Minor Prophets Obadiah

Judgment On Edom And Others

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Established King Obadiah 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 695 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እስካሁን ከአስራ ሁለት ታናናሽ ነቢያት ጥናታችን ዉስጥ ሆሴዕን፣ ኢዩኤልን እና አሞጽ አጥንተናል ፡፡ ዛሬ ወደ አጭሩ መጽኃፍ ወደ አብድዩ እንሄዳለን ፡፡ ሁሉም ታናናሽ ነቢያቶች እንዲሁም ደግሞ ታላላቅ ነቢያቶች ወደ አሶራዊያን ወይም ደግሞ ወደ ባቢሎናዊያን ምርኮ ይመራሉ ፤ በተጨማሪም ሁሉም ነቢያቶች ለሰሜኑ መንግስት ለእስራኤል ወይም ደግሞ ለደቡቡ መንግስት ለይሁዳ መልዕክት ነበራቸው ፤ ሁሉም ፍርድበአሶራዊያን ወይም በባቢሎናዊያን ሰራዊት በኩል እየመጣ እንደነበር ተናግረዋል ፡፡ ይሁን እንጂ የአብድዩ መልዕክት ከሌሎቹ ከሁሉም ነቢያት የተለዬ ነበር ፡፡

የአብድዩ ስም “ የእግዚአብሄር አገልጋይ “ ማለት ነው ፡፡ የአብድዩ መጽሐፍ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ አጭሩ መጽሐፍ ነው ፡፡ በመጽሐፉ ዉስጥ አንድ ምዕራፍ ብቻ ነው ያለው ፡፡ ስለ ነቢዩ አብድዩ የሚታወቅ ምንም ነገር የለም ፡፡ ስሙ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ አስራ አንድ ጊዜ ተጠቅሷል ነገር ግን ነቢያትን በማመልከት አልተገለጠም ፡፡ አንዳንድ ምሁራን አብድዩ በተደጋጋሚ ይሁዳን፣ ኢየሩሳሌምን እና ፂዎንን ስለጠቀሰ የደቡቡ መንግስት የይሁዳ አካል እንደ ነበር ያምናሉ ፡፡

ምሁራን አብድዩ የኤልያስ እና የኤልሳ ዘመን ሰዉ እንደ ነበር ያመለክታሉ ፡፡ ማክአርቱር “ የተፃፈበትን ቀን በሚገባ ለመወሰን ስለሚያስቸግር በቁጥር (10-14) እንደተገለፀው በኢየሩሳሌም ላይ ከኤዶምያስ ጥቃት ጋር የተገናኘ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ በመሰረቱ በብሉይ ኪዳን ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ አራት ወረራዎች ነበሩ አብድዩም ከእነርሱ ከአንዱ በኋላ ጻፈ ፤ ማክአርቱርእነዚህን ወረራዎች አስቀምጧቸዋል፡ “ 1) ከክርስቶስ ልደት 925 በፊት በሮብዓም ዘመን በግብፅ ንጉስ በሺሻቅ (1ነገ 14፡ 25, 26, 2ዜና መዋዕል 12)፣ 2) ከክርስቶስ ልደት (848-841) በፊት መካከል በይሁዳ ንጉስ በኢዮራም ዘመን በፍልስጤማዊያን እና በአረቦች (2ዜና 21፡ 8-20)፣ 3) ከክርስቶስ ልደት 790 በፊት በእስራኤል ንጉስ በኢዮአስ (2ነገስት 14, 2ዜና መዋዕል 25) እና 4) ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በኢየሩሳሌም መዉደቅ በባቢሎን ንጉስ በናቡከደነፆር “ ፡፡ ማክአርቱር በታሪካዊ ማስረጃነት መሰረት ሁለተኛዉ እና አራተኛዉ ወረራዎች ትክክለኛነት እንዳላቸው ነገር ግን በቁጥር 1 ከተሰጠው መረጃ የተነሳ ሁለተኛዉ ወረራ የሚሆን እንደሚመስል ይናገራል ፡፡

ኤዶማዊያን ከይስሐቅ እና ከርብቃ ታላቅ ልጅ የኤሳዉ ወገን/ልጆች ናቸው (ዘፍ 25፡ 24-26) ፡፡ ኤሳዉ የያዕቆብ መንታ ወንድም እና በማህፀን ዉስጥ ከያዕቆብ ጋር የታገለ ነበር (ዘፍ 25፡ 22) ፡፡ ወንድማማቹቹ በፍጹም አልተግባቡም ያዕቆብም እርሱ በኩር እንዲሆን ብኩርናዉን እንዲሸጥለት ኤሳዎን ሸወደው ፡፡ የኤሳዉ ስም ትርጉም “ በሁሉም አካሉ ላይ በጸጉር የተሸፈነ ልብስ ይመስል ስለነበር “ “ ፀጉሯም “ ማለት ነው ፡፡ በተጨማሪም ኤሳው ብኩርናዉን “ ለቀይ ወጥ “ ስለሸጠ (ዘፍ 25፡ 30) ቀይ ማለት በሆነዉ ኤዶም በማለትም ይጠራል ፡፡ ያዕቆብም እስራኤል በመባል ይታወቅ ነበር ፡፡

ኤሳዉ ከእግዚአብሄር ጋር ያለዉን የኪዳን ስምምነት በመጣስ ሁለት ከነዓናዊያንን ሴት እና ከዚያም የእስማኤልን ልጅ አገባ (ዘፍ 26፡ 34, 28፡ 9) ፡፡ ኤሳው እግዚአብሄር ባርኮት በነበረዉ ዘር በአብርኃም፣ በይስሐቅ እና በያዕቆብ ላይ ማድረግ የሚችለዉን ሁሉ አደረገ ፡፡ ልጆች በነበሩበት ጊዜ ኤሳዉ እንደ አዳኝ ወጪ ዉጪ ማለትን ሲመርጥ ያዕቆብ ደግሞ ቤት መቀመጥን መረጠ (ዘፍ 25፡ 27) ፡፡ ኤሳዉ ከሙት ባህር በስተ ደቡብ በኩል በሚገኝ በተራራማ ስፍራ ላይ ሰፈረ ፤ ያዕቆብ በመልካም መሬት ላይ ተቀመጠ ፡፡ እነዚህ ሁለት ወንድ ልጆች ቀድሞ ተነግሮ እንደ ነበረው እርስ በእርስ ጠላት የሆኑ ሁለት ሕዝቦችን መሩ (ዘፍ 25፡ 23) ፡፡ በግልጽ የእግዚአብሄር እጅ በያዕቆብ እና በኤሳዉ ላይ ነበር በኤሳዉ እና በኤዶም ላይ ደግሞ እግዚአብሄር በተቃራኒ ነበር ፡፡

ትምህርት

አብድዩ (1-9)፡ በቁጥር 1 እግዚአብሄር ስለ ኤዶምያስ ቃልን በማወጅ በኤዶምያስ ላይ እንዲነሱ በአሕዛብ መካከል መልዕክተኛን ልኮ እንደ ነበር ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር የኤዶምያስን ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ያነሰ እንደሚያደርገዉ እና በኃይለኛዉ የተናቁ እንደሚሆኑ ተናገረ (ቁጥር 2) ፡፡ እግዚአብሄር እንደማይነኩ ይሰማቸዉ በነበረዉ በዋሻ ዉስጥ መኖራቸው የዉሸት ደህንነት ይሰማቸዉ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 3) ፤ ኤዶማዊያንን ማግኘት ለሰዉ አስቸጋሪ ቢሆንም እግዚአብሄር ወደታች ያወርዳቸዋል (ቁጥር 4) ፡፡ እግዚአብሄር ኤዶማዊያን ቤታቸዉን በከዋክብት ላይ ቢሰሩም እንኳን አሁንም በፍርዱ አዉርዶ ያመጣቸዋል ፤ ኤዶምያስ ብቻ ሳይሆን የሚያወርደው በጣም ተኩራርተዉበት የነበረው ኃብታቸዉም የተዘረፈ ይሆናል (ቁጥር 5-6) ፡፡ እንደ ዋይርስቤ ገለፃ “ እግዚአብሄር ስለሚሰራ ጥምረታቸው የተሰበረ ይሆናል (ቁጥር 7) “ ፡፡

“ በዚያ ቀን “ እግዚአብሄር የኤዶምያስን ጥበብ እንደሚያጠፋ ቃል ገባ (ቁጥር 8) ፡፡ ዋይርስቤ “ የምስራቅ ሰዎች በጥበባቸው የታወቁ እንደነበሩ ( 1ነገ 4፡ 30) እና ይህምኤዶማዊያንን እንደሚያካትት…..የኢዮብ ወዳጅ ኤልፉዝ በኤዶምያስ ከቴማን ነበር (ኢዩ 2፡ 11, ኤር 49፡ 7) ፤ ያለ ጥበብ የኤዶማዊያን መሪዎች ትክክለኛ ዉሳኔ ማድረግ እንደማይችሉ እና ዉጤቱም ጋራ የሚያጋባ እንደሚሆን “ ይገልፃል ፡፡ ቴማን የኤሳዉ የልጅ ልጅ ነበር የቴማንም ሰራዊት ይጠፋል (ቁጥር 9) ፡፡

አብድዩ (10-14)፡ ኤዶምያስ በእፍረት የተሸፈነ ይሆናል በያዕቆብ/በእስራኤል ላይ ስላደረጉት ግፍ ለዘላለም ይጠፋሉ (ቁጥር 10) ፤ ለኤዶምያስ ቅሬታዎች እንዲድኑለት ተስፋ እንዳልነበረዉ አስተዉሉ ፡፡ በቁጥር 11 እግዚአብሄር በይሁዳ ላይ የኤዶምያስን ኃጢዓት አሳዬ - እስራኤል ስትያዝ እና ቅድስቷ ከተማ ኢየሩሳሌም ስትዘረፍ ቆመዉ ሲመለከቱ ነበር ፤ ኢየሩሳሌምን ወረዉ የነበሩትን በመርዳት በይሁዳ ዉድቀት ተደሰቱ (ቁጥር 12) ፤ እንዲሁም ኤዶምያስ ከተማዋን በመዝረፍ ዉድቀታቸዉን በማምጣት ተራዳ ፡፡ የኮበለሉትን እንኳን ከምርኮ እንዳያመልጡ ከለከሏቸው (ቁጥር 13-14) ፡፡

አብድዩ (15-18)፡ እግዚአብሄር የክርስቶስ ተመልሶ መምጫ በቀረበ ጊዜ “ በእግዚአብሄር ቀን “ በእስራኤል ላይ በዞሩት ሕዝቦች ሁሉ ላይ ይመጣባቸዋል አለ ፡፡ አሕዛቦች በእስራኤል ላይ አድርገዉት የነበረዉ ነገር በእነርሱ ላይ ይሆናል (ቁጥር 15) ፤ እስራኤልን ያለ አግባብ ለጎዱት ሌሎች ለሁሉም ሕዝቦች ምን እንደሚሆንባቸዉ ኤዶምያስ ምሳሌ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን የቁጣ ጽዋ ይደርስባቸዋል በፍጹምም ሆኖ እንደማያዉቅ ይሆናል (ቁጥር 16) ፡፡ የፂዎን ተራራ ነፃ በመዉጣት እንደ ገና ቅዱስ ይሆናል (ቁጥር 17) ፤ የያዕቆብ እና የዮሴፍ ቤት ሌሎች ሕዝቦችን ወደ ገለባ ለመቀየር የሚነድድ እሳት ይሆናሉ (ቁጥር 18) ፡፡ በእስራኤል ላይ ቆመዉ የነበሩት ድኖ የሚተርፍ አይኖራቸዉም ፡፡

አብድዩ (19-21)፡ አይሁዶች በመጀመሪያ ለእነርሱ ተሰጥታ ወደነበረችዉ ምድር ይመለሳሉ (ቁጥር 19-20) ፡፡ ለመግዘት “ አዳኞች “ በፂዎን ተራራ ላይ ይሆናሉ መንግስቱም የእግዚአብሄር ይሆናል (ቁጥር 21) ፡፡ “ አዳኞች “ የሚለዉ ቃል “ ነፃ አዉጪዎች “ በማለት መረዳት ይቻላል ፡፡ ዋይርስቤ “ ንጉሱ መሲህበሕዝቦች ላይ ሲፈርድ/ሲያስተዳድር የሚረዱት አዳኞች እንደሚኖሩት “ ይገልፃል ፡፡

መደምደሚያ

አብድዩ ለሺዉ አመት መንግስት የተዘጋጀን እንድንሆን ያመለክታል ፤ ራዕ (11፡ 15) “ ሰባተኛዉም መልዓክ ነፋ ፤ በሰማይም የዓለም መንግስት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሳል “ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1001.

  2. MacArthur, p. 1001.

  3. MacArthur, p. 1001.

  4. MacArthur, p. 1001.

  5. MacArthur, p. 1001.

  6. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 373.

  7. Wiersbe, p. 375.

  8. Wiersbe, p. 375.

ጥያቄዎች

  1. አብድዩ መልዕክቱን ከእግዚአብሔር እንዴት ተቀበለ ? ራዕዩ ስለማን ነበር ?
  2. ኤዶማዊያን ከማን የወጡ/የመጡ ነበሩ (ዘፍ 25፡ 24-26, 36፡ 8) ? የያዕቆብ እና የኤሳዉ ያለፈ ታሪክ ምን ነበር ? ኤሳዉ ለእግዚአብሔር እንዴት ያልታዘዘ ነበር ? (ዘፍ 25፡ 22, 25, 27, 30, 26፡ 34, 27፡ 38-40, 28፡ 9)
  3. የኤዶም የሚገልፀዉ ባህሪይ ምን እንደ ነበር ምን ትላላችሁ (ኤር 49፡ 16, አብ 3) ? እብሪተኛ ወይም ትዕቢተኛ ልብ ምንን ታስከትላለች (ምሳ 11፡ 2, 16፡ 18, ሕዝ 7፡ 10-12) ? እግዚአብሔር ስለ ትዕቢት እንዴት ይናገራል ? (ሉቃ 14፡ 11, ያዕ 4፡ 6)
  4. ኤዶም ምን ኃጢዓትን አድርጎ ነበር ? (አብ 10-16)
  5. እግዚአብሄር ለራሱ ሕዝቦች ምን ሰዎስት ተስፋዎችን ሰጠ ? (አብ 17-18, 19-20, 21)
  6. በአብድዩ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Obadiah 1:15

“For the Day of the LORD is near, against all the nations. As you have done, so it will be done to you; what you deserve will return on your own head.”

እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ ትንቢትን ይናገር ዘንድ አብድዩን ጠራው ፡፡ አብድዩም በእስራኤል ላይ ስለሰራሽው በደል ትዋረጃለሽ ለዘላለምም ትጠፍያለሽ በማለት በኤዶምያስ ላይ ተናገረ ፡፡ በአብድዩ በኩል የመጣው የእግዚአብሔር መልዕክት በእስራኤል ላይ በጠላትነት የተነሱ ህዝቦች ሁሉ የእግዚአብሔርን ፍርድ እንደሚቀበሉ ይናገራል፡፡

የአብድዩ መጽሐፍ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ያስጠነቅቃል ነገር ግን ደግሞ የእግዚአብሔርንም ፍቅር እንድታከብሩ ያደርጋችኋል ፡፡ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን እየመጣ ነው! ክርስቶስም ተመልሶ ይመጣል ይገዛም ዘንድ በጽዮን ተራራ ላይ ይቀመጣል ፡፡ የእርሱን ክቡር የሆነ ዳግም ምጽዓት ስትጠባበቁ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን ለመመልከት አይኖቻችሁን ግለጡ፡፡ ሌሎች በእምነታቸው ፈተና ውስጥ ሲገቡ ወይም የመከራ ጊዜን ሲያሳልፉ ስታዩ ልክ እንደ ኤዶማውያን በእነርሱ ላይ የሚያሾፍ፣ በውድቀታቸው ደስ የሚሰኝና በሀዘናቸው የሚስቅ እንዳትሆኑ ፡፡ ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር የተመረጠ ዕቃ የፍቅሩ መገለጫ ሁኑ፣ ምህረትን ቸርነትን አድርጉ፣ የዋህነትን አድርጉ፡፡ በዚህ መንገድ ለክርስቶስ ዳግም ምጻት ሰዎች ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ እናንተም ትዘጋጃላችሁ፡፡ እግዚአብሔርም ሰዎች ሁሉ የእርሱን ታማኝ ፍቅርና ምህረት ያውቁ ዘንድ ይፈቅዳል፡፡

“የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።”

  • አብድዩ 1፡15

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 145:8 — “እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፡፡”

ሐዋርያት ስራ 9:15 — “ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ”

ራእይ 11:15 — “ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።”