False Repentance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Unconditional Love Hosea 5-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሆሴዕ ትንሽ ትንቢትን የተናገረ ታናሽ ነቢይ ነው ፤ በታላላቅ ነቢያት (ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል) እና በታናናሽ ነቢያት መካከል ያለዉ ብቸኛዉ ልዩነት የመፅኃፉ ርዝመት ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሆሴዕ የትንቢታዊ አገልግሎቱን እንዲኖርበት ጠየቀው ፤ እግዚአብሄር ሆሴዕ ጎሜርን እንዲያገባ አዘዘው ፡፡ “ እግዚአብሄር ይበትናል “ የሚል ትርጉም ያለዉ ኢይዝራኤል ልጃቸዉ ነበር ፤ ቆይተዉም የስሟ ትርጉም “ አልምርም “ የሚል አንዲት ሴት ልጅ እና “ ሕዝቤ አይደሉም “ የሚል የስም ትርጉም ያለዉ አንድ ወንድ ልጅ ነበሯቸው ፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝቦች የተበታተኑ ቢሆኑም፣ ቸርነትን/ርህራሄን ባያሳያቸዉም እና የእሱ ሕዝብ እንዳልነበሩ ቢታዩም እንኳን እግዚአብሄር ያለማቋጥ ሕዝቡን የማይቀየር ፍቅርን አሳያቸው ፡፡
ጎሜር ገለሞታ ሴት ነበረች ፡፡ ከማግባቷ በፊት ገለሞታ እንደ ነበረች ወይም ደግሞ ካገባች በኋላ ይህን ባህሪ እንደጀመረች እርግጠኞች አይደለንም ፤ በአንዱ መንገድ ጎሜር ለሆሴዕ የታመነች አልነበረችም ፡፡ ታማኝ ባለመሆን ሂደት ዉስጥ ሆሴዕን ዋጋ አትሰጠዉም ፤ ጎሜር ለእግዚአብሄር ያልታመነችዉ እና ዋጋ ያልሰጠችዉን የእስራኤልን መልክ ሆነች ፡፡ እግዚአብሄር ሆሴዕን እግዚአብሄር እንዴት ሕዝቡን እንደሚወድ እንደ ማሳያነት ያለምክንያት ሚስቱን እንዲወድ መራው ፡፡
ትምህርት
ሆሴዕ 5፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ ምዕራፍ 5 በእግዚአብሄር ካህናቱን እና ንጉሱን ሁለቱንም የእስራኤልን መሪዎች በማዉገዝ እንደሚጀምር ፃፈ ፡፡ በእስራኤል ሁሉም ከክፋታቸዉ የተነሳ ይሰናከላሉ (ቁጥር 5) ፡፡ ሕዝቡን አዘን ማጥቃት በጀመረ ጊዜ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሄር ይመለከታል ነገር ግን እግዚአብሄር አልመለሰላቸዉም (ቁጥር 6) ፤ የማይለወጠዉ ፍቅር ጠንካራ ፍቅር ሊሆን ቢችልም ፡፡ ኤፍሬም “ ደዌዉን “ ባስተዋለም ጊዜ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ሳይሆን ወደ አሶር ዞረ (ቀጥር 13) ፤ ይህ በጎሜር የተወከለዉ አለመታመን ነበር ፡፡ ለእስራኤል በሚያናድድ ሁኔታ የአሶር ንጉስ “ ሊያድናቸዉ እና ከቁስላቸዉ ሊፈዉሳቸዉ አልቻለም “ (ቁጥር 13) ፡፡ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ የሚወድቀዉን ፍርድ በመገነጣጠል ከሚወስዳቸዉ አንበሳ ጋር አወዳደረው (ቁጥር 14) ፡፡ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሄር መገኘት እስራኤል “ ጥፋታቸዉን በማመን ፊቱን እስኪሹ “ (ቁጥር 15) ድረስ ይለያቸዋል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ንስኃ ለመግባት እና ጌታን ለመፈለግ ከመዘጋጀታችን በፊት በሚገባ ድንጋይ የሆነን ነገር መምታት አለብን ፡፡
ሆሴዕ (6፡ 1-3)፡ በመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ቁጥሮች የእስራኤል ሰዎች ተናገሩ ፡፡ በእነርሱ ላይ የተፈፀመዉ ጥፋት በእግዚአብሄር እጅ እንደተፈፀመ አስተዋሉ፡ “ እርሱ ሰብሮናልና እርሱም ይፈዉሰናል “ (ቁጥር 1) ፡፡ በኃሳብ ደረጃ ትክክል ቢሆኑም ዋይርስቤ የተጠቀሙበት ንግግር/ቋንቋ “ የሕዝብን ሐሰተኛ ንስኃን “ እንደሚገልፅ ፅፏል ፡፡ ሕዝቡ ስለኃጢዓታቸዉ ኃላፊነትን አልወሰዱም ፤ አመለካከታቸው “ እግዚአብሄር ይህን ነገር በእኛ ላይ ስላደረገ ያስተካክለዋል “ የሚል ይመስላል ፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሄርን ስለ ማወቅ እና ስለ መከተል ቢያወሩም የሙሉ ንስኃ የመግባት ነገር አልነበረም ፡፡
ሆሴዕ (6፡ 4-6)፡ እግዚአብሄር ለእርሱ የእስራኤላዊያንን ታማኝነት “ ከማለዳ ደመና “ እና “ በማለዳም ከሚያልፍ ጠል “ (ቁጥር 4) ጋር በማወዳደር ምላሽ ሰጠ ፡፡ እግዚአብሄር ከኃይማኖታቸዉ ድርጊት/ተግባር በላይ በእስራኤላዊያን ልብ ሁኔታ እና ከእርሱ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት በይበልጥ ያተኮረ ነበርሰ (ቁጥር 6) ፡፡ እስራኤላዊያን ድርሻቸዉን መጫወት ችለዋል ነገር ግን እግዚአብሄር የኃይማኖት ስርዓታቸዉን ከማድረግ በላይ ፈለገ ፡፡ ሳሙኤል ተመሳሳይ ስሜትን/ሀሳብን ገልፆ ነበር፡ “ ሳሙኤልም፡- በዉኑ የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሄር በሚቃጠልና በሚታረድ መስዋዕት ደስ ይለዋልን ? እነሆ መታዘዝ ከመስዋዕት ማዳመጥም የአዉራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል ፡፡ ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢዓት እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው ፤ የእግዚአብሄርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሄር ንጉስ እንዳትሆን ናቀህ አለ “ (1ሳሙ 15፡ 22-23) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር የሚመለከተዉን የንስኃ መግባት አመለካከትን ገልፆአል፡ “ አቤቱ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያወራል ፡፡ መስዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር ፤ የሚቃጠለዉም መስዋዕት ደስ አያሰኝህም “ (መዝ 51፡ 15-16) ፡፡
ሆሴዕ (6፡ 7)፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ከእርሱ ጋር ያደረጉትን ኪዳን በመተላለፍ ከሰሳት ፤ እግዚአብሄር የጠቀሰዉ ኪዳን በእግዚአብሄር መካከል በሲና ተራራ ላይ የተደረገ የሙሴ ኪዳን ነበር፡ “ አሁንም ቃሌን በእዉነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልናላችሁ ፤ እናንተም የካህናት መንግስት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ ፡፡ ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው “ (ዘጸ 19፡ 5-6) ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረዉን ኪዳን የእስራኤል መካድ በሁሉም መንገድ መልሶ በኤደን ገነት እግዚአብሄርን የአዳምን መካድ የሚያስታወስ ነበር (ቁጥር 7) ፡፡
ሆሴዕ (6፡ 8-11)፡ በቁጥር 8-9 የመማፀኛ ከተማ የነበሩት ገለዓድ እና ሴኬም ስለፈፀሙት ኃጢዓት ተጠቅሰዋል ፡፡ የእስራኤል ኃጢዓት ታላቅ ስለ ነበር የመማፀኛ ከተሞችም እንኳን የኃጢዓት ማደረጊያ ስፍራ ሆነው ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህ ከተሞች ሰዎች መፅናናትን ማግኘት የሚችሉባቸው የተረጋጋን ስፍራን የሚሰጡ ከተሞች እንደ ነበሩ ነገር ግን ከኃጢዓት ጋር የተነካኩ እንደሆኑ አመለከተ ፡፡ በጣም የከፋ ሊሆን ስለሚችል እግዚአብሄር ራሱ ስለ ሕዝቡ ኪዳንን መጣስ መስክሮ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን (የሰሜኑን መንግስት) ስለ ኪዳን ማፍረሳቸዉ ሲናገር ማክአርቱር “ ነቢዩ እየጠበቃቸዉ ያለ የፍርድ ቀን እንዳላቸዉ እንዳስታወሰ ፃፈ ፡፡
እግዚአብሄር ስለ ኃጢዓታቸዉ የተሰበረ እና ፀፀት የሞላበት ልብ እንዲኖራቸዉ ፈለገ ፤ እስራኤል ግን የራሳቸዉን ኃጢዓትን እንኳን ሳያምኑ የንስኃ ድርጊትን ለማድረግ እና እንዲረዳቸዉ እግዚአብሄርን መጠየቅን ይዞ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን አይነት ልብን ገልፆአል፡ “ ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል ፡- የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያዉ አደርግ ዘንድ የተቀጠቀጠዉንም ልብ ሕያዉ አደርግ ዘንድ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ “ (ኢሳ 57፡ 15) ፡፡ ሆሴዕ እስራኤላዊያንን እንዲህ አይነት የተዋረደ እና የተፀፀተ ልብ እንደሌላቸዉ አሳዬ ፡፡ ከችግሩ እንዴት እንደሚወጡ ብቻ በይበልጥ ያስቡ ነበር ፤ ራሳቸዉን ያገኙበትን ሁኔታ ያለ ንስኃ እንዲያወጣቸዉ በእግዚአብሄር ላይ እያሳበቡ ነበር ፡፡
ሆሴዕ 7፡ ሁሉንም ነገር እያለ እግዚአብሄር ሕዝቡን እንደሚፈዉስ ተስፋን ሰጠ ፤ ነገር ግን ፈዉስ ሲመጣ “ የተጋለጡ ይሆናሉ “ (ቁጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም የእስራኤልን ኃጢዓት አይቶ ነበር ፤ ከዘህም የተነሳ መፅናናትን በመፈለግ በአሶር እና በግብፅ መካከል ወደ ፊትን ወደ ኋላ እንደሚነጥር “ አዕምሮ እንደሌላት ሰነፍ እርግብ ሆኑ “ (ቁጥር 11) ፡፡
ሆሴዕ 8፡ እግዚአብሄር ለእርሱ የእስራኤልን አለመታመን ማሳየቱን ቀጠለ ፡፡ ከሁሉም ነገር ሌላ ተጨማሪ በጥፋታቸዉ ላይ ጣዖት አምልኮን ጨመሩ ፡፡ የእግዚአብሄር ብስጭትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ፡ “ እስከ መቼ ድረስ ንጹሕ ሊሆኑ አይችሉም (ቁጥር 5) “ ?
መደምደሚያ
ይህ ቀጣዩን ለማስተካከል በኃጢዓት የኑሮ እስታይል እንዴት መኖር እንዳለብን አይደለምን ? ይህ አይሰራም ፡፡ ሆሴዕ 6, 7 እና 8 በኃጢዓት ማስተካከያ እንዲኖራቸው ስለቀጠሉ ስለ እስራኤል ዉሸቶች ናቸው ! ይህ ሁሉም ነገር እያለ አሁንም እግዚአብሄር ሕዝቡን ወደዳቸው ፤ ለጥሪዉ በመታዘዝም ሆሴዕ አሁንም ጎሜርን ወደዳት ፡፡
J. Vernon McGee, “Notes on Hosea,” https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/hosea/hosea-outline.cfm.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Hosea (Colorado Springs: David C. Cook, 2002), p. 322.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1032.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 977.
ጥያቄዎች
-
በሆሴ (6፡ 3) እንዳለዉ በመፅኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የቀድሞዉ እና የአሁን ዝናብ የተጠቀሰ ነው (ኢዩ 2፡ 23, ሐዋ 2፡ 17-21) ? በሁለቱ ማጣቀሻዎች/ማሳያዎች መካከል ልዩነቶች አሉ ?
-
ኢየሱስ ፍቅር/ምህረት ከሚቃጠል መስዋዕት ይበልጣል አለ (ማቴ 9፡ 13, 12፡ 7) ፤ እነዚያ ፅሁፎች በሆሴ (6፡ 6) እንዳለዉ ተመሳሳይ ነገር የሚያስተምሩ ናቸው ? ለምን ?
-
የእስራኤል ሰዎች/ሕዝቦች በአንድ በኩል ከበሰለ ቂጣ ጋር የተወዳደሩ ነበሩ (ሆሴ 7፡ 8) ፤ በአንድ በኩል የበሰለዉ ቂጣ ጉዳዮች ምንድን ናቸው ? ከቂጣ ጋር ለምን ነበር የተወዳደሩት ?
-
በሆሴዕ (5-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hosea 6:6
“For I desire loyalty and not sacrifice, the knowledge of God rather than burnt offerings.”
ልክ እግዚአብሔር አስራኤልን እንደወደደ ሁሉ ሆሴዕም ምንም እንኳ በትዳርዋ ታማኝ ባትሆንም ጎሜርን ወደዳት ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያን የእውነት ንስሀ እንድገቡ ስለሚፈልግ እነርሱ ፡- እግዚአብሔርን ለማወቅ እንትጋ ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እርሱም ይፈውሰናል በማለት ሲናገሩ ውሸታም ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ትሁት ልብን እንጂ ሰዎች እግዚአብሔርን እየተከተሉ እንደሆነ ለማስመሰል የሚያደርጉትን ለታይታ የሚደረግ ኃይማኖታዊ ድርጊትን አይደለም ፡፡ ምንም እንኳ ኃጢአትን ቢሰሩም ፣ እግዚአብሔር ታገሳቸው ለእነርሱም ያለውን ፍቅር አልቆመም ፡፡
በብዙ መንገድ ዛሬም ይህ የከንፈር ብቻ የሽንገላ አገልግሎት ለእግዚአብሔር ይቀርባል ፡፡ እግዚአብሔር ልባችሁን ይፈልገዋል ፡፡ እርሱ ታማኝነታችሁን ይፈልገዋል ፡፡ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ይፈልጋል ፡፡ እርሱ ከንቱ የሆነ የኃይማኖት ስርዓት አይፈልግም ፡፡ እርሱ እናንተ በፍጹም ልባችሁ እንድትወዱት ይፈልጋል ፡፡ ልባችሁን ትሁት ሳታደርጉ የውሸት ንስሀ አትግቡ ፡፡ ፍቅሩን ታገኙ ዘንድ በታማኝነት በፍጹም ትህትና ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ደግሞም በቀጥታ ይቅርታውን ለምኑ ፡፡ ጽዋችሁን መሙላት የሚችለው ፣ ጥማታችሁን ማርካት የሚችለው ደግሞም ሊፈውሳችሁ የሚችለው እርሱ ብቻ እንደሆነ እውቅና ስጡ ፡፡ ነገር ግን በእርሱ ፊት እውነተኛ መሆን ይገባችኋል ፡፡ ዛሬ በፊቱ ቅረቡ ፡፡ በራሳችሁ ኃይል መታገል አቁሙ ፡፡ እውነተኛ ሁኑ ፡፡ ግልጽ ሁኑ ፡፡ ሁሉን ነገር በመስቀሉ ስር ጣሉት ፡፡ ፍቅሩን ተቀበሉ በመታዘዝም ተመላለሱ ፡፡
“ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን ፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና ። ” - ሆሴዕ 6፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
- 1ኛ ሳሙኤል 15:22 — “ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።”
- መዝሙር 51:16-17 — “መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም። የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።”
- ኢሳይያስ 57:15 — “ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።