Minor Prophets Hosea

Repentance And Restoration

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Unconditional Love Hosea 12-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 690 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሆሴዕ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ገፀ ባህሪያቶች ሆሴዕ እና ሚስቱ ጎሜር ነበሩ ፡፡ ሰዎስት ልጆች ነበሯቸው ነገር ግን ለሆሴዕ ታማኝ አልነበረችም ፡፡ በዚህ ሁሉ እግዚአብሄር ሆሴዕ ላልታመነች ሚስቱ የማይቀየር ፍቅርን እንዲያሳይ ጠየቀው ፤ የሆሴዕ እና የጎሜር ኑሮ እግዚአብሄርን እና ያልታመነችዉን እስራኤልን ይወክላል ፡፡ ፍሬ ኃሳቡ እስራኤልን የምትወክለዉ ጎሜር እግዚአብሄርን ለሚወክለዉ ለሆሴዕ አለመታመኗ ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር እንዳልታመኑት ጎሜርም በጋብቻ መታመንን እምቢ አለች ፡፡

ትምህርት

ሆሴዕ 12፡ በሆሴ (12፡ 1) ኤፍሬም ሸቀጦችን ለመሻሻጥ/ለመገዛዛት ከግብፅ ጋር ኪዳንን አደረገ ፡፡ የእስራኤላዊያን አለመታመን በራሳቸዉ ብልፅግናቸዉ ላይ በመደገፋቸው የታዬ ነበር ፤ ከእግዚአብሄር ይልቅ ለራሳቸዉ ባመረቷቸዉ/ባመነጯቸዉ ሁሉም ነገሮች ላይ እምነታቸዉን አስቀመጡ ፡፡ ለእነርሱ የሆነዉን የእግዚአብሄር እንክብካቤ ተጠራጠሩት ፡፡

ሕዝቡ በእነርሱ ላይ ወንጀል እንዳልነበር እና ለመኖር የሚያስፈልጋቸዉን ብቻ እያደረጉ እንደ ነበር ተናገሩ ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሄር ተስፋ ይልቅ እምነታቸዉን በራሳቸዉ ብልፅግና ላይ ማስቀመጥን ስለመረጡ የእግዚአብሄር ፍርድ በእነርሱ ላይ ይመጣል ፡፡

ጄ.ቬረኖን ማክጊ “ እዚህ ጋር በጣም የሚያስደንቅ ትንቢታዊ የጎን መብራት አለ ፤ በዳንኤል ራዕይ (ዳንኤል 7) ባቢሎን እንደ አንበሳ ተስላለች፣ ግሪክ ( በታላቁ አሌክሳንድሪያ ስር) እንደ አቦሸማኔ ተስላለች እንዲሁም የሜዶና ፋርስ ጋዛት ደግሞ በድብ ተስሏል ፤ አሁን ደግሞ እዚህ በሆሴዕ ትንቢት እግዚአብሄር በሚመጣዉ ጊዜ በእነርሱ ላይ እንደ አንበሳ እና እንደ አቦሸማኔ እመጣባቸዋለሁ እያለ ነው ነገር ግን ወደፊት በቅርቡ/በፍጥነት በቅርቡ በአሶር ተሸንፎ የነበረዉን በሜዶን እና ፋርስን በሚወክለዉ በድብ ይመጣባቸዋል “ በማለት ይናገራል ፡፡ የእስራኤል ሕዝቦች እግዚአብሄር እንጂ ሌላ የሚገኝ እረዳት አልነበራቸዉም ፤ በእርሱም መታመንን አልመረጡም ነበር ፡፡

እግዚአብሄር ንጉስ ሳዖል እና እየመጣ ስለነበረዉ ፍርድ እዉነት አመለከተ ፡፡ ጳዉሎስ በ 1ቆሮ (15፡ 55) ሆሴ (13፡ 14) ጠቅሷል የእስራኤል ሰዎች ሊረዱት የሚችሉበት ብቸኛዉ መንገድ በእግዚአብሄር ነፃ መዉጣት ስለሚችሉ ሞት ኃዘን እንደማይሆን ነበር ፤ የእግዚአብሄር ፍቅር የማይለወጥ ነበር ፡፡

ሆሴዕ 13፡ ሆሴ (13፡ 14-16) የጥፋተኝነት እና የከባድ ቅጣት ማሳያ ነው ፤ እነዚህ ቁጥሮች ለምዕራፍ 14 መግቢያ ይሰጣሉ ፡፡ ኮንስታብል “ በአብዛኛዉ በሆሴ ክፍል እንደተለመደው የመታደስ ተስፋ የፍርድ አዋጅን ይከተላሉ ፤ ይህ የመጨረሻ የመታደስ ተስፋ ክፍል ለንስኃ በመለመን እና በሙሉ እና በተሟላ ተስፋ መታደስ እንደሚጀምር “ ይናገራል ፡፡

ሆሴዕ (14፡ 1-8)፡ በቁጥር 1 ሆሴዕ ትህትናና የተፀፀተ መንፈስ እንዲኖራቸዉ አጥብቆ ተናገረ ፡፡ ሕዝቡ በእዉነት ንስኃ ከገቡ በእግዚአብሄር በነፃነት እንዲመላለሱ ይፈቀድላቸዋል ፡፡ አለመታዘዛቸዉ እና አለመታመናቸዉ እያለ እንኳንሕዝቡ በማንኛዉም ጊዜ በእዉነተኛ ምስጋና እና ንስኃ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ይችላሉ ፡፡

ማክአርቱር “ እስራኤል እንዲትመለስ፣ በመታዘዝ የሆነ የንስኃን ቃል እንድታመጣ እና ፍፁም በሆነ በከንፈር መስዋዕትነት የእግዚአብሄርን የከበረ መቀበል እንደ ገና እንድትከፍ (ዕብ 13፡ 15) ተጋብዛ ነበር ፤ እግዚአብሄር የከንፈር አገልግሎት አምልኮን ይነቅፋል (ኢሳ 29፡ 13, ማቴ 15፡ 8) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ሆሴዕ 14 የከንፈር አገልግሎትን/የዉሸት አገልግሎትን ሳይሆን እዉነተኛ ንስኃን እያመለከተ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በእስራኤል ሁኔታ ላይ የሆነ ነገርን እያደረገ ነበር ፤ ሕዝቡን መዉደዱን እና ከክህደት ነፃ ማዉጣቱን ቀጠለ ፡፡ ሁኔታቸዉን ይፈዉሳል ፡፡

እስራኤልጌታ/እግዚአብሄር እንደሚያስፈልጋቸዉ አስተዋሉ ፤ ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሄር ቁጣ ከእነርሱ ተመለሰ ፡፡ እግዚአብሄር አዲስ ሕይወትን ይሰጣቸዋል ፤ የእነርሱ አዲስ ሕይወት ምንጭ እግዚአብሄር ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር (2-5) እንደ “ ይቀበለናል (ቁጥር 2-3), ያድሰናል (ቁጥር 4) እና ያነቃቃናል/ያስነሳናል (ቁጥር 5-8) “ በማለት አስቀምጧቸዋል ፡፡ በመጨረሻም ሕዝቡ ንስኃ እንደሚያስፈልጋቸዉ አስተዋሉ ፡፡

ኮንስታብል የእነዚህ ቁጥሮችን አስፈላጊነት ይገልፃል፡ “ እስራኤል ለአይን እና ለአፍንጫ ሳቢ እና ምርታማ ትሆናለች በስምም፡ በአጠቃላይ ታምራለች/ትቆነጃለች ፤ እግሮች መቆም/መረጋጋትን ያመለክታል፣ ዉበት እይታን ሲያመለክት መዓዛ ደግሞ ተፈላጊነትን ያሳስባል “ ፡፡ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር ይመለሳል ፡፡ ማክአርቱር “ ጣዕማቸዉ (መታሰቢያቸው) አለማቀፍ ዝናን እና አድናቆትን እንደሚወክል “ ይናገራል ፡፡ ኮንስታብል “ ሌሎች ሕዝቦች ከእስራኤል መልካም ተፅዕኖ በመጠቀም የሚያፈሩ/የሚበለፅጉ እንደሚሆኑ “ አመለከተ ፡፡

ሆሴዕ (14፡ 9)፡ አሁን እስራኤላዊያን በጣዖት የሚያደርጉት ተጨማሪ ነገር ሊኖራቸዉ እንደማይገባ አስተዋሉ ፡፡ ቁጥር 9 የሁሉንም የሆሴዕን መልክ ይወክላል ፡፡

መደምደሚያ

የሆሴዕ መፅኃፍ መልዕክት ስለ እግዚአብሄር የማይለወጥ ፍቅር እና ይህም የክርስቶስን መልዕክት መቅደም እንደሆነ ነው ፡፡ ክርስቶስ ገና ኃጢዓተኞች ሳሉ ሁሉንም ነፃ ማዉጣት ፈለገ ፡፡ ሮሜ (3፡ 23) ሁሉም ኃጢዓትን እንዳደሩ ይናገራል ፤ ሮሜ (6፡ 23) ኃጢዓት ወደ ሞት እንደሚመራ ነው ፡፡ ሮሜ (5፡ 8) በእግዚአብሄር ፍቅር ተስፋን ያቀርባል ፤ ክርስቶስ በሞቱ የሰዎችን ድነት አቀረበ ፡፡ ኤፌ (2፡ 8-9) ድነት የእግዚአብሄር ስጦታ እንደ ሆነ ይናገራል ፡፡ ኃጢዓት፣ ሞት፣ ፍቅር፣ እምነት እና ሕይወት የሆሴዕን መልዕክት የገለፁ አምስት ቃላቶች ናቸው ፡፡ ሆሴዕ ማለት “ ድነት/መዳን “ ማለት ነው ፡፡

ከሆሴዕ የምንወስደው የጌታ መንገዶች ትክክሎች መሆናቸዉን የሚያካትቱ ናቸው ፡፡ ሆሴዕ ሁለት ሁኔታዎችን አቅርቧል፡ 1) መታዘዝ ወይም ደግሞ 2) አለመታዘዝ ፡፡ አስተዋይ ሲታዘዝ ሞኝ ደግሞ አይታዘዝም ፤ በመጨረሻም አለመታዘዛቸዉ እያለ እግዚአብሄር ከማይለወጥ ፍቅሩ የተነሳ ቸርነትን አሳያቸዉ/አደረገላቸው ፡፡

  1. J. Vernon McGee, Thru the Bible Volume 3: Proverbs-Malachi, (Nashville Thomas Nelson Publishers, 1983), p. 655.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 2; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/joshua.pdf.

  3. Charles Wesley; quoted in Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua (Nashville: Thomas Nelson Publications, 2003), p. 16.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament, The Prophets Isaiah-Malachi (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 329, 330.

  5. Constable, p. 107.

  6. MacArthur, p. 981.

  7. Constable, p. 107.

ጥያቄዎች

  1. በመፅኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ከእግዚአብሄር ጋር ሲታገል የያዕቆብን ታሪክ ልታገኙት ትችላላችሁ (ዘፍ 32፡ 24-30) ? ምን እንደሚመስል ምን ታስባላችሁ ? ራሱ እግዚአብሄር ነበር ? በዘፍ (32፡ 30) ያዕቆብ እግዚአብሄርን ፊት ለፊት አየሁት አለ ፤ ዮሐ (1፡ 18 እና 4፡ 12) ሁለቱም በማንኛዉም ጊዜ እግዚአብሄርን በፍፁም ያየው የለም ካሉ በዚህ ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ዘዳ 5፡ 4፣ 34፡ 10)
  2. በሆሴ (13፡ 11) ሆሴዕ ማንኛዉን ንጉስ እያመለከተ ነው (1ሳሙ 9፡ 15-17) ? ራሱ እግዚአብሄርን እንደመቃዎም ሰዎች በራሳቸዉ ላይ የሚያስተዳድራቸዉን መሪ ለምን እንደፈለጉ ምን ታስባላችሁ ? ይህ ከዛሬዉ ፖለቲካዊ/አለማዊ እይታ ጋር እንዴት ይመሳሰላል ?
  3. ሆሴ (13፡ 14) እንዴት የኢየሱስ የሚያድን ፀጋ ትንብያ ነው ? (1ቆሮ 15፡ 55-56)
  4. በሆሴ (14፡ 9) ሆሴዕ ምን እያለ ነበር ? (ኢዮ 34፡ 10-12, ሮሜ 9፡ 32-33)
  5. በሆሴዕ (12-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hosea 14:1-2

“Israel, return to Yahweh your God, for you have stumbled in your sin. Take words of repentance with you and return to the Lord. Say to Him: ‘Forgive all our sin and accept what is good, so that we may repay You with praise from our lips.’”

ጎሜር ሆሴዕን በመተው ሌሎችን ብትወድም እንኳ ሆሴዕ ግን እርሷን መውደዱን አላቆመም ፡፡ ምንም እንኳ ጎሜር ለሆሴዕ የገባችውን የጋብቻ ኪዳን ብታፈርስም እንኳ ሆሴዕ ግን እርሷ ወደ እርሱ በተመለሰች ጊዜ መልሶ ይቀበላት ዘንድ ፍቃደኛ ነበር ፡፡ ሆሴዕ ያለ ምንም ምክንያት ያለ ወረት ወደዳት ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም እስራኤልን ያለምክንያት ይወደዋል ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኪዳን ቢኖራቸውም እርሱን ትተው ሌሎች አማልዕክትን አመለኩ ፡፡ እንዲህ አድርገውም እንኳ እስራኤላውያን ሁልጊዜም ወደ አምላካቸው ወደ ያህዌ መመለስ ይችላሉ ፡፡ እግዚአብሔር ንስሀቸውን ይቀበላል ደግሞም በእርሱ ላይ ወደ ተመሰረተ ህይወት ያመጣቸዋል ፡፡

ዛሬ ይህንን እውነት ትፈልጉታላችሁን ? በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ ሌሎችን አማልዕክት የፈለጋችሁት ለምንም ያህል ጊዜ ይሁን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ለእናንተ አሁንም አለ ፡፡ ድምጹ ወደ እርሱ እንድትመለሱ ሲጠራችሁ ትሰሙታላችሁን ? እርሱን የፍቅርና የእርካታ ምንጫችሁ አድርጋችሁ ወደ እርሱ በትህትና እንድትመለሱ የሚወተውታችሁ ነገር በልባችሁ አለን ? ወደ አንዱ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስና ወደ ማይለወጥ ፍቅሩ ተመለሱ ፡፡ እርሱ ይፈውሳችኋል ፡፡ እርሱ መልሶ ያቆማችኋል ፡፡ እርሱ አዲስን ህይወት ይሰጣችኋል ፡፡ በእርሱ ላይ ስር ስደዱ እርሱም ያሳድጋችኋል ፡፡ ለእርሱ በፍጹም ልባችሁ ስትማረኩ ፣ እንደ አዲስ ታብባለችሁ ፡፡ ዛሬ በፍጹም ልባችሁ ለእርሱ ተማረኩና ጌታ የልባችሁ ንጉሥ እንድሆን ጠይቁት ፡፡

“እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሳችሁ፦ ኃጢአትን ሁሉ አስወግድ፥ በቸርነትም ተቀበለን፥ በወይፈንም ፋንታ የከንፈራችንን ፍሬ እንሰጣለን።”

  • ሆሴዕ 14፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ሆሴዕ 14:4-7a — “ቍጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ።ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል።ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፥ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል፤ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ።”

ሆሴዕ 14:9 — “ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ፥ የሚያውቃትም አስተዋይ ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው፥ ጻድቃንም ይሄዱበታል፤ ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታል።”

ኤፌሶን 2:8-9 — “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”