General Letters 3 John

Those Who Walked In Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Example 3 John 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 685 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ 3 ዮሐንስ ስንጓዝ ያ ማለትም በአንድ ላይ የሚሰሩ በእንጨት ላይ እንደተሳለ ሰዎስት ስዕል ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎስት ስዕሎች ይኖሩናል ማለት ነው ፡፡ በመጀመሪያዉ ስዕል ቀዩ ቱሊፕ የክርስቶስን ደም እና ለእኛ ያለዉን ፍቅር ይወክላል ፡፡ በሁለተኛዉ ስዕል ዉስጥ መፅኃፍ ቅዱስ በክርስቶስ ዉስጥ ያለዉን እዉነት ይወክላል ፤ ሰዎስተኛዉ ስዕል የክርስቶስን ፍፁም ምሳሌ እና በእምነታችን እንዴት እንደምንኖር ያመለክታል ፡፡ ስዕሉ ክርስቶስ እንዳደረገው በእምነት መመላለስን ለመወከል ሰዎስት ጥንድ እግሮችን ያሳያል ፤ በ 3 ዮሐንስ ብዙ ሰዎች በጌታ እንዴት እንደተመላለሱ እንደ ምሳሌ ተጠቅሞባቸዋል፡ ስለ ጋይዮስ እና ድሜጥሮስ ፡፡ በ 2ዮሐ (2፡ 6) ዮሐንስ “ በእርሱ እኖራለሁ የሚል ካለ እርሱ እንደተመላለሰ ሊመላለስ እንደሚገባው “ ተናገረ ፡፡ በስዕሉ ላይ አበባው የአማኞችን አንድነት እና ሕብረት ይወክላል ፡፡

የ 3ዮሐንስ መፅኃፍ በዮሐንስ ሕይወት ቆይታ ዉስጥ የተፃፈ ሌላ አጭር መልዕክት ነው፡፡ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ በመፅኃፍ ቅዱስ ዉስጥ አምስት መፅኃፍትን ፅፏል፡ የዮሐንስ ወንጌልን፣ 1፣ 2 እና 3 ዮሐንስን እና ራዕይን ፡፡ የዮሐንስ መልዕክት ሂደት እንዴት እንደ ሆነ ተመልከቱ፡

  • 1ዮሐንስ በእስያ ግዛት ዉስጥ ለተበተነዉ የጉባኤ ቡድን የተፃፈ ነበር ፡፡
  • 2ዮሐንስ ጉባኤ ሊሆን በሚችል እና አባላቱ ሴቲቱ እና ልጇ ሊሆን ለሚችል ለተመረጠች ሴት እና ለልጇ ተፃፈ ፡፡
  • 3ዮሐንስ በተለዬ ለተወደደ ወዳጁ ለጋይዮስ ተፃፈ ፡፡

በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ጊዜ የተለመዱ 18 ስሞች ነበሩ ከእነዚያ ዉስጥም አንዱ ጋይዮስ ነበር ፡፡ ስሙም “ መደሰት “ ማለት ነው ፡፡ ዮሐንስ ተሳትፎበት ከነበረዉ ቤተ ክርስቲያን አባል ከመሆኑ በስተቀር ስለ ጋይዮስ ብዙ አይታወቅም ፡፡ ሐዋ (19፡ 29) ከጳዉሎስ የጉዞ ጓደኞች ዉስጥ ጋይዮስ የሚባለዉን ይጠቅሳል ነገር ግን ዮሐንስ በዚህ መፅኃፍ ዉስጥ የደረሰዉ ጋይስ አልነበረም ፡፡ ሐዋ (20፡ 4) ከደርቤኑ የሆነዉን ጋይዮስን ይጠቅሳል ፤ ማክአርቱር ጋይዮስን “ ለሚዘዋወር አገልግሎት ትክክለኛዉን የክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነትን መስፈርት የሚያስፋፋ “ “ የሐዋሪያዉ የተወደደ ወዳጅ እና ለእዉነት የታመነ ደጋፉ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡

ዮሐንስ ዋጋ ያላቸዉን የጋይዮስን ድርጊቶች ሐሰተኛ አስተማሪ ከሆነዉ ከከድሜጥሮስ ድርጊቶች ጋር አወዳደረ ((ቁጥር 6-10) ፡፡ እንደ ገና ዮሐንስ በዚህ ጊዜ በጋይዮስ ምሳሌ የእንግዳ ተቀባይነትን መስፈርት ደረሰ/ተናገረ ፡፡

ትምህርት

3-ዮሐንስ (1-2)፡ ዮሐንስ እንደ ገና “ በእዉነት “ ለሚወድደው ለዉድ ወዳጁ ለጋይዮስ በሰላምታዉ “ ሽማግሌ “ የሚለዉን ቃል ተጠቀመ (ቁጥር 1) ፡፡ ጋይዮስ በኢየሱስ የሚያስደንቅ ምልልስ እንዳለዉ የሚታወቅ ነበር ፡፡ ዮሐንስ የጋይዮስ አካላዊ ጤንነት ልክ እንደ መንፈሳዊ ጤንነቱ እንዲሆን ፀለየ (ቁጥር 2) (1ጢሞ 4፡ 6-7) ፤ ይህ ትዕዛዝ በመንፈሳዊ ነገር የሰለጠነ/የተለማመደ እንደ ነበረው በአካላዊም ነገር እንዲሰለጥን/እንዲለማመድ ለጋይዮስ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ጋይዮስን “ በሁሉም ነገር እንዲበለፅግ “ አበረታታው ፡፡

እዉነት ለመናገር በግሌ በዚህ እፈተናለሁ ፡፡ ጊዜዬን በምሽት እና በማለዳ በግልፅ ለማጥናት የምጠቀምበት ነው ፤ በህይወቴ በዚህ ወቅት ለስራ ለመሄድ ጊዜ የለኝም፤ ነገር ግን በምሰራ ጊዜ ጥሩ ነገር ይሰማኛል የተሻለ ምስክር መሆን እችላለሁ ፡፡ በዮሐንስ ንግግር ዉስጥ በህይወት ዉስጥ መመጣጠንን የመጠበቅ እዉነት አለ ፤ አካላዊ ጤንነት ምስክርነታችንን እና ምስክር የመሆን ችሎታችንን ተፅዕኖ ያደርጋል ፡፡

በተጨማሪም ሁልጊዜም በመፅኃፍት የመንሰራ መሆን ያስፈልገናል ፤ 2ቆሮ (4፡ 16) “ ስለዚህም አንታክትም ነገር ግን የዉጭም ሰዉነታችን ቢጠፋ እንኳ የዉስጡ ሰዉነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል “ ፡፡ በጌታ የማደግ ክፍል በእርሱ እረፍትን መማር ነው ፡፡ ለእናንተ የእኔ ጥያቄ/ሙግት ህይወታችሁ ላይ በመመልከት በህይወታችሁ ዉስጥ ከመጠን ያለፈዉ/ከባላስ የወጣዉን እንድታዩ ነው - መንፈሳዊዉ ወይስ አካላዊዉ - ህይወታችሁን ወደ መመጣጠን/ባላንስ ወደ መመለስ ላይ አትኩሩ ፡፡

3-ዮሐንስ (3-8)፡ ዮሐንስ ሰዎች ለእዉነት ስለ ጋይዮስ ታማኝነት ለእርሱ ስለመሰከሩለት ደስታዉን አመለከተ (ቁጥር 3-4) ፤ ዮሐንስ እንደ ገና ጋይዮስን እንደ ዉድ ወዳጁ በመናገር በክርስቶስ ለወንድሞቹ እና ለእንግዶች በድርጊቱ የጋይዮስን መታመን አስታወቀ (ቁጥር 5) ፡፡ ጋይዮስ ቤቱን ተጓዝ ለነበሩ ሰባኪዎች የእግዚአብሄር ለሆኑ ሰዎች ለእንግዶች ከፍቷል - ለክርስቶስ እና ለቤተ ክርስቲያን ያለዉን የጋይዮስንም ፍቅር መስክረዉ ነበር (ቁጥር 6)፡፡ ማክአርቱር “ ለእግዚአብሄር እንደሚገባ “ የሚለዉ ሐረግ “ እግዚአብሄር እንደሚቀበላቸው ሰዎችን የመቀበልን ሐሰብ የያዘ (ማቴ 10፡ 40) እና እንግዳ ተቀባይነት የሚደረግበት ቁልፍ ነገር መሆን እንዳለበት (ማቴ 25፡ 40-45) “ በማለት ያመለክታል ፡፡

በቁጥር 7 ዮሐንስ የጋይዮስ ድርጊት ለሐሰተኛ አስተማሪዎች እንዳልነበር ነገር ግን “ ከጣዖት ምንም ነገር ባለመቀበል ራሳቸዉን ስለ ስሙ በመለየት “ የክርስቶስን እዉነት እያስተማሩ ተጉዘዉ ለነበሩት እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ዮሐንስ እነዚህን እንግዶች እንደ “ እዉነት አብሮ ሰራተኞች “ የደገፈበትን የጋይዮስን ድርጊት አከበረ (ቁጥር 8) ፡፡

3-ዮሐንስ (9-11)፡ ዮሐንስ በጌታ የጋይዮስን ምልልስ ከማክበር የዲዮጥራጢስ ድርጊት ወደ መኮነን/ማወገዝ ሄደ ፡፡ ዮሐንስ ምናልባትም ከጉባኤዉ ጋር ይጋራ ላልነበረው ለቤተ ክርስቲያን መሪዉ ለዲዮጥራጢስ ቀደም ብሎ የፃፈውን የጠፋዉን መልዕክት ያመለክታል ፡፡ ዲዮጥራጢዮስን ትዕቢተኛ እንደሆነ፣ ሁሉንም የሚበልጥ መሪ መሆን የሚፈልግ እንደ ሆነ እና በአገልግሎት ዮሐንስ የላካቸዉን ለመቀበል እምቢ ያለ እንደ ነበር ገልፆታል (ቁጥር 9) ፡፡ ዮሐንስ ዲዮጥራጢስ እርሱን አምቶት እንደ ነበር፣ በክርስቶስ ወንድሞች የሖኑትን እንደማይቀበል፣ ሌሎች እንግዳ ተቀባይነትን እንዳያደርጉ እንዳስቆመና እነዚህን ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን እንዳባረራቸዉ ጨመረ (ቁጥር 10) ፡፡ በቁጥር 11 ዮሐንስጋይዮስን እና ዲዮጥራጢስን ወደ መልካም እና ክፉ በማለት ከፋፈላቸው - ጋይዮስ ከእግዚአብሄር የመጣዉን መልካምን እንዳደረገ እና ዲዮጥራጢስ እግዚአብሄርን በፍፁም እንዳላየዉ ያሳይ የነበረዉን ክፉን እንዳደረገ ፡፡

3-ዮሐንስ (12-14)፡ በመቀጠልም ዮሐንስ እርሱን ከሚያዉቁት እና የክርስቶስን እዉነት ካልያዙት መልካም ምስክርነትን በተቀበለዉ በድሜጥሮስ ላይ ሌላ መልካም ምሳሌን አቀረበ ፤ ዮሐንስም በግሉ ስለ ድሜጥሮስ እምነት መሰከረ (ቁጥር 12) ፡፡ ዮሐንስ ማጠቃላያዉንበፅሁፍ መፃፍ/ማስቀመጥ የማይፈልገዉ የሚነግራቸዉ ብዙ ነገር እንደ ነበረዉ በመናገር ጀመረ (ቁጥር 13) ፤ ከዚያም ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር በቅርብ እንደሚሆን ተስፋ እንደሚያደርግ እና በአካል ፊት ለፊት ማዉራት እንደሚችሉ ተናገረ ፡፡ ዮሐንስ ይህን ጉባኤ ስለሚወደዉ በክርስቶስ ሰላምን ተመኘላቸው ፡፡ ዮሐንስ ከጓደኞቹ ሰላምታን በመስጠት አጠቃለለ ፡፡

መደምደሚያ

ሁለቱ የመፅኃፍ ቅዱስ መፅኃፍት (1 እና 2 ዮሐንስ) በክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነት ላይ ስለሚናገሩ ይህ እስካሁን ያስደንቀኛል ፡፡ ሁለቱም መፅኃፍት ያ(እንግዳ ተቀባይነቱ) እንዴት እንደሚሰራ መስፈርትን ይሰጣሉ ፡፡ በጣም አስፈላጊዉ/ጠቃሚው ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለሆኑት ሳይሆን በጌታ እዉነት ለሚመጡት በራችሁን መክፈት ነው ፡፡

አንዳንዶቻችሁ ቤታችን ልታነፁ ያስፈልጋችኋል - በአካል ወይም በመንፈሳዊ ወይም በግል ነገር - ያ ከሆነ ወንጌልን ለሚሰብኩት/ለያዙት በእንግዳ ተቀባይነት በእግዚአብሄር ጥቅም ላይ የምትዉሉ መሆን ትችላላችሁ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1974.

  2. MacArthur, p. 1974-1975.

  3. MacArthur, p. 1976.

ጥያቄዎች

  1. በ 3ዮሐንስ 2 የመበልፀግ/የመከናወን ሐሳብ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል ፤ ካለ በሁለቱ መጠቀስ መካከል ያለዉ ልዩነት ምን ሊሆን ይችላል ? ለማበልፀግ ለእናንተ ነፍስ ይህ ምን ማለት ነው ?
  2. ለሚጓዙ ፓስተሮች/አስተማሪዎች በምትሰጡ ጊዜ ራሳችሁን ለእግዚአብሄር እንደ ታማኝ ታስቡታላችሁ ? በ 3ዮሐ (5-8) መሰረት ለእነርሱ በሰጣችኋቸዉ ጊዜ በሚገባ ማድረግ ያለባችሁን እንዳደረጋችሁ እና ከእነርሱም ጋር አጋር ትሆናላችሁ ፡፡
  3. 3 ዮሐንስ (9-10) ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች የማይታዘዝን ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ አንዳንድ ቁጥጥር ያለዉ ስለሚመስል አንድ ሰዉ ይገልፃል ፤ በአሁኗ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ይህን አይታችሁታል ? ይህ በሚመስሉ ሰዎች ላይ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ምን ታስባላችሁ ? ይህን ቤተ ክርስቲያን ለመጎብኘት በመጣ ጊዜ ዮሐንስ ምን እንደሚያደርግ ተናገረ ?
  4. በ 3ዮሐንስ 11 መሰረት መልካም የሆነዉን እንጂ ክፉ የሆነውን አንመስልም ፤ ምን ሌላ መፅኃፍ ይህን ይደግፋል ? (1ቆሮ 4፡ 16, 11፡ 1, 2ተሰ 3፡ 9, ዕብ 6፡ 12, 13፡ 7, 1ዮሐ 2፡ 6)
  5. በ 3ዮሐንስ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 3 John 1:3–4

“For I was very glad when some brothers came and testified to your faithfulness to the truth—how you are walking in the truth. I have no greater joy than this:to hear that my children are walking in the truth.”

ዮሐንስ ልጆቹ ፣ የዳኑት ወይም አማኞች በእርሱ አገልግሎት የተገለገሉት በእውነት እየተመላለሱ እንደሆነ ከመስማት የበለጠ ደስታ የለውም ነበር ፡፡ በአገልግሎት ላይ ላሉ አገልጋዮች ስለሚያደርጉት እንክብካቤና ድጋፍ ምስክርነት በመስማቱ የዮሐንስ ልብ ደስ ተሰኘ ፡፡ ዮሐንስ ልጆቹን ክፉውን ሳይሆን በጎ የሆነውን እንድመስሉ አዘዛቸው ፡፡

ልጆቻችሁ ኢየሱስን በፍጹም ልባቸው፣ ነፍሳቸውና አሳባቸው እንድከተሉ ማስገደድ እንደማትችሉት ሁሉ ፣ ደቀ መዝሙርነት የምታስተምሯቸውንም ሰዎች ከኢየሱስ ጋር በእምነት እንድጓዙ ማስገደድ አትችሉም ፡፡ ነገር ግን እናንተ የሆነ አካል ልጆች ናችሁ ፡፡ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ፡፡ እንዴት ይሆን ሰዎች ታማኝነታችሁን የሚመሰክሩት ? ክርስቶስን ትመስላላችሁ ? ወይስ ክፉ የሆነውን ነው የምትመስሉት ? እንክብካቤን ታደርጋላችሁን ? በእግዚአብሔር ጸጋ ነው የምትመላለሱት ወይስ ነገሮችን አንድ አድርጎ ለማቆየት በራሳችሁ ኋይል ትታገላላችሁ ? ጓደኞቼ ዛሬ ለእናንተ የሆነውን የክርስቶስን ፍጹም ፍቅር ተቀበሉ ፡፡ እርሱ እንዲሁ እንዳላችሁ ይወዳችኋል ፡፡ የእርሱን ፍቅር በመቀበል ፣ አይኖቻችሁን በእርሱ ላይ በማድረግ እርሱን እንደ ጓደኛችሁ፣ አዳኛችሁና እንደ ሰማዩ አባታችሁ አድርጋችሁ በማወቅ እደጉ ፡፡ የእርሱን ፍቅር ወደ ሌሎች አጋቡ ፡፡ ክርስቶስ ቢሆን ይህን ሰው እንዴት ነበር የሚወደው ፣ ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ ፡፡ ከዚያም ፍጹሙን ምሳሌ ኢየሱስን በመከተል፣ እውነት እንደሆነ የምታውቁትን ታማኝነት ተከተሉ ፡፡

“ወንድሞች መጥተው አንተ በእውነት እንደምትሄድ ስለ እውነትህ ሲመሰክሩ እጅግ ደስ ብሎኛልና።ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።”

  • 3ኛ ዮሐንስ 1፡3-4

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤፌሶን 5:2 — “ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።”

3ኛ ዮሐንስ 1:5–6 — “ወዳጅ ሆይ፥ ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፥ እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ”

3ኛ ዮሐንስ 1:11 — “ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።”