General Letters 1 John

Abiding In Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Love 1 John 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 680 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬም የአጠቃላይ መልዕክት (በጳዉሎስ ያልተፃፉትን መልዕክት) ጥናታችንን እንቀጥላለን ፡፡ ለ 1ዮሐንስ ሐረጋችን ፍፁም ፍቅር የሚል ነው (4፡ 18) ፡፡ በክርስቶስ በኩል ፍፁም ፍቅር ስለተቀበልን በፍርኃት አንመላለስም ፤ በትክክል ለዮሐንስ ለሁሉም መልዕክቶች ቃሉ ፍቅር ሊሆን ይችላል ፡፡

ትምህርት

1-ዮሐንስ (2፡ 1-6)፡ ዮሐንስ ይህንን መልዕክት አንባቢዎቹን ከኃጢዓት ለመጠበቅ ፃፈው ያ ማለት በፍፁም እንደ ገና ኃጢዓት አያደርጉም ማለት ሳይሆን ኃጢዓት ቢያደርጉም እንኳን ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ጋር አስታራቂአቸዉ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ማክአርቱር “ ስለ ኃጢዓት በአባታቸዉ ፊት ሰይጣን አማኞችን ቀን እና ሌሊት ቢከሳቸዉም (ራዕ 12፡ 10) የክርስቶስ ከፍ ያለዉ የክህነት አገልግሎት የራራል ብቻ ሳይሆን ነፃም አዉጥቶናል (ዕብ 4፡ 14-16) “ በማለት ጽፏል ፡፡

ኃጢዓትን ሸክም ለረጅም ጊዜ ልትሸከሙ ትችላላችሁ ነገር ግን አታደርጉትም ? ኢየሱስጠበቃችሁ ስለሆነ ጥፋትን/ኃጢዓትን ሁሉ ያስወግድላችኋል ፤ ነገር ግን ይህ አዉቀን ኃጢዓት እናደርጋለን ማለት አይደለም ፡፡

ዮሐንስ ኢየሱስን ለአለም ሁሉ ኃጢዓት ማስተሰሪያ የሆነ እንደ “ ፃድቅ “ ይገልፀዋል (ቁጥር 2) ፤ ማስተሰሪያ የሚለዉ ቃል ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባደረገው ነገር በመለመን ደስታን ማግኘት/መርካት ማለት ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ማስተሰሪያ የሚለዉን “ በመለኮታዊ ይቅር ባይነት ምህረት የተሞላበት የጥፋት ማስወገድ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ በኑሮአችን እና ለሰው ሁሉ ለስርየት ብቸኛዉ መንገድ በመስቀል ላይ በኢየሱስ ሞት ብቻ ነው ፡፡

ትዕዛዙን በመጠበቅ ክርስቶስን ወደ ማወቅ እንመጣለን (ቁጥር 3) ፡፡ ማክአርቱር “ መታዘዝ ዉጫዊ እና የሚታይ የድነት ማረጋገጫ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች እንደ ሆኑ የሚናገሩ ነገር ግን ትዕዛዙን የማይታዘዙ ዉሸታሞች ናቸው (ቁጥር 4) ፡፡

አብዛኞቻችን ክርስቲያን እንደ ሆኑ የሚናገሩ ነገር ግን በዉጪ የሚታይ መንፈሳዊ ፍሬ ስለሌለ በእርግጥ እንደ ሆኑ እርግጠኞች ያልሆንባቸዉን ሰዎች እናዉቃለን ፤ ምናልባትም ይህ ክርስቶስን የሚያውቁትን ነገር ግን በኃጢዓት የሚመላለሱ ሰዎች ይሆናል ፡፡ ምሳሌ አንድ አማኝ ጊዜዉን ወይም ጊዜአዋን ፖርኖግራፊ በመመልከት የሚያሳልፍ ፤ ያ አማኝ ዉሸታም ነው ምክንያቱም እሱ/እሷም በክርስቶስ ትዕዛዝ ዉስጥ ስላልታዘዙ ፤ ያ ጥብቅ ንግግር እንደ ሆነ አዉቃለሁ ነገር ግን ይህ ፅሁፉ የሚለዉ ነው ፡፡

ማክአርቱር በ 1ዮሐ (3፡ 4) “ ማድረግ/የሚያደርግ “ የሚለዉ ቃል “ የተለመዱ ድርጊቶችን ኃሳብ ከሚያሳይ “ የግሪካ ቃል የተተረጎመ እንደ ሆነ ይጽፏል ፡፡ የኃጢዓት ተፈጥሮ ስላለን ኃጢዓትን ልናደርግ እንችላለን ፤ ይሁን እንጂ ኃጢዓታችንን በመናዘዝ የእግዚአብሄርን ይቅርታ በተቀበልን ጊዜ ኃጢዓትን የለመደ እንዳንሆን መጣስ እንችላለን ፡፡ ማክአርቱር ክርስቲያኖች ለምን በተደጋጋሚ/በመልመድ ኃጢዓት ማድረግ እንደማይችሉ አራት ምክንያቶችን ያቀርባል፡

  1. “ ጠንካራ ክርስቲያኖች ኃጢዓትን መለማመድ አይችሉም ምክንያቱም ኃጢዓት ከሚታዘዙት ከእግዚአብሄር ሕግ ጋር የማይጣጣም ስለሆነ “ ፡፡
  2. “ ጠንካራ ክርስቲያኖች ኃጢዓትን መለማመድ አይችሉም ምክንያቱም ኃጢዓት ከክርስቶስ ስራ ጋር የማይጣጣም ስለሆነ “ ፡፡
  3. “ ጠንካራ ክርስቲያኖች ኃጢዓትን መለማመድ አይችሉም ምክንያቱም ክርስቶስ የኃጢዓት ሊቀ የሰይጣንን ስራ ሊያጠፋ ስለ መጣ “ ፡፡
  4. “ ጠንካራ ክርስቲያኖች ኃጢዓትን መለማመድ አይችሉም ምክንያቱም ኃጢዓት በዉስጣችን ከሚኖረዉ ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ጋር የማይጣጣም ስለሆነ “ ፡፡

የእግዚአብሄር ፍቅር የክርስቶስን ትዕዛዝ በሚጠብቁት ዉስጥ ፍፁም ነው (ቁጥር 5) ፤ ያ ማለት በእርሱ በመሆን እንሱ እንደ ተመላለሰው ለሚመላለሱት ማለት ነው (ቁጥር 6) (1ቆሮ 11፡ 1) ፡፡ ማክአርቱር “ ክርስቲያን ነን የሚሉ የመንፈሱን መገኘት እና ኃይል ስለተቀበሉ እሱ እንደኖረዉ ሊኖሩ እንደሚገባቸው “ ፅፏል ፡፡

1-ዮሐንስ (2፡ 7-17)፡ እንግዲህ ዮሐንስ ስለ ቀደመችዉ ትዕዛዝ “ በጊዜ አኳኋን/ሁኔታ አዲስ ያልሆነ ነገር ግን በጥራት፣ በአይነት እና በቅርፅ አዲስ ስለሆነ ያለፈዉን ነገር ስለሚተካዉ ነገር “ ፅፏል (ቁጥር 8) ፡፡ ዮሐንስ በቁጥር (9-10) አንድ አማኝ ወንድሙን የማይወድ ከሆነ አሁንም በጨለማ እንደ ሆነ እና ወንድሙን የሚወድ ግን ያለ ኃጢዓት ማሰናከያ በብርኃን እንዳለ በመግለፅ በተመሳሳይ ጭብጥ ቀጠለ (ቁጥር 9-11) ፡፡

ዮሐንስ አንባቢዎቹን በኢየሱስ ኃጢዓታቸዉ ይቅር እንደተባለ ለማስታወስ ፃፈ ፤ ክርስቶስን ካወቁ በሰይጣን እና በኃጢዓት ላይ ድል አድራጊዎች መሆን ይችላሉ (ቁጥር 12-13) ፡፡ የአባቶች፣ የጎልማሶች/ጎበዞች እና የልጆች የመንፈሳዊ እድገት ሂደትን አሳሰበ (ቁጥር 13) ፤ አባቶች በይበልጥ መንፈሳዊ ብስሎች ስለ ነበሩ እግዚአብሄርን ያውቃሉ ፤ ጎበዛዝቶች ጠንካራ አስተምሮ ነበራቸዉ ነገር ግን እንደ አባቶች የመንፈሳዊ ልምምድ አመት አልነበራቸዉም/አልደረሱም ፡፡ ልጆች ስለ እግዚአብሄር መሰረታዊ መረዳት ነበራቸዉ ነገር ግን ማደግ/መብስል አስፈለጋቸው ፡፡ የእያንዳንዱ ቡድን የመንፈሳዊ እድገት ደረጃን ምንም ቢሆን ከእነርሱ ዉስጥ ማንኛቸዉም በአለም ወይም በአለም ነገር ላይ ያተኮሩ ነበር (ቁጥር 15)

የነገሮች ፍቅር ከአባት የበለጠ አይሆንም ፡፡ የአለም የሆኑት ነገሮች - ዝሙት፣ የስጋ ምኞት፣ ትዕቢት/ኩራት - ከእግዚአብሄር የሚመጡ አይደሉም (ቁጥር 16) ፡፡ የአለም ነገሮች ጊዜአዊ ሲሆኑ ከእግዚአብሄር የሆኑት ነገሮች ብቻ ዘላለማዊ ናቸው (ቁጥር 17) ፡፡

1-ዮሐንስ (2፡ 18-27)፡ የእግዚአብሄር በሆኑ ነገሮች ላይ አተኩሩ ምክንያቱም “ የክርስቶስ ተቀዋሚ እየመጣ ስለሆነ “ (ቁጥር 18) ፡፡ ታላቁ የመከራ ቀን እየመጣ ስለሆነ ያ እስከሚሆን ድረስ ብዙ ሰዎች ለእኛ ሐሰተኛ ክርስቶስን መስለዋል ፤ በቁጥር 19 እነዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች (ሐሰተኛ አስተማሪዎች) በቀደመዉ ጊዜ አማኞችን ከእግዚአብሄር እዉነት ዞር በማድረግ መርተዋል ፤ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያን/አማኞች ስለዚህ ነገር አይጨነቁም ምክንያቱም በቅዱሱ ስለተቀቡና ስለ እዉነቱ እዉቀት ስላላቸው (ቁጥር 20) ፡፡

እነዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እግዚአብሄርን ይክዳሉ ኢየሱስ መሲህ እንደ ሆነ ይክዳሉ (ቁጥር 22) ፡፡ ቁጥር (23-24) ይህ እንዴት እንደሚሆን ያስጠነቅቃል ፤ ነገር ግን በኢየሱስ በኩል የዘላለም ህይወት ተስፋ አለን (ቁጥር 25) ፡፡ ዮሐንስ አንባቢዎቹን የተታለሉ እንዳይሆኑ አስጠነቀቃቸው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ ቅባትን ተቀብለናል (ቁጥር 27) ፡፡

መደምደሚያ

ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት በሚኖራችሁ ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ ምን የእግዚአብሄር ምን ደግሞ የእግዚአብሄር ያልሆነ እንደ ሆነ ያሳያችኋል ፡፡ እሱ እንደተመላለሰው በቅባቱ ተመላለሱ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1951.

  2. MacArthur, p. 1951.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1707.

  4. MacArthur, p. 1952.

  5. MacArthur, p. 1951.

  6. MacArthur, p. 1951.

  7. MacArthur, p. 1952.

  8. MacArthur, p. 1953.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዮሐ (2፡ 1-2)አስታራቂ እና አስተሰረዪ ማለት ምን ማለት ነው ? ኢየሱስ ለአብ እንዴት የኛ አስታራቂ እና ስለ ኃጢዓታችን እንዴት አስተሰሪ/ተተኪ ነው ?
  2. ዮሐንስ ኢየሱስን በእዉነት እንደምናዉቀው እንዴት ተናገረ ? ምን ማድረግ ያስፈልገናል ? እዚህ ጋር እየጠቀሰዉ ያለዉ “ የቀድሞው ትዕዛዝ “ ምንድን ነው (1ዮሐ 2፡ 3-7)
  3. እንደ ክርስቲያን ከእግዚአብሄር ስለሚያርቁን የማንወዳቸው ሰዎስት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ምሳ 27፡ 20, ሮሜ 13፡ 14, 1ዮሐ 2፡ 15-16)
  4. ልጁን መካድ (ክርስቶስን) መካድ እንዴት አባቱን (አብን/እግዚአብሄርን) እንድትክዱ ያደርጋችኋል (ዮሐ 8፡ 19, 10፡ 30, 17፡ 1-5, 1ዮሐ 2፡ 22-23, 4፡ 15) ?
  5. 1ዮሐ (2፡ 28-29) ስለ ምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ኤፌ (2፡ 8-9) እና ያዕ (2፡ 18, 26) አንብቡ ፤ እነዚህ ጥቅሶች እርስ በእርሳቸዉ ይጋጫሉ/ይጣረሳሉ ? ለምን ወይስ ለምን አይጣረሱም ?
  6. በ 1ዮሐንስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 John 2:10–11

“The one who loves his brother remains in the light, and there is no cause for stumbling in him. But the one who hates his brother is in the darkness, walks in the darkness,and doesn’t know where he’s going, because the darkness has blinded his eyes.”

ሐዋርያው ዮሐንስ “ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን” በማለት በክርስቶስ ወደ መኖር መሰረቶች ይመለሳል ፡፡ አዎን ይሄ ነው መሰረቱ ! አንተም ክርስቶስን አውቃለሁ ካልክ ህጉን ጠብቅ ፡፡ “ኢየሱስን እናውቃለን !“ እያላችሁ ወንድማችሁን የምትጠሉ ከሆነ ፣ እናንተን ዮሐንስ በጨለማ የሚመላለሱ፣ ውሸታሞች ብሎ ይጠራችኋል ፡፡ እናንተም ጨለማው ማየት ስለከለከላችሁ ወደየት እንደምትሄዱ አታውቁም ፡፡

በታማኝነት “ ወንዲሞቼንና እህቶቼን እወዳለሁ “ ማለት ትችላላችሁ ? ወይም በሆነ ሰው ላይ ጥላቻ ፣ ቅናት ወይም ቂም አለባችሁን ? በታማኝነት መልሱ ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ውስጣችሁን ከከነከኗችሁ ከቆረቋሯችሁ ምናልባት ይህ ጊዜ እግዚአብሔርን ለመፈለግና ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን መውደድን ልትከታተሉ ጊዜው አሁን ነው ፡፡ የሚመራችሁን የእርሱን መንፈስ አድምጡ ፤ ለንስሃና ለይቅርታም ራሳችሁን አዋርዱ ፡፡ በታማኝነት ደግሞም እግዚአብሔርን በመውደድና ከእርሱ ጋር አብሮ በመራመድ ለመኖር ከፈለጋችሁ በህይወታችሁ ውስጥ ጨለማ ስለሆኑት ስለተደበቁት ጉዳዮቻችሁ ግልጽ ሁኑ ፡፡ ጌታ ለህይወታችሁ ነጻነትንና ፈውስን ያደርግ ዘንድ ጨለማውን ሁሉ ወደ ብርሃን አውጡት ፡፡ ያኔ ህጉን ትከተላላችሁ የእግዚአብሔርንም ይቅር ባይ ፍቅር ጥልቀት ታውቃላችሁ ፡፡ ዛሬ በብርሃን ስትመላለሱ ርህራሄን ፣ ትህትናንና ይቅርታን ልበሱ ፡፡

“ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።”

  • 1ኛ ዮሐንስ 2፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤፌሶን 4:31–32 – “መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።”

ቆላስያስ 3:12–13 — “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ ፡፡“

1ኛ ዮሐንስ 2:3–6 – “ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።”