Minor Prophets Jonah

Jonah's Preaching

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Resurrection Jonah 1-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 696 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ታናናሽ ነቢያቶች ከታላላቅ ነቢያቶች ያነሱ ፅሁፍን ቢፅፉም ታናናሽ ነቢያቶች ኃይለኛ መልዕክት አላቸው ፡፡ ዮናስ ከሚታወቁት ታናናሽ ነቢያቶች ዉስጥ አንዱ ሲሆን መጽፉም ለእኛ ብዙ የሚጠቅሙ እይታዎች/ኃሳቦችን ይዟል ፡፡ ምናልባትም ሁላችንም የሆነ ስፍራ/ስዓት ላይ ልክ እንደ ዮናስ ተሰምቶናል ፡፡

የዮናስ ስም “ እርግብ “ ማለት ነዉ ፡፡ በዮናስ ጊዜ በመጽሓፉ መጀመሪያ ላይ በመሸሽ እና ለጌታዉ ለመታዘዝ እምቢ ያለ እርግብ ነበር ፡፡ በመጽሐፉ ዉስጥ ዮናስ ራሱን እንደ ሰዎስተኛ ሰዉ ጠቅሷል ፡፡ ማክአርቱር ይህ ተግባር በብሉይ ኪዳን ዉስጥ እንዳልተመደ ያጋራል ፡፡

ዮናስ በ 2ነገ (14፡ 25) የተጠቀሰ ነበር፡ “ የጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ እጅ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሄር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ “ ፡፡ ጋትሔፌር ናዝሬት አጠገብ የነበረች እና ከክርስቶስ ልደት (ከ793-7ከ53 በፊት) በኢዮርብዓም ሁለተኛ ዘመን ጊዜ የተመሰረተች ነበረች ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ ዮናስ አሞጽ በሁኔታዉ ላይ ከመምጣቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ለሰሜኑ መንግስት ለእስራኤል ነቢይ ነበር ፡፡ የአይሁድ ታሪኮች ዮናስ ኤልያስ ከሞት ያስነሳዉ የመበለቲቱ የሰራፕታ ልጅ እንደ ነበር ይዘዋል (1ነገስት 17) ፡፡

በዮናስ አገልግሎት ጊዜ አሶር እና ሶሪያ ኢዮርብዓም ሁለተኛ የእስራኤልን ድንበር በዳዊት ዘመን ጊዜ እስከ ነበረዉ ስፍራ እንዲያስፋፋ የፈቀዱ በአንፃራዊነት ደካማ ነበሩ ፡፡ ይህ በመንግስቱ የሰላም እና የብልፅግና ዘመን ነበር ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንፈሳዊ ድህነት ዉስጥ ነበር ፡፡ ማክአርቱር፡ “ ኃይማኖት ስርዓት እንደ ነበርና ጣዖት አምላኪነት እንደጨመረ እንዲሁም ፍትሕ የተከለከለ እንደ ነበር ….. ከዚህም የተነሳ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት እግዚአብሄር ከአሶሪያዉያን ጥፋትን እና ምርኮን በማምጣት ሊቀጣት እንደ ነበር “ ተመልክቷል ፡፡ ዮናስ እንደ ሁለተኛ አካል በሚያገለግለዉ በናሆም ትልቅ ታሪክ ዉስጥ እንደ መጀመሪያ አካል ሊታይ ይችላል ፡፡

በመጨረሻም በዮናስ ዮናስ ለእግዚአብሄር ትዕዛዝ ታዛዥ ከሆነ በኋላ ስለ ኃጢዓትዋ የነነዌን ንስኃ መግባት እናያለን፡፡ በነነዌ ከአገልግሎቱ ስኬት የተነሳ ዮናስ በቀዳሚነት እንደ እስራኤል ነቢይ አልታሰበም ፡፡ ነነዌ የአሶር ዋና ከተማ ነበረች ፤ ማክአርቱር እንደ ተመለከተው ነነዌ “ በጭካኔዋ/በጋፏ የታወቀች ነበረች “ በተጨማሪም “ የእስራኤል እና የይሁዳ ታሪካዊ ጠላት ነበረች “ ፡፡ ነነዌ በኖህ የልጅ ልጅ በኒምሮድ የተመሰረተች እና ምናልባትም በቀደመዉ አለም ታላቅ ከተማ ነበረች ፡፡

ትምህርት

ዮናስ (1፡ 1-12)፡ እግዚአብሄር ዮናስን ወደ ነኔዌ በመሄድ “ በእርሷ ላይ እንዲሰብክ “ አዘዘው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ዮናስ ሄዶ የሚሰብካቸዉ ከሆነ ነነዌዋዊያን ንስኃ እንደሚገቡ ስላወቀ “ ከእግዚአብሄር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኮብለል ተነሳ “ (ቁጥር 3) ፡፡ ዮናስ ለነነዌ ስበክ ከሚለዉ ከእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለመራቅ በጀልባ ለመጓዝ ከፈለ ፤ ፅሁፉ ዮናስ “ ከእግዚአብሄር ፊት ሽሽትን “ እንዳደረገ በቁጥር 3 ዉስጥ ሐረጉን ሁለት ጊዜ በመጠቀም ግልፅ ያደርገዋል ፡፡

ማክአርቱር በምዕራፍ 1 አራት የዮናስ ታሪክ ክፍሎችን ፅፏል፡

  1. “ የዮናስ ተልዕኮ (1፡ 1-2) “
  2. “ የዮናስ ጎዞ (1፡ 3) “
  3. “ የዮናስ ፍላጎት (1፡ 4-16) “ - ዮናስ በጀልባዋ ላይ በእንቅልፍ ወደቀ ፤ ማዕበልም በባህሩ ላይ ማናወጥ ጀመረ ፤ ዮናስም ለተሳፋሪዎቹ ማዕበሉ ለእግዚአብሄር ባለመታዘዙ ምክንያት እንደነበር በመናዘዝ አንስተዉ እንዲወረዉሩት ነገራቸው ፡፡
  4. “ የዮናስ ማቆያ (1፡ 17) “ - ዮናስ “ በትልቅ አሳ “ በመዋጥ ለሰዎስት ቀን እና ምሽት በሆዱ ዉስጥ ነበር ፡፡

ዮናስ 2፡ ማክአርቱር በምዕራፍ 2 “ ለእግዚአብሄር ፍቃድ የዮናስ መታዘዝን “ በአራት ደረጃዎች ተመልክቶታል፡

“ የዮናስ ረዳት ማጣትን (2፡ 1-3) “

“ የዮናስ ፀሎት (2፡ 4-7) “

“ የዮናስ ንስኃ መግባት (2፡ 8-9) “ በመጨረሻም ዮናስ ለእግዚአብሄር የሚያስፈልገውን እና መታዘዙን ለእርሱ አሳወቀ ፡፡

“ የዮናስ ነፃ መዉጣት (2፡ 10) “

ዮናስ 3፡ ዮናስ ለእግዚአብሄር ፍቃድ ከታዘዘ በኋላ ለነነዌ በመስበክ የታዘዘ እንዲሆን ሁለተኛ እድል ተሰጠው (ቁጥር 1-3) ፡፡ ዮናስ ነነዌ ለመድረስ ከጆፓ 500 ማይል ይጓዛል ፡፡ ነነዌ በራሷ ትልቅ ነበረች በአጠቃላይ ከተማዋን ለመዞር ሰዎስት ቀን ትወስዳለች ፡፡ ዮናስ ነነዌ በ40 ቀናት ዉስጥ እንደምትጠፋ አወጀ ፤ የነነዌ ሕዝቦችም ታዛዡ ነቢይ የእግዚአብሄርን መልዕክት እንዳወጀ በማመን ፆምን በማወጅ በንስኃ ማቅ ለበሱ (ቁጥር 5) ፡፡

ኢየሱስ ለዮናስ መልዕክት የነነዌዋዊያን ምላሽ ትዉልዱን እንደመዉቀሻነት ተጠቅሞታል፡ “ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው ፡- ክፉና አመንዝራ ትዉልድ ምልክት ይሻል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠዉም ፡፡ ዮናስ በአሳ አንባሪ ሆድ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት እንደ ነበር እንዲሁ የሰዉ ልጅ በምድር ልብ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት ይኖራል ፡፡ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትዉልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል ፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና እንሆም እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ ! “ (ማቴ 12፡ 39-41) ፡፡ ኢየሱስ በአሳዉ ሆድ ዉስጥ የዮናስን ጊዜ ከሞት እንደሚነሳ ትንቢት ለመናገር እንደ መንገድ ተጠቀመበት ፤ ለዮናስ ቃላችን ትንሳኤ የሆነዉም ለዚያ ነው ፡፡ “ ኢየሱስም ፡- ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያዉ ይሆናል “ አላት (ዮሐ 11፡ 25) ፡፡ የዮናስ መፅኃፍ መልዕክት ወንጌልን ይሰብካል ፡፡

የነነዌ ንስኃ በሙሉ ነበር ንጉሱ እንኳን ሳይቀር “ ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያዉን አወለቀ ማቅም ለበሰ በአመድም ላይ ተቀመጠ “ (ቁጥር 6) ፤ እንስሳትን ጨምሮ ሁሉም ከዉኃና ከምግብ እንዲፆዉ አዋጅን አስነገረ ፡፡ ዮናስ ከተሳሳተ በኋላ እግዚአብሄር ዮናስን ሁለተኛ በመስጠት እግዚአብሄር ታላቂቱን ከተማ ወደ ንስኃ ለመምራት ተጠቀመበት ፡፡ ነነዊዋዊያን “ ከክፉ መንገዳቸዉ ስለተመለሱ እግዚአብሄርም ያደርግባቸዉ ዘንድ የተናገረዉን/ያሰበዉን ጥፋት ተወው “ (ቁጥር 10) ፡፡

ዮናስ 4፡ የነነዌዋዊያን ንስኃ ዮናስን “ በኃይለኛው አበሳጨው/አላስደሰተውም “ (ቁጥር 1) ፡፡ ዮናስ የእግዚአብሄር ፍቃድ ካደረገ በኋላ የእግዚአብሄርን ፍቃድ አድርጎ እንደ ነበር ወይስ እንዳልነበር መጠየቅ ጀመረ ፤ ከዚያም ዮናስ በእግዚአብሄር ተገሰፀ (ቁጥር 6-11) ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ነነዌዋዊያን ስለሚያስብ ንስኃቸዉን ይፈልገዋል ፡፡

ትምህርት

ዮናስ ወንጌልን ገለጠ ፤ ያንግ ለሙኤል ዮናስ ወንጌልን የገለጠበትን ስድስት መንገዶች ለይቷል/አስቀምጧል፡

“ ልክ እንደ ዮናስ ኃጢዓታችን ከእግዚአብሄር ፊት ይለየናል “

“ የኃጢዓት ሕይወት ለመያዝ በጣም ትልቅ የሆነ ማዕበልን ያመጣል “

“ ተፅዕኖ “ - ኃጢዓታችን ሌሎች ላይ ተፅዕኖ አለው ፤ የዮናስ ኃጢዓት በመርከቧ ላይ ላሉት ተሳፋሪዎች ለችግር ምክንያት ሆኗል ፡፡

“ የዮናስ ታሪክ የእግዚአብሄር ፍቅር ያሳያል “

“ ኢየሱስ ከዮናስ ይበልጣል “

“ እምነት የእግዚአብሄር ቃል ከመስማት የሚመጣ ነው “ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 1006.

  2. MacArthur, p. 1006.

  3. MacArthur, p. 1007.

  4. MacArthur, p. 1008.

  5. MacArthur, p. 1007.

  6. MacArthur, p. 1008-1010.

  7. MacArthur, p. 1011.

  8. Lemuel Young, “6 Ways Jonah Reveals the Gospel”; available at https://www.grace.one/blog/6-ways-jonah-reveals-the-gospel.

ጥያቄዎች

  1. በዮና (1፡ 4-5) መሰረት ታላቅ ማዕበል በተነሳ ጊዜ ዮናስ በመረከቡ ታችኛዉ ክፍል ላይ ተኝቶ ነበር ፤ ይህ በማቴ (8፡ 24-25) ካለዉ ከመሲሁ ጋር እንዴት ይመሳሰላል ?
  2. በማቴዎስ ዉስጥ አንዳንድ ዝርዝሮች የዮናስ ክፍል ነጸብራቅ ሊሆን ይችላል ፤ በዮና (1፡ 14) በመርከቡ ላይ ያሉት ሰዎች ቃል እና በማቴ (27፡ 25) ካለዉ የሕዝብ ቃል ጋር እንዴት ይለያያል ? ሰ
  3. ዮናስ በታላቁ አሳ ሆድ ዉስጥ ምን ያክል ጊዜ ቆዬ (ዮና 1፡ 17) ? ይህ እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል ? (ማቴ 12፡ 40)
  4. በምዕራፍ 2 የትኛዉ የዮናስ ጸሎት ወደ መሲሁ ያመለክታል ?ሰ (መዝ 16፡ 10, 103, 4, ዮና 2፡ 2, 4, ማቴ 28፡ 6)
  5. ዮናስ (ዮና 4፡ 2) እግዚአብሔር በነነዌ ንስኃን ካዬ ዮናስን በእነርሱ ላይ እንዲያዉጅ የላከዉን መቅሰፍት እንደሚተወዉ ያውቃል (ዘጸ 34፡ 6, ዘኁ 14፡ 18, ነህ 9፡ 31, መዝ 86፡ 5, 15, 103፡ 8, 145፡ 8) ፤ እግዚአብሔር የመቅሰፍት ማስጠንቀቂያን በእነርሱ ላይ ባመጣ ጊዜ ከእስራኤል እና ከይሁዳ እንዲህ አይነት ምላሽን ይፈልጋል ( 2ዜና 7፡ 13-14, ኢሳ 30፡ 15, 18, ኤር 18፡ 5-11) ? ነነዌ ንስኃ ገብታ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለምን እንዳልገቡ ምን ታስባላችሁ ?
  6. በዮናስ (1-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jonah 2:7–9

“As my life was fading away, I remembered Yahweh. My prayer came to You, to Your holy temple. Those who cling to worthless idols forsake faithful love, but as for me, I will sacrifice to You with a voice of thanksgiving. I will fulfill what I have vowed. Salvation is from the LORD!”

እግዚአብሔር ለነነዌ ሰዎች መልዕክቱን ያደርስለት ዘንድ ዮናስን ጠራው፡፡ ሆኖም ግን ዮናስ ከተሰጠው ጥሪ ሸሸ አመለጠ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በዮናስ ህይወት ላይ ወጀብን አስነሳ ከዚህም አልፎ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ጭምር እንድገባ አደረገው፡፡ ልክ ዮናስ በነነዌ ከተማ መልዕክቱን ሲናገር፣ የነነዌ ሰዎች ከክፉ መንገዳቸው በመመለስ እግዚአብሔርን ፈለጉ፡፡ ዮናስም እግዚአብሔር ለነነዌ ሰዎች ባደረገው ምህረት በመናደድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም ዮናስን ገሰጸው፡፡

እናንተም ምናልባት ከዮናስ ጋር በሆነ መንገድ ወይም በጠቅላላው የሚመሳሰል ታሪክ ይኖራችሁ ይሆናል፤ ምናልባት እናንተም ፡- ከእግዚአብሔር ፍቃድ መሮጥ፣ በህይወት ውስጥ ወጀብ መነሳት፣ በታማኝነት የእግዚአብሔርን ጥሪ መፈጸም፣ እግዚአብሔር በኃይል ሲሰራ ማየት፣ በዙሪያችሁ ባሉ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ሲያንጸባርቅ ማየት፣ ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ወይም መጸለይ ወይም ደግሞ በእግዚአብሔር መገሰጽ፡፡ ያላችሁት የትም ይሁን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ እርሱ ሉዓላዊ ነው ደግሞም ይሰራል፡፡ እርሱ በድካማችሁ የሚያበረታችሁ ነው፡፡ ዛሬ ኢየሱስን ለማመን እምነት ይኑራችሁ ደግሞም በእያንዳንዷ የህይወታችሁ ወቅት ጊዜ ውስጥ እርሱ እንደሚሰራ እመኑ፡፡ እርሱን ፈልጉት፣ አይኖቻችሁንም በእርሱ ላይ አድርጉ፤ እርሱን ማየት በማትችሉበት ጊዜ ሳይቀር እንኳ እመኑት፡፡ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው አዎን በእርግጥም እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፡፡

“ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።”

  • ዮናስ 2፡7-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 12:39–41 — “ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።”

ሉቃስ 11:30 — “ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል።”

ሮሜ 10:9–10 — “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።”