Back To Basics
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Love 1 John 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አሁን በአዲስ ኪዳን ዉስጥ እንደ አጠቃላይ መልዕክት በሚታየዉ እና የመፅኃፍ ቅዱስ አምስተኛ መፅኃፋችንን 1-ዮሐንስ እናጠናለን ፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት ትምህርቱን እያጠናቀቀ ነው ፡፡ አንደኛ ዮሐንስ የሐዋሪያዉ ዮሐንስን ከተሸከሙት ከሰዎስቱ ተከታታይ መልዕክቶች ዉስጥ የመጀመሪያዉ እና ትልቁ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ መልዕክቱ ተልኮ ለነበረዉ የተለዩ ቤተ ክርስቲያንን፣ ስፍራን ወይም ግለሰቦችን ካለዬ ምድቡ/አይነቱ አጠቃላይ መልዕክት ነው ፤ መልዕክቱ ፀኃፊዉን አይለይም ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን ጠንካራ፣ የፀኑ የቀደሙት ምስክርነቶች ደቀ መዝሙሩና ሐዋሪያዉ ዮሐንስ እንደ ሆነ ያሳስባሉ (ሉቃ 6፡ 13) “ በማለት ይገልፃል ፡፡
በቀደመችዉ ቤተ ክርስቲያን ዮሐንስ በጣም ታዋቂ ስለ ነበርበመልዕክቱ ላይ ስሙ መዘርዘሩ አያስፈልግም የሚል አስደሳች ክርክር አለ ፡፡ ማክአርቱር “ እንደ ሐዋሪያ የዮሐንስ ታዋቂነት የሚያውቅ ሰው እና ከሁሉ የላቀ ማንነት ያለዉ ብቻ በግልፅ ራሱን ሳይገልፅ ያለምንም የስልጣን ስህተት ከአንባቢዎቹ ሙሉ መታዘዝን በመጠበቅ መፃፍ እንደሚችል “ ፅፏል ፡፡
መነሻው/ታሪኩ፡ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ያዕቆብ የዮሐንስ ወንድም ነበር ፡፡ ኢየሱስ እነዚህን ወንድማማቾች የዘብዴዎስ ልጆች በማለት (ማቴ 10፡ 2) እና “ የነጎድጓድ ልጆች “ በሚል ስያሜ ጠቅሷቸዋል ፡፡ ዮሐንስ ከጴጥሮስ እና ከያዕቆብ ጋር ከሰዎስቱ ለኢየሱስ በጣም ቅርብ ከሆኑት ወዳጆቹ አንዱ ነበር ( ማቴ 17፡ 1, 26፡ 37) ፡፡ ዮሐንስ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት ላይ የአይን ምስክር እና ተሳታፊ ነበር (1ዮሐ 1፡ 1-14) ፡፡ ከእነዚህ ከሰዎስቱ መልዕክቶች በተጨማሪ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን እና የራዕይ መፅኃፍ ፅፏል ፤ ዮሐንስ ሁልጊዜ ራሱን “ በኢየሱስ የተወደደ ደቀ መዝሙር “ ብሎ ይጠቅሳል ፡፡
1 ዮሐንስ መቼ ተፅፎ እንደ ነበር የሚያመለክት ታሪካዊ አመላካቾች የሉም ፤ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተፃፈ ይመስላል ፡፡ ማክአርቱር “ የቤተ ክርስቲያን ታሪኮች ያለማቋረጥ ዮሐንስን በእድሜዉ መጀመሪያ አካባቢ በእስያ ግዛት በኤፌሶን በብቃት እንደፃፈው እንደሚገልፁ “ ይናገራል ፡፡ አብዛኞቹ ምሁራን ዮሐንስ መጀመሪያ የዮሐንስ ወንጌልን ከዚያም በኋላ በአዲስ ኪዳን ሰዎስቱን መልዕክት በማስከተል ከዚያም በኋላ ከጥቂት አመታት በኋላ ራዕይን እንደ ፃፈ ያምናሉ ፡፡
ምንም እንኳን ዮሐንስ ትልቅ ቢሆንም መልዕክቱን በመፃፍ በአገልግሎት በንቃት አገለገለ ፡፡ ይህን መልዕክት በሚፅፍ ጊዜ ዮሐንስ በዚያ ተጀምረዉ የነበሩትን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች ባገለገለበት በኤፌሶን እየኖረ ነበር ፡፡ ዮሐንስ መልዕክቱን በሚፅፍበት ጊዜ ኤፌሶን የእዉቀት ማዕከል ሆና ነበር ፡፡
ተነስቶ የነበረዉ አንዱ ኃሳብ መመራመር/መፈላሰፍ በመባል ይታወቅ ነበር ፤ ማክአርቱር ምርምር “ ነገሮች በተፈጥሮአቸዉ ክፉዎች እንደ ነበሩና መንፈስ ግን ጥሩ እንደ ነበር እደሚያረጋግጥ “ ፅፏል ፡፡ ከዚህም የተነሳ ምርምር የክርስቶስን ሰዉ መሆን ክዷል ፤ በተጨማሪም ምርምር በመለኮታዊ መገለጥ ላይ የሰዉን ስልጣን ከፍ ያደርጋል ማለትም መፅኃፍት ስልጣን እንዲኖራቸዉ አላደረገም ነበር ማለት ነው ፤ ከዚያ ይልቅም የሰዉ ግንዛቤ የበላይ/ባለ ስልጣን ነበር ፡፡ በአጠቃላይ ምርምር ከሁለቱ በአንዱ ስፍራ ይወድቃል ፤ በመጀመሪያው ስፍራ አንዳንድ ምርምሮች የኢየሱስ አካል እዉነት እንዳልነበር ነገር ግን እዉን ለመሆን የተገለጠ እንደ ነበር ያረጋግጣሉ ፤ በዚህም የተነሳ ዮሐንስ በዚህ ምዕራፍ ገና ከመጀመሪያው ላይ “ ያየነዉን “፣ “ የሰማነዉን “ እና “ በእጆቻችን የዳሰስነዉን “ (ቁጥር 1) የሚለዉን ቃል የተጠቀመው ፡፡ በሁለተኛዉ ስፍራ ደግሞ ሌሎቹ ምርምሮች የኢየሱስ መንፈስ በሰዉ በኢየሱስ ላይ በጥምቀቱ ጊዜ እንደወረደበት እና ሲሰቀል ደግሞ እንደ ተለየዉ ያምናሉ ፤ በምላሹም ዮሐንስ “ በዉኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ በዉኃዉና በደሙ እንጂ በዉኃው ብቻ አይደለም “ (ዮሐ 5፡ 6) ፡፡ የኢየሱስን ሰዉ መሆን በመካድ ምርምር ኢየሱስ የሰዉን ኃጢዓት ዋጋ ለመክፈል ሙሉ በሙሉ ሰዉ ስለሆነ የኢየሱስን ሞት ስርየት ካዱ ፡፡
ለምርምሩ ጥያቄ/ሙግት ምላሽ ማክአርቱር “ የ 1ዮሐንስ አጠቃላይ ጭብጡ ወደ ክርስትና መሰረት መመለስ የሚል እንደ ሆነ “ ተመልክቷል ፡፡ ተገቢ እምነት በክርስቶስ መታዘዝን ያመጣል፤ መታዘዝ ደግሞ ሌሎችን ወደ መዉደድ ይመራል ፡፡ ከዚያም ፍቅር ደስታን ያመጣል ፡፡ ማክአርቱር “ ከክርስቲያን መሰረታዊ መታመን አንፃር የሰዎስቱ ንዑስ ጭብጦች የማያቋራጥ ድግግሞሽ አጠቃላይ ጭብጡን ያጠናክራሉ፡ 1) ደስታ (1ዮሐ 1፡ 4)፣ 2) ጽድቅ (1ዮሐ 2፡ 1) እና 3) ማረጋገጫ (1ዮሐ 5፡ 13) ፤ ለመሰረታዊዉ በመታመን አንባቢዎቹ በኑሮአቸዉ ያለማቋጥ እነዚህን ሰዎስቱን ዉጤቶች እንደሚያገኙአቸዉ “ ይገልፃል ፡፡
ለ 1ዮሐንስ የሜንዲ ስዕል የክርስቶስን ፍቅር እና ስለ እኛ የፈሰሰዉን ደም የሚወክሉ የእስራኤል ሀገር አበባዎች የፀኃይ አይን ቱሊፕ ተብለዉ የሚጠሩ ሰባት አበባዎችን ያሳያል ፡፡ ሰባት የ 1ዮሐንስ ጭብጥ ሙሉ እና ፍፁም ፍቅር ስለሆነ ሙሉና ፍፁም ስዕልን ይወክላል ፤ ለ 1ዮሐንስ ሐረጋችን ፍፁም ፍቅር ነው፡ “ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አዉጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርኃት የለም ፍርኃት ቅጣት አለዉና ፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም “ (1ዮሐ 4፡ 18) ፡፡
ትምህርት
1-ዮሐንስ (1፡ 1-4)፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የነበረው “ የሚለዉ ሐረግ አራቱን ትርጓሜ ሊሆን ይችላልል
- ስለ ክርስቶስ መገለጥ ፡፡
- የክርስቶስ ትምህርቶች ፡፡
- ዘላለማዊ ሕይወት በክርስቶስ መታየቱን ፡፡
- ክርስቶስን ራሱን ፡፡
በመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ዉስጥ ዮሐንስ ለኢየሱስ አገልግሎት የአይን ምስክር እንደ ነበር ያብራራል ፡፡ ዋይርስቤ ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር ሕይወትን እንደተለማመደ እንዲሁም ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ሕይወቱን እንደተጋራ ያብራራል ፡፡ እምነት እና ሕይወት በአንድ ላይ በመጋራት ደስታን ያመጣሉ (ቁጥር 4) ፡፡
1-ዮሐንስ (1፡ 5-10)፡ “ እግዚአብሄርብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም “ (ቁጥር ) ብሎ በማብራራት ዮሐንስ በእግዚአብሄር ሰዎች ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ኃጢዓት እንደሌለ በእግዚአብሄርም በልጁም እንደሌለ ተናገረ ፡፡ ኢየሱስን እናዉቀዋለን የሚሉ ነገር ግን “ በጨለማ የሚመላለሱ “ (ቁጥር 6) ዋሽተዋል ፡፡ በራዕይ ዮሐንስ “ ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው ፤ ይኸውም ሁለተኛ ሞት ነው “(ራዕ 21፡ 8) ፡፡ ኢየሱስን እናዉቀዋለን ብንል ነገር ግን ኑሮአችን በጨለማ መመላለስ ከሆነ በእዉነት ወደ እርሱ ካልተመለስን በቀር በመጨረሻ እግዚአብሄር ይፈርድብናል ፡፡
“ ብንል “ የሚለዉ ሐረግ በቁጥር (6-10) አምስት ጊዜ ተደጋግሟል ፡፡ በቁጥር 6, 8 እና 10 ያለው በእዉነት ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት የሌላቸዉን ሰዎች ያመለክታል ፤ በቁጥር 7 እና 9 ያለዉ ደግሞ በክርስቶስ እዉነተኛ አማኞችን ያመለክታል ፡፡ በብርኃን መመላለስ እና ከሌሎች አማኞች ጋር ሕብረት ጋር ማድረግ ኃጢዓትን የሚያነፃውን በኢየሱስ ያለዉን እዉነተኛ እምነት ያሳያል (ቁጥር 7) ፡፡ ኃጢዓቱን የማይናዘዝ ሰው በኢየሱስ እምነት እንደሌለዉ ያሳያል (ቁጥር 8) ፤ ኃጢዓታችንን ስንናዘዝ ኢየሱስ ይቅር ይለናል (ቁጥር 9) ፡፡ ኃጢዓታችንን የማንናዘዝ ከሆነ ዉሸታም ያደርገናል “ ቃሉም በእኛ ዉስጥ የለም “ (ቁጥር 10) ፡፡
መደምደሚያ
ሁለት የሰዉ ቡድኖች አሉ ፤ የመጀመሪያዎቹ ቡድኖች ኃጢዓተ እንደሌለባቸው ራሳቸዉ የሚጠብቁ ፤ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር በመጋጨት ራሳቸዉን ዉሸታሞች እንደሆኑ ያሳያሉ ፡፡ ሁለተኞቹ ቡድኖች በብርኃን ስንመላለስ እና በእርሱ ነፃነትን ስንመላለስ በሚቀጥል ሂደት ዉስጥ ኢየሱስ ከኃጢዓት እንደሚያነፃን ያዉቃሉ ፡፡ ነፃ እንዲያወጣችሁ ጌታን መጠየቃችሁን ቀጥሉ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1944.
MacArthur, p. 1944.
MacArthur, p. 1944.
MacArthur, p. 1944.
MacArthur, p. 1944.
MacArthur, p. 1945.
MacArthur, p. 1945.
MacArthur, p. 1945-1946
MacArthur, p. 1946.
MacArthur, p. 1946.
Earl Radmacher, et. al., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1704.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 961–962.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዮሐ (1፡ 1) ዮሐንስ “ ከመጀመሪያ “ ብሎ በጠቀሰ ጊዜ ምንን ሊያመለክት ይችላል ? (ዮሐ 1፡ 1, 1ዮሐ 2፡ 7, 24)
-
እግዚአብሄር ለእኛ ራሱን እንዴት ገለጠ ወይም አሳዬ ? (ዮሐ 1፡ 1, 14፡ 9, ሮሜ 1፡ 20, ቆላ 1፡ 15, ዕብ 1፡ 1-3, 1ዮሐ 1፡ 1-2)
-
በክርስቶስ ያለ እምነት እና በክርስቶስ ያለ ፍቅር በእናንተ ዉስጥ ምን ያመነጫል/ያመጣል ? (1ዮሐ 1፡ 4, 2፡ 1, 5፡ 13)
-
ዮሐንስ የተናገራቸው ዉሸታም ሊያደርጓችሁ የሚችሉ ሰዎስት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (1ዮሐ 1፡ 6-10)
-
በ 1ዮሐንስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 John 1:5
“Now this is the message we have heard from Him and declare to you: God is light, and there is absolutely no darkness in Him.”
ዮሐንስ ለአማኞች ወደ እምነታቸው መሰረት እንድመለሱና በእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር እውነት ውስጥ እንድመላለሱ ለመምከር ጻፈላቸው ፡፡ ይህንንም እውነት አካፈላቸው ፡- እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም ፡፡ ክርስትያኖች ከኢየሱስ ጋር ህብረት እንዳለቸው ቢናገሩ ነገር ግን በኃጢአት ቢመላለሱ ፣ እየዋሹ ነው ፡፡ ማንም ከኢየሱስ ጋር ህብረት አለኝ እያለ በጨለማ ቢመላለስ እርሱ እራሱን ያስታል ፡፡ በእርሱም ዘንድ እውነት የለም ፡፡ ነገር ግን ማንም ኃጢአቱን የሚናዘዝ እርሱ ኢየሱስ ይቅር ይል ዘንድ የታመነ መሆኑን ያያል ፤ ኢየሱስም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻዋል ፡፡
ምናልባት “ ኢየሱስ ጌታዬ ነው “ በማለት እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ለማታለል ሞክረህ ይሆናል ነገር ግን በልብህ እየዋሸህ ነው ደግሞም በፍጹም ልብህ እግዚአብሔርን አታምንም ፡፡ የራስህን ዕቅዶች እያወጣህና ለአንተ ብቻ የሚጠቅሙ ምርጫዎችን ብቻ እየመረጥክ ነውን ? ጓደኛዬ በኃጢአትህ በመሸማቀቅ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መኖር አይገባህም ፡፡ በውሸት ምንም የሚገኝ ነገር የለም ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያያል ፡፡ እርሱ የዓለም ብርሀን ነው ፡፡ የክርስቶስ ፍጹም ፍቅር ብርሀን ወደ ጨለማህ ውስጥ ዘልቆ እንድገባ ፍቀድ ፡፡ በቃ የእርሱን ብርሀን ተቀበል ! ዛሬ ኃጢአትህን ተናዘዝ ! ኢየሱስ ይቅር ይልሃል ከኃጢአትህም ያነጻሃል ! ወደ እግዚአብሔር ፊት በሙሉ መሰጠትና ታማኝነት ቅረብ ደግሞም ወደ ብርሀኑ ግባ ፡፡
“ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።”
- 1ኛ ዮሐንስ 1፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 27:1 — “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
ዮሐንስ 8:12 — “ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
1ኛ ዮሐንስ 1:6–9 — “ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።