Reason For Punishing Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Restorer Amos 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አሞፅን ጨምሮ 12 ታናናሽ ነቢያቶች አሉ ፡፡ በሰሜን አዉራጃ/ግዛት ነበር ፤ ስሙም ሸክም ማለት ነበር ፡፡ አሞፅ ከኢየሩሳሌም አስር ማይል በስተደቡብ ቴቁሔ ከምትባል ትንሽ ሰፈር የሆነ እንደ ማንኛዉም ሰው ነበር ፡፡
አሞጽ ነቢይ እንዲሆን ከመጠራቱ በፊት ስራዉን የተናገረ ብቸኛዉ ነበይ ነበር ፤ ከዘር የመጣ/የተዋረደ ካህንነት አይደለም በግ አርቢ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን ለማምጣት ማንኛዉንም ሰዉ ይጠቀማል ፡፡ ነቢይ እንዳልነበርና የነቢይ ልጅም እንዳልነበር ተናገረ ፤ ስለዚህም በመሰረታዊነት ለዛፎች እና ለበጎች ጥንቃቄን ያደርጋል ፡፡ ሐዋ (4፡ 13) ኢየሱስን የተከተሉትን ሰዎች መግለጫን ሰጥቷል ፤ ፅሁፉ የጴጥሮስን እና የዮሐንስን ደረጃ አስቀምጧል ፤ ያልተማሩ እና ያልሰለጠኑ የተለመዱ ሰዎች ነበሩ ነገር ግን በኢየሱስ መገኘት ዉስጥ ነበሩ ፡፡
የአሞጽ ፅኁፍ ኢዮርብዓም ሁለተኛው ከክርስቶስ ልደት በ793 እና በ753 በፊት መካከል ንጉስ እንደ ነበር ተከናወነ ፤ ከሚታወሰዉ የምድር መናወጥ ሁለት አመት በፊት ፃፈ ፡፡ ዘካሪያስ በዘካ (14፡ 5) እንደ ማጣቀሻ ሆነ ከነበረበት ከ200 አመት በኋላ የመሬት መናወጡን ጠቅሶታል ፡፡
ማክአርቱር “ አሞጽ በቀዳሚነት ለሰሜኑ ነገድ ለእስራኤል መልዕክትን እንዲያደርስ የተጠራ አይሁዳዊ ነቢይ ነበር ፡፡ ፖለቲካሊይ የአባቱን ምሳሌ ዮአስ በተለይም የእስራኤልን ግዛት የመለሰዉን (2ነገ 13፡ 25) በሚከተለው በረጅም እና ደህንነት ባለዉ በኢዮርብዓም ዘመን ስር ለእስራኤል የብልፅጋና ጊዜ ነበር (2ነገ 14፡ 25) ፤ ይህ በይሁዳ እና ለሩቅ ወዳጆቿ የሰላም ጊዜ ነበር፣ ምናልባትም በዮናስ ስብከት ከነነዌ ንስኃ የተነሳ (ዮና 3፡ 10) በወቅቱ የአሶር ስጋት ዝምብሎ/በርዶ ነበር ፤ ይሁን እንጂ በመንፈሳዊነት ኃይለኛ የመበላሸት እና የስነ ምግባር መዛግ ጊዜ ነበር (አሞ 4፡ 1, 5፡ 10-13, 2ነገ 14፡ 24) “ ተናግሯል ፡፡
አሞጽ (4፡ 1) ባለፀጋ ሴት ድሀዋን ያስጨነቀችበት እና ድሆችን የጨቆነችበት የመንፈሳዊነታቸዉ መበላሸጽ አንድ ምሳሌ ነበር ፡፡ አሞጽ የሚያመጣው ሁለት መልዕክት ነበረው ፤ እዉነተኛ ፍትህ ማጣት እና እዉነተኛ አምልኮ አለመኖር ነበር ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ “ በአምልኮ ኃይማኖታዊ ስርዓት ድርጊታቸው መካከል ላይ ከልባቸዉ እግዚአብሄርን እየተከተሉ አልነበረም (አሞ 4፡ 4-5, 5፡ 4-6) በወዳጆቻቸዉም የፍትህ ስርዓቱን እየተከተሉም አልነበረም (አሞ 5፡ 10-13, 6፡ 12) “ ፡፡ ስርዓት አልነበረም ፡፡
ነቢያት ከእግዚአብሄር የሆነዉን ቃል ሲሰጡ ማንም ከእነርሱ መስማት አልፈለገም ፡፡ በአሞጽ 9 ታዳጊዉ ምን እንደሚመስል ማጣቀሻ ነበር ፤ በአሞ (9፡ 11-15) እግዚአብሄር ተስፋ ገብቷቸዉ የነበረዉን ሁሉንም ነገር እንደሚያድስ ተናገረ ፤ ይህ ክርስቶስ በኑሮአቸዉ ምን እንደሚያደርግ ጥላ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ታዳጊዉ ምን እንደሚመስል አሳይቷል ፡፡ እግዚአብሄር መታደስን እንደሚያመጣ አወጀ/ተናገረ ፡፡
ትምህርት
አሞጽ (1፡ 1-5)፡ ምዕራፍ 1 ማን እንደ ነበር እና ምን ይሰራ እንደ ነበር አሞጽን በመግለፅ ጀመረ ፡፡ ይመጡ ይነበሩት የመጀመሪያዎቹ ብዙ ፍርዶች በቁጥር (3-5) ተዳሰዋል/ተደርሰዋል ፡፡ ፍርድ በሶሪያ ላይ በተለይም ደግሞ የጭካኔ ዋና ከተማ በሆነችዉ በደማስቆ ላይ ይመጣል ፡፡ የሶሪያ ወንጀሎች እጅግ ብዙ እና በክፋት አይነትም ከእግዚአብሄር አካሄድ ዉጪ ነበሩ ፡፡
አሞጽ (1፡ 6-8)፡ እግዚአብሄር አሕዛቦችን ከመቅጣት ችላ አይልም/አይዘገይም ፤ በፍልስጤም ከተማ በጋዛ ወንጀላቸዉ ከስራቸዉ አንፃር ከእግዚአብሄር ሰዎች በተቃራኒ እና በመጨቆን ነበር ፤ የሰዎችን ባሪያዎች እየሰሩ ነበር፡፡
አሞጽ (1፡ 9-10)፡ በምዕራፍ 1 በመጀመሪያዎቹ ጥቅሶች መፅኃፍት የመፅሃፍቱ ሂደት በቁጥር (9-10) ተደግሟል ፤ በጢሮስ ላይ በሜደትራንያን ላይ በአዳራሾች ስፍራ በጢሮስ ላይ ፍርድ እየመጣ ነበር ፡፡
አሞጽ (1፡ 11-12)፡ በቁጥር (11-12) እግዚአብሄር ሆሴዕን እነዚህን ሁሉ ከተሞች እንደሚፈርድባቸዉ ለሕዝቡ እንዲነግራቸዉ ነግሮት ነበር ፡፡ ማክጊ “ በኤዶምያስ ላይ የነበረዉ ፍርድ ከበቀልተኝነት መንፈሳቸዉ የተነሳ ነበር ፤ ከበቀል ኋላ አንድ የተለመደ ቅንአት ይገኛል ፤ ኤዶማዊያን በወንድሞቻቸዉ የቀኑ እንደ ነበሩ “ ተናግሯል ፡፡
አሞጽ (1፡ 13-15)፡ በቁጥር (13-15) ስለ ጨካኝነታቸዉ እና ስለ ክፉ ወንጀሎቻቸዉ በአሞናዊያን ላይ ፍርድ መጣ ፡፡ ረባት የአሞን ዋና ከተማ ነበረች ፡፡
አሞጽ (2፡ 1-3)፡ ምዕራፍ 2 በእግዚአብሄር የሚፈረድባቸዉ ከተሞችን ዝርዝር ይቀጥላል ፡፡ ሞዓብ ሙት የሆኑትን ንግስናዎችን ካለማክበሩ የተነሳ ፍርድ እንደሚገጥመዉ የተጠቀሰ ቀጣዩ ከተማ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 2 ቁጥር (1-3) በተሸለ ከምዕራፍ 1 ጋር ይገናኛል ፡፡
አሞጽ (2፡ 4-5)፡ በቁጥር (4-5) ለዉጥ ነበር ፤ አሁን ሆሴዕ በይሁዳ እና በእስራኤል ላይ የሚመጣዉን ፍርድ ደርሷል ፤ ፍርዱ በዙሪያ እንዳሉት ሕዝቦች የሚቆይ አልነበረም ፡፡ ነገስታት እና ነቢያቶች የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ንቀዉ/ትተዉ ነበር ፡፡ እስራኤል ፍርድ እየደረሰባቸዉ ከነበሩት ሌሎች ከተሞች የተለየች አልነበረችም ፤ መሪዎቻቸዉ ሕዝቡን በማሳሳት መርተዉታል ፤ ለእግዚአብሄር ትዕዛዝ እና ሕግ አክብሮት አልነበረም ፡፡
አሞጽ (2፡ 6-16)፡ እነዚህ ጥቅሶች በተለዬ በእስራኤል ላይ ይመጣ ስለ ነበረው ፍርድ ደርሰዋል/ተናግረዋል ፡፡ የእስራኤል ኃጢዓቶች ከሌሎች ከተሞች ኃጢዓቶች የተለዩ አልነበሩም፣ በተጠቀሱት በሁሉም ከተሞች ላይ ሁሉም የፍርድ ንግግሮች/ፁኁፎች ሰዎስት ወንጀሎች፣ ምናልባትም አራቱ በእግዚአብሄር እና በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ የተፈፀሙ ነበሩ ፡፡
አሞጽ (3፡ 1-2)፡ ምዕራፍ 3 እግዚአብሄር ከእስራኤል ሕዝቦች ጋር የጠበቀ እና የተመረጠ ትስስር/ግንኙነት እንደነበረው ያመለክታል ፡፡ ይሁን እንጂ እስራኤል በእግዚአብሄር ስነ ምግባር ማጣትን፣ ስድብን እና ሌሎች ኃጢዓቶችን በማካተት በብዙ ኃጢዓቶች ጥፋተኛ ነበረች ፡፡ ማክጊ “ ይህ እዚህ ጋር እግዚአብሄር ያስቀመጠዉ ታላቅ መርህ ነው ፤ በጨለማ ካሉት ይልቅ ብርኃንን የተቀበሉትን በኃይለኛ ሁኔታ መዳኘት እንደሚፈልግ “ ተናግሯል ፡፡ እስራኤል የእግዚአብሄርን መንገድ ታውቃለች ፤ እስራኤላዊያን አሁን ፍርድ እየመጣ እንደ ነበር አለበት መጠን ድረስ እንኳን አልታዘዙም ፡፡ የእግዚአብሄርን ስርዓት ትተዉ ነበር ፡፡
አሞጽ (3፡ 3-8)፡ ቀጥሎም አምስት ጥያቄዎች አሉታዊ መልስን ለመቀበል የተነሱ ሲሆኑ ሁለት ጥያቄዎች ደግሞ አዎንታዊ መልስን ለመቀበል የተነሱ ናቸው ፡፡ ኮንስታብል “ አሞጽ በቁጥር (3-6) እስራኤላዊያንን ፍርዳቸው እንደማይቀር ለመርዳት ሰባት የተጋነኑ ጥያቄዎችን ጠየቃቸው ፤ በእያንዳንዳቸው ነቢዩ የተወሰነ ምክንያት የተወሰነ ዉጤት ማምጣቱ የማይቀር እንደ ሆነ አመለከተ ፡፡ በቁጥር (3-5) አምስቱ ጥያቄዎች አሉታዊ መልሶችን ሲጠብቁ በቁጥር 6 ሁለቱ ደግሞ አዎንታዊን ይጠብቃሉ ፤ ቁጥር (7-8) መደምደሚያዉን ያስቀምጣል ፡፡ ንፅፅሩ በሰላማዊነት ጀመረ (ሁለት ሰዎች በአንድ ላይ በመጓዝ) ነገር ግን በጋለ ስሜት ጨመረ ( እስከ ከተማን እስከ ማጥቃት) ፤ ይህ በዉስጥ የተጋነነ ድምፅን እንደሚፈጥር “ ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ራሱን እየገለጠ ነበር ይህንንም በነቢዩ በአሞጽ አደረገው ፤ ከፍርዱ ሕዝቡን ቀድሞ አስጠነቀቃቸው ፡፡
ሕዝቡ ትክክል ነገር ማድረግ አይችሉም ነበር ፤ ጣዖት አምላኪ ሕዝቦች ከእስራኤል ይበልጥ ፃድቃን ለመሆን ተገልጠዋል ፤ ፍርድ እነርሱን ለመቅጣት በጠላትነት መልክ ወደ እስራኤል እየመጣ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
አሞጽ ከፍርዱ በኋላ የሚቀሩ ጥቂት የእስራኤል ቅሬታዎች እንደሚኖሩ አመለከተ ፡፡ እግዚአብሄር በሕዝቡ ተስፋ የቆረጠ መስሏል ፡፡ እግዚአብሄር ሐሰተኛ ኃይማኖቶቻቸዉን ያጠፋል ፤ ኃብታቸዉን በስህተት ከመጠቀማቸዉ የተነሳ እስራኤል ፍርድ ይደርስባታል ፡፡ መልዕክቱ አልተቀየረም ነበር እግዚአብሄር መታዘዝን ነዉ የሚጠብቀው ፡፡ በመጨረሻም አሁንም እግዚአብሄር በመገለጥ ሁኔታዉን እና ሕዝቡን ያድሳል ፡፡
4 McGee, 694.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 992.
MacArthur, p. 992.
J. Vernon McGee, Thru the Bible Volume 3: Proverbs-Malachi, (Nashville Thomas Nelson Publishers, 1983), p. 687.
Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Amos, p. 34; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/amos.pdf.
ጥያቄዎች
-
በአሞጽ 1 እና በአሞጽ 2 መጀመሪያ ላይ አሞጽ በላያቸዉ ላይ ፍርድን የተናገረባቸዉ ስድስት አሕዛብ ሕዝቦች እነማን ነበሩ ?
-
የእግዚአብሄር ቃል ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አሞጽ ከየት ነበር ምንስ እየሰራ ነበር ? (አሞ 1፡ 1)
-
በአሕዛቦች ላይ ያሉት ፍርዶች ካለ ጥቂት ተመሳሳይነታቸዉ ምን ነበር ልዩነታቸዉስ ?
-
አሕዛቦች ለምን ነበር የተፈረደባቸው (ሮሜ 2፡ 14-15) ? ይሁዳ እና እስራኤል ለምን ተፈረደባቸው ? (ዘዳ 28፡ 15-19, አሞ 3፡ 2)
-
ስለ አሞ (3፡ 1, 4፡ 1 እና 5፡ 1) አጀማመር ምን ታስተዉላላችሁ ? አሞጽ እነርሱን ለመድረስ ለምን እየሞከረ ነበር ?
-
በአሞጽ (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Amos 2:4-5
“I will not relent from punishing Judah for three crimes, even four, because they have rejected the instruction of the LORD and have not kept His statutes. The lies that their ancestors followed have led them astray. Therefore, I will send fire against Judah, and it will consume the citadels of Jerusalem.”
እግዚአብሔር ከቴቁሔ ላም ጠባቂዎች መካከል አሞጽን ጠራው ፤ ለእስረኤልም እንድናገር ትንቢታዊ መልዕክትን ሰጠው ፡፡ መልዕክቱም በእስራኤልና በዙሪያዋ ባሉት ላይ ስለሚሆነው ጥፋት ይናገራል ፡፡ አሞጽ በእግዚአብሔር ላይ አምጸዋልና እግዚአብሔር እነዚህን ሀገራት ሳይቀጣና ሳያጠፋ እንደማይተዋቸው ደግሞ ደጋግሞ ይናገራል ፡፡ አሞጽ በተደጋጋሚ እግዚአብሔር “ እሳትን ይሰድዳል……ትበላላች” በማለት ይናገራል ፡፡
ዛሬም እንኳ ጭምር በህይወታችሁ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ነው ፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ውጪ ሌላ አማልክትን ስታመልኩ ወይም እርሱን ቀድማችሁ ከመፈለግ ይልቅ በዓለም ውስጥ ደስታን ስትፈልጉ ያያችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ያለወረት ያለምክንያት ነው የሚወዳችሁ ሆኖም ግን እርሱ ቀናተኛ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ ከምንም ነገር አብልጣችሁ እንድታመልኩትና እንድትወዱት ይፈልጋል ፡፡ እርሱ እንድታመልኩትና እርሱ ማን እንደሆነ አውቃችሁ እንድትፈሩት ይፈልጋል ፡፡ እርሱም በመንግስቱ ውስጥ ለተጠራችሁበት ዓለማ ትውሉ ዘንድ የእርሱ እሳት እንድያጠራችሁ በፈተና ውስጥ ያሳልፋችኋል ፡፡ በአስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ ስታልፉ ይህን እወቁ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ፡፡ በእሳቱ ውስጥ እርሱን ፈልጉት፣ እርሱ በዚያ አለ ፡፡ በቃጠሎው ውስጥ እንኳ ቢሆን፣ ሱሙን አመስግኑ፡፡ የእርሱ ያልሆነውን በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን የትኛውንም ነገር እንድያቃጥል ፍቀድሉት ፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ታዳጊያችሁና ተቤዣችሁ አድርጋችሁ አመስግኑ ፡፡ አትናወጡም ፡፡
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ሐሰታቸው አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም አዳራሾች ትበላለች።”
- አሞጽ 2፡4-5
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 4:23-24 — “አምላካችሁም እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።”
ኢሳይያስ 33:14 — “በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?”
ዕብራውያን 12:28-29 — “ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።