The Certainty Of God's Testimony
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Love 1 John 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዮሐንስ ለኢየሱስ ሕይወት እና ለሐዋሪያት ኑሮ መግለጫ የአይን ምስክር የሆነ ሰዉ ነበር ፡፡ እየፃፈላቸዉ እና እያወራቸዉ ለነበሩት የመናገር ስልጣን ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ዮሐንስ (5፡ 1-21)፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ቁጥሮች ስለ መፅደቅ ይደርሳሉ ፡፡ አንድ ግለሰብ አንዴ ክርስቶስን ሲቀበል ኃጢዓቱ ተወግዷል ፤ ይሁን እንጂ የኃጢዓት ተፈጥሮ/ማንነት አሁንም በዚያ አለ ፡፡ አማኞች የቅድስናን እና የፅድቅን ሂደት ይከታተላሉ ፡፡ የመክበር/የክብር ሂደት በኢየሱስ ሁለተኛ መምጣት ላይ ይመጣል ፤ መንፃት እና ፍፁምነት ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ ይሆናሉ/ይከናወናሉ ፡፡ አንደኛ ዮሐንስ ስለ መቀደስ እና ኃጢዓት ከፅድቅ ጉዳይ ጋር ያወሳል ፡፡ መቀደስ በመታዘዝ የመመላለስ መልክ/ቅርፅ ነው ፡፡
የ 1ዮሐንስ ጭብጥ እግዚአብሄርን መዉደድ እና ሌሎችን መዉደድ ነው ፡፡ በ 1ዮሐንስ 5 መጀመሪያ ላይ የተነሳዉ ጥያቄ አማኞች መቀደስን በደስታ መከታተል ይፈልጋሉ የሚል ነበር ? አማኞች ፅድቅን ቅር በመሰኘት መከተል የለባቸውም ፡፡
በቁጥር 3 ዮሐንስ ለእግዚአብሄር መታዘዝን አዘዘም ፈለገም ፤ ትዕዛዙን በመጠበቅ ለእግዚአብሄር ፍቅሩን ገለፀ ፡፡ በህይወት ዉስጥ የእግዚአብሄርን መልክ ለማሳየት/ለማንፀባረቅ ፍላጎት ከነበር በዉስጡ ደስታ ይኖረዋል ፤ ሰዉ ጌታን የሚወድ ከሆነ በኑሮአቸዉ የተቀደሱ ለመሆን ፍላጎት አለ ፡፡
ዮሐንስ በፅድቅ መኖር ሸክም የሚሆን ከሆነ አማኞች ያንን ለእግዚአብሄር መናዘዝ/መናገር ያስፈልጋቸዋል ፡፡ በቅድስናቸው ዉስጥ የአማኞችን መፍትሄ ለማግኘት እግዚአብሄርን መጠየቅ የመጀመሪያዉ እርምጃ ነው ፤ በክርስቶስ መኖር እንደ እድል መታዬት አለበት ፤ ወደ ደስተኛ መታዘዝ መቀየር/መተርጎም አለበት ፡፡ ዋይርስቤ “ ዝም ብሎ መታዘዝ ብቻ ሳይሆን በደስታ መታዘዝ ! ትዕዛዞች ሸክሞች/ከባዶች አይደሉም (1ዮሐ 5፡ 3) “ በማለት ይናገራል ፡፡
የክርስቶስ ድል መንሳት አለምን ሁሉ አሸንፏል ፤ ስለዚህም በክርስቶስ የተወለዱት አማኞች አለምን ማሸነፍ ይችላሉ ፤ አማኞች በመታዘዛቸዉ ደስታ አለምን ለማሸነፍ/ለመቋቋም የሰለጠኑ/የተዘጋጁ ናቸው ፡፡
መዝ (119፡ 97) የእግዚአብሄር ትምህርቶች በዘመን ሁሉ እንዳሉ ይናገራል ፤ ይህ ሰዎች የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ እንዲጠብቁ ይረዳቸዋል ፡፡ አማኞች የእግዚአብሄር ቃል በሚገለጥበት መንገድ የተደሰቱ መሆን አለባቸው ፤ በእግዚአብሄር ቃል ዉስጥ ዋጋ አለ ፤ ለአማኞች የእግዚአብሄር ተስፋ ከሆነዉ ቃል ዉስጥ የደስታ መንፈስ አለ ፡፡
መዝ (119፡ 14 እና 162) በእግዚአብሄር ቃል ስለመደሰት ያወራል ፤ መዝ (119፡ 16 እና 24) በእግዚአብሄር ቃል ደስተኛ ስለመሆን ይጠቅሳል ፤ መዝ (119፡ 103) ለእግዚአብሄር ቃል መራብን ይጠቅሳል ፡፡ መዝ (119፡ 54) ስለ ቃሉ ፍቅር መዝሙርን ያካትታል ፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል የሆነ ደስታ በተለያዬ መንገድ መጥቷል ፡፡ አማኞች ከእግዚአብሄር ቃል የሆነን ነገር በደስታ እና በሚያስደስት ስሜት እንጂ ሸክም በሆነ ስሜት አያደርጉም ፡፡
በቁጥር 5 ዮሐንስ የአለምን መንገድ ማሸነፊያዉ መንገድ በክርስቶስ ባለ እምነት እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ አማኞች የማይከታተሉ/የማያተኩሩ ከሆነ ወደ አለም መንገድ ተመልሰዉ ሊሸራተቱ ይችላሉ ፡፡ ዋይርስቤ “ በእንደዚህ አይነት ፍቅር ለመጀመር መዘራት አለበት ፤ ይህ የጥላቻ ወይም የተሳሳተ ጓደኝነት ዉጤት አይደለም ! የቀደመዉ ጥናት አማኝ ወደ አለም ወደኃላ ደረጃ በደረጃ እንደሚሸራተት አመልክቷል፡ 1) ከአለም ጋር ጓደኝነት መፍጠር (ያዕ 4፡ 4)፣ 2) በአለም መበከል (ያዕ 1፡ 27)፣ 3) አለምን መዉደድ (1ዮሐ 2፡ 15-17)፣ 4) አለምን መምሰል (ሮሜ 12፡ 2) “ ፡፡
የሰይጣን ግብ አማኞች ወደቀዉ ማግኘት ነው ፤ ያም ከአለም ጋር ጓደኝነት/ወዳጅነት በሚኖር ጊዜ ይጀምራል ፡፡ ፈተናው ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ወዳጅነት/ዝምድና መጠበቅ ነው ፤ ያ ወዳጅነት/ዝምድና የሚጠበቅበት መንገድ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ጊዜን በማሳለፍ ነው ፡፡
በቁጥር 13 ዮሐንስ እነዚህን ነገሮች ፅፎ ስለ ነበር አማኞች የዘላለም ሕይወት እንደ ነበራቸዉ መረዳት ይኖራቸዋል አለ ፤ በተጨማሪም አንባቢዎቹ በክርስቶስ መሰረት እንደነበራቸው እንዲያውቁ ፈለገ ፡፡ አማኞች እግዚአብሄር እንደሚሰማቸው በፀሎት ሙሉ እምነት ሊኖራቸዉ ይገባል ፤ እግዚአብሄር ወደ አማኞች ፀሎት ማድመጥ/መስማት ይፈልጋል ፡፡
በቁጥር 14 እና 15 ዮሐንስ አማኞች ማንኛዉንም ነገር መጠየቅ እንደሚችሉ እና እግዚአብሄር እንደሚሰማቸዉ እና ጥያቄአቸዉን እንደሚያከብር ይናገራል ፡፡ በፀሎት ዉስጥ የሚገኝ ነፃነት ነበር ፤ ፀሎታቸዉ እንዲመለስ ወደ እግዚአብሄር ሲመጡ በኑሮአቸዉ ዉስጥ ንስኃ ያልገቡበት ኃጢዓት መኖር የለበትም ፡፡
ዋይርስቤ “ ክርስቲያኖች ፍርዱን በሙሉ መተማመን እንደሚጠብቁት በፀሎት ሙሉ መተማመን አላቸው(1ዮሐ 2፡ 28, 4፡ 17) ፡፡ እንዳየነው የቃሉ ሙሉ መተማመን ማለት የመናገር ነፃነት ማለት ነው ፡፡ ወደ አብ በነፃነት በመምጣት የሚያስፈልገንን መናገር እንችላለን ፤ በእርግጥ ሟሟላት ያለብን ሁኔታዎች አሉ ፡፡ መጀመሪያ የማይከስ/የማይኮንን ልብ ሊኖረን ይገባል (1ዮሐ 3፡ 21-22) ፤ ሁለተኛ በእግዚአብሄር ፍቃድ መፀለይ አለብን ፤ እንደሚሆን (ማቴ 6፡ 10)“ ፡፡
መደምደሚያ
አንደኛ ዮሐንስ እግዚአብሄር እኛን ስለወደደን ሌሎችን መዉደድ እንደምንችል ይገልፃል ፤ ክርስቶስ ፍፁም ፍቅር ስላሳየን አማኞች ኑሮአቸዉን ከእግዚአብሄር ጋር በትክክለኛ አቋም መመላለስ ይችላሉ ፡፡ በመታዘዝ እና እርሱን በመከተል ዉስጥ ሙሉ የሆነ ደስታ አለ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament, Volume II (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 523.
Wiersbe, p. 526.
3 Wiersbe, p. 528.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዮሐንስ 5 መሰረት እዉነተኛ አማኞች በክርስቶስ ያሏቸዉ አምስት ድፍረቶች ምንድን ናቸው (1ዮሐ 5፡ 13, 14-17, 18, 19, 20) ? ከእነዚህ ዉስጥ በእዉነት በማመን ዉስጥ ትግል የሆነባችሁ አለ ?
-
አብን/አባቱን የምንወድ ከሆነ በተጨማሪ ማንን መዉደድ አለብን ? የእግዚአብሄር ትዕዛዞች ለምን ሸክም አይሆኑም (1ዮሐ 5፡ 3) ?
-
በፍጥረት ዉስጥ ሁሉም ነገር ከሰዉ በስተቀር የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለምን እንደሚያከብሩ ምን ታስባላችሁ (መዝ 148፡ 8, ኢሳ 29፡ 13) ? ዮሐንስ ፍቅርን ከመታዘዝ ጋር ለምን አስተካከለው ?
-
በ 1ዮሐ (5፡ 7-8) ዮሐንስ የጠቀሳቸዉ ሰዎስት ምስክሮች እነማን ወይም ምንን ነው ? ከ (ማር 1፡ 1, ዮሐ 20፡ 31, ዕብ 4፡ 14) በመስማማት እነዚህ ሰዎስቱ ምንድን ናቸው ?
-
እግዚአብሄር በግልፅ ልጆቹ ምን እንዲያዉቁ ይፈልጋል (1ዮሐ 5፡ 10-13) ? በእርግጠኝነት የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ ወይም ወደ ሲዖል እንደምትሄዱ ማወቅ እንደማትችሉ ለሚያምን ሰዉ ይህን ታላቅ እዉነት እንዴት ትገልፁለታላችሁ ?
-
በ 1ዮሐንስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 John 5:3–5
“For this is what love for God is: to keep His commands. Now His commands are not a burden, because whatever has been born of God conquers the world. This is the victory that has conquered the world: our faith. And who is the one who conquers the world but the one who believes that Jesus is the Son of God?”
ዮሐንስ የዓለምን ጨለማነትና ጠላት እንዴት ሊሰርቅ ፣ ለገድልና ሊያጠፋ እንደሚሻ ተረድቷል ፡፡ ዮሐንስ በስቃይና በመከራው ውስጥ ተጽናና ፡፡ አማኞች ከእግዚአብሔር ስለ ተወለዱ ፣ በክርስቶስም አዲስን ህይወት ስለተቀበሉ ደግሞም ዓለምን ያሸነፉ ስለሆነ፣ ዮሐንስ በእውነት መከራቸው ፡፡ አሸናፊነት በክርስቶስ ዘንድ ነው! በርግጥም ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው ፡፡ የማይታው ነገር ወደ ፊት እንደሚመጣ እንደሚፈጸም እመኑ ፡፡ ኢየሱስን አዳኝ አድርጋችሁ ስለምታምኑ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ ፡፡
ጓደኞቼ ኢየሱስን አዳኝ አድርጋችሁ ስታምኑ ፣ ድልን ትቀዳጃላችሁ ፡፡ በዓለም ላይ ድል ፤ በጨለማ ላይ ድል ታደርጋላችሁ ፡፡ ድልን ትቀዳጃላችሁ! እስኪ አይኖቻችሁን ጭፍናችሁ ራሳችሁን ዓለምን እየጠፋችሁ እንዳለ አድርጋችሁ ሳሉ ፡፡ ጽኑና ጠንካራ ሆናችሁ ትቆማላችሁ ፡፡ በጭንቀት፣ በፍርሃት፣ በድብርት ውስጥ አትወድቁም ወይም ከጠላት የሆኑት ውሸቶች አትችሉም ፣ አይደላችሁም ፣ አትሆኑም ፣ ትሞታላችሁ ፣ ትወድቃላችሁ ወይም ብቻችሁን ትቀራላችሁ የሚሉት ሁሉ አያስፈሯችሁም ፡፡ በእምነት በመራመድ በውሸቶች ላይ ድልን ተቀዳጁ ፡፡ አሳባችሁን በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ አድርጉ ፤ በእርሱ እመኑ በእርሱም ኑሩ ፡፡ ዛሬ ጮክ ብላችሁ እንዲህ በሉ ፡- “ አሸናፊ ነኝ! በክርስቶስ ዓለምን ማሸነፍ እችላለሁ ፡፡”
“ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?”
- 1ኛ ዮሐንስ 5፡3-5
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 15:57 — “ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።”
1ኛ ዮሐንስ 4:4 — “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።”
1ኛ ዮሐንስ 5:14 — “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።