፡ 2 እና 6፡ 1-2) ሚክያስ የፍርድ ቤት ሀሳብ የሚመስልን ስዕል ተጠቀመ ፤ ሚክያስ መልዕክቱን በይሁዳ ላይ በፍርድ ፍርድ ቤትን የሚመስልን ስሏል ፡፡ በሚክያስ መጽሐፍ ዉስጥ ሰዎስት ሸክሞች ወይም ማስጠንቀቂያዎች አሉ ፡፡ “ ስሙ “ የሚለዉ ትዕዛዝ በእያንዳንዱ ላይ ጥቅም ላይ የዋለ ነበር (ሚክ 1፡ 2, 3፡ 1, 6፡ 1) ፡፡ በእያንዳንዱ ትዕዛዝ ስሙ በሚለዉ ሚክያስ ከጨለማ ወደ ተስፋ ይጓዛል ፡፡ የሰዎስቱ ክፍል እያንዳንዳቸው የሕዝቡን ኃጢዓት፣ የሚመጣዉን የእግዚአብሄርን ፍርድ እና ከፍርዱ በኋላ ለታመኑት የተስፋን ቃል ኪዳን ያካትታል ፡፡

ትምህርት

ሚክያስ (1፡ 1-7)፡ ትንቢቱ በሰማሪያ ላይ ነበር ከዚያም ኢየሩሳሌም ይደርሳል ፡፡ ሰማሪያ የሰሜኑ መንግስት ዋና ከተማ እና የወርቅ ጥጃ የተመለከባት ስፍራ ነበረች ፡፡ በቁጥር 2 መሰረት እግዚአብሄር በሰማሪያ ላይ ፍርድን እያመጣ ነበር ፤ አሶራዊያን ሰማርያን ለመቅጣት የእግዚአብሄር መሳሪያ በመሆን ይጠቅማሉ ፡፡ ብዙ ምሁራን ቁጥር 4 በፍርድ በክርስቶስ ተመልሶ መምጣት ጊዜ የሚሆኑትን ክስተቶች እንደሚገልፅ ያምናሉ ፡፡ ኢየሩሳሌም የአረማዊ አምልኮ ስፍራ ሆና ስለ ነበር የእግዚአብሄር ፍርድ ትቀበላለች (ቁጥር 5) ፤ ቁጥር (6-7) የሚመጣዉን ፍርድ ይገልፃል፡፡ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት ጥፋት በአሶራዊያን በሰማሪያ ላይ መጥቷል ፤ ከዚያም ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በባቢሎናዊያን የኢየሩሳሌም ጥፋት መጣ ፤ ነገር ግን ብዙ ምሁራን ይህ ክርስቶስ ተመልሶ በመምጣት በሕዝቡ እና በሌሎች ሕዝቦች ላይ በፈረደ ጊዜ የሚሆነዉን ፍርድ እንደሚያመለክት ያምናሉ ፡፡

ሚክያስ (1፡ 8-16)፡ እነዚህ ጥቅሶች የሚክያስን ኃዘን ይዘዋል ፡፡ እንደ አንድ ነቢይ ይህን ቃል ከእግዚአብሄር እንደ መጣ ሲናገር ሚክያስን ደስታን አላመጣለትም ፤ በሕዝቡ እና በከተማዉ ላይ በሚሆነዉ ነገር ደስተኛ አልነበረም ፡፡ ሚክያስ የጌት ከተማ (“ የለቅሶ ከተማ “)፣ የቤትዓፍራ ከተማ (“ የትቢያ ከተማ “)፣ የሻፊር ከተማ (“ የዉበት ከተማ “)፣ የጸዓናን ከተማ (“ የዘመቻ ከተማ “)፣ የማሮት ከተማ (“ የምሬት ከተማ “)፣ የለኪሶ ከተማ (“ የሰረገላ ከተማ “) እና የአክዚ ከተማ (“ የዉሸት ከተማ “) ስለሚሆኑ ያለቅሳል ፡፡

ሚክያስ (2፡ 1-11)፡ ሚክያስ በሕዝቡ ላይ የሚመጣዉን ኃዘን መግለፅ ጀመረ በተለይም በብልፅግና ኃጢዓት ላይ፡፡ ክፋትን ያልማሉ ያደርጉትማል (ቁጥር 1) እርሻን፣ ቤቶችን እና የሌሎችን ዉርስን መዉሰድ ያልማሉ (ቁጥር 2) ፤ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ጥፋትን አቀደ (ቁጥር 3-5) ፡፡ አንዴ ነቢዩ ቃሉን ሲናገር ሐሰተኛ ነቢያቶች በምስሉ ላይ ገቡ ፤ “ ስብከትሕን ዘቁም/ዝም በል “ አሉ (ቁጥር 6) ፡፡ ሐሰተኛ ነቢያቶች ሚክያስን ከመስማት ይልቅ የብልፅግና የሐሰት መልዕክትን ተናገሩ/አወሩ ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄር ቃል እርሱን በሚታዘዙት እና በማይታዘዙት ለሚገፉት የተገለጠ ነው ፡፡ የሐሰተኛ ነቢያቶች መልዕክት በመንፈስ ቅዱስ መልዕክት የሚፃረር ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር ድሆችን የሚያስጨንቁትን እና የመበለቶችን ጥቅም የሚወስዱትን ጠራቸው (ቁጥር 8-9) ፤ በእነዚህም ምክንያቶች እግዚአብሄር ወደ ጥፋት ያመጣቸዋል (ቁጥር 10) ፡፡

ሚክያስ (2፡ 12-13)፡ ሁልጊዜ በጥፋት መካከል ላይ እንዴት ትንሽ ተስፋ እንዳለ አስታዉሱ? እግዚአብሄር ለእርሱ የታመኑ የነበሩትን ቅሬታዎች እንደሚሰበስብ ቃል ገባ ፡፡ እረኛዉ በጎቹን ይሰበስባል ለመንጋዉም ያስባል ፤ ኢየሱስ ሕዝቡን የሚሰበስብ መልካም እረኛ ነው ፡፡ በዮሐ (10፡ 11) ኢየሱስ “ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ፡፡ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል “ አለ ፡፡ ኢየሱስ በጎቹን ያዉቃቸዋል እነርሱም ያውቁታል (ዮሐ 10፡ 14) ፤ ሚክ (5፡ 7-8) ተመሳሳይ ነገር ይላል ፡፡ እንደ እረኛ እግዚአብሄር ስለ ኃጢዓታቸዉ በይሁዳ ላይ ፍርድ ቢመጣም እንኳን አሁንም ሕዝቡን እንደሚሰበስብ ይናገራል ፡፡ ቅሬታ በሚክያስ መጽሐፍ አስፈላጊ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ለዘላለም አይቆጣም፣ በታመነ ፍቅሩ ይደሰታል ፡፡ ታጋሽ እና የሚወድ ስለሆነ እግዚአብሄር የታመኑት የቅሬታዎቹ አካል እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡

ቅሬታ በሚለዉ ቃል ላይ “ እንደ ገና መሰብሰብ “ የሚለዉን ቃል ጨምሩበት ፡፡ በሁሉም ስፍራ የተበታተኑ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሄር የታመኑትን መልሶ ወደ ስፍራቸዉ መሰብሰብ ጀመረ ፡፡ ቁጥር 13 መሪያቸዉ እና ንጉሳቸዉ የሚሆነዉን መልክ ይስላል ፤ ይህ ሁሉ በሺዉ አመት ዘመን ይከናወናል ፡፡ እረኛዉ መንጋዉን ይሰበስባል ነገር ግን ንጉሱ እንደ ነገስታት ንጉስ እና እንደ ጌቶች ጌታ በእነርሱ ላይ ይፈርዳል/ያስተዳድራል ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር ቅሬታዎቹ “ በሀገራዊ ክህደት መካከል ዉስጥ ይህን የጽድቅ ቅሬታ ለመስራት በሉዓላዊዉ ፀጋዉ የተጠበቁ የእግዚአብሄር ሕዝቦች ትንሽ ማዕከል እንደሆኑ “ ተናግሯል ፡፡

መደምደሚያ

ሁልጊዜ እግዚአብሄር ታዛዦች የሆኑ፣ የተጠበቁ፣ የሚያከብሩና ወደ እርሱ የሚመለከቱ ጥቂቶችን ያገኛል ፤ ሁልጊዜ እረኛ ቅሬቶቹን የሚመለከት ነው ፡፡

በሚክያስ ላይ ተጨማሪ ጥናታችንን ነገ እንቀጥላለን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1014.

  2. MacArthur, p. 1014.

  3. MacArthur, p. 1014.

  4. MacArthur, p. 1014.

  5. MacArthur, p. 1014-1015.

  6. MacArthur, p. 1015.

  7. J. Vernon McGee, Thru the Bible Commentary: Jonah and Micah (Nashville: Thomas Nelson, 1991), n. p.

  8. MacArthur, p. 772.

ጥያቄዎች

  1. በሚክ (2፡ 13) “ በሩን የሚሰብረዉ ሰባሪው “ ከፊታቸዉ ይሄዳል ፤ ይህ ለመሲሁ ማሳያ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ?
  2. ሚክ (3፡ 2-4) መሪዎችን የሚመሯቸዉን ስጋ እንደበሉ እና ቆዳቸዉን እንደገፈፏቸው ይገልፃል ፤ ከሕዝቡ አንጻር መሆን ያለበት የመሪዎች ሚና ምን ነበር ? ገላ (5፡ 15) አንብቡ ፤ የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ ችግር የተያዘች ትመስላለች ፡፡ ይህ አንዱ ሌላዉን መብላት እና ማጥቃት አሁንም በቤተ ክርስቲያን እንደሚሆን ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን ይመስላል ?
  3. ሚክያስ ለነቢያቱ ይህ ምሽት እና ጨለማ ይሆንባችኋል ባለ ጊዜ ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ (ሚክ 3፡ 6) ?
  4. በሚክያስ (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Micah 3:8

“As for me, however, I am filled with power by the Spirit of the LORD, with justice and courage, to proclaim to Jacob his rebellion and to Israel his sin.”

እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ትንቢትን ይናገር ዘንድ ነቢዩ ሚክያስን ጠራው፡፡ ምንም እንኳ እስራኤላውያን ከአመጽ መንገዳቸው ባይመለሱም እግዚአብሔር ግን ለእነርሱ መገለጡን አላቆመም ነበር ፡፡ ሚክያስን የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል፣ በፍርድና ለእስራኤላውያን ስለ በደልና አመጻቸው በሚናገርበት ድፍረት ሞልቶት ነበርና ከሌሎች ሀሰተኛ ነቢያት ራሱን ልይቶ ተቀመጠ፡፡ ሚክያስ ጠንከር ካሉ የፍርድ፣ የማስጠንቀቂያና የጥፋት መልዕክቶቹ በተጨማሪ ጌታ ታላቁ እረኛ ቅሬታዎቹን እንደሚሰበስብና እንደሚመራቸው፣ ይህንን የእግዚአብሔርን ተስፋና ትድግናም ጨምሮ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር በስማቸው ያውቃቸዋል እነርሱም ድምጹን ያውቃሉ፡፡

ጓደኞቼ መንፈስ ቅዱስ ያስታጥቃችኋል፣ ያጎለብታችኋል ደግሞም ይመራችኋል፡፡ እርሱም በደስታና በሰላም ይሞላችኋል በተስፋም ትትረፈረፋላችሁ፡፡ እግዚአብሔር እረኛችሁ ሁኖ ይመራችሁ ዘንድ ይሻል፡፡ እርሱ አመጻችሁን ከእርሱም የተለየ መንገዳችሁን ያያል፤ እርሱ ልባችሁን ያውቃል በጠንካራ ክንዶቹም አቅፎ ይይዛችሁ ዘንድ ይናፍቃል፡፡ እግዚአብሔር የእርሱን ስራ ትሰሩ ዘንድ በስሙ ኃይልን ያስታጥቃችኋል፡፡ ጥሪያችሁን ሆነ የሰማዩ አባታችሁን ፍቃድ በራሳችሁ ኃይል መፈጸም አይጠበቅባችሁም፡፡ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእናንተ ይናገራል፣ ይመክራችኋል፣ ይመራችኋል ደግሞም ያስተምራችኋል፡፡ ዛሬ የጌታን ስም ተጣሩ እርሱም ኃይል ይሆናችኋል፡፡

“እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ።”

  • ሚክያስ 3፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ሚክያስ 2:12 — “ያዕቆብ ሆይ፥ ሁለንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፤ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።”

ዮሐንስ 10:11 — “መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”

ሮሜ 15:13 — “የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ።”