Minor Prophets Amos

Contending For The Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Restorer Amos 4-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 693 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አሞጽ በጎችን ይጠብቅ የነበረ ከቴቁሔ እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፡፡ አሞጽ ለሰሜኑ መንግስት ለእስራኤል እየፃፈ ነበር ፡፡ የአሞጽ ቃላት/ንግግር ሁለት የመጀመሪያ ኃጢዓቶችን ደርሷል፡ የእዉነተኛ አምልኮ አለመኖርን እና የፍትህ አለመኖርን ፡፡ ባለፉት ምዕራፎች ዉስጥ እስራኤላዊያን ስለሚደሱባቸዉ ፍርዶች አጥንተናል ፡፡

ትምህርት

አሞጽ (4፡ 1-13)፡ ጄ.ቬሮን ማክጊ “ በቁጥር (1-3) (አሞጽ) በሰሜኑ መንግስት ላይ መራር ፍርዶቹን እንደሚያዝዝ ፤ በቁጥር (4-5) (አሞጽ) በአሽሙር በመናገር ሕዝቡን ወደ መተላለፍ እንደ ጋበዛቸው ፤ የወርቅ ጥጃ አምልኮ ብለዉ እንደጠሩት ፤ በቁጥር (6-13) (አሞጽ ) ምርታቸዉን በማሳጠር፣ በነፍሳት መቅሰፍት/በዋግ/በአሪማሞ፣ በመቅሰፍት፣ በጦርነት እና በጥፋት ፈርዶባቸዉ እንደ ነበር አመለከተ ፤ ከእነዚህም ዉስጥ አንድኛዉም ከኃጢዓታቸዉ መልሷቸዉ እንዳልነበር “ ፅፏል ፡፡ ሁኔታዉ ወይም ሌሎች ችግሮች ወደ ጨዋተ በሚመጡ ጊዜ እግዚአብሄር ወደ እርሱ እንድንመለስ መልጓል ማለት ትክክል እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ በእስራኤላዊያን ምን የሚያጠፉ ነገሮች ቢሆኑም በፍፁም ወደ እግዚአብሄር አልተመለሱም አልጮኹምም ፡፡

አሞጽ (5፡ 1)፡ ምዕራፍ 5 እስራኤላዊያን ስለሚያገኙት ፍርድ መግለጫን ይሰጣል ፤ ያላደረኳቸዉን ሁሉንም ነገሮች ከሰማሁ በኋላ እነዚህን ፍርዶች መስማት ጭንቀታም /ደንጋጣ እሆናለሁ ! እስራኤላዉያን ዉጤታቸዉን እየተቀበሉ ነበር ፡፡ ይህ ምዕራፍ እንደ ሀዘን በሙሾ ይጀምራል ፡፡

አሞጽ (5፡ 2-3)፡ እንደ አንድ ጎልማሳ ሕዝብ እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን “ አጠፋችኋለሁ “ ያለዉን መረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን የምድር ስጦታ በመቀበል ወደ ሞት ስፍራ ቀይረዉት ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ አብዛኞቹ (ከወታደሮቹ) በዉጊያ ተገድለዉ የነበሩ ወይም በምርኮ (90ፐርሰንት ጉዳትንየመረጡ) የተወሰዱ እንደሆኑ፣ በቁጥር ትንሽ የሆኑ ብቻ እንደተመለሱ “ ፅፏል ፡፡ ይህ ጥሩ መዝሙር አልነበረም ፡፡

አሞጽ (5፡ 4-5)፡ እነዚህ ቁጥሮች ለእግዚአብሄር ምስጋና ነበሩ ፡፡ የአሞጽ ዜማ መቀየር ጀመረ ፤ “ ፈልጉኝ ትኖራላችሁ ! “ በጣም የተሻለ መዝሙር ነው ! ዋይርስቤ “ እግዚአብሄርን መፈለግ ማለት መጀመሪያ አስተሳሰባችንን መቀየር ማለት እንደሆነ እና ህይወታችንን ወደ ሌላ መንገድ የሚመራንን ከንቱ ሀሳብን መተዉ ማለት እንደ ሆነ “ ይፅፍል ፡፡ በትክክል እግዚአብሄርን መፈለግ እርሱን መከተል ነው ፡፡

አሞጽ ለእስራኤላዊያን ከአንዳንድ ኃይማኖቶች እርቀዉ እንዲቀመጡ ማስጠንቀቂያዎችን ፃፈላቸው ፡፡ ከሰሜን የሆኑት ሰዎች ሐሰተኛ አማልዕክቶችን ለማምለክ ድንበሮችን አቋርጠዉ ይሄዱ ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን ፈለግ ሕይወት ይኖራችኋል ፡፡ ዋይርስቤ “ ነቢዩ እግዚአብሄርን የምንፈልግበትን ሰዎስት ምክንያቶችን እንደ ሰጠ ይገልፃል የመጀመሪያው በህይወት እንዲኖረን (ቁጥር 4)…. ሁለተኛዉ ምክንያት እግዚአብሄርን መፈለግ ያለብንመንፈሳዊ በረከትን ለማግኘት ሌላ መንገድ ስለሌለ (ቁጥር 5)…. እግዚአብሄርን የምንፈልግበት ሰዎስተኛዉ ምክንያት ፍርድ እየመጣ ስለሆነ ነው (ቁጥር 6) “ ፡፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን መከተል በመተዉ ብቻ አልነበረም የወደቁት ሐሰተኛ አማልዕክቶችን እና ጣዖቶችን በመከተልም ነበር ፡፡

አሞጽ (5፡ 6)፡ ብዙ ሰዎች አሞጽ የእግዚአብሄር ፍርድ “ ልክ እንደ እሳት በዮሴፍ ቤት ላይ ይሰራጫል “ ብሎ በፃፈበት በቁጥር ስድስት ይፈተናሉ ፡፡ እሳት የእስራኤልን ቤት ሁሉንም ነገር ለመብላት እየመጣ ነበር ፡፡ ስለ ኢየሱስ በምትናገሩ/በምታጋሩ ጊዜ ስለ ገሀነም ማዉራት እንደሌለባቸሁ የሚናገሩ ብዙ ወንጌላዊያን እና ክርስቲያኖች አሉ ፡፡ አሞጽ የተጠቀመዉ ይህ ቋንቋ ሰዎች ለምን በክርስቶስ ማመን እንዳለባቸዉ በማስደነቅ የሚረዳ ኃሳብ ይሆናል ፡፡ ክርስቶስን ለምንድን ነዉ ማመን ያለብን ? ምክንያቱም በእርሱ በኩል የዘላለም ህይወትን እና መንፈሳዊ በረከትን ስለምናገኝ ! ከክርስቶስ በስተቀር የእግዚአብሄርን ቸርነት የምናገኝበት ሌላ መንገድ የለም ፡፡ “ በክርስቶስ የማትታመኑ ከሆነ ሲዖል ትገባላችሁ “ ለማለት ችግር የለብኝም ፤ ይህም እዉነታ ነው ፡፡ እግዚአብሄርን የምትፈልጉ ካልሆናችሁ ፍርድ እየመጣ ነው ፤ እሳት እየመጣ ነው ፡፡ ስለሚመጣዉ ነገር ይህ የተለዬ ጥላ/ማሳያ ነው ፡፡

የአሞጽ መልዕክት ለእስራኤላዊያን በአሁኑም ጊዜ ለክርስቲያኖች ተግባራዊ የሚሆን ነው ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን (እንዲሁም እኛን) እርሱን እንዲፈልጉ እና እንዲከተሉት ብዙ እድሎችን ሰጥቷቸዋል ፡፡ በሁሉም ነገር እግዚአብሄርን መፈለግ አለብን ፤ በኃጢዓት መሆን የለበትም ፤ በኑሮአችን በማንኛዉም ዉሳኔ ሊመጣ ይችላል ፡፡

አሞጽ (5፡ 7-8)፡ ማክአርቱር “ ፍትህ መራር በሆነ ጣዕሙ እንደሚታወቀዉ አረም የእንጨት ትል በጣም የተዛባ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ እስራኤላዊያን መልካም የነበሩ ነገሮችን እየወሰዱ እና ወደ መጥፎ እየቀየሯቸዉ ነበር ፡፡ በቁጥር 8 አሞጽ ፕሌይዴስና እና ኦሪዮን ጠቅሷል ፤ ማክአርቱር “ ፕሌይዴስ የታዉረስ ከዋክብት ስብስብ አካል እንደ ሆነ እና ኦሪዮን ደግሞ የእግዚአብሄርን ኃይል እና ጥበብ ያሳያል ፤ እስራኤል ፈጣሪ ይልቅ ከዋክብቶችን በማምለክ ጥፋተኛ እንደ ነበረች “ ፅፏል ፡፡

አሞጽ (5፡ 10-13)፡ የእግዚአብሄር ፍርድ እየመጣ ስለ ነበር እስራኤላዊያን ለማስወገድ ተመለከቱት ፤ በእነርሱ ላይ መጥፎ ነገር የሚናገርን ወይም በሀቀኝነት የሚናገርን ማንኛዉንም አይወዱትም አይቀበሉትም ነበር ፡፡ አሞጽ የእስራኤላዊያንን መጥፎ ባህሪያትን መዘርዘር ጀመረ ፤ አሞጽ እያመለከታቸዉ የነበሩት የተለመዱ ኃጢዓቶች ነበሩ፡፡ አሞጽ የፃፈበት ዘመን አስተዋይ ሰዉ ዝም የሚልበት በጣም የከፋ ነበር ፡፡

አሞጽ (5፡ 14-15)፡ እግዚአብሄርን መፈለግ፣ መልካም ነገር መፈለግ ፤ አሞጽ ምን ያክል ግልፅ ሊሆን ይችላል ?

አሞጽ (5፡ 16-17)፡ ከእግዚአብሄር ፍርድ በኋላ ኃዘን እና ለቅሶ ይሆናል ፡፡ ማክአርቱር “ በዘጸዓት ላይ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አለፈ፣ እዚህ ጋር በሙሴ ዘመን በግብፃዊያን ላይ እንዳደረገው በመካከላቸዉ አለፈ “ በማለት ፅፏል፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር ሕዝቡን እያዳነ አልነበረም ፡፡

አሞጽ (5፡ 18-20)፡ እነዚህ ጥቂት ጠንከር ያሉ የሚያምሩ ቃላቶች ናቸው ፡፡ እግዚአብሄር በኃይማኖታቸዉ ዉሸት ሰራ ፤ ማክአርቱር “ ክፉዎች የእግዚአብሄርን ቀን እንዲመጣ በመፈለግ ከፍርድ ይልቅ ድል ማድረግን/በረከትን ይዞላቸዉ እንደሚመጣ በስህተት አሰቡ (ሶፎ 1፡ 14-18) “ ፅፏል ፡፡

አሞጽ (5፡ 21-24)፡ እስራኤላዊያን በአምልኮ እንቅስቃሴ ዉስጥ እያለፉ ነበር ፤ አምልኮ፣ መስዋዕት እና የተቀደሱ በዓላትም እንኳን በተሳሳተ የልብ መሻጽ በሚፈፀሙ ጊዜ እግዚአብሄርን አያስደስቱትም ፡፡

አሞጽ (5፡ 25-27)፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የእስራኤል አምልኮ እንደ ጩኸት እና ግርግር ካጠፋ በኋላ እግዚአብሄር ለእዉነተኛ ምስጋና እና እግዚአብሄርን ለማምለክ ወደ ብቸኛዉ መሰረት የፍትህ የሚፈስስ ዉኃን እና የጽድቅ የሚወርድ ወንዝን እንደተጣራ “ ይናገራል ፡፡ ይህ እግዚአብሄር የሚፈልገዉ መልክ ነው ፡፡

አሞጽ 6፡ ማጊ “ እስራኤል በግፍ ዘመን በቅጦት መቀመጥን እንደ ቀላል አድርጋ ወስዳዉ እንደ ነበር “ ይፅፏል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ አሞጽ የእስራኤላዊያንን ሰዎስት ሀገራዊ ኃጢዓቶችን አዉርቷል፡ ሆዳምነትን/ስግብግብነትን፣ አረሜናዊነት ሙዚቃን እና ስካርን ፡፡ አሞጽ እግዚአብሄር እንዴት የእስራኤላዊያንን ድርጊት እንደጠላ እና ድርጊታቸው እንደሚቀጣ አመለከተ ፡፡ ምዕራፉ በሕዝቡ ላይ ሌላ ምርኮኝነት እንደሚመጣ በማስጠንቀቅ ያበቃል ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን እንዲፈልጉት ብዙ እድሎችን ሰጥቷቸዋል ፡፡ ምንም እንኳን ይህ በጨለማ ወቅት የከበደ ምዕራፍ ቢሆንም ተስፋን መዉሰድ እና እግዚአብሄር ታዳጊ እንደሆነና ሁልጊዜ ለመታደግ ስለሚመለከት አመስጋኞች መሆን እንችላለን ፡፡

10 Magee, N.A.

  1. J. Vernon McGee, “Outline for Amos”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/amos/amos-outline.cfm.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary, Nashville: Thomas Nelson, Inc, 2005, p.997.

  3. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 356.

  4. Wiersbe, pp. 356-357.

  5. MacArthur, p. 997.

  6. MacArthur, p. 997.

  7. MacArthur, p. 997.

  8. MacArthur, p. 997.

  9. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Biblical Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1054.

ጥያቄዎች

  1. በአሞ (4፡ 1) “ የባሳን ላሞች “ የሚለዉን ሐረግ በተጠቀመ ጊዜ አሞጽ ማንን አመለከተ ምንስ ማለቱ ነው ? (ኢሳ 3፡ 16-26, ኤር 4፡ 30)
  2. በአሞ (4፡ 4-5) ሾፍን በመጠቀም አሞጽ በምን ከሰሳቸው ? እግዚአብሄር ስለ ግብዝነት እንዴት ይሰማዋል (ሉቃ 6፡ 46, 12፡ 2, 1ጴጥ 2፡ 16, 1ዮሐ 4፡ 20) ? በአሞ (5፡ 5) አሞጽ ተቃራኒ እንዲያደርጉ ለምን ነገራቸው ?
  3. በአሞጽ (5፡ 1) ምን አይነት መልዕክት ነበር የተሰጠው ? በሕይወት ለመኖር ለእስራኤል ብቸኛዉ መንገድ ምን ነበር ? (አሞ 5፡ 4, 6, 14)
  4. ክፉዉን መጥላት መልካሙን መዉደድ ማለት ምን ማለት ነው (አሞ 5፡ 15) ? ያ ለእስራኤላዊያን ምን ይመስላል ? ዛሬስ ለእናንተ ያ ምን ይመስላል ? (መዝ 119፡ 163, ምሳ 6፡ 16, 8፡ 13, ኢሳ 5፡ 20, ማር 12፡ 30, ሮሜ 12፡ 2, 9)
  5. በአሞ (5፡ 23) እግዚአብሄር ወደ እስራኤላዊያን አምልኮ ለምን አላዳመጠም /አላዘነበለም (ዘሌ 26፡ 27, 31, መዝ 51፡ 16-17, 19, 66፡ 18) ? ልባችሁ ወይም የቤተ ክርስቲያን ልብ በኃጢዓት በሚሆን ጊዜ ይህ የእግዚአብሄር መልስ እንደሚሆን አስቡ ፤ ይህ በአምልኮ እግዚአብሄርን እንዴት እንደምትቀርቡት እንዴት ይቀይረዋል ?
  6. በአሞጽ (4-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Amos 5:4

“For the LORD says to the house of Israel: Seek Me and live!”

አሞጽ ለእስራኤላውያን እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ያልተመለሱባቸውን ጊዜያቶች እየጠቀሰ መናገሩን ቀጠለ ፡፡ ህዝቡም በጣም ብዙ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሱም ነበር ፡፡ እግዚአብሔርም ጠበቅ አድርጎ በግልጽ ለእስራኤል ቤት ተናገረ ፡- እኔን ፈልጉ በህወትም ትኖራላችሁ፡፡ ያህዌን ፈልጉ በህይወትም ትኖራላችሁ ፡፡ ይሁን እንጅ ህዝቡ ምን ማድረግ ነበር የቀጠሉት? ከእግዚአብሔር መሸሽ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ከእናንተ ከተመረጣችሁ፣ ያድናችሁም ዘንድ ልጁን ከላከላችሁ ከእናንተ ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት እንድኖረው ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሔር ከምንም ነገር አብልጣችሁ እርሱን በፍጹም ልባችሁ፣ ነፍሳችሁና አሳባችሁ እንድትወዱ ያዛችኋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ ፡- እግዚአብሔርን ፈልጉት ታገኙትማላችሁ ይላል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፡፡ እግዚአብሔርን ጠይቁ ትቀበሉማላችሁ፡፡ በርን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል፡፡ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስትን ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡ እግዚአብሔር እናንተ ከእርሱ ጋር ህብረትን እንድታደርጉ ይሻል፡፡ ጸልዩ፣ ቃሉን አንብቡ፣ ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረትን አድርጉ ደግሞም እግዚአብሔር በህይወታችሁ እንዲሰራ ይህን ፈልጉ፡፡እርሱን ስትሹ ደግሞም እርሱን ባላችሁ ነገር ሁሉ ስትወዱ እርሱ ይገኝላችኋል እናንተም በህይወት ትኖራላችሁ ፡፡ እርሱን ስትሹ እርሱ በእናንተ ላይ ሊያፈሰው በሚወደው የተትረፈረፈ ፍቅር ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡

“ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፡፡ “

  • አሞጽ 5፡4

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘዳግም 4:29 — “ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።”

ኤርምያስ 29:13 — “እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”

አሞጽ 5:14 — “በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።”