Minor Prophets Amos

Amos' Visions

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Restorer Amos 7-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 694 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ከታናናሽ ነቢያት ዉስጥ አንዱ የሆነዉን የአሞጽ ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ ታናናሽ ነቢያት አስፈላጊነቱ ከመወሰኑ የተነሳ ነገር ግን የመልዕክቱን እርዝማኔ ለመግለፅ እንጂ “ ታናናሽ “ በሚለዉ አልተሰየሙም ፡፡ የአሞጽ መልዕክት በሰሜኑ መንግስት ለአስሩ ነገዶች ነበር ፡፡ በደቡቡ መንግስት ይሁዳ፣ ቢንያም እና ዋና ከተማቸዉ ኢየሩሳሌም ነበረች ፡፡ በታሪክ ዳዊት እና ልጁ ሰለሞን ሁለቱም አንድ በሆነዉ መንግስት ላይ አስተዳድረዋል ነገር ግን ከሰለሞን የአርባ አመት ዘመን በኋላ አንድ የሆነዉ መንግስት ወደ ሁለት ተከፈለ ፡፡

ታናናሽ ነቢያቶች ለእነዚህ መንግስታት ከእግዚአብሄር እየራቁ እየራቁ በሄዱ ጊዜ ተናግረዋል ፤ እዉነታው ከአንድኛቸዉም መንግስት ማንኛዉም ሕዝብ ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ የተጣሩትን የታናናሽን እና የታላላቅን ነቢያት ቃል አልያዙም ፡፡

አሞጽ (7-8) የፍርድ መልዕክት ነው ፡፡ አጠቃላይ ለአሞጽ መጽሐፍ ኢየሱስን የሚያንጸባርቀዉ ቃል ታዳጊ የሚል ሲሆን በአሞጽ መጨረሻም ላይ ይገኛል ፡፡

ትምህርት

አሞጽ (7-8)፡ በምዕራፍ 7 እግዚአብሄር አሞጽን በፊቱ የሆነ ነገር ሲሆን ሲመለከት ራዕይን ሰጠው ፤ ራዕዩ ከእግዚአብሄር የሆነ የአንበጣ መንጋ በመከር ወቅት ጊዜ በመምጣት በምድሪቱ ላይ ያለዉን ቅጠል ሁሉ ሲበሉት ነበር ፤ አሞጽ አንበጣዉ የእግዚአብሄርን ፍርድ እንደሚወክል በመረዳት ያዕቆብ (የማለትም የሰሜኑ መንግስት) እንዴት ይድናል በማለት ጠየቀ ፤ እግዚአብሄርም ፍርድ እንዲሆን እንደማይሆን ተስማማ (ቁጥር 1-3) ፡፡

ከዚያም እግዚአብሄር አሞጽን ምድሪቱን የሚበላ ሁለተኛ የእሳት እራዕይን ሰጠው ፤ እንደ ገና አሞጽ ስለ ሕዝቡ ለመነ እግዚአብሄርም የሚያመጣዉን ፍርዱን ተወው (ቁጥር 4-6) ፡፡

ከዚያም ሰዎስተኛዉ ራዕይ ታዬ ፤ እግዚአብሄር ወደታች ከቆመዉ ግድግዳ ቀጥሎ በእጁ ቱንቢን ይዞ ነበር ፤ እግዚአብሄር አሞጽን የማይታዘዙትን ሕዝቦቹን ለመዳኘት ቱንቢን እንደሚጠቀምባቸው ነገረው (ቁጥር 7-9) ፡፡ ፍርዱ በንጉስ ኢዮርብዓም ቤት ላይ ይመጣል ፡፡

ካህኑም አሜስያስ ስለ አሞጽ በሰማ ጊዜ በንጉሱ እና በኢዮርብዓም መንግስት ላይ የአሞጽን ቃል በሴራ/በተንኮል ላከው ፤ በተጨማሪም አሜስያስ አሞጽን ከዚያ ወደ ይሁዳ በመሄድ በዚያ መልዕክቱን እንዲሰጥ ነገረው ፡፡ አሞጽም እንዲሰራዉ/እንዲያደርግ ተጠርቶት እንደ ነበረዉ የእግዚአብሄርን መልዕክት ለእስራኤል እንደተናገረ መለሰለት (ቁጥር 10-16) ፤ በመቀጠልም አሞጽ የአሜስያስ ሚስ ገለሞታ እንደምትሆን፣ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቹ እንደሚሞቱ፣ ምድሪቱም የተከፋፈለች እንደምትሆን እና አሜስያስ እና ሌሎች ወደ ግዞት የተወሰዱ እንደሚሆኑ ትንቢትን ተናገረ (ቁጥር 17) ፡፡

አሞጽ (8፡ 1-14)፡ አራተኛዉ ራዕይ በምዕራፍ 8 ነው ፡፡ አሞጽ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አዬ ፤ ዋይርስቤ “ ይህ ፍሬ ለመበላት እንደተሰበሰበ የእስራኤል ሕዝቦችም ለፍርድ ይሰበሰባሉ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መጨረሻ መጥቷል አለ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ቁጥር (3-8) እስራኤል አድርጋዉ ስለ ነበረዉ ክፋት ይናገራል ፤ ስለዚህም እግዚአብሄር በዓላታቸዉን/ድግሳቸዉን ወደ ኃዘን ይቀይረዋል ሁሉም በኃዘን በማቅ ልብስ ይሆናሉ (ቁጥር 10) ፡፡ ጄ.ቬሮና ማክጊ ቁጥር (11-14) “ የጨለማ ቀን ይመጣል “ በሚል ያጠቃልላቸዋል ፡፡

አሞጽ (9፡ 1-10)፡ በአምስተኛዉ ራዕዩ አሞፅ ጌታን በመሰዊያዉ አጠገብ ቆሞ አየው (ቁጥር 1) ፤ ይህ ተስፋ ያለዉ ንግግር/ፅሁፍ ይመስላል ነገር ግን ከሌሎቹ የከፋ ነበር ፡፡ ቁጥር (1-10) ስለ ፍርድ እና ጥፋት ናቸው ፤ ቤተ መቅደሱ የጠፋ ይሆናል ሕዝቡም ለማምለጥ ያልተሳካ ሙከራ ያደርጋሉ ፡፡ ለመደበቅ የትም ቢሞክሩ ምንም የለም ፤ ሲዖል ጥልቀት ድረስ ወይም ከአለም ከፍተኛ ስፍራ ሰማይ ላይ ቢሄዱም የሚያድን የለም ፣ ከስፍራቸዉ ከፍተኛዉ ስፍራ ቀርሜሎስ ተራራ ላይ መዉጣት ቢችሉም ወይም ዝቅተኛዉ ስፍራ ባህር ዉስጥ ቢሄዱም የሚያድን የለም ፡፡ እግዚአብሄር በባህሩ ወለል ላይ ለመደበቅ ከሞከሩ የባህሩን እባብ እንዲነድፋቸዉ አዘዋለሁ አለ ፡፡ በምርኮ ተወስደዉ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር እንደሚያገኛቸዉ እና በእነርሱ ላይ ፍርዱን ያሳልፋል (ቁጥር 1-4) ፡፡ በሮሜ (8፡ 38-39) ጳዉሎስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሄር ፍቅር ማንም ሊለየን እንደማይችል ፅፏል ፡፡

አሞጽ የእግዚአብሄርን ኃይል እንደ ፈጣሪ ምድርን መንካት እንደሚችል እና እንደምትቀልጥ ገለፀ ፡፡ ማክአርቱር “ አመቱን ሙሉ በታላቅነት በዳርቻዎቹ በመፍሰስ ለገበሬዎች ዉኃን እና የበለፀገ የአፈር ፍርስራሽን እንደሚሰጠዉ የናይል/የአባይ ወንዝ ፍርድ ስለ ሕዝቡ ፅድቅ ስለሌለዉ ትዕቢታቸው በእስራኤል ምድር ላይ እንደሚፈስስ “ ይገልፃል ፡፡

በቁጥር 7 እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እንደ ኩሾች፣ እንደ ፍልስጤማዊያን እና እንደ ሌሎች ኃጢዓተኛ ሕዝቦች እንደ አረማዉያን ተመሳሳይ እንደ ነበሩ ነገራቸው ፡፡ ይሁን እንጂ የእስራኤል ፍርድ እንደ እነዚህ ሕዝቦች የከፋ አይሆንም ምክንያቱም እግዚአብሄር እስራኤልን ሙሉ ለሙሉ ስለማያጠፋ ፡፡ የእግዚአብሄር አይኖች በእስራኤል ሕዝቦች ላይ ነበሩ (ቁጥር 8) ፡፡ በሌሎች ሕዝቦች የእስራኤልን ቤት እያናወጠ ነበር ነገር ግን የእስራኤል ቅሬታ ያስቀራል (ቁጥር 9) ፤ በሚያናድድ ሁኔታ በቸልተኝነት እና በኃጢዓታቸዉ ጥፋት አያገኘንም ብለዉ የሚያስቡት በሰይፍ ይሞታሉ (ቁጥር 10) ፡፡

አሞጽ (9፡ 11-15)፡ ይሁን እንጂ አደገኛ ማስጠንቀቂያዎቹ እያሉ በአሞጽ መልዕክት ዉስጥ ተስፋ ነበር ፡፡ ለዳዊት የሚታደሱ ቅሬታዎች ይኖሩታል (ቁጥር 11) ፡፡ ምድሪቱ መልሳ ትገነባለች ቅሬታዎቹም እስራኤልን ባሸነፏት ሕዝቦች ላይ ስልጣን/ኃይል የተሰጣቸዉ ይሆናሉ ፤ እግዚአብሄር ይህ ሁሉ እንዲሆን ያደርጋል (ቁጥር 12) ፡፡

ቁጥር 13 በብልፅግና ስዕል/መልክ ይጀምራል ፡፡ ወይን ጠማቂ አራሾች፣ ዘርን ዘሪ ገበሬዎች ወደ ስራቸዉ ይመለሳሉ ፤ ተራሮች እና ኮረብቶች የሚንጠባጠብ ወይንን ያፈስሳሉ ፤ የሕዝቡም ምርኮ የተመለሰ ይሆናል፣ ከተሞቻቸዉን እንደ ገና ይገነባሉ፣ ወይንን እንደ ገና ይተክላሉ እንዲሁም አትክልቶችን ይተክላሉ (ቁጥር 14) ፡፡ እግዚአብሄር ቅሬቶቹን በምድራቸዉ እንደሚተክላቸው እና ከዚህ በኋላ እንደ ገና በፍጹም እንደማይነቅላቸዉ ቃል ገባ (ቁጥር 15)፡፡

ቁጥር (11-15) የሚመጣዉ የሺዉ ዘመን መንግስት መልክ ናቸው ፡፡ ከሰባቱ የመከራ አመታት በኋላ ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ለአንድ ሺህ አመት ይገዛል ፤ ያ ዘመን በእነዚህ ቁጥሮች የተገለፀዉ ነው ፡፡

መደምደሚያ

አሞጽ ከፍርድ ወደ መታደስ ሄደ ፡፡ ክርስቶስ በሚመለስ ጊዜ መልሶ በምድራቸዉ አይሁዶችን ይተክላቸዋል ፤ ኢየሱስ የመጨረሱ ታዳጊ ስለሆነ እንደ ገና በፍጹም አይነቀሉም ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 365.

  2. J. Vernon McGee, “Outline for Amos”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/amos/amos-outline.cfm.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 999; see note for Amos 8:8.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር የመጀመሪያዉን ራዕይ ባሳየው ጊዜ አሞጽ ለሕዝቡ እንዴት ማለደ (አሞ 7፡ 1-3) ? በመጽሃፍ ላይ ሌሎች ሰዎች ለሕዝቡ በምን ማለዱ ? (ዘፍ 18፡ 22-32, ዘጸ 32፡ 30-32, ሮሜ 9፡ 1-3)
  2. እግዚአብሄር ለአሞጽ የሰጠዉ አምስት ራዕዮች ምን ነበሩ ? (አሞ 7፡ 1-9, 8፡ 1-3, 9፡ 1-6)
  3. አሞጽ ለሕዝቡ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ራዕዮች ለምን እንደማለደ ነገር ግን በመጨረሻዎቹ በሰዎስቱ ለምን እንዳልማለደላቸው ምን ታስባላችሁ ? (ኤር 7፡ 16, 11፡ 14, 14፡ 11)
  4. ካህኑ አሜስያስ ለአሞጽ ትንቢት እንዴት ምላሽን ሰጠ (አሞ 7፡ 10-13) ? አሞጽ ጥሪዉ ከእግዚአብሄር እንደሆነ በምን እዉቅና ሰጠ ?
  5. እግዚአብሄር አሞጽ ከአሜስያስ አስቸጋሪ ፈተና ሲገጥመዉ እና እንዲናገር ጠንካራ ራዕዮችን ሲሰጠው ከሁለቱም በኋላ እንዴት አበረታው (አሞ 9፡ 11-15) ? በመጽኃፍ ላይ በአስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ ካለፉ በኋላ ሌሎችን እግዚአብሄር እንዴት አበረታቸው (ሐዋ 18፡ 9-11, 27፡ 21-26, 2ጢሞ 4፡ 16-17) ? እግዚአብሄር በአስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ ስትሄዱ ወይም ስትወጡ ያበረታችሁን ጊዜ አስቡ
  6. በአሞጽ (7-9) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Amos 7:14–15

“So Amos answered Amaziah, ‘I was not a prophet or the son of a prophet; rather, I was a herdsman, and I took care of sycamore figs. But the Lord took me from following the flock and said to me: Go, prophesy to My people Israel.’”

አሞጽ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ለእስራኤል ቤት መልዕክት እያደረሰ ሳለ፣ ከአሜስያስ ተቃውሞ ገጠመው ፡፡ አሞጽ ላም ጠባቂ መሆኑና ከነቢያት ቤተሰብም ባለመገኘቱ ምክንያት የእርሱ ለእግዚአብሔር ነቢይ መሆን ለሌሎች የሚስማማ አልነበረም ፡፡ ሆኖም ግን አሞጽ በጥሪው ጸንቶ ቆመ ከእግዚአብሔርም ራዕዮችን መቀበልና የተቀበላቸውን መልዕክቶች መናገሩን ቀጠለ ፡፡

እግዚአብሔር ለሆነ ነገር ጠርቷችኋልን ? ምናልባት እናንተ የፋብሪካ ሰራተኛ ወይም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ልትሆኑ ትችላላችሁ ፡፡ ምናልባትም ጡረታ ወጥታችሁም ሊሆን ይችላል ፡፡ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ለመጪው ትውልድ ቃሉን ታስተምሩና ትናገሩ ዘንድ ጠርቷቸኋል፡፡ ከአገልጋይ ቤተሰብ ስላልተገኛችሁ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስላልገባችሁ ይህ ጥሪ ልክ ስለመሆኑ ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ልክ እግዚአብሔር ወደ ሆነ ነገር ሲጠራችሁ ይህን አስታውሱ ፡- እርሱ እንደሚያግዛችሁ ፤ እርሱ እንደሚመራችሁ፤ እርሱ እንደሚያበረታችሁ፡፡ ከዓለም እና ከሰይጣን ተቃውሞ እንደሚገጥማችሁ እወቁ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጆችና እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ እርሱ መታመኛችሁ ይሆናል እግሮቻችሁንም ከመንሸራተት ይጠብቃል፡፡ የጠራችሁ እርሱ የታመነ ነው ፤ እርሱ ሁልጊዜም ታማኝ ነው፡፡

“ አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፦ እኔ ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤እግዚአብሔርም በጎቹን ከመከተል ወሰደኝ፥ እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ለሕዝቤም ለእስራኤል ትንቢት ተናገር አለኝ።”

  • አሞጽ 7፡14-15

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 3:26 — “እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና።”

ዮሐንስ 15:16 — “እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።”

1ኛ ተሰሎንቄ 5:24 — “የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።”