General Letters 1 John

Knowing God Through Love

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Love 1 John 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 682 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሚጠበቀዉ መጨረሻ ሲቀርብ ዮሐንስ አማኞች የነቁ/የተጠነቀቁ መሆን እንደነበረባቸው አብራራ ፡፡ ክርስቲያኖች በመስመር መመላለስ፣ በፍቅ መመላለስ እና አለማመቻመች ያስፈልጋቸዋል ፤ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎችም በተጠንቀቅ የሚጠብቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል ፡፡

በ 1 ዮሐንስ በተለይም በምዕራፍ 2, 3 እና 4 የፍቅር ፍሬ ነገር/ጭብጥ አለ ፡፡ እንደ ዮሐንስ አገላለፅ የፍቅር የመጨረስ መልክ የሾክ አክሊል/ዘዉድ መድፋት ነው ፡፡

በ 1ዮሐንስ መፅኃፍ ዉስጥ ለክርስቶስ ሐረጉ ፍፁም ፍቅር የሚል ነው ፡፡ ክርስቶስ ካደረገው ከሞቱ፣ ከመቀበሩ እና ከትንሳኤዉ የተነሳ ፍርኃጽን ሁሉ ያስወግዳል ፡፡ ፍርኃት ቅጣት ማለት ሲሆን በክርስቶስ ፍርኃጽ ሁሉ ተወግዷል ፡፡

ትምህርት

1-ዮሐንስ (4፡ 1-21)፡ የዮሐንስ ሰላምታ በፅኁፉ ለደረሳቸዉ ጉባኤ ፍቅሩን ያሳያል ፡፡ ማክአርቱር “ በ (3፡ 12) የመንፈስ ቅዱስ መጠቀስ ዮሐንስ ሐሰተኛ አስተምሮን የሚያሰራጩ ሐሰተኛ ነቢያትን እና ሐሰተኛ አስተማሪዎችን የሚያመነጩ ሌሎች መናፍስቶች (ማለት የአጋንንት መናፍስቶች) እንዳሉ ለአንባቢዎቹ እንዲነግራቸው እንደሚያዘጋጀው “ ይናገራል ፡፡ የአጋንንት መናፍስቶች በመኖራቸዉ የሐሰት እዉነትን የሚናገሩ ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ያመነጫሉ ፡፡ የዮሐንስ ፅኁፍ ከእግዚአብሄር ያልሆኑ ሌሎች መናፍስቶች በዚያ እንዳሉ ለማሳየት ነው፡፡

ዮሐንስ ሁሉንም መናፍስት የሚናገሩት ከእግዚአብሄር እንደሆነ ለመወሰን መፈተን እንደሚያስፈልግ ይናገራል ፤ የአስተማሪን አስተምሮ ተጠራጣሪ መሆን ያስፈልጋል ፤ ፈተናው አስተማሪዉ ከእግዚአብሄር እንደሆነ ወይም ደግሞ እንዳልሆነ በግልፅ ይገልፃል ፡፡

በሐዋሪያት ስራ 17 ቤሪያዊያንከአስተማሪዎች መልዕክትን ለመቀበል የጓጉ ነበሩ ነገር ግን ትምህርቶቹ ትክክል ወይም ደግሞ ሐሰት እንደ ነበሩ ለመወሰን መፅኃፍትን ዕለት በዕለት መረመሩ ፡፡ ሁልጊዜ በመፅኃፍት ላይ ያሉ ትምህርቶችን መፈተን ያስፈልጋል ፡፡

እምነት የሚጣልበት ትምህርት ኢየሱስ በስጋ እንደ መጣ ይናገራል ፤ እነዚህ ትምህርቶች ከእግዚአብሄር የመጡ ናቸው ፡፡ መፅኃፍ ቅዱስ ለእዉነት እንደ መለኪያ በትር ያገለግላል ፡፡

ዮሐንስ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ወደ አማኞች አለም እየገቡ እንደ ነበር አስጠነቀቀ ፡፡ ክርስቶስን ተቃዋሚዉ ከመምጣቱ ቀድሞ ሐሰተኛ አስተማሪዎች የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስን ያንፀባርቃሉ ፤ ከጌታ ከእግዚአብሄር ያልሆነ ትዕዛዝ፣ ሕግ እና መጥፎ ልምድ አላቸው ፡፡ የ 1ዮሐንስ ሚና አማኞችን ከክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ማስጠንቀቅ ነው ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ፣ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ እና ክርስቶስ እንደ ሞተ፣ እንደ ተቀበረ እና ተመልሶ ወደ ሕይወት እንደመጣ ከሚለዉ መልዕክት ተጨማሪ የሐሰት ትምህርትን የያዘ ነው ፡፡ ዮሐንስ እዉነቱን ለመግለፅ እና ሰዎችን ከሐሰተኛ ትምህርት ስቦ ለማዉጣት እየሞከረ ነው ፡፡

ማክአርቱር ለክርስቶስ ተቃዋሚ ብዙ ስሞች/ቃሎች እንዳሉ ይገልፃል፡ “ ለክርስቶስ ተቃዋሚ ሌሎች ስሞች (1ዮሐ 2፡ 18, 4፡ 3), 1) ትንሽ ቀንድ -(ዳን 7፡ 8)፣ 2) ንጉስ - ዳን (8፡ 23)፣ 3) የሚመጣዉ አለቃ - ዳን (9፡ 26)፣ 4) የኃጢዓት ሰው - 2ተሰ (2፡ 3)፣ 5) የዓመፅ ልጅ - (2ተሰ 2፡ 3) እና 6) አዉሬዉ - ራዕ (13፡ 4) “ ፡፡

የክርስቶስ ተቃዋሚ ከሰይጣን ይለያል ፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሰይጣን የሚጠቀምበት የሰዉ መሳሪያ/መጠቀሚያ ነው ፡፡ 1 ዮሐ (2፡ 18) የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ያላቸው ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለሆኑ ሰዎች ማጣቀሻ/ማሳያ እንዳሉ ይገልፃል ፡፡ የእዉነት ሰሪ/አድራጊ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄርና እንደ አዳኝ ለይቶታል/አስቀምጦታል ፡፡ የይሁዳ እና የ 1ዮሐንስ መፅኃፍት ሐሰተኛ አስተማሪዎችን እና ትምህርቶችን ለመከላከል ተፃፉ ፡፡

በቁጥር 4 ዮሐንስ በአማኞች ዉስጥ ያለዉ በአለም ካለዉ እንደሚበልጥ ይናገራል ፤ በመቀጠልም ዮሐንስ ሐዋሪያት እና ትምህርታቸዉ ከጌታ እንደ ነበር አመለከተ (ቁጥር 6) ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያውቁ አማኞች ይሰማቸዋል ፡፡ የእዉነትን መንፈስ ከዉሸት መንፈስ ጋር አነፃፀሩ ፡፡

ዮሐንስ እግዚአብሄር የፍቅር መሰረት/መገለጫ ስለ ነበር እርስ በእርሳቸዉ እንዲዋደዱ አበረታታቸው ፡፡ ማክአርቱር “ ዮሐንስ ለምን ክርስቲያኖች እንደሚዋደዱ ከአምስቱ ምክንያቶች አንዱን - ምክንያቱም እግዚአብሄር ፍቅር ስለሆነ የሚለዉን ለአንባቢዎቹ እንዳሳወቃቸው “ ይገልፃል ፡፡

አማኞች ሁሉንም ሰዉ እንዲወዱ የሚጠበቁ ናቸው ፤ ጠላቶቻቸዉን ይወዳሉ ነገር ግን የጠላቶቻቸዉን መልዕክት አይቀበሉም ፡፡ ፍቅር/መዋደድ አማኞች በእግዚአብሄር ማን እንደሆኑ የሚያንፀባርቁበት/የሚያሳዩበት አንድ መንገድ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ክርስቶስ ለአለም ቢሞት እና አለም ቢድንም አለም ሁሉ በእርሱ ያምናሉ ማለት አይደለም ፡፡

ለመዳን መስፈርቱ ሰዉ ክርስቶስን እንደ ጌታ ማመን ነው ፡፡ በሚመጣዉ ፍርድ ፍቅር የክርስቲያኖች ድፍረት/መተማመኛ ነው ፡፡ የማያምኑት በክርስቶስ ካመኑ መልዕክቱ የተስፋ መልዕክት እንጂ የፍርኃት አይደለም ፡፡

የእግዚአብሄር ፍቅር አማኞች ወንድሞቻቸዉን እና ጎረቤቶቻቸዉን/ወዳጆቻቸዉን እንዲወዱ ይጠይቃል ፤ ልጁን እግዚአብሄርን እንደ አዳኝ ከያዙ አንዱ ሌላዉን ሊወደዉ ይገባል ፡፡ አማኞች በእግዚአብሄር እንደ ተወደዱ ይዋደዳሉ፡፡

መደምደሚያ

መዉደድ ብቻ እንችላለን ምክንያቱም መጀመሪያ ክርስቶስ ስለወደደን ፡፡ እግዚአብሄር ክርስቶስን ለእኛ በመስቀል እንዲሞት ስለላከው ፍቅርን ማወቅ እንችላለን ፡፡ እግዚአብሄር አማኞች ወንድሞቻቸዉን እንዲወዱ ተስፋ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ጥያቄው ማነዉ ወንድሜ ወይም ወዳጄ የሚል ነው ? ትክክለኛዉን እዉነት ለእነርሱ በመናገር ፍቅርን ሊታይ ይችላል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1962.

  2. MacArthur, p. 1963.

  3. MacArthur, p. 1964.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዮሐ (4፡ 1) ከእግዚአብሄር የሆኑ እንደ ሆኑ ለማየት መንፈስን እንድንፈትን ተነግሮናል ፤ እንዴት እንፈተናቸዉ/እንመረምራቸዋለን (1ዮሐ 4፡ 2-3) ?
  2. በ 1ዮሐ (4፡ 4) ዮሐንስ እንደ ልጅ እየደረሰ የነበረዉ ማንን ነበር ? በቁጥር (4-6) ላይ በምትመለከቱ ጊዜ በዚህ ክፍል ዮሐንስ ስለ እነርሱ ምን እያስተማረ ነበር
  3. በ 1ዮሐንስ 4 የፍቅር ርዕስ እንዴት የታወቀ እንደሆነ ተመልከቱ ፤ ዮሐንስ ስለዚህ(ስለ ፍቅር) ለምን ብዙ እንዳወራ ምን ታስባላችሁ ? “ እግዚአብሄር ፍቅር ስለሆነ የማይወዱ ሰዎች እግዚአብሄርን አያዉቁትም “ የሚለዉ ንግግር በዙሪያችሁ ካሉት ጋር ያላችሁን መስተጋብር እንዴት ተፅዕኖ ያደርግበታል ?
  4. አንደኛ ዮሐንስ (4፡ 12-16) ከዮሐ (15፡ 4-7) ጋር ተመሳሳይ ነገር ይናገራል ፤ በእነዚህ በሁለቱም መፅኃፍት ላይ በመመልከት ለመታመን ምን ማለት እንደሆኑ አሰላስሉአቸዉ
  5. በ 1ዮሐ (4፡ 18) መሰረት ፍፁም ፍቅር ፍራትን አዉጥቶ ይጥላል ፤ በፍርኃት ትፈተናላችሁ ? አዎ ከሆነ ምናልባት በጌታ ላይ እምነት ከማጣት የተነሳ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? በፍርኃታችሁ እንዴት ትኖራላችሁ / ትሰራላችሁ ?
  6. በ 1ዮሐንስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 John 4:17–19

“In this, love is perfected with us so that we may have confidence in the day of judgment, for we are as He is in this world. There is no fear in love; instead, perfect love drives out fear, because fear involves punishment. So the one who fears has not reached perfection in love. We love because He first loved us.”

ዮሐንስ ለአማኞች የክርስቶስ ፍጹም ፍቅር ፍርሀትን አውጥቶ እንደሚጥል ይነግራቸዋል ፡፡ ክርስቶስ ይህን ፍቅር የገለጸው እናንተ ገና ኃጢአተኞች ሳላችሁ ስለ እናንተ በመሞት ነው ፡፡ እርሱ ለእናንተ ያለው ፍቅር ፍጹም ነው በህይወታችሁም ውስጥ ያለውን ፍርሃት ሁሉ አውጥቶ ይጥላል ፡፡ በፍርሃታችሁ ውስጥ እንኳ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ይቆማል ፣ እርሱ ይወዳችኋል ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር አብሮ እንደሚወጣ ይናገራል ፡፡ ከእርሱም ታላቅ ፍቅር የተነሳ እናንተም ትወዳላችሁ ፡፡

እናንተ ትወደዱ ዘንድ ክርስቶስ ከሞተ ፣ እርሱም ቀድሞ ስለወደዳችሁ እናንተ ሌሎችን ትወዳላችሁ ፣ እናንተም ልክ እንደ ክርስቶስ ትወዱ ዘንድ ለራሳችሁ መሞት አለባችሁ ፡፡ ለራሳችሁ መሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ገብቷችኋል ? ሌሎችን ለመውደድ እየተቸገራችሁ ከሆነ ፣ የራስ ወዳድነት ፍላጎታችሁን ግደሉ ፣ ትምክታችሁን ግደሉ ፣ ፍላጎቶቻችሁ እንዳይቆጣጠሩዋችሁ እነርሱን ግደሉ ፡፡ እነዚህን ተውና፣ በክርስቶስ ኑሩ ፡፡ ልክ ክርስቶስ እንዳደረገው ሁሉ እናንተም ህይወታችሁን ለሆነ ሰው ስትሉ በመተው ውደዱ ፡፡ ለራስ መሞት ማለት “ እንዲህ ቢሆንስ “ እያሉ በፍርሃት መኖር ማለት አይደለም ነገር ግን በእውነት ውስጥ በተስፋ መኖር እንጂ ፡፡ ልክ እንደ ኢየሱስ ውደዱ ፡፡ ይህንን እንድታደርጉ ነው የተጠራችሁት ደግሞም እንዲሁ ፍጹም ፍቅር በውስጣችሁ ሲኖር ማድረግ የምትችሉት ይህንን ነው ፡፡

“ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና። ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።”

  • 1ኛ ዮሐንስ 4፡17-19

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 5:8 — “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”

ገላትያ 2:19b–20 — “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።”

1ኛ ዮሐንስ 4:16 — “እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።”