Walking In Truth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Truth 2 John 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አጠቃላይ መልዕክት የሆነዉን መልዕክት እያጠናን ነው ፤ እስካሁን ዕብራዉያንን፣ ያዕቆብን፣ 1 እና 2 ጴጥሮስ እና 1ዮሐንስን ፡፡ ዛሬ 2ዮሐንስን እንመለከታለን ፡፡ በ 2ዮሐንስ ኢየሱስን የምናይበት ቃላችን እዉነት የሚል ነው ፤ ይህም ከ 2ዮሐ (1፡ 4) ይመጣል “ ከልጆችሽ በእዉነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል “ ፡፡ የሜንዲ ስዕል ለ 2ዮሐንስ መጽኃፍ ቅዱስ አለው ፤ ሜንዲ መፅኃፍ ቅዱስን ስትስል ይህ የመጀመሪያ እና ኢየሱስ በቃሉ የፈፀመዉን እዉነት ይወክላል ፡፡ የ 2ዮሐንስን የመጀመሪያዎቹን ሰዎስት ጥቅሶች ስታነቡ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የዋለው የቃሉን እዉነት ታያላችሁ ፡፡ ክርስቶስ እዉነት ነው ፡፡ ሁለተኛ ዮሐንስ ከሰዎስቱ መልዕክት ሁለተኛዉ ነው ፡፡
ማክአርቱር 2 እና 3 ዮሐንስ “ ከግለሰብ ወደ ግለሰቦች ደርሶ የነበረ በግሪክ-ሮም ዘመናዊዉ አለም መልዕክት ቅርፅ እና በአዲስ ኪዳን ካለዉ መልዕክት ጋር በመቀራረብ እንደቀረበ “ ይናገራል ፡፡ እነዚህ ከ300 የግሪክ ቃላት በታች የያዙ አጭር የአዲስ ኪዳን መልዕክቶች ናቸው ፤ ሁለተኛ ዮሐንስ በጣም አጭር ስለሆነ ከአንድ ገፅ መፃፊያ ወረቀት ጋር የሚመጣጠን/የሚሞላ ነው ፡፡ ልክ እንደ 1ዮሐንስ 2 እና 3 ዮሐንስም በሐዋሪያዉ ዮሐንስ የተፃፉ ነበሩ ፡፡ በ 2ዮሐንስ 1 ዮሐንስ ራሱን እንደ “ ሽማግሌ “ ለይቷል ፤ እዚህ ስፍራ ላይ ዮሐንስ እድሜዉ ማገባደጃ ላይ ነበር ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት ሐዋሪያትም በሕይወት ያለ የመጨረሻው ሐዋሪያ ነበር ፡፡ ይህንን መልዕክት የፃፈበት ቀን አይታወቅም ነገር ግን ምናልባት ከኤፌሶን በኋለኛዉ አመታት ከክርስቶስ ሞት (90-95) በኋላ ሳይፃፍ አይቀርም ፡፡
ሁለተኛ ዮሐንስ ልክ እንደ አንደኛ ዮሐንስ ተመሳሳይ ችግርን ደርሷል - በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የሐሰተኛ አስተማሪዎች መነሳትን (1ዮሐ 2፡ 18-19, 22, 23) ፤ በ 2ዮሐንስ ዮሐንስ እዉነት ከሆነዉ ከኢየሱስ ከዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አባላትን እየጎተቱ/ዞር እያደረጉ የነበሩትን ተለዋዋጭ አስተማሪዎችን ይደርሳል ፡፡ ሐሰተኛ አስተማረዎች ወደ አባላት ቤት ለመግባት የክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነትን በመጠቀም ከዚያም ከኢየሱስ አርቀዉ እየመሩ ነበር፡፡ ይህ በ 3ዮሐንስም ተመሳሳይ ሁኔታ ነበር ፡፡
ማክአርቱር 2ዮሐንስ “ ከ 1ዮሐንስ ስለ እምነት መሰረታዊነት ወይም ወደ ክርስትና መሰረታዊነት ደግሞ ከሚናገረው ጭብጥ ጋር ይመሳሰላል (ቁጥር 4-6) ፤ ለዮሐንስ የክርስትና መሰረቶች ከእዉነት (ቁጥር 4)፣ ከፍቅር (ቁጥር 5) እና ከመታዘዝ (ቁጥር 6) ጋር በማጣበቅ/በማገናኘት የተጠቃለሉ ናቸው “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች የክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነትን ለመስጠት መመሪያን/ምሪትን ይሰጣሉ (ሮሜ 12፡ 13) ፡፡ ክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነት በቤታችሁ በማገልገል በእምነት መጓዝ/መመላለስ ነው ፤ ይሁን እንጂ ዮሐንስ ክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነት እንዴት መቅረብ እንዳለበት ማስጠንቀቂያን ተናግሯል ፡፡
ትምህርት
2-ዮሐንስ (1-3)፡ ዮሐንስ ይህንን መልዕክት “ ለተመረጡ ሴቶች እና ልጆቻቸው “ ደርሷል ፡፡ መፅኃፍ ቅዱሳዊ ምሁራን ይህ የመልዕክቱ ተደራሽነት ቅርፅ እነማን እንዳካተተ እርግጠኞች አይደሉም ነገር ግን ብዙዎች በቀጥታ - ዮሐንስ የተወሰኑ ሴቶችን እና ልጆቻቸዉን እንደደረሳቸው ይተርጉሙታል ፡፡ ዮሐንስ ራሱን በማስተዳደር/በማዘዝ ሚና በማቋቋም እዉነትን ከሚያዉቁት ሁሉ ጋር አቋሙን አካተተ ፡፡ በቁጥር 2 ዮሐንስ ኢየሱስ የዘላለም እዉነት እንደ ሆነ አመለከተ ፤ በቁጥር 3 ዮሐንስ ለቤተሰብ የግል ሰላምታን ሰጠ ፡፡ ከአገልግሎቱ በአንዳንድ ደረጃዎች ላይ ያውቃቸዋል ፡፡
2-ዮሐንስ (4-6)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (4-6) በእዉነት መመላለስ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፤ እነዚህ ቁጥሮች በተፈጥሮ ተግባራዊ እና እንዴት በእዉነት መመላለስ እንደተፈፀመ የሚገልፁ ናቸው ፡፡ “ አንዳንድ “ ልጆቿ በእዉነት እየተመላለሱ ከነበር የሚለዉ አዉዱ/ንግግሩ ምናልባትም አንዳንድ ልጆቿ በእዉነት የሚመላለሱ አልነበሩም ማለት ነው (ቁጥር 4) ፡፡ ዮሐንስ ሴቲቱን መጀመሪያዉኑ ኢየሱስ ነግሯቸዉ እንደ ነበር በፍቅር በእዉነት እንድትመላለስ አሳሰባት (ቁጥር 5) ፡፡ ይህንን ደግሞ ለመፃፍ ለዮሐንስ የደረሰዉ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተስብ ዉስጥ ነበር (ቁጥር 6) ፡፡
2-ዮሐንስ (7-11)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (7-11) በክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነት መዋቅር ዉስጥ በእዉነት ለመጣበቅ እንደ ትዕዛዝ ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታ ያልተቀበሉትን አታላዮችን ድርጊታቸዉን “ ከአሳቾች “ (ከሰይጣን) እና “ ከክርስቶስ ተቃዋሚዎች “ ጋር በማጣመር ገልጾቸአዋል (ቁጥር 7) ፡፡ ማር (13፡ 22-23) እነዚህን ሐሰተኛ አስተማሪዎች/አሳቾች ይገልፃል ፤ ማርቆስ አማኞችን ለመግለፅ “ የተመረጡት “ የሚለዉን ቃል ተጠቅሟል (1ጢሞ 4፡ 1-4, 1ጴጥ 2፡ 1, 1ዮሐ 4፡ 1) ፡፡ ከእነዚህ አሳቾች የተነሳ ዮሐንስ አድማጮቹን ሐሰተኛ አስተማሪዎች ወደ ቤታቸዉ ስለሚመጡ እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 8) ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ ቁጥር 7 “ በዚህ መልዕክት ዉስጥ የዮሐንስ ሀሳብ ጭብጥ/ፍሬ ነገር ነው…. አማኞች ከእዉነት ጋር የጠበቀ ጓደኝነት በማድረግ በስህተት ላይ ጠንቃቆች መሆን አለባቸው “ ፡፡ ከዚያም ዮሐንስ በክርስቶስ ትምህርት ያልሆኑ ነገር ግን የሐሰት ትምህርቶችን የተቀበሉ እግዚአብሄር እንደሌላቸው አመለከተ (ቁጥር 9) ፡፡ “ አልፎ መሄድ “ ማለት እግዚአብሄር ያላካተታቸዉን ነገሮች በእግዚአብሄር ቃል ላይ መጨመር ማለት ነው ፤ በእግዚአብሄር ትምህርቶች ላይ በምንጣበቅ ጊዜ በእዉነቱ ላይ እንመላለሳለን ፡፡ ዮሐንስ ሴቲቱን ከእግዚአብሄር እዉነት በተቃራኒ የሚያስተምርን ማንኛዉንም ወደ ቤቷ “ እንዳትቀበል “ አዘዛት (ቁጥር 10) ፡፡
ማክአርቱር “ እነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች የክርስትናን መሰረታዊ እና መሰረት የሆኑትን እዉነቶች ለማጥፋት የማያቋርጥ ዘመቻ እያደረጉ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሰይጣን የሚያደርገዉ ያን አይደለም ? በቁጥር 11 ዮሐንስ ለእነዚህ ሰዎች ወደ ቤት እንዲገቡ/እንዲመጡ መፍቀድ አዘጋጁ የሐሰተኛ አስተማሪዎቹ ክፉ ስራ ተካፋይ እንደሆነ ተናገረ ፤ ማክአርቱር “ እንዲህ አይነት ዉግዘት ሙሉ መፈታት ለጠንካራ/ለጎበዝ አማኞች ብቻ ተገቢ የተግባር ትምህርት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ይህ የእንግዳ ተቀባይነት ስጦታ ላላቸዉ ሰዎች አስቸጋሪ ነው ፡፡
ሐሰተኛ አስተማሪዎች ወደ ቤታችን እንዲገቡ የማንፈቅድባቸዉ ሰዎስት ምክንያቶች ፤ ሐሰተኛ አስተማሪን በመጋበዝ፡
- የሐሰት ትምህርቶቹ እዉነት እንዳላቸው ለጎረቤቶቻችን መነሳሳትን እንሰጣለን ፡፡
በሐሰት ትምህርቶቹ የተበከልን ልንሆን እንችላለን ፡፡
እዉነት ያልተጠበቀ እዲሆን ልናደርግ እንችላለን ፡፡
2-ዮሐንስ (12-13)፡ ዮሐንስ መልዕክቱን መፃፍ ከቻለው በበለጠ የሚያጋራቸዉ/የሚነግራቸዉ ብዙ ነገር እንደ ነበረዉ እና በአጋል ማድረግ እንደሚፈልግ በመናገር አጠቃለለ ፤ በመቀጠልም ዮሐንስ ከሴቲቱ እህት ወይም ከሌላ ጉባኤ ብዙ ሰላምታዎችን ሰጠ ፡፡
መደምደሚያ
የዮሐንስ የሁለተኛዉ መልዕክት ማስጠንቀቂያ ነበር - መልካም ለመሆን በመሞከር እና የክርስቲያናዊ እንግዳ ተቀባይነትን በመስጠት በአማኞች ኑሮ ዉስጥ ሰርገዉ የሚገቡትን ሐሰተኛ አስተማሪዎች የነበሩትን ሰዎች እንዳይፈቅዱላቸው ፡፡ ቀድመዉ የእግዚአብሄርን እዉነት ሰምተዉ ስለነበር አሁን በነገሩ ላይ እየሰሩ ነበር ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1971.
MacArthur, p. 1971.
MacArthur, p. 1971.
MacArthur, p. 1971-1972.
MacArthur, p. 1972.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 2 John (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 535.
Wiersbe, p. 537.
MacArthur, p. 1973.
MacArthur, p. 1973.
MacArthur, p. 1973.
Wiersbe, p. 537-538
ጥያቄዎች
-
በ 2ዮሐንስ በመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ዉስጥ አምስት ጊዜ የተደጋገመዉ ቃል ምንድን ነው ? በአንባቢዎቹ ላይ ምን ለማግኘት እየሞከረ ነበር ?
-
“ በእዉነት መመላለስ “ የሚለዉ ሐረግ ምን ማለቱ ነው ? ያን በሕይወታችሁ ላይ እንዴት ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ (1ነገ 2፡ 4, መዝ 86፡ 11, ዮሐ 14፡ 15) ?
-
ዮሐንስ የተመረጠችዉ ሴት ከመጀመሪያ ሰምታዉ የነበረዉ ትዕዛዝ ጠቀሰው ፤ ያ ትዕዛዝ ምንድን ነው ? ዮሐንስ ፍቅርን እንዴት ገለፀው (ዮሐ 15፡ 10, 1ዮሐ 2፡ 7-11, 2ዮሐ 5-6) ?
-
ሰዎች በክርስቶስ ትምህርት የማይሆኑ/የማይፀኑ ከሆነ የት ይቆማሉ/ይሆናሉ (1ዮሐ 2፡ 23) ? ሰዎች በክርስቶስ ትምህርት የሚሆኑ/የሚፀኑ ከሆነ የት ይቆማሉ ?
-
ሰዎች ከሌላ ኃይማኖት ወይም እምነት ወደ በራችሁ በሚመጡ ጊዜ 2ዮሐ (10-12) በተግባራዊነት እንዴት ትይዙት/ታደርጉታላችሁ ? 2ዮሐ (5-6) (ማቴ 22፡ 37-39) ?
-
በ 2ዮሐንስ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 John 1:6
“And this is love: that we walk according to His commands. This is the command as you have heard it from the beginning: you must walk in love.”
ዮሐንስ እርስዋና ልጆችዋ በክርስቶስ እውነትና ፍቅር ይመላለሱ ዘንድ በማዘዝ መልዕክትን ለአማኞች ይጽፋል ፡፡ እርሱም የኢየሱስን እውነት ከሚክድ ሐሰተኛ ትምህርት እራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ አስጠነቀቃቸው ፡፡ በተጨማሪም በክርስቶስ ትምህርት ብቻ እንድኖሩ አሳቾችን ግን ወደ ቤታቸው እንኳ እንዳይጋብዙ አዘዛቸው ፡፡
እግዚአብሔር ለህይወታችሁ ያዘጋጀውን መንገድ ስትከተሉ በእውነትና በፍቅር ትመላለሱ ዘንድ ተጠርታችኋል ፡፡ ለክርስቶስ እሺ ስትሉ፣ በድል ትራመዳላችሁ ፡፡ ከብዷችሁ ፣ ዝላችሁ እንኳ ሳለ በፍቅር ትመላለሳላችሁ ፡፡ በፍቅር ስትመላለሱ፣ ክርስቶስን ትመስላላችሁ ደግሞም በክርስቶስ ትዕዛዛት ውስጥ ትኖራላችሁ ፡፡ በእርሱም ስትኖሩ ፡- ይቅር ማለትን ትወዳላችሁ፣ መስጠትን ትወዳላችሁ፣ በቀልን መተው ትመርጣላችሁ ደግሞም ሐሰተኛ አስተማሪዎች በመንገዳችሁ ሲመጡባችሁ ሳታወላውሉ ጸንታችሁ ትቆማላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር ድል የማድረግንና የማሸነፍን ጥበብ ይሰጣችኋል ፡፡ በክርስቶስ ፍቅርና እውነት የምትጓዙበት መንገድ ቀላል ወይም የተመቻቸ እንደሚሆን አይጠበቅም ፡፡ ነገር ግን ጓደኞቼ እናንተ በፍቅር በመመላለስ ስትጸኑ በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ ይከተሉዋችሁ ዘንድ እግዚአብሔር በቸርነትና በምህረቱ ይባርካችኋል፡፡
“እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።”
- 2ኛ ዮሐንስ 1፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 143:8 — “አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።”
ኤፌሶን 5:1–2 — “እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።”
2ኛ ዮሐንስ 1:4 — “ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።