Love In Action
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Love 1 John 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ክፍል በጳዉሎስ ካልተፃፈ መልዕክት የመፅኃፍ ቅዱስ ምልዕክት ከሆኑ ከአጠቃላይ መልዕክት ዉስጥ መጣ ፤ በ 1ዮሐንስ 2 ከዮሐንስ የሆነዉ ንግግር እንደ ክርስቶስ መመላለስ የሚል ነው ፤ ይህም በብርኃን መመላለስ የሚለዉንም ያመለከተ ነው ፡፡ በ 1ዮሐ (2፡ 28) ለአማኞች ማጣቀሻው/ማሳያው እንደ ሕፃን ልጅ ነው ፤ መደምደሚያው በክርስቶስ ፃድቅ እንደ ነበሩ ነበር ፡፡
በመቀደስ መመላለስ ማለት አማኞች በክርስቶስ የተወለዱ ናቸው ማለት ነው ፤ መጽደቅ/መቀደስ በእግዚአብሄር አይን ልክ/ትክክል መሆን በማለት የሚተረጎም ነው ፡፡ ቅድስና ጽድቅ ወይም በክርስቶስ በትክክል አቋም መመላለስ ነው ፡፡ ክብር/መክበር አማኞች ክርስቶስ እንደ ገና እስኪመጣ ድረስ ሊያሟሉት የማይችሉት የፍፁምነት ልክ ነው ፡፡ አማኞች በክርስቶስ እንዲመላለሱ የተበረታቱ ስለሆነ በሚገለጥ ጊዜ ይመላለሱ በነበረበት ነገር አያፍሩም ፡፡
ትምህርት
1-ዮሐንስ (3፡ 1-10)፡ ዮሐንስ አማኞች የእግዚአብሄር ልጆች እንደ ሆኑ አስቀምጧል ፡፡ ዮሐንስ አለም አማኞች የእግዚአብሄር ልጆች እንደ ሆኑ ያላወቀበት ምክንያት እግዚአብሄርን ስላላወቀዉ እንደ ነበር ገልፆአል ፡፡ እግዚአብሄር አማኞችን ፍቅሩን ስለሰጣቸው ሁሉም የእግዚአብሄር ልጆች እና ቤተሰቦች ተብለዉ ይጠራሉ ፡፡ ሁሉም እግዚአብሄርን አያምንም አያውቅም ፤ ሁሉም የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዲቀበሉ ስላልተመረጡ እርሱን አያዉቁትም፡፡
በቁጥር 2 ዮሐንስ አማኞች የእግዚአብሄር ልጆች እንደ ሆኑ ነገር ግን እስካሁን የመክበርን/የክብርን ልክ እንዳላሳኩ ይናገራል ፡፡ ፊል (3፡ 21) ክርስቶስ በሚመጣ ጊዜ የአማኞች ሰዉነት እግዚአብሄርን ወደ ሚመስል እንደሚቀየር እና የከበረ እንደሚሆን ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ “ አንደኛ ዮሐንስ (3፡ 1) ምን እንደሆንን እና 1ዮሐ (3፡ 2) ምን እንደምንሆን እንደሚናገር “ ፅፏል ፡፡ በሞቱ፣ በመቀበሩ እና በትንሳኤዉ በኩል ያለዉ ተስፋ - አማኞች ዘላላዊ ሕይወት እንዳላቸዉ ያመለክታል ፤ በተጨማሪም አማኞች በክርስቶስ ያላቸዉ ተስፋ በመጨረሻም ለዘላለም ከክርስቶስ ጋር እንደሚሆኑ ነው ፡፡ በክርስቶስ ያለን ተስፋ ያነፃናል ይቀድሰናልም ፤ አማኞች እርሱን ይመስላሉ ፤ በመጨረሻም መንፃት/መጽደቅ በመክብር ደረጃ/ልክ ላይ ይመጣል ፡፡ በመጨረሻም አማኞች ሕያዉነትን በማግኘት ከኃጢዓት ተፈጥሮ የነፁ ይሆናሉ ፡፡
በቁጥር 4 ዮሐንስ ሁሉም ሰዉ ኃጢዓትን እንደሚያደርግ ይናገራል ፤ ኃዓት የሚያደርግ ሁሉ ሕጉን ይጥሳል ፡፡ ሕግ አልባነት/እንከን በሕጉ ላይ ማመፅ ነው ፡፡ በቁጥር 5 ዮሐንስ በክርስቶስ ኃጢዓት የለም አለ ፤ አማኞች በክርስቶስ በመጣበቅ ቃላቸዉን ሲጠብቁ ኃጢዓት አያደርጉም ፡፡
ክርስቶስ ኃጢዓትን ሊያስወግድ ስለ መጣ በእርሱ ያሉት ኃጢዓትን አያደርጉም ፤ ኃጢዓት ለሚያደርግ ሁሉ አንድ አስተሰሪይ አላቸው ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ በኃጢዓት ድርጊት ዉስጥ የእግዚአብሄር ራዕይ የለም ፤ ኃጢዓት እግዚአብሄርን ችላ የማለት እና የጭፍንነት ዉጤት ነው (2ጴጥ 1፡ 9) ፡፡ አማኝ የሚፈፅመው ሁሉም ኃጢዓት ስለ እግዚአብሄር የተሳሳተ አስተሳሰብ ዉጤት ነው ፤ በእርግጥ አማኝ ስለ እግዚአብሄር በፍጹም ስህተት ካላሰበ በፍፁም ኃጢዓት አያደርግም/አታደርግም ፡፡ በጥቂቱ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ አዕምሮን/ሀሳብን ሁሉ በመማረክ ወደ ክርስቶስ እንድናመጣ በማሳሰብ አዝዞናል (2ቆሮ 10፡ 5) ፡፡ ማለፍ የማንችለዉ ፈተና የሆነ የምንዝናናበት ማንኛዉም ኃሳብ ክስ እንዲያነሳ ለሰይጣን እድል ይሆናል (ሐዋ 5፡ 2, 3) ፡፡
ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ዉስጥ ነው ፤ ምንም እንኳን በአዲስ ኪዳን እንደተቀመጠው በአሮጌዉ እና በአዲሱ ተፈጥሮ/ማንነት መካከል የማያቋርጥ ዉጥረት/ጠላትነት ቢኖርም የእግዚአብሄር መንፈስ በፍፁም አማኞችን አይተዉም ፡፡ ምንም ይሁን ምክንያቱ ኃጢዓት የነበረን ሕግ መተላለፍ አማኞች በግልፅ ተግባራዊ የሚያደርጉባቸው ክስተቶች ነበሩ ፡፡
በቁጥር 7 ዮሐንስ ክርስቶስ አማኞች በእርሱ በኩል አንዴ ከነፁ በኋላ ኃጢዓት እንደማያደርግ እንደሚያዉቅ ይናገራል ፡፡ ሰይጣን ያለማቋረጥ አማኞች ኃጢዓት እንዲያደርጉ ይገፋል ፤ ስለዚህም ክርስቶስ ለሁለት አላማ ነዉ የመጣው፡ 1) ኃጢዓትን ሊያስወግድ እና 2) የክፉን ስራ ሁሉ ለማጥፋት ፡፡ እዉነታው ሰይጣን አሁንም በምድር ላይ በስራ ላይ እንዳለና አጭር ጊዜ እንዳለዉ ነው ፡፡ ሰይጣን የአማኞችን አይን ከክርስቶስ ላይ ለማንሳት ማድረግ የሚችለዉን ሁሉ ያደርጋል ፤ ጦርነቱ አማኞች ያለማቋጥ ሰይጣን የሚሰጣቸዉ አቅጣጫ ባለመቀበል ኃጢዓትን ለማስወገድ በክርስቶስ ላይ አይናቸዉን ማድረግ ነው ፡፡ ክርስቶስ ተከታዮቹን በፅድቅ እንዲመላለሱ አስተማራቸው፡፡
በቁጥር 8 ሰይጣን የተገለፀበት ብዙ መንገዶች አሉ ፤ እንደ ጠላት ወይም ተቃዋሚ/ባላንጣ የተገለፀ ነው ፤ በተጨማሪም እንደ ክፉ ወይም እንደ ከሳሽ ተገልፆአል ፡፡ ሰይጣን አጥፊ እና የዚህ አለም አለቃ በመባል የተጠራ ነው፡፡ ተፈጥሮ የሆነዉ ሰይጣን ሌሎች ክርስቶስን እንዲከተሉ ሳይሆን የሱን መንገድ እንዲከተሉ በዚህ ምድር/አለም ላይ ነው ፡፡ ክርስቶስ አማኞች አይኖቻቸዉን በእርሱ ላይ የሚያደርጉ ከሆነ ኃጢዓት እንደማያደርጉ ተናግሯል ፡፡
ዘሩ ክርስቶስ በአማኞች ዉስጥ ከሆነ አማኞች ክርስቶስ እንደተመላለሰዉ ይመላለሳሉ ፡፡ የእግዚአብሄርም ልጆች የሚለዩት በዚያ ነው - በክርስቶስ በሚመላለሱት ምልልስ ፡፡ ግለሰቦች ወንድሞቻቸዉን የማይወዱ ከሆነ የእግዚአብሄር ልጆች አይደሉም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ክርስቲያኖች ቅድስናን በማድረግ ማንነታቸዉን/ተፈጥሮአቸዉን ያሳያሉ (3፡ 7) ፤ የክፉዉ ልጆች ኃጢዓትን በማድረግ መሰረታዊ ማንነታቸዉን / ተፈጥሮአቸዉን እንደሚያሳዩ “ ይገልፃል ፡፡
1-ዮሐንስ (3፡ 11-24)፡ በቁጥር 11 ዮሐንስ አማኞችን እርስ በእርሳቸዉ እንዲዋደዱ ይነግራቸዋል ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ “ ቃየል የሰይጣን መንፈሳዊ ልጅ በማለት የተለየዉ ሲሆን ፤ ወንድሙን አቤልን እንደ እግዚአብሄር ልጅ በማለት የተለዬ ነው “ ፡፡ በቁጥር 13 አማኞች አለም በእነርሱ ላይ እንደሚነሳባቸዉ አስጠንቅቋቸዋል ፡፡
አማኞች ስለሌሎች በምሬት መንፈስ መስራት/መኖር አይችሉም ፤ ክርስቶስ በአማኞች ሕይወት ካደረገዉ የተነሳ ወንድሞቻቸዉን ይወዳሉ ፡፡ ከክርስቶስ የተነሳ አማኞች ከሞት ወደ ሕይወት ተጉዘዋል ፡፡ የማንንም ሕይወት የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ይመስላል ፤ ነፍሰ ገዳዮች ባልሆኑት ዉስጥ የዘላለም ሕይወት ይኖርባቸዋል ፡፡
በቁጥር 16 ዮሐንስ የፍቅርን የመጨረሻውን ምሳሌ ይሰጣል - ለአለም የክርስቶስ ሕይወቱን መስዋዕትነት ነው ፡፡ የመስዋዕትነት ፍቅር አንዳን ተጨባጭነት ያላቸዉን ዉጤቶች እና በክርስቶስ መንገድ መመላለስን ይጠይቃል ፡፡ እዉነት እና ተግባር በእዉነተኛ ፍቅር ዉስጥ አንዱ ለሌላው የሚያስፈልጉ ናቸው ፡፡
መደምደሚያ
አማኞች በትክክለኛ መንገድ በመቆም እየተመላለሱ እንደሆነ የሚታወቁበት መንገድ በእዉነታቸዉ እና በድርጊታቸዉ ነው ፡፡ ከእግዚአብሄር የሆነዉ ትዕዛዝ መጀመሪያ በጌታ ማመን በመቀጠል ወዳጆቻችንን / ጎረቤቶቻችንን መዉደድ ናቸው ፡፡ ጥያቄ የሚሆነው በዙሪያችን ያሉትን በእዉነት እንወዳቸዋለን ?
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament, vol. II (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 504.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1711.
Wiersbe, p. 507.
Nelson’s Commentary, p. 1712.
Nelson’s Commentary, p. 1712.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዮሐንስ 3 መሰረት የእግዚአብሄር ልጅ ለምን አላማ ነበር የተገለጠው ?
-
ወንድሞቻቸዉን ስለሚጠሉት ዮሐንስ ምን አለ (1ዮሐ 3፡ 15) ?
-
ኢየሱስ ስለ እኛ ሕይወቱን ከሰጠን ለወንድሞቻችን ምን ማድረግ አለብን (1ዮሐ 3፡ 16) ? ይህን እንዴት እናደርጋለን ?
-
1ዮሐ (3፡ 18) “ በስራና በእዉነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ “ ይላል ፤ በዚህ ምን ማለቱ ነው ?
-
1ዮሐ (3፡ 22) አንብቡ ፤ ከዚህ በፊት እንደፀለዩና የሚፈልጉትን እግዚአብሄር እንዳልሰጣቸዉ የሚናገሩት በዚህ ቢከራከሯችሁ ምን ትሏቸዋላችሁ ? (ዮሐ 8፡ 29, 9፡ 31, ያዕ 4፡ 3, 5፡ 16)
-
በ 1ዮሐንስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 John 3:10–11
“This is how God’s children—and the Devil’s children—are made evident. Whoever does not do what is right is not of God, especially the one who does not love his brother. For this is the message you have heard from the beginning: We should love one another.”
ዮሐንስ ለአማኞች ፡- በህይወታችሁ የእግዚአብሔርን ፍቅር ስለተቀበላችሁ ፣ እናንተ ደግሞ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ውደዱ በማለት የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ያስታውሳቸዋል ፡፡ ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጆች ወይም የሰይጣን ልጆች መሆንን የሚገልጸው የፍቅር መኖር ወይም አለመኖር እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል ፡፡ ወንድማችሁን ወይም እህታችሁን የማትወዱ ከሆነ እናንተ ትክክል የሆነውን እያደረጋችሁ አይደለም ማለት ነው ፡፡
ልባችሁን ፈትሹ ፡፡ እስኪ ስለጎዷችሁ ወንድሞችና እህቶች አስቡ ፡፡ ምናልባት በህይወታችሁ ውስጥ እነርሱን ልትተዋቸው ፤ እነርሱንና ያደረሱባችሁን ጉዳት ልትረሱት ወስናችሁም ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ከልባችሁ ይቅር ብላችኋቸው ታውቃላችሁ ? እነርሱን እንደምትወዷቸው መናገር ትችላላችሁ ? ፍቅር በተግባር ይገለጻል ፡፡ ወንድማችሁን ወይም እህታችሁን ይቅር ማለት ምርጫ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ልክ እንደ ኢየሱስ እንድትወዱና ይቅር እንድትሉ ያዛችኋል ፡፡ ዛሬ ይቅር ልትሉት የሚገባ ሰው ካለ እግዚአብሔርን ጠይቁ ፡፡ በነጻነት ለመራመድ ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ምናልባት ይህ ከዚህ በኋላ ማንንም አለመጥላትን ይልቁንም ለመውደድ መወሰንን ያካትታል ፡፡ እናንተም ልክ እንደ እግዚአብሔር ገደብ አልባ ፍቅር መግለጫ አድርጋችሁ ለወንድሞቻችሁና ለእህቶቻችሁ ነፍሳችሁን አሳልፋችሁ ትሰጡ ዘንድ ተጠርታችኋል ፡፡ በርግጥ ጉዳቱ ጥልቅ ሲሆን ይህን ማድረግ ከባድ ነው ፡፡ ኢየሱስ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል ብሏል ፡፡ እናንተ ይህን ፍቅር ከኢየሱስ ተቀብላችኋል ፣ እና ግን እናንተስ በህይወታችሁ ይህን ፍቅር ለሌሎች ትሰጣላችሁ ? ልክ እንደ ኢየሱስ ሌሎችን በትህትና ስትወዱ ፣ ጌታ እንደመራችሁ እነርሱን ይቅር በሏቸው ከዚያም የእርሱን ታላቅ ፍቅር መያዝ ትጀምራላችሁ ፡፡
“የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤ “
- 1ኛ ዮሐንስ 3፡10-11
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 17:3-4 — “ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፦ ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።”
1ኛ ጴጥሮስ 4:8 — “ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።”
1ኛ ዮሐንስ 4:20–21 — “ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።