Minor Prophets Hosea

The Lord's Love For Israel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Unconditional Love Hosea 9-11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 689 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሆሴዕ ከታናናሽ ነቢያቶች አንዱ ነበር ፡፡ ለደቡብ እና ለሰሜን የእስራኤል መንግስት ነቢይ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ትንቢቱ አካል በአስቸጋሪ ልምምድ ዉስጥ የሚሄድ ሆሴዕ ነበረው ፤ መጀመሪያ ሆሴዕ በእግዚአብሄር ጎሜርን እንዲያገባ ተነገረው ፤ ሰዎስት ልጆች ነበሯቸው ፡፡ የልጆቹ ስም እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እንደሚበትናቸዉ እና በአሉበት በወቅቱ ሁኔታ እንደማይጠነቀቅላቸው የሚያመለክቱ ነበሩ ፡፡ ጎሜር ገለሞታ ወይም ደግሞ በቀላሉ አመንዝራ ነበረች ፤ ሆሴዕም ይህ ሁሉ እንደሚታወቅ ይመለከት ነበር ፡፡

ትምህርት

ሆሴዕ 11፡ እግዚአብሄር ሆሴዕን ለእርሱ ምን ጥንቃቄ/ትኩረት የማታደርገዉን ሚስቱን ያለገደብ/ያለምክንያት እንዲወዳት ነገረው ፤ በመሰረቱ ሚስቱ ሆሴዕን ለእርሷ በቂ እንዳልነበር ነግራዋለች ፡፡ የሆሴዕ እና ለጎሜን ያልተወሰነ ፍቅሩ ስዕል እግዚአብሄር ለእስራኤል የሚያደርገዉን ተመሳሳይ ስዕል ይወክላል ፤ እግዚአብሄር ለእስራኤል ከሁኔታ ያለ ፍቅር እንደ ነበረዉ አረጋግጧ ፡፡

እስራኤል ድንጋይ ራስ/የማትሰማ ነበረች ፤ ሆሴዕ እስራኤል እንደ ሰባ/እንደማትሰማ ጊደር/ላም እንደ ሆነች ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር ሆሴዕን ሕዝቡን እንደሚበትን እና ለእነርሱ እንደማይጠነቀቅ ነገረው ፤ የተገደሉ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ቢያንስ በምርኮ ይያዛሉ ፡፡

በሆሴዕ (11፡ 9) ጄ.ቬሮን ማክጊ ቁጥሩ እስራኤልን ወደኋላ እንደሚሸራተቱ ጊደሮች እንደገለፃት ጽፏል፡

“ በዚህን ጊዜ እስራኤል በሕዝቡ ዉስጥ ሁሉም ነገር ልክ እንደ ነበር እንደ አመላካችነት ወደ ብልፅግና መመልከት እየጀመረች ነበር ፤ በሌላ ቋንቋ/አነጋገር የገንዘባቸዉን መጠን ለመጨመር እየሞከሩ ነበር በተጨማሪም የምድራቸዉን ምርታማነት ለመጨመር እየሞከሩ ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ወደኋላ የሚንንሸራተት ጊደር እንጂ ምንም እንዳልነበሩ ተናገረ ፡፡ በብልፅግና ባርኳቸዉ ነበር ያም የመንፈሳዊ ሁኔታቸዉን እዉነታን አሳዉሮቧቸዉ ነበር “ ፡፡

ከእግዚአብሄር ይልቅ በምድሪቱ እና ብልፅግናዋ ላይ ተመለከቱ/አተኮሩ ፡፡

ቀድሞ እስራኤል ሐሰተኛ ነቢያቶችን እና የሐሰት ኃይማኖችን ተመልክታ ነበር ፤ አሁን ወደ ብልፅግና እና ቁሳዊ ንብረት ላይ ዞረዉ ነበር ፡፡ ሆሴዕ እስራኤልን ከአንድ አመንዝራ ጋር አወዳደራት ፡፡ እስራኤል ደህንነቷ በምድሯ እንደ ነበር ተሰማት ነገር ግን ምድሪቱን ስለማጣት ነበር ፡፡ እስራኤል አኗኗራቸዉን ለመጠበቅ ፈለጉ ይህም ወደ የሕዝብ ሞት እና ጥፋት መራቸው ፡፡ ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ለሞት ይይዛሉ ፤ ኃጢዓት የሞላበት ኑሮ ወደ አጭር የእድሜ ጣሪያ ይመራል ፡፡ ማክአርቱር “ የግብርና ብልፅግና በመንፈሳዊነት ብክለት የመጣ እንደ ነበር (ሕዝ 16፡ 10-19) “ ይገልፃል ፡፡ እስራኤል ከመጀመሪያ ፍቅሯ ከእግዚአብሄር ፊቷን አዙራ ነበር ፤ እግዚአብሄር በመጨረሻም ሕዝቡን ይፈርድበታል ፡፡

ሆሴዕ (11፡ 1-4)፡ እዚህ ላይ ከግብፅ በማዉጣት የእግዚአብሄር ፍቅር ለሕዝቡ መልክ ነው ፤ ከግብፅ ያመጣቸዉ ሕዝቦች የኢየሱስ የዘር መስመር ይሆናሉ ፡፡ ሆሴዕ ከእግዚአብሄር የነበረዉ ቃል ከዚህ ሕዝብ ዉስጥ የወጣዉን ልጁ ብሎ ለምን እንደሚጠራዉ እንደሚናገር ገልፆአል ፤ በእነዚህ ፁኁፎች ዉስጥ የምናገኘው እግዚአብሄር ሕዝቡን እንደሚወድ እና እግዚአብሄር ልጁን እንደሚወድ ነው ፡፡ ሁለቱም ከግብፅ ወጥተዉ ወጥተዉ ነበር ፡፡

ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በብዙ እዉነትን ሲሰሙ በብዙ ለባዖል መስዋዕትን በመሰዋት ሌሎች ጣዖቶችን አመለኩ፡፡ ሆሴዕ (12፡ 10) እግዚአብሄር በነቢያት ለሕዝቡ እንደ ተናገረ ይገልፃል ፤ ነገር ግን ይህ በብዙ ሆሴዕ ሕዝቡን ሲናገራቸው በብዙ በመተው በእግዚአብሄር ላይ በመዞር ተገለጠ ፡፡

በቁጥር 1 ለዉጡ/ሂደቱ በልጅ እና በአባት መልከ ጀመረ ፡፡ እግዚአብሄር ከሕዝቡ ጋር እንደ ነበር ሊያስተምራቸዉ ሞከረ ፤ ሕዝቡ እግዚአብሄር ለእነርሱ ሕይወትን ሰጥቷቸዉ እንደ ነበር እረሱት ፡፡ እስራኤል የራሷ ልብ እየተከተለች ነበር ጎሜርም የራሷ ልብ እየተከተለች ነበር ፡፡

በቁጥር 4 ያለዉ ስዕል እግዚአብሄር ሕዝቡን በገመድ ፍቅር እንደ መራ ነበር ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ የቁጥር 3 ስዕል እግዚአብሄርን እንደ ገበሬ እና እስራኤልን ከጭካኔ ሸክም ጋር በማወዳደር ይቀይራል ፤ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ መስመር እና ጓደኛ የሆነ ገደብን አስቀመጠ ይሁን እንጂ ስርዓቱ/ደንቡ በኃይል ወይም በማስቸገር ከማስቀመጥ ይልቅ ለሕዝቡ ፍቃድ ያለዉን ሀሳብ ያንፀባርቅ/ይገልፃል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር መንገዱን እና ሂደቱን እያሳያቸዉ ነበር ፡፡

ሆሴዕ (11፡ 5-7)፡ በቁጥር (5-7) መፅኃፍ ይመጣ የነበረዉን ቅጣት አድርሷል/ዳስሷል ፤ የእስራኤል ሕዝቦች ወደ እስራኤል ምድር አይመለሱም ፡፡ በሕዝቡ ዉስጥ የትህትና መንፈስ አልነበረም ፤ ንስኃ መግባትን እምቢ አሉ ፡፡

ቁጥር 7 ወደኋላ የመንሸራተት ሁለተኛው ማጣቀሻ ነበር ፤ በሆሴዕ ወደኋላ ለመንሸራተት ሰዎስት ዋና ዋና ማሳያዎች/ማጣቀሻዎች ነበሩ፡ 4፡ 16፣ 11፡ 7 እና 14፡ 4 ፡፡ “ ወደኋላ ተንሸራታች/ተመላሽ “ የሚለዉ ቃል ብዙጊዜ በነቢያት ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡ ማክአርቱር ቃሉ “ እዚህ ጋር ወደኋላ የተመለሰን/የዞረን ሰዉ ለመግለፅ ጥቅም ላይ ዉሏል ፤ በሞኞች፣ በክፉዎች እና በማይታዘዙት ምድብ ዉስጥ የሆነዉን ሰዉ እና ከእግዚአብሄራዊ ማስተዋል ተቃራኒ እንደ ሆነ ለመግለፅ ጥቅም ላይ እንደሚዉል ፤ ነቢያቶች ከሀዲ አላማኞችን ለመግለፅ የተጠቀሙበት ቃል እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ኤር (3፡ 6) ከእስራኤል ጋር በማነፃፀር ለአመንዝራ እና ለማያምን ማጣቀሻን ይሰጣል ፡፡

ሆሴዕ (11፡ 8-9)፡ ቁጥር 8 ለጠቅላላ ለሆሴዕ ጭብጡን ሀሳብ ይይዛል ፡፡ የእግዚአብሄር ርህራሄ በመነሳት ልቡ ተነካ ፤ አሁንም ለሕዝቡ ርህራሄ ነበር ፡፡ ሮሜ (5፡ 8) በቁጥር 8 እንደ ተገለፀዉ የማይለወጥ ተመሳሳይ ፍቅር ተጠቅሷል ፤ እግዚአብሄር ወደ ሕዝቡ በቁጣ አይመጣም ፡፡

ሆሴዕ (11፡ 10-12)፡ በቁጥር 10 የእግዚአብሄር ስዕል እንደ አንድ አንበሳ ነው ፤ ሰላም የሆነ መልክ ነው ፡፡ ኮንስታብል “ በሚመጣዉ ዘመን/ወደፊት እስራኤላዊያን ጌታን ይከተላሉ ( ቁጥር 2, 5) ፤ እንደ ገና ፍላጎቱን እንደሚያገሳ አንበሳ ያሳዉቃቸዋል (ሆሴ 5፡ 14, 13፡ 7, አሞ 1፡ 2, 3፡ 8) ፤ ይሁን እንጂ በዚህን ጊዜ አደኑን እንደሚበላ አንበሳ አይደለም ወደ ደህንነት ልጆቹን እንደሚመራ አንበሳ እንጂ ፡፡ እስራኤላዊያን ከምዕራብ በመምጣት እርሱን ይከተሉታል (ሆሴ 3፡ 5, ዘጸ 19፡ 16) “ በማለት ይናገራል ፡፡

ሕዝቡ ከምዕራብ ይመጣሉ የሚለዉ ማሳያ ሕዝቡ ከሁሉም የምድር አካል በመምጣት ተመልሰዉ ወደ እግዚአብሄር እንደሚመጡ የሚያሳይ ነበር ፡፡ ከምስራቅ መምጣት ከምርኮ መመለስ ነው ፤ ይህ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መገኘት መልሶ መሰብሰብ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ሆሴ (11፡ 8) ወደ ማይለወጠዉ ፍቅር ወደ እግዚአብሄር ልብ ልክ እንደ መስኮት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር እንዲሄዱ አይፈቅድላቸዉም ፤ ይህ የሆሴዕ ልጆች ወደ እርሱ የመመለስ መልክ በመጠቀም የእግዚአብሄር ልጆች መመለስን ስዕል መልክ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ የሚጮኸዉ አንበሳ ሁሉም ሕዝብ ወደ እርሱ እንዲመለሱ የሚጠራዉ የእግዚአብሄር መልክ ነበር ፤ በመጨረሻም ሕዝቡ ወደ ምድሪቱም ይመለሳሉ ወደ እግዚአብሄር ይመለሳሉ (ኢሳ 11፡ 11-12) ፤ ይህ የተስፋ መልክ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ፍቀር ሕዝቡ እንዲሄዱ አይፈቅድም ፡፡

  1. J. Vernon McGee, Thru the Bible Volume 3: Proverbs-Malachi, (Nashville Thomas Nelson Publishers, 1983), p. 644.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 978.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 978.

  4. MacArthur, p. 712.

  5. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Hosea; p. 90, available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/hosea.pdf.

ጥያቄዎች

  1. በሆሴ (9፡ 1) ሆሴዕ እስራኤልን በአመንዝራነት እና በግሉሙትና ከሰሰ ፤ ያዕ (4፡ 4) እንዲህ አይነቱን መንፈሳዊ “ አመንዝራነትን “ እንዴት ይገልፃል ? እግዚአብሄር እስራኤል ከሌሎች ሕዝቦች በበለጠ የጣዖት አምልኮዋን በተለዬ መስፈርት ያየዋል/ይመለከተዋልን ?
  2. ሆሴ (9፡ 16) እና ማር (11፡ 13-14) አንብቡ ፤ እነዚህ ሁለት ፅሁፎች እንዴት የሚመሳሰሉ ናቸው ? በማርቆስ ያለዉ ፅሁፍ በቀጥታ ምሳሌያዊ ሊሆን እንደሚችል ታስባላችሁ ?
  3. በሆሴ (10፡ 5) ሆሴዕ ቤትአዌን ጠቅሷል ፤ የዚህ ስም ትርጉሙ “ የክፋት ቤት “ ማለት እንደ ሆነ የሚታመን ነው ፡፡ እግዚአብሄርን የቤቴልን (የእግዚአብሄርን ቤት) ከተማ ለምን እንደ ቤትአዌን አመለከተ ? በብሉይ ኪዳን የቤቴል አስፈላጊነት/ጥቅም ምን ነበር ? (ዘፍ 28፡ 11-19, መሳ 20፡ 18, 26-28, ሆሴ 12፡ 5) ?
  4. በሉቃ (23፡ 30) ኢየሱስ ሆሴ (10፡ 8) ጠቀሰ ፤ ሆሴዕን በጠቀሰ ጊዜ ሁኔታዉ ምን ነበር ለምንስ እንደጠቀሰዉ ምን ታስባላችሁ ?
  5. ሆሴ (10፡ 12-13) በምታነቡ ጊዜ ገላ (6፡ 7-8) ታስቡታላችሁ ? መፅኃፍ የመዝራትን እና የማጨድን ማመሳሰል ሂደት ሲጠቀም ታዩታላችሁ ? (ምሳ 11፡ 18, ሆሴ 10፡ 13, ሉቃ 6፡ 38, 1ቆሮ 3፡ 6-9, 2ቆሮ 9፡ 6, ገላ 6፡ 7-9)
  6. በማቴ (2፡ 15) ፀኃፊው ሆሴ (11፡ 1) ጠቅሷል ፤ ማቴዎስ ማንን እየጠቀሰ ነበር ? በእስራኤል የኋላ ታሪክ ዉስጥ ከግብፅ የተጠራው ሌላ ማን ነበር ? ይህን ማቴዎስ እንደ መሲሀዊ ትንቢት እንዴት እንዳስተዋለዉ ምን ታስባላችሁ ?
  7. በሆሴዕ (9-11) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hosea 11:8

“How can I give you up, Ephraim? How can I surrender you, Israel? How can I make you like Admah? How can I treat you like Zeboiim? I have had a change of heart; My compassion is stirred!”

ምንም እንኳ የእስራኤላውያን ልብ ዓመጸኛ ቢሆንም እንኳ የእግዚአብሔር ርህራሄ ቀጥሏል ፡፡ እግዚአብሔር ለልጆቹ ያስባል ፡፡ እነርሱ ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ ናፈቀ ፡፡ ልቡም አዘነ ስለዚህም እንዲሁ ዝም ብሎ ሊተዋቸው አልቻለም ፡፡ ያለምክንያት ወደዳቸው ፤ ከእንደዚህ አይነቱም ፍቅር ምንም ነገር መለየት አይችልም ፡፡ እግዚአብሔር ለልጆቹ ምህረትንና ጸጋን አበዛ ፡፡

ሆሴዕ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብጽ ያወጣበትን መንገድ ሲገልጽ “ በፍቅር ገመድ “ ይለዋል ፡፡ እስኪ አስቡት በጣም ብዙ ሰው በሚስተናገድበት አየር መንገድ ውስጥ አባት ልጁን ሲመራ ፡፡ ልጁ ከእርሱ ርቆ እንዳይሄድና እንዳይጠፋበት እንደመጠባበቂያ በሚያገለግልና አባቱ መያዝ እንድችል በሚያደረግ ገመድ ልጁ ይታሰራል ፡፡ ይህ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ፍቅር የሚያሳይ ምስል ነው ፡፡ የእርሱ ልጆች ሆይ እርሱ በጣም ይወዳችኋል ፡፡ እርሱ ብቸኛ ልጁን ኢየሱስን በመላክ በፍቅር ገመድ ከባርነት ሊያወጣችሁ ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሔር ያለምክንያት ይወዳችኋል ደግሞም ፈጽሞ አይተዋችሁም ፡፡የፍቅር ገመዱ ርዝመት ምንም ያህል ይሁን የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ፈጽሞ መቼም ቢሆን ከፍቅሩ ርቃችሁ እንድትሄዱ አይለቃችሁ ፡፡ ለእናንተ የእግዚአብሔር ርህራሄ አያልቅም ፡፡ ስለ እናንተ ማንም ግድ እንደማይለው ሲሰማቸሁ ይህን እወቁ እግዚአብሔር ስለእናንተ ግድ እንደሚለውና ደግሞም እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆን ዘንድ ቃል እንደገባ ፡፡ ፍቅሩ ሰፊ ነው ከፍ ያለ ነው ደግሞም ጥልቅ ነው ፡፡ ዛሬ የእርሱን ታላቅ ፍቅር ለመቀበልና እርሱን መሪያችሁ ለማድረግ ፍቃደኛ ናችሁ ?

“ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።”

- ሆሴዕ 11፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሆሴዕ 11:1, 4 — “እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት………በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ቀምበርን ከጫንቃቸው ላይ እንደሚያነሣ ሆንሁ፥ ድርቆሽም ጣልሁላቸው፡፡”
  • ሮሜ 5:8 — “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”
  • ኤፌሶን 3:17-19 — “ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፣ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።”