General Letters Jude

Contending For The Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Merciful Lord Jude 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 686 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የይሁዳ ጥናታችን የአጠቃላይ መልዕክት ክፍልን ይጨርሳል ፡፡ የይሁዳ መፅኃፍት በመጨረሱ ዘመን ስለ እምነት ተፎካካሪ ስለመሆን ነው ፡፡ በመጨረሻው ዘመን ላይ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ላይ በራሳቸዉ አጀንዳ እና በስሕተት አስተምሮ እና ትምህርት ቀስ በማለት ይመጣሉ ፡፡ ይሁዳ መልዕክቱን ስለ ድነት በማዉራት እንደሚፈልግ ነገር ግን በይበልጥስለ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ማስፈራት እንደሚያተኩር በመናገር ጀመረ (ቁጥር 3)

“ ይሁዳ “ የሚለዉ ርዕስ “ ይሁዳን እና ይሁዳህ ቅርፅ የሆነና በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን የተለመደ ስም ነበር ፡፡ ምሁራን ፀኃፊዉ ይሁዳ ከኢየሱስ አራት የእናት ወንድሞች ዉስጥ አንዱ እንደ ነበር ይስማማሉ ፤ በማቴ (13፡ 55) እና ማር (6፡ 3) እንደ ይሁዳም ተብሎ ተዘርዝሯል ፡፡

ይሁዳ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ አራተኛዉ አጭሩ መፅኃፍ ነው (ከ 2ዮሐንስ፣ ከ 3ዮሐንስ እና ከፊልሞና በመቀጠል ) ፡፡ ይሁዳ ይሁዳ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን ጥቅስ አልጠቀሰም ነገር ግን ዘጠኝ ማሳያዎችን አድርጓል ፤ ማክአርቱር የማሳያዎቹን ዝርዝር ይሰጣል፡ 1) ከግብፅ መዉጣታቸዉን (ቁጥር 5)፣ 2) የሰይጣንን አመፅ (ቁጥር 6)፣ 3) ሰዶምንና ገሞራን (ቁጥር 7)፣ 4) የሙሴን ሞት (ቁጥር 9)፣ 5) ቃየልን (ቁጥር 11)፣ 6) በለዓምን (ቁጥር 11)፣ 7) ቆሬን (ቁጥር 11)፣ 8) ሄኖክን (ቁጥር 14) እና 9) አዳምን (ቁጥር 14) ፡፡ በሐሰተኛ አስተማሪዎች ላይ ስለ እምነቱ በመታገል ይሁዳ የእግዚአብሄርን ቃል ማወቁን ማስተዋል አስፈላጊ ነው ፡፡

ማክአርቱር “ በይሁዳ የተገለፀዉ አስተምሮ እና የባህሪይ ትምህርት (ቁጥር 4-18) ከ 2ጴጥ (2፡ 1 – 3፡ 4) በመመሰል የቀረበ እንደሆነ “ ይፅፋል ፡፡ ምንም ነገር የጠቀሰ ባይሆንም ምናልባትም መፅኃፉ ከኢየሩሳሌም መዉደቅ በፊት (ከክርስቶስ ሞት 70 በፊት) እና ከ 2ጴጥሮስ በኋላ (ከክርስቶስ ሞት 68-70) በኋላ የተፃፈ ነበር ፡፡ በ 1ቆሮ (9፡ 5) የኢየሱስ ወንድሞች ሚስቶቻቸዉን በአገልግሎት ጉዞአቸዉ ጓደኞቻቸዉ አድርገዉ ይዘዋቸዉ እንደሄዱ ይናገራል ፤ በብዛት መፅኃፉ በኢየሩሳሌም ተፅፎ እንደ ነበር ይመስላል ፡፡

በመጀመሪያ ይሁዳ ኢየሱስን እንደ መሲህ አልተቀበለም (ዮሐ 7፡ 1-9) ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ በሌሎች ወንድሞቹ የተቀየረ ነበር (ሐዋ 1፡ 14) ፡፡ ማክአርቱር በሚያስደንቅ ሁኔታ “ የሮም ክሊመንት (ከክርስቶስ ሞት 90 በኋላ) እና የአሌክሳንዲሪያ ክሊመንት (ከክርስቶስ ሞት 200 በኋላ) ስለ ይሁዳ እርግጠኝነት እንደጠቀሱ /እንዳሳዩ “ አመለከተ ፡፡ በይሁዳ የህይወት ዘመን ጊዜ “ ክርስትና ከሮም በአደገኛ ፖለቲካ ጥቃት ስር እና ብዙ የሖነ የአስተምሮ ስህተትን ለመሰብሰብ የተትረፈረፈ ዘርን የዘሩት እንደ ከሀዲዎች እና ነፃነትን አስተማሪ ከሆኑት ከፍልስፍና/ከምርምር አደገኛ በሆነ መንፈሳዊ ስርገት ስር ነበር ፡፡ ይህ ከ25 አመታት በኋላ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ በመልዕክቱ ለሚገጥመዉ የምርምር/የፍልስፍና ቀዶሞ የዳበር ሊሆን ይችላል “ ፡፡ ይሁዳ በእነዚህ የሐሰት ትምህርቶች ላይ ቤተ ክርስቲያን አቋም እንድትወስድ ተጣራ ፤ የእሱ መፅኃፍ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ “ ከትክክለኛዉ የመፅኃፍ ቅዱስ እዉነት የሚያጣምምን ክህደት በኃይለኛዉ አትኩሮ የነበረ “ ብቸኛ ነው ፡፡

ትምህርት

ይሁዳ (1-10)፡ ይሁዳ ራሱን የእናቱ ልጅ የኢየሱስ አገልጋይ በማድረግ እና የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪ የነበረዉ የያዕቆብ ወንድም እንደሆነ በማቅረብ መልዕክቱን የተቀበሉት እንዲሆኑ ለመነ ፡፡ ራሱን ከሐዋሪያት ለዬ ፤ በእግዚአብሄር ለተጠሩ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ለደህንነት እግዚአብሄር በሚጠብቃቸዉ ላይ በማስቀመጥ ኃላፊነቱን ተናገረ (ቁጥር 1) ፡፡ ይሁዳ ምህረት፣ ሰላም እና ፍቅር እንዲበዛላቸዉ ተመኘ (ቁጥር 2) ፡፡ ስለ ተደራሲያኑ “ እንደ ተወደዱ ወዳጆች “ ብሎ ከሚደርሳቸዉ ዉጪ ስለ ተደራሲያኑ ምንም ማስረጃ አልተሰጠም ፤ ምሁራን ይሁዳ ከብሉይ ኪዳን ዘጠኝ ምሳሌዎችን ከተጠቀመ እነዚህ ወዳጆች የአይሁድ ክርስቲያኖች እንደ ነበሩ ያመለክታሉ ፡፡ አንባቢዎቹን “ ለእምነት “ እንዲታገሉ አበረታታቸዉ ፡፡ ማክአርቱር የይሁዳን ቃል “ በሁሉም አይነት በስህተት ላይ ጦርነትን እንደ ማወጅ እና ቅዱሱን ንብረት በመጠበቅ ኃላፊነት አየታመነ እንደ ሆነዉ ጠባቂ አንድ ወታደር ስለ እዉነት በኃይል መዋጋት “ በማለት ይተረጉመዋል ፡፡

በቁጥር 4 ዮሐንስ እነዚህን ሐሰተኛ አስተማሪዎችን እንደ ተደበቁ፣ እግዚአብሄር የማይመስሉ እንደ ሆኑ፣ የእግዚአብሄር ፀጋ ወደ ሴሰኝነት እንደ ቀየሩ እና ኢየሱስን እንደ ጌታ የካዱ እንደ ሆኑ ገልፆአቸዋል ፡፡ ማክአርቱር ከቁጥር (4-19) 18 የከሀዲን ባህሪያትን ይዘረዝራል፡ “ 1) ከሀዲ (ቁጥር 4)፣ 2) በስነ-ምግባር የተለወጠ (ቁጥር 4)፣ 3) ክርስቶስን የካደ (ቁጥር 4)፣ 4) ስጋን ያረከሰ (ቁጥር 8)፣ 5) አመፀኝነት (ቁጥር 8)፣ 6) ቅዱሳን መለዓክትን መንቀፍ (ቁጥር 8)፣ 7) ህልመኝነት (ቁጥር 10)፣ 8) አለማወቅ (ቁጥር 10)፣ 9) መበላሸት (ቁጥር 10)፣ 10) ማጉረምረም (ቁጥር 16)፣ 11) ችግር ፈላጊነት/ጠቃሽነት (ቁጥር 16)፣ 12) ለራስ አሳቢነት/ራስ ወዳድነት (ቁጥር 16)፣ 13) በኃይል ናገር (ቁጥር 16)፣ 14) ሸንጋይነት (ቁጥር 16)፣ 15) አሸአፊነት (ቁጥር 18)፣ 16) ለመከፋፈል ምክንያት መሆን (ቁጥር 19)፣ 17) አለማዊ አስተሳሰብ (ቁጥር 19) እና 18) ያለ መንፈስ መሆን ቁጥር (19) “ ፡፡ እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚናገሩ እና እንደሚመስሉ የምታስተዉሉ ሁኑ ፡፡

ይሁዳ ዘጸዓትን እግዚአብሄር ሕዝቡን ከግብፅ እንዳዳነ ለማሳየት ተጠቀመበት ነገር ግን አንዳንዶች ችላ በማለት አላመኑም (ቁጥር 5) ፡፡ በመቀጠልም ይሁዳ ያልተቀደሱ እና ብልሹ ስነ ምግባር ያላቸዉ በመሆን የወደቁትን መለዓክት ጠቀሰ (ቁጥር 6) እንዲሁም ደግሞ በሰዶሞ እና በገሞራ ከተሞች ያለዉን ብልሹ ስነ ምግባርንም ጠቀሰ (ቁጥር 7) ፡፡ በተመሳሳይ ሐሰተኛ አስተማሪዎች “ ስጋቸዉን በማርከስ፣ ስልጣንን በመናቅ እና ጌትነትን በመሳደብ “ በቤተ ክርስቲያን ላይ መጡ (ቁጥር 8) ፡፡

ከዚያም ይሁዳ በመለዓክት አለቃ በሚካኤል እና በዲያቢሎስ መካከል በሙሴ ስጋ ላይ የተደረገዉን ክርክር በማመልከት ሚካኤል “ እግዚአብሄር ይገስፅህ ! “ በማለት መለሰለት እንጂ በእርሱ ላይ የስድብ ፍርድን እልተጠቀመም አለ (ቁጥር 9) (ዘካ 3፡ 2, ራዕ 12፡ 7) ፡፡ ማክአርቱር “ እንደ ሰይጣን ኃይለኛ መለዓክትን በግል/በራስ ከመርገም ይልቅ ሚካኤል ለሁሉን ቻዩ እና ለኃያሉ እግዚአብሄር አስተላለፈ ….. ይህ ክርስቲያኖች እንዴት በሰይጣን እና በአጋንንት ላይ መነጋገር እንዳለባቸው የላቀ ማሳያ ነው ፤ አማኞች በእነርሱ ላይ የእግዚአብሄር ኃይል ጣልቃ ገብነት ይፈልጋሉ እንጂ እንደ ማይደርሷቸዉ/እንደ ማይፈርዱባቸው “ ያመለክታል ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ያልተረዱትን ማንኛዉንም ነገር በመስደብ በሂደቱ ራሳቸዉን እያጠፉ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡

ይሁዳ (11-19)፡ ይሁዳ በገዳዩ በቃየል መንገድ በመጓዝ ለትርፍ በበለዓም ስህተት ላይ የተጣበቁ እና በቆሬ ሰዎች አመፅ በማፁት በሐሰተኛ አስተማሪዎች ላይ ኃዘንን ተናገረ (ቁጥር 11) ፡፡ የእነዚህ ከሀዲዎች የተለመደ ባህሪይ በጌታ የቱ ትክክል ወይም በጎ ብሎ ከማሰብ ይልቅ የራሳቸዉን አጀንዳ መከተላቸዉ ነው ፡፡ ዮሐንስ ራሳቸዉን ብቻ ለመመገብ በአማኞች የበሉ ድግስ እና ቁርባን የሚወድዱ አደገኛ እድፍዎች በማለት ገልፆቸዋል ፡፡ ዝናብ የለለዉ ደመና እና መከር ካለፈ በኋላ እንዳለ ደረቅ ዛፍ ነበሩ - ዋጋ የሌላቸዉ እና የማያፈሩ (ቁጥር 12) ፡፡ በተጨማሪም የክፉ ተግባራቸዉን እፍረታቸዉን አረፋ የሚያስወጣ ማዕበሎች እና ለጨለማ ብርኃን ያላመጣ የሚንከራተት ከዋክብቶች ነበሩ (ቁጥር 13) ፡፡

ይሁዳ የእግዚአብሄር ሰዉ ሄኖክ በእነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ላይ (ዘፍ 5፡ 1-24) እግዚአብሄርን በማያከብር ድርጊታቸዉ ላይ ፍርድን ሊያደርግ ከቅዱሳን ሰራዊት ጋር በእነርሱ ላይ ይመጣል በማለት ትንቢትን እንደ ተናገረ ገለፀ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ፍርዱ ሁለተኛ መምጣቱን ያመለክታል/ይጠቅሳል ፡፡ ይሁዳም በተጨማሪም ለራሳቸዉ ፍላጎት የሚጨነቁ፣ የሚፈልጉትን ለማግኘት ሰዎችን የሚሸነግሉ የማይታገሉ አጉረምራሚዎች እንደሆኑ ገለፃቸው (ቁጥር 16) ፡፡ ይሁዳ አንባቢዎቹን ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ለመዋጋት/ለመታገል እንዲረዳቸዉ ስለ መጨረሻዉ ዘመን የሐዋሪያትን ትምህርቶች እንዲያስታዉሱ አሳሰባቸው (ቁጥር 17-18) ፡፡ በዉስጣቸዉ መንፈስ ቅዱስ ስለሌላቸው እነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ መከፋፈልን ፈጥረዋል (ቁጥር 19) ፡፡

ይሁዳ (20-25)፡ ይሁዳ እነዚህን ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለመታገል የተወሰኑ ትዕዛዞችን ሰጥቷል፡ ራሳችሁን በእምነት ማጎልበት፣ በመንፈስ ቅዱስ መፀለይ (ኤፌ 6፡ 18)፣ በእግዚአብሄር ፍቅር በመጣበቀ፣ ተስፋ የተገባዉን የዘላለም ህይወትን ወደፊት በመመልከት፣ ለሚጠራጠሩት ምህረትን ማሳየት፣ ሌሎችን ከሀሰት ትምህርቶች ማዳን እና በክፉ ስራ የረከሰን ልብስ (የሐሰተኛ አስተማሪዎች ኑሮን) መጥላት (ቁጥር 20-23) ፡፡ ይሁዳ አንባቢዎቹን በጌታ በመባረክ ጨረሰ ፡፡

መደምደሚያ

በሐሰተኛ አስተማሪዎች እና ከሀዲዎች ላይ ስለ እግዚአብሄር ቃል የምንታገል እንድንሆን በጌት በኢየሱስ ክርስቶስ በመፅናት በእምነታችን የምንተጋ መሆን አለብን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1978.

  2. MacArthur, p. 1979.

  3. MacArthur, p. 1978.

  4. MacArthur, p. 1978.

  5. MacArthur, p. 1978.

  6. MacArthur, p. 1979.

  7. MacArthur, p. 1979.

  8. MacArthur, p. 1980.

  9. MacArthur, p. 1982.

  10. MacArthur, p. 1982.

ጥያቄዎች

  1. በይሁ (1፡ 3) እግዚአብሄር ስለ ሰጠን እምነት “ መከላከል “ ወይም “ መታገል “ ምን ማለት ነው ? እምነታችሁን ስትከላከሉ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ ? በምን መንገድ ?
  2. ይሁ (1፡ 6) በምድር ላይ ለመኖር (ዘፍ 6፡ 4) እና አሁን ስለ ታሰሩት (2ጴጥ 2፡ 4) “ ስልጣናቸዉን ያልጠበቁትን ነገር ግን ትክክለኛ ስፍራቸዉን ስለለቀቁት “ መለዓክት ይናገራል ፤ በግል አስተያየታችሁ ለዕስራታቸዉ ምክንያት ምን ስለተፈጠረነው ?
  3. እንደ አንድ አማኝ ይሁዳ (1፡ 20) እንዴት ትኖሩበታላችሁ ? ሌሎችን እንዴት ትሰሩበታላችሁ ? እንዴት “ በመንፈስ ቅዱስ ትፀልያላችሁ “ ?
  4. በይሁዳ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jude 1:3

“Dear friends, although I was eager to write you about the salvation we share, I found it necessary to write and exhort you to contend for the faith that was delivered to the saints once for all.”

የኢየሱስ ወንድም የሆነ ይሁዳ ለተጠሩት ፣ ለተወደዱትና በኢየሱስ ለተጠበቁት መልዕክቱን ጻፈ ፡፡ እስኪ ይህን በደንብ አስቡት ፡፡ ተጠርታችኋል፣ ተወዳችኋል በአዳኛችሁም ተጠብቃችኋል ፡፡ ይሁዳ መጀመሪያ መሰረታዊ ስለሆኑት ልክ እንደ ድነት ስላሉ እርዕሶች ሊያወራ ፈልጎ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር የተጠሩትን ለኃይማኖታቸው እንድጋደሉ መምከርን አስፈላጊ ሆኖ አገኘው ይህም ፡- እንድበረቱ ፣ እንድታገሉና ኃይማኖታቸውን እንድጠብቁ ነው ፡፡ እርሱም ወንድሞቹንና እህቶቹን ራሳቸውን በእምነት እንድያሳድጉና በመንፈስ ቅዱስ እንድጸልዩ አበረታታቸው ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረትን ጠይቁ ለሌሎችም ምህረትን አድርጉ ፡፡ ክፉ የሆነውን ጥሉ መልካም የሆነውንም አጥብቃችሁ ያዙ ፡፡ በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ተመላለሱ ፡፡

ጓደኞቼ ክፉ በዓለም አለ በዙሪያችሁም ተግዳሮቶች አሉ ፡፡ እውነት በቀላሉ የሚጠፋ ይመስላል ፡፡ የዚህ ዓለም ኃይላት በእናንተ ላይ ጦርነት ያስነሳሉ ፤ ኢየሱስን ከማመንና ከመከተልም ሊከለክሉዋችሁ ይፈልጋሉ ፡፡ ስለዚህም ተዘጋጁ ፤ የቦክስ መጨዋቻ ጓንታችሁን አድርጉ እናም ኋይማኖታችሁን ለመጠበቅ ተጋደሉ ፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ኑሩ በእርሱም እደጉ ፡፡ በየማለዳም አዲስ የሆነውን ምህረቱን ተቀበሉ ፡፡ ለሌሎችም ምህረትን እያደረጋችሁ፣ ውደዱ ፡፡ እናንተ ለኋይማኖታችሁ ተጋዳዮች ናችሁ ፡፡ በጌታ በርቱ፣ በትህትናም ተመላለሱ ፡፡ አሸናፊነት በጌታ ዘንድ ነው!

“ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”

  • ይሁዳ 1፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

ፊልጵስዩስ 2:5–8 — “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።”

ይሁዳ 1:1 — “የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ ፡፡“

ይሁዳ 1:20–23 — “እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።”