Minor Prophets Hosea

Hosea's Marriage And Children

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Unconditional Love Hosea 1-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 687 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ታናናሽ ነቢያት ተብለዉ በሚታወቁት በ 12 መፅኃፍት ላይ አዲስ ክፍልን ጀምረናል ፡፡ በታላላቅ እና በታናናሽ ነቢያት መካከል ያለዉ ዋና ልዩነት የትንቢታቸዉ እርዝማኔ ነው ፡፡ ታላላቅ ነቢያት ኢሳይያስን፣ ኤርምያስን፣ ሕዝቅኤልን እና ዳንኤልን እንዲሁም ደግሞ በኤርምያስ ስለተፃፈ የሰቆቃዉ ኤርምያስንም መፅኃፍ ይይዛል ፡፡ ዛሬ በሆሴዕ መፅኃፍ ላይ እናተኩራለን ፤ የሆሴዕ ስም ትርጉሙ “ ድነት/ደህንነት “ ማለት ነው ፤ ስሙ ስማቸዉ “ድነት “ የሚለዉን የሚያመለክቱትን ኢያሱን እና ኢየሱስን ሁለቱንም ያሳያል ፡፡ እነዚህን ታናናሽ ነቢያት ስናጠና/ስንዳስስ ተመልሰን በአሶር እና በባቢሎን ስር በምርኮ እንዳለን ይሰማናል ፡፡

ሆሴዕ አስሩ በአስሩ የእስራኤል ነገዶች በሰሜኑ መንግስት ቋንቋ የተፃፈ ነበር ፡፡ የደቡቡ መንግስት የይሁዳን እና የቢንያምን እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ከተማ ይይዛል ፡፡ ፀኃፊዉ ሆሴዕ እንደ ሆነ እናዉቃለን ነገር ግን ስለ እርሱ እና ስለ አባቱ ብኤር ብዙ አናዉቅም (ሆሴ 1፡ 1) ፡፡ ማክአርቱር ዮሐንስ “ ምናልባትም ሆሴዕበታሪኩ፣ በሁኔታዎች፣ በሰሜኑ መልከዓ ምድር ላይ አድስእንዳልሆነ/አዋቂነቱን ካሳዬ የእስራኤል የሰሜኑ መንግስት ነዋሪ ነበር …. እስራኤልን (የሰሜኑን መንግስት ) እና ይሁዳን (የደቡቡን መንግስት) ሁለቱንም ቢደርስም የእስራኤልን ንጉስ ንጉሳችን በማለት እንደለየዉ (7፡ 5) “ ተናግሯል ፡፡ የሆሴዕ አገልግሎት ረጅም ነበር - ከክርስቶስ ልደት ከ760-715 በፊት ነበር ፤ በዚህን ጊዜ የደቡቡ መንግስት ነገስታት ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝ እና ሕዝቅያስን ይይዛል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ በእስራኤል በመጨረሶቹ ስድስት ነገስታቶች ዘመን አገልግሏል ፡፡

ሆሴኤ በሰሜኑ መንግስት የአሞፅን ስብከቶች ከተለ ፤ ኢሳይያስ እና ሚክያስ ባገለገሉበት በተመሳሳይ የጊዜ መዋቅር ዉስጥ አገለገለ ፤ ይህን በአሰራር ሲቀመጥ ኢሳይያስ ስለ ምርኮዉ ፃፈ ነገር ግን በፍፁም አላደረሰበትም ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት የሚያስፈልግ ቀን ነው ምክንያቱም የደቡቡ መንግስት በባቢሎን ምርኮ የወደቀበት ጊዜ ሲሆን በብዛት በታናናሽ ነቢያት ዉስጥ የምን መለከተው የሰሜኑ መንግስት በአሶር ስር የወደቀበትን ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት ቀን ነው ፡፡ ስለ ሰሜኑ እና ደቡቡ መንግስት ሌላ ማስታወስ የሚያስፈልገው ነገር በመንፈሳዊ ነገር ጠንካሮች እንዳልነበሩ ነው ፡፡ ተስፋን አቅርቦ የነበረዉ ብቸኛዉ ንጉስ ሆሴዕ ብቻ ነበር ፡፡ ሆሴዕ በአስቸጋሪ ሁኔታ/አካባቢ ዉስጥ እዉነትን ተናገረ ፡፡

እንደ ማክአርቱር ገለፃ ሆሴዕ የብሉይ ኪዳን “ ቅዱስ ዮሐንስ “ በመባል ይጠራል ምክንያቱም ዮሐንስ በፍቅር የሚታወቅ ሐዋሪያ ስለ ነበር ፡፡ ሆሴዕ በፅኁፉ ዉስጥ “ የማይቀየር ፍቅር “ የሚለዉን ሐረግ ይጠቀማል ፤ ሆሴ (11፡ 1) እግዚአብሄር ሕዝቡን ምን ያክል እንደሚወዳቸዉ ይገልፃል ፤ ሆሴዕ ጣዖቶቻቸዉ እያሉ እንኳን ለኪዳን ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ፍቅርን ያሳያል ፡፡ በትክክል ሆሴዕ ክርስቶስ ለእኛ ላደረገው ጥላ ነበር ፡፡ በመፅኃፉ ዉስጥ “ የኃጢዓት፣ የፍርድ እና የይቅርታ ፍቅር “ ፍሬ ነገሮች አሉ ፤ ይህ ጭብጥ/ፍሬ ነገር ወደ ሮሜ (5፡ 8) “ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሄር ለእኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ! “ መንፈሳዊ ጣዖት አምልኮአችንን ሳያይ ያደረግነዉን ሳያይ ክርስቶስ ስለ እኛ ሞት ያለ ገደብ/ ያለ ሁኔታ ወደደን ፡፡

ትምህርት

ሆሴዕ (1፡ 1-2)፡ እግዚአብሄር ሆሴዕን ገለሞታ ሴት እንዲያገባ ነገረው ፤ ኮንስታብል ቶም ለዚህ ጥቅዝ ብዙ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጓሜዎችን ገልፆአል፡ ምናልባትም “ እግዚአብሄር ሆሴዕን ሚስቱ ገለሞት እንደ ነበረች ወይም እንደምትሆን ራዕይ እንደ ሰጠው ወይም ምሳሌን እንደነገረው “ ፤ ምናልባትም ሐሰተኛ አማልዕክትን ስለምታመልክ መንፈሳዊ ጋለሞታ ነበረች ፡፡ ምናልባትም ሆሴዕ እርሷን ሳያገባት በፊት በወሲብ ጋለሞታ/አመንዝራ ነበረች ፤ ወይም ደግሞ ምናልባት ከተጋቡ በኋላ የታመነች አልሆነችም ነበር ማለት ይሆናል ፡፡ የተወሱ አለመታመኖች ቢኖሩባትም እንኳን እግዚአብሄር ሆሴዕ ለባለቤቱ በመታመን እንዲቀመጥ ፈለገ ፡፡

ሆሴዕ (1፡ 3-5)፡ ይህንን ስናጠና ሆሴዕን በእግዚአብሄር እና ጎሜርን በእስራኤላዊያን ስፍራ ልንስል ይገባናል ፡፡ የሆሴዕ የመጀመሪያ ልጅ ስሙ ኢይዝራኤል ነበር ፤ ስሞች በመፅኃፍት በጣም አስፈላጊዎች ናቸው ፤ ኢይዝራኤል ማለት “ እግዚአብሄር ይበትናል “ ማለት ነው ፡፡ በትንቢታዊነት ይህ አሶር እስራኤን የያዘበትን ጊዜ እና በአሕዛቦች ተበታትነዉ የነበረዉን እዉነት እንድናስብ ያደርገናል ፤ ይህ ከክርስቶስ ልደት በ722 በፊት “ በዚያ ቀን ላይ “ ስለ

አሶር መያዝ ትንቢታዉ ቃል ነበር ፡፡

ሆሴዕ (1፡ 6-7)፡ በመቀጠልም ጎሜር የስሟትርጉም “ ምህረት የለም /አልምርም “ የሆነ ሎሩሃማ የምትባል አንድ ሴት ልጅ ወለደች ፤ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ምህረት/ርህራሄ እንደማይኖረዉ አስጠነቀቀ ፡፡ የልጂቱ ስም “ አለመራራት “ ማለትም ስለሆነ እግዚአብሄርም ለእስራኤል ርህራሄ አይኖረዉም ፡፡ በተቃራኒው እግዚአብሄር በይሁዳ ቤት ላይ ርህራሄ ይኖረኛል አለ (ቁጥር 7) ፤ ከክርስቶስ ልደት በ701 ፊት እግዚአብሄር ይህን ርህራሄ 185,000 አሶራዊያንን በገደለ ጊዜ (2ነገስት 19) ለይሁዳ አሳይቷል ፡፡ አዎ አሁን እግዚአብሄር ሕዝቡን ይወዳል ነገር ግን በእነርሱ እንዳልተደሰተ እንዲያዉቁ ፈለገ ፡፡

ሆሴዕ (1፡ 8-10)፡ ሴቷ ልጅ ጢት መጥባት ባቆመች ጊዜ (በእናቷ ወተት መደገፍን ባቆመች ጊዜ) ጎሜር በመፀነስ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች ፤ ስሙም ሎዓሚ ነበር ትርጉሙም “ ሕዝቤ አይደላችሁም ማለት “ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ያለዉን ኪዳን እየሰበረ እንደ ሆነ የሚናገር ቢመስልም ለእርሱ ስላለመታመናቸዉም ዉጤቱ እንዲደርስባቸው ፈቀደ፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤል ካለዉ ከሁኔታ ያለፈ ፍቅር የተነሳ “ ሕዝቤ አይደላችሁም “ ቢልም እንኳን “ የህያዉ እግዚአብሄር ልጆች ተብላችሁ ትጠራላችሁ “ አላቸው ፡፡ በአለመታመናቸዉም እንኳን እግዚአብሄር ለእርሱ የታመነ ቅሬታን ያስነሳል ፤ ይህ መቼ ነዉ የሚሆነው ? ይህ እርግጠኛ ድምፅ ስለ ሺዉ አመት በረከትን ይመስላል ፡፡ ሆሴዕ ስለ መጀመሪያዉ መምጣት እያወራ አልነበረም ምክንያቱም በግልፅ እስራኤል ክርስቶስን ስላልያዘች ፤ ሆሴዕ ከሰባት አመቱ መከራ በኋላ ስለሚመጣዉ ሁለተኛዉ መምጣት አወራ ፡፡ ይህ እስራኤል የህያዉ እግዚአብሄር ልጆች እንደ ሆኑ መረዳት የሚጀምሩበት ጊዜ ነው ፡፡ ሮሜ (8፡ 14) “ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸዉና “ ይላል ፡፡ የሆነ ስፍራ/ጊዜ ላይ አይሁዶች ይህ ይይዛሉ ፤ በዮሹዋ/በኢየሱስ በሚያምኑ ጊዜ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመቀበል ራሳቸዉን እንደ እግዚአብሄር ወንድ እና ሴት ልጆች ይለያሉ ፡፡

ሆሴዕ (1፡ 11)፡ ይህ ሆሴዕ ስለ ሺዉ አመት በረከት እያወራ እንደ ነበር የምናዉቅበት ነው ፡፡ የሆነ ስፍራ ላይ ሁሉም 12 የእስራኤል ነገዶች እና ይሁዳ በአንድ ላይ በመሰብሰብ አንድ ንጉስን ይሾማሉ ፤ የሚመጣዉን መሲህ እያመለከቱ ነው - የኢየሱስን መጀመሪያዉን መምጣት አይደለም - የኢየሱስን ሁለተኛዉን መምጣትን እንጂ ፡፡

ይህን መልክ እወድዋለሁ፡ እግዚአብሄር ይበትናቸዋል ነገር ግን አሁን እንደ ገና ሁሉምበአንድ ላይ ተሰብስበዉ መጥተዋል ፡፡ ለሁሉም ከሁኔታ ያለፍ ፍቅር የሚያሳይ አንድ ንጉስ አንድ አስተዳዳሪ ይኖራቸዋል ፡፡

ሆሴዕ (2፡ 1- 4፡ 19)፡ ጄ. ቬሮን ማክጊ የእነዚህን ምዕራፎች አጠቃላይ እይታን ይሰጣል ፡፡ ጎሜር ታማኝ አለመሆኗን አረጋገጠች ፤ እስራኤል ታማኝ አለመሆኗን አረጋገጠች ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ታማኝነቱን አረጋገጠ፡፡ በሆሴዕ 3 ጎሜር መጥፎ ነገር ባደረገች ጊዜ እግዚአብሄር ሆሴዕን ነገሩን በመተዉ ለሚስቱ ፍቅር እንዲያሳያት ነገረው ፤ በዘሌዋዊያን ሕግ መሰረት ጎሜር በድንጋይ ተወግራ መሞት አለባት ፡፡ ነገር ግን ይህ የማይለወጠዉ ፍቅር እነዚህን ሁሉ ኃጢዓቶቿን ሸፈነላት/አስወገደላት ፡፡ በሆሴዕ 4 ጎሜር ከሆሴዕ ዞር ማለቷ እስራኤል ከእግዚአብሄር ዞር የማለቷ መልክ ነው ፤ ሆሴዕ ሁሉንም በመተዉ ሚስቱን መያዙ/መቀበሉ ሁሉንም በመተዉ እግዚአብሄር እስራኤልን የያዘበት/የተቀበለበት መልክ ነው ፡፡ በሆሴዕ 4 እስራኤል ግልሙትናዋን መጫወት ቀጠለች ፤ ሕግን በመተላለፍ እና በስነ ምግባር ብልሹነት ጥፋተኞች ናቸው ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ችላ የሚሉ እና የማያስቡ/የማይጠነቀቁ ናቸው ፤ በምድሪቱ እዉነት የለም፣ የታመነ ፍቅር የለም እንዲሁም የእግዚአብሔር እዉቀት የለም (ሆሴ 4፡ 16) ፡፡ እስራኤል በግልፅ ወደኋላ በመንሸራተት እንደ እልከኛ ላም/ጊደር እምቢ አለች (ሆሴ 4፡ 16) ፤ እስራኤል ባያስብም/ባይጨነቅም እግዚአብሄር እስራኤልን ወደደ ፡፡

መደምደሚያ

በዚያን ጊዜ የማታስብ/የምትጠነቀቅ በምትመስል ጊዜ እግዚአብሄር እስራኤልን እንደ ወደዳት ሆሴዕ ባታስብም/ባትጠነቀቅም ጎሜርን ይወዳታል ፡፡ ሆሴዕ ሁኔታዎቹ እያሉ በማይለወጥ ፍቅር የመዋሀድ መልክ ነው ፤ ይህ ለሆሴዕ መፅኃፍ ጭብጥ ነው ፡፡ ነገ ሆሴ (5-7) ማጥናታችንን እንቀጥላለን ፡፡

8 McGee, np.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 970.

  2. MacArthur, p. 970.

  3. MacArthur, p. 971.

  4. MacArthur, p. 971.

  5. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Notes on Hosea, p. 20; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/hosea.pdf

  6. Constable, p. 21.

  7. J. Vernon McGee, Thru the Bible Commentary Series: Hosea and Joel (Nashville: Thomas Nelson, 1975, 1991), np.

ጥያቄዎች

  1. ከእግዚአብሄር (ልክ በሆሴ (1፡ 2) እግዚአብሄር ለሆሴዕ እንደ ነገረው) አመንዝራ/ጋለሞታ ሴት እንድታገቡ ብትጠየቁ እንዴት እንደምታደርጉ ምን ታስባላችሁ ?
  2. ሆሴዕ 2 የእግዚአብሄርን ፍቅር ለልጆቹ እንዴት አድርጎ መሰለው ?
  3. በሆሴ (3፡ 2) ሆሴዕ ጎሜርን በ15 ብር፣ በጥቂት ገብስ እና ወይን መልሶ ገዛት ፤ በዘጸ (21፡ 32) ተጎድቶ ከነበረዉ ባሪያ/አገልጋይ ጋር ዋጋዉ እንዴት ተወዳደረ ? ዋጋዉ ለምን የተለያዬ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
  4. በ ሆሴዕ (1-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hosea 3:1

“Then the LORD said to me, ‘Go again; show love to a woman who is loved by another man and is an adulteress, just as the LORD loves the Israelites though they turn to other gods and love raisin cakes.”

ሆሴዕ የሚያደርገው ትንቢታዊ መልዕክቶችን ለእስራኤላውያን መናገር ብቻ አልነበረም ይልቁንም እርሱም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመቀበል ትንቢቶቹን በመታዘዝ ይፈጽምም ነበር እንጂ ፡፡ በእግዚአብሔርም ትዕዛዝ መሰረት ሆሴዕ ጎሜር የተባለች ሴት አዳሪ ሴትን አገባ ፡፡ ምንም እንኳ ጎሜር ከሆሴዕ ጋር የገባችውን የጋብቻ ቃል ብታፈርስም እንኳ ሆሴዕ ልክ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ወደ ሌሎች አማልክቶች ፊተቸውን ያዞሩትን እስራኤላውያንን እንደወደዳቸው ሁሉ እርሱም ዘማዊ የሆነች ሚስቱን ይወድድ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተከተለ ፡፡

ልክ ሆሴዕ የሚስቱ ታማኝ አለመሆን ሳይገድበው እርሷን ደግሞ ደጋግሞ እንደወደዳት ሁሉ ፣ እግዚአብሔርም ፍቅሩን ለመግለጽ ጋና ኃጢአተኞች ሳላችሁ ስለእናንተ ይሞት ዘንድ ልጁን ላከ ፡፡ በኢየሱስ ስታምኑ ፣ በነጻ የእግዚአብሔርን ጸጋ ፣ ፍቅርና የዘላለም ህይወትን ታገኛላችሁ ፡፡ የክርስቶስን ፍቅር እንድታገኙ የሚያደርግ ምንም ነገር አልሰራችሁም ፡፡ እርሱ እንዲሁ እንዳላችሁ ይወዳችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው ፍቅር ፈጽሞ አያልቅም ፡፡ ከእርሱ እርቃችሁ ብትሄዱ እንኳ እርሱ እንደገና ወደ እናንተ መጥቶ ፍቅሩን ያሳያችኋል ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ፈጽሞ ከእናንተ አይለየም ፡፡ በተመሳሳይ እናንተም ሌሎች እየጎዷችሁ እየራቋችሁ እንኳ ሳሉ አነርሱን ትወዱ ዘንድ ተጠርታችኋል ፡፡ ልክ ሆሴዕ ጎሜርን እንደወደዳት ሁሉ እናንተም እንደገና እንድትሄዱና ፍቅርን እንድታሳዩ ተጠርታችኋል ፡፡ ዛሬ እንደገና ሂዱና የክርስቶስን ፍቅር በዙሪያችሁ ላሉ አሳዩ ፡፡

“በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው ።”

- ሆሴዕ 1፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሮሜ 5:8 — “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”
  • ሮሜ 8:38-39 — “ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።”
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:19 — “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።”