Minor Prophets Joel

Judgement Of The Nations

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Avenger Joel 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 691 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ሳምንንት ከታናናሽ ነቢያት አንዱ በሆነዉ በሆሴዕ ላይ ቀድመን ተመልክተናል ፡፡ ሆሴዕ በግልፅ ለእስራኤላዊያን ለሰሜኑ እና ለደቡቡ መንግስት ለሁለቱም ቃል ነበረው ፡፡ ይህ በታናናሽ ነቢያት በኢዩኤል ላይ የመጀመሪያ እና ብቸኛ ክፍል ነው ፡፡ የኢዩኤል መፅኃፍ በእዉነት ከሚወደዱት ዉስጥ አንዱ ነው ፡፡ የኢዩኤል የስሙ ትርጉም “ እግዚአብሄር አምላክ “ ማለት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ቢያንስ 12 ሰዎች በአዲስ ኪዳን ደግሞ አንድ ሰዉ ኢዩኤል የሚባለዉ ስም ነበር ፡፡ በኢዩ (1፡ 1) ፀኃፊው “ የባቱኤል ልጅ ኢዩኤል “ በመባል ተለይቷል ፡፡

ማክአርቱር “ ኢዩኤል ለቤተ መቅደሱ መስዋዕት ከፍተኛ ጉጉትን ቢያሳይም (ኢዩ 1፡ 9, 2፡ 13-16)፣ በእርባታ እና በግብርና ህይወት የለመደ መሆኑና ከካህናት የተለዬ መሆኑ (ኢዩ 1፡ 13, 14፣ 2፡ 17) ሌዋዊ እንዳልነበር እንደሚያመለክቱ “ አመልክቷል ፤ ይሁን እንጂ ተጨማሪ መፅኃፍ ቅዱሳዊ ፅሁፎች ኢዩኤል የሮቤል ነገድ አባል እንደ ነበርና በሮቤል እና በጋድ ድንበር ሰሜን ምዕራብ ትገኝ ከነበረች ከቤቶም ወይም ከቤተሀራም እንደ ነበር ይናገራሉ ፡፡ በራሱ በመፅኃፉ ዉስጥ ያሉ ማስረጃዎች ኢዩኤል ይሁዳዊ እና ከኢየሩሳሌም እንደ ነበር ያመለክታሉ ፤ ይህ በእንግዳ እይታ ባለመፃፉ እዉነት መሰረት ነበር ፡፡

የመፀኃፉ ቀን/የተፃፈበት ቀን በመፅኃፍ ሕግ ላይ በተቀመጠበት እንዲሁም ደግሞ በመፅኃፉ ዉስጥ ባለ ታሪካዊ ማስረጃ እና በመፅኃፉ ቋንቋ እና አፃፃፍ ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ 1) በቀደሙት ኃላን አለም በግልፅነት የተጠቀሰ ባለመኖሩ (በአሶር፣ በባቢሎን ወይም በፋርስ )፣ 2) የኢዩኤል እስታይል ከኋላዉ ከመጡት ነቢያት ይበልጥ ከሆሴዕ እና ከአሞፅ ጋር ከመመሳሰሉ እዉነት የተነሳ እና 3) ከክርስቶስ ልደት 9 ክፍለ ዘመን በኋላ በኢዮስያስ ዘመን ጊዜ ( ከክርስቶስ ልደት ከ835-796 በፊት) ከነበሩት ሌሎች ነቢያት ጋር ቃሉ ከመመሳሉ የተነሳ በደንብ የሚያሳምን እንደሚመስል “ ይገልፃል ፡፡ በሚያስደን መልኩ ጄ.ቬርኖን ማክጊ ኢዩኤል ኤልያስን እና ኤልሳዕን ሁለቱንም እንደሚያዉቃቸዉ ያመለክታል ፡፡

በኢዩ (3፡ 2-4) መሰረት ጢሮስ፣ ሶዶና እና ፍልስጤም ወደ እስራኤል ወታደራዊ ጥቃት አድርገዉ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ የተስፋፋ ድርቅ እና ከፍተኛ የሆነ የአንበጣ ወረራ ከምድሪቱ ላይ ሁሉንም አረንጓዴ ነገር አጥፍቶት ስለ ነበር አስከፊ የኢኮኖሚ ጥፋትን በማምጣት የደቡቡን መንግስት ደካማ እንዳደረገው “ ይገልፃል ፡፡ ኢዩኤል በኃጢዓት ላይ እንደሚመጣ የእግዚአብሄር ፍርድ እና “ በጌታ ቀን ጊዜ የሚመጣዉ የእግዚአብሄር ፍርድ በጣም እንደሚበልጥ “ ለማሳየት እንደ ምሳሌነት የአንበጣ ወረርሽኝን ተጠቅሟል ፡፡ 19 ጊዜ “ የጌታ ቀን/የመከራዉን ቀን “ የሚለዉን ሐረግ ከተጠቀሙ ስምንንት የብሉይ ኪዳን ፀኃፊዎች ዉስጥ ኢዩኤል በሚገባን ማብራሪያን አስቀምጧል ፤ ይህ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ አራት ሌሎች ጠቀሜታዎች አሉት ፡፡ ኢዩኤል በጌታ ቀን የታወቀ ነቢይ ሲሆን ትንቢቶቹም ከማቴዎስ እና ከራዕይ ጋር ይያያዛሉ ፡፡ የጌታ ቀን/የታላቁ መከራ ቀን ለጌታ “ ምናልባትም ርህራሄ በለሌዉ ግዴለሽነት “ ይመጣል ፡፡

ማክአርቱር የጌታ ቀን ሁልጊዜ መጨረሻ ላይ የሚመጣዉን ክስተት ብቻ ቀድሞ ለመናገር ብቻ ጥቅም ላይ እንደማይዉል ይገልፃል ፤ “ የቀረቡ ታሪክ መፈፀምንም “ (ሕዝ 13፡ 5) ለመግለፅ ጥቅም ላይ ሊዉል ይችላል ፡፡ ብዙጊዜ የጌታ ቀን “ የመሬት መናወጥን፣ ኃይለኛ የአይር ፀባይን፣ ደመናን እና ድቅድቅ ጨለማን፣ የህዋን መናወጥ/ብጥብጥን እና እንደ ታላቅና ኃይለኛ መከራ ከሁሉን ቻይ አምላክ የሚመጣን ቀን ለመግለፅ ጥቅም ላይ ይዉላል (ኢዩ 1፡ 15) “ እንዲሁም ደግሞ የተስፋን ቃል ኪዳን እና “ በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ የሚፈስሰዉን መንፈስ “ ያመለክታል ፡፡

ለኢዩኤል ቃላችን ተበቃይ የሚል ነው ፡፡ በኢዩኤል በጌታ ቀን ላይ በሰባት አመቱ የመከራ ቀን መጨረሻ ላይ በኢዩሳፍጥ ሸለቆ ላይ ከእስራኤል እና ከንጉሱ ኢየሱስ ጋር ለመዋጋት አሕዛቦች በአንድ ላይ ይመጣሉ ፡፡ ኢየሱስ እንደ ተበቃይ በማገልገል (ኢዩ 3፡ 19-21) ለሚሰራው ብልሹ ነገር ስህተት የሰራን ሰዉ በስትክክል ይቀጣል ፡፡ ኢየሱስ በመጨረሻ ጊዜ በመምጣት በሕዝቡ ላይ ስህተትን ያደረጉ ሰዎችን ይበቀላል ፡፡

ትምህርት

ኢዩኤል (1፡ 1-14)፡ ኢዩኤል ስለ አንበጣ መቅሰፍት ትንቢትን ተንግሯል ፡፡ ሁሉንም ነገር ማጥፋት የሚቀጥሉ አራት አይነት አንበጣዎችን ገልፆአል ፡፡ በቁጥር 5 አንበጦቹ የወይን ተክሉን አጥፍተዉታል ፤ በቁጥር (6-7) ኢዩኤል አንበጦቹን ከወራሪ ሰራዊት ጋር አወዳድሯቸዋል ፡፡ ወራሪ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ነገር ያጠፋል (ቁጥር 8-10) ፡፡ ኢዩኤል ከአንበጦቹ የተነሳ የሚቸገሩ እና የሚያዝኑ አስር ቡድኖችን አስቀምጧል፡ ሰካራሞች፣ ገበሬዎች፣ አትክልተኞች፣ ካህናቶች፣ የመሰዊያዉ አገልጋዮች፣ የእግዚአብሄር አገልጋዮች፣ በአምልኮ የምድሪቱ ነዋሪዎች እና ሽማግሌዎች እና አጠቃላይ ጉባኤው ፤ ለእርዳታ ሁሉም ወደ ጌታ ይጮኻሉ (ቁጥር 9-14) ፡፡

ኢዩኤል (1፡ 15 -2፡ 32)፡ ኢዩኤል የጌታ ቀን የቀረበ እንደ ነበርና ፍርዱ እንደሚመጣ ተናገረ ፡፡ ቁጥር (16-20) የመቅሰፍቱን/የመዓቱን ዉጤቶች ይገልፃል ፡፡ በኢዩ (2፡ 1-10) ኢዩኤል የጌታ ቀን እየቀረበ ስለ ነበር ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል በመግለፅ እንዲነቁ ነገራቸው ፤ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ጨለማ ምድርን ይሸፍናታል ፡፡ በቁጥር (12-17) ኢዩኤል ለንስኃ አንድ የመጨረሻ ጥሪ እንዳለ ተናገረ ፤ ቁጥር 14 ቅሬታዎቹን ይጣራል ፤ እግዚአብሄር ወደ እርሱ እንዲመለሱ ለሕዝቦቹ ጥሪን አደረገ ፡፡ ቁጥር (18-19) የእግዚአብሄርን በረከቶች ይሰጣል በመቀጠልም እግዚአብሄር መልሱ የሚወሩትን ሰራዊቶች ማምጣት ይጀምራል (ቁጥር 20-24) ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ምድሪቱ መታደስን ያመጣል (ቁጥር 26-27) ፡፡ ቁጥር (28-32) በጴጥሮስ ተጠቅሷል (ሐዋ 2፡ 16-21) የእግዚአብሄር መንፈስም በሰዎች ላይ እንደሚወርድ ተስፋን ሰጥቷል ፡፡

ኢዩኤል (3፡ 1-10)፡ እግዚአብሄር የሕዝቡን እድል ይመልሳል/ያድሳል ከዚያም አሕዛቦችን በኢዮሳፍጥ ሸለቆ ይሰበስባቸዋል ፡፡ አይሁዶችን በስርዓት ያልያዙትን/ያልተንከባከቡትን ሕዝቦች ይፈርድባቸዋል (ቁጥር 1-6) ፡፡ አይሁዶች ለባርነት ተሸጠዉ ስለ ነበር በገንዘብ እና በንብረት ወደ አመንዝራነት ተገደዱ ፡፡ የቤተ መቅደሱ የወርቅ እና የብር እቃዎች ተዘርፈዉ ነበር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎችም ለእንግዳ ጌቶች ተሸጠዉ ስለ ነበር ከምድራቸዉ ላይ ተፈናቀሉ/ተወሰዱ ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን መልሶ በማምጣት በእነዚህ ላይ የሚገባቸዉን ቅጣት በማምጣት በአይሁዶች ላይ አድርገዉት እንደ ነበረዉ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ እንደሚሆን ቃል ገባ (ቁጥር 7-8) ፡፡ እግዚአብሄር አሕዛቦችን ለቅዱሱ ጦርነት እንዲዘጋጁ ነገራቸው (ቁጥር 9) ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ማረሻን ወደ ሰይፍ ማጭዳቸዉን/ቢላዋቸዉን ወደ ጦር መሳሪያ ይቀጠቅጣሉ ፤ ደካሞች እንኳን እንደ ብርቱ አስፈለጉ (ቁጥር 10) ፡፡

ኢዩኤል (3፡ 11-21)፡ እግዚአብሄር ሁሉንም ወደ ሚዳኝበት ስፍራ በፍጥነት እንዲመጡ ነገራቸው (ቁጥር 11-13)፡፡ ኢዩኤል የእግዚአብሄር ቀን እንደቀረበ የእግዚአብሄር ቀን ከመቅረቡም የተነሳ ዉሳኔዉን ለመስማት ብዙ ሕዝብ ወደ ሸለቆዉ እንደሚመጣ ተናገረ (ቁጥር 14) ፤ ይህ የአርማጌድዮንን ጦርነት ያመለክታል ፡፡ ፀሐይ እና ጨረቃ ይጨልማሉ ከዋክብትም እንኳን አይበሩም (ቁጥር 15) ፤ እግዚአብሄር ከፂዎን ይጮኻል ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ ፡፡ እግዚአብሄርም ለአይሁዶች ለሕዝቡ መሸሸጊያ ይሆናል (ቁጥር 16) ፡፡

በዚህም ሁሉም እግዚአብሄር የእስራኤላዊያን አምላክ እንደ ሆነና ኢየሩሳሌምም ቅዱስ ከተማዉ እንደሆነች ያውቃሉ (ቁጥር 17) ፡፡ ቁጥር 18 በሕዝ (45፡ 1-5) የተገለፀው የሚፈስስ ዉኃ ያለዉ ቤተ መቅደስ መልክ ነው ፡፡ ግብፅ እና ኤዶምያስ በይሁዳ ላይ ካደረጉት ድርጊት የተነሳ ባድማ ይሆናሉ (ቁጥር 19) ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ለዘላለም መኖሪያ ይሆናሉ (ቁጥር 20) ፡፡ እግዚአብሄር በፂዎን ስለሚያድር ደም አፈሳሽነት ጥፋተኝነታቸዉን ይቅር ይላል (ቁጥር 21) (ዘፍ 12፡ 3, ማቴዎስ 25 - በግ እና ፍየል ሕዝቦች ፡፡

መደምደሚያ

የዚህ ስዕል የሚያምረዉ ነገር ንስኃ በምንገባበት ጊዜ፣ ወደ እርሱ በምንመለስበት ጊዜ፣ ወደ እግዚአብሄር በምንጮኽ እና በምንፀለይ ጊዜ ሁልጊዜ እግዚአብሄር ደጀናችን እንደሚሆን ነው ፡፡ ኢየሱስ ከእኛ በተቃራኒ መሄድን በመረጡት ላይ እንደ ተበቃይ ያገለግላል/ይሰራል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 982.

  2. MacArthur, p. 982.

  3. MacArthur, p. 982.

  4. J. Vernon McGee, “Notes for Joel”; https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/joel/joel-notes.cfm.

  5. MacArthur, p. 982.

  6. MacArthur, p. 982.

  7. MacArthur, p. 982.

  8. MacArthur, p. 983.

ጥያቄዎች

  1. ኢዩ (1፡ 1-4 እና 7) ከአሞ (4፡ 9-10) ጋር እንዴት ይነፃፀራል ? ሁለቱም ነቢያቶች በተመሳሳይ ጊዜ ለተመሳሳይ ተደራሲያን እየተናገሩ ነበር ? በአጠቃላይ ሰዎች ከትናት ስተታቸዉ ይማራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይህ ለእኛ ስለ እግዚአብሄር ምህረት ምን ይለናል ?
  2. በኢዩ (1፡ 13-14) ነቢዩ ኢዩኤል ሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው ? በአሁኑ ጊዜ ከዚህ የተሸለ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን በተሸለ ሁኔታ ትሆናለች ብላችሁ ታምናላችሁ ?
  3. የእግዚአብሄር ሰዎች ንስኃ ከገቡ እና ልባቸዉን ወደ እርሱ ከመለሱ እግዚአብሄር ምን ለማድረግ ተስፋ ገባ ? (ኢዩ 2፡ 12-13)
  4. በአዲስ ኪዳን በኢዩ (2፡ 28-32) ላይ ያለዉን የነቢዩ የኢዩኤልን ቃል የጠቀሰዉ ማነው (ሐዋ 2፡ 14-21) ? ለምን ጠቀሳቸው ? ምን እየሆነ ነበር ?
  5. በኢዩኤል (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joel 2:26-27

“You will have plenty to eat and be satisfied. You will praise the name of Yahweh your God, who has dealt wondrously with you. My people will never again be put to shame. You will know that I am present in Israel and that I am Yahweh your God, and there is no other. My people will never again be put to shame.”

የእግዚአብሔር ቀን እየመጣ ስለሆነ ኢዩኤል ለህዝቡ እንድሰበሰቡና መለከትን እንድነፉ ይናገራል ! ኢዩኤል አንበጣ የእስራኤልን ምድር እንደሚወርርና ጥፋትን እንደሚያመጣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሊታደጋቸው እንደሚመጣ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሔርን ስላልፈለጉ ትልቅ ኃይል በእስራኤላውያን ላይ ይነሳል ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ህዝቡን ይታደጋል ፡፡ እግዚአብሔርም ብዙ የሚበላና የሚጠጣ ይሰጣል እነርሱም ይጠግባሉ ፡፡ ህዝቡም የአምላካቸውን የያህዌን ስም ጠርተው ከእንግዲህ ወዲያ ፈጽመው አያፍሩም ፡፡ ታላቅ የሆንኩት እኔ በእስራኤል መካከል አለሁ ፤ እኔም አምላካቸው ነኝ ፡፡ ሌላ አምላክ የለም ፡፡ እግዚአብሔርም በህዝቡ መካከል ድንቆችን ያሳያል ፡፡ የጌታንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል ፡፡

ለጌታ ቀን ዝግጁ ናችሁ ? እግዚአብሔር ጥፋትን ሊያመጣ ይችላል ሆኖም ግን ለእናንተ ትድግናን ያዘጋጃል ፡፡ ወደ እርሱ ስትመለሱ እርሱ ያጠግባችኋል ፡፡ አህዛብም ይሰበሰባል ከአንዱ እውነተኛ አምላክ፣ ከታላቁ ታዳጊ በቀር ሌላ አምላክም እንደሌለ ያውቃል ፡፡ መንፈሱም በህልም፣ በራዕይ፣ በትንቢትና በድንቆች ሁሉ በላይ በሰማይ በታች በምድርም ይሰራል ፡፡ ልክ ኢየሱስ እናንተን ሁላችሁን ለመውደድ እንደመጣ ሁሉ ፣ እናንተም እንደ ክርስቶስ ልትወዱ ተጠርታችኋል ፡፡ በእናንተ ውስጥ ከሚፈሰው ፍቅር ከዚያ፣ መንፈሱ ይሰራል ዓለምም ሁሉ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል ፡፡ ዛሬ ጸንታችሁ ቁሙ ለጌታም ቀን ራሳችሁን አዘጋጁ ፡፡

“ ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም ።እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።”

  • ኢዩኤል 2፡26-27

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 22:26 — “ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፤ እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል።”

ኢሳይያስ 44:6 — “የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።”

ኢዩኤል 2:28-30a — “ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።”