The Day Of The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Master of Truth 2 Peter 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁለተኛ ጴጥሮስ በአዲስ ኪዳን ከአጠቃላይ መልዕክቶች ዉስጥ አንዱ ሲሆን በ 1ጴጥሮስ ላይ ላሉት ተመሳሳይ ተደራሲያንም የተፃፈ ነው ፡፡ ጴጥሮስ በስደት ላይ በመናገር በ 1ጴጥሮስ እንዴት በአካል እንደሚያዝ /እንደሚደርስ ፅፏል ፡፡ ይህ የጴጥሮስ ሁለተኛዉ መፅኃፍ በመጨረሻዉ ዘመን በኃሰብ እንዴት ስደትን/መከራን እንደሚያዝ ነው ፡፡
በ 1ጴጥሮስ (5፡ 12) ጴጥሮስ ይህንን መልዕክት ሊያበረታቸው እና ይህ እዉነተኛ የእግዚአብሄር ፀጋ እንደ ነበር ሊመሰክርላቸው እንደፃፈው ይናገራል ፡፡ አማኞች ችግር ሲደርስባቸው ጴጥሮስ የእግዚአብሄርን ፀጋ በመያዝ ፀንተዉ እንዲቆሙ አበረታቶአቸዋል ፡፡
በ 2ጴጥሮስ (3፡ 1) ጴጥሮስ የመልዕክቱ አላማ በነቢያት እና በሐዋሪያት ቃል በማስታወስ የላቀ መረዳትን እንዲያሳድጉ አማኞችን መርዳት እንደ ነበር አብራርቷል ፡፡ በመሰረቱ 2 ጴጥሮስ ተፅፎ ስለ ነበር አማኞች ተብሎ/ተነግሮ የነበረዉን እና ስለ አዳኙ ክርስቶስ ተፅፎ የነበረዉን እንደ ገና ይናገራሉ ፡፡
ጴጥሮስ አማኞች በሐዋሪያት እና በነቢያት መሰረት ላይ እንዲፀኑ መርዳት ፈለገ ፤ አማኞች ሐሰተኛ አስተማሪዎችን እና ትምህርታቸዉን መቋቋም እንዲችሉ ፈለገ ፡፡ ተምረዉት የነበሩትን የአንባቢዎቹን አይምሮ ለማደስ እየሞከረ ነበር ፡፡
ትምህርት
2-ጴጥሮስ (3፡ 1-4)፡ በቁጥር 3 ጴጥሮስ እንደ ገና ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ይገልፃል ፡፡ ጴጥሮስ በመጨረሻው ዘመን እንደ ነበሩ በማሰብ በመጨረሻው ዘመን ዘባቾች ይመጣሉ በማለት ተናገረ ፤ ዘባቾች/አሻፊዎች በእዉነት ላይ የሚቀልዱ እና የሚስቁ ነበሩ ፡፡ የሐሰት መልዕክትን የተናገሩ እንደ ራሳቸዉም ፍቃድ የኖሩ ናቸው ፡፡
እነዚህ ዘባቾች እዉነትን ትተዋል/አልተቀበሉም ፡፡ ማክአርቱር የሐሰተኛ ነቢይ እና የሐሰተኛ አስተማሪ መለያ ምልክትን ለይቷል፡ “ 1) የሚያጠፋ ኑፋቄዎችን ያስተምራል (2ጴጥ 2፡ 1)፣ 2) ክርስቶስን ይክዳል (2ጴጥ 2፡ 1)፣ 3) የእግዚአብሄርን ስም/መንገድ ይሳደባል (2ጴጥ 2፡ 2)፣ 4) መፅኃፍን ይጠመዝዛል (2ጴጥ 2፡ 2, 3)፣ 5) ይመኛል (2ጴጥ 2፡ 3, 14)፣ 6) የራሱን ፍቃድ ያደርጋል (2ጴጥ 2፡ 10)፣ 7) ስነ-ምግባር የሌለዉ ነው (2ጴጥ 2፡ 10, 14)፣ 8) ዓመፀኛ (2ጴጥ 2፡ 12, 14)፣ 9) እዉነተኛ እምነትን ወደ ብልሹ ተግባር ያመጣል (2ጴጥ 2፡ 15) እና 10) በክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ላይ ያሾፋል (2ጴጥ 3፡ 4) “ ፡፡ አማኞች ስለ እምነታቸው ይከራከራሉ ፤ ክርክሩ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ባሉት እና ከሐሰተኛ አስተማሪዉቹ ይመጣል ፡፡ በዚህ በመጨረሻው መልዕክቱ የጴጥሮስ ማብራሪያ አማኞች እዉነቱን እንዲያስታዉሱ መፈለጉ ነበር ፤ አማኞች እዉነቱን የሚያስታዉሱ ከሆነ የትኛዉ ትምህርት ሐሰት እንደ ነበር መለየት ይችላሉ ፡፡
ጴጥሮስ በጌታ ቀን የሚመጣዉን ጥፋት ማሳያን/ማመላከቻን ለመስራት ከብሉይ ኪዳን የሆነዉን ጎርፍ ተጠቀመ ፤ ባለፈዉ ጊዜ በዉኃ ሙሉ ጥፋት እንደ ነበር ነገር ግን ቀጣዩ ጥፋት በእሳት እንደሚመጣ ደግሞ ተናገረ ፡፡ የዉኃዉ ማሳያ እና ማመላከቻ በምድር ላይ ሙሉ ጥፋት እንደ ነበር ነገር ግን በዚህ ጊዜ የግል ጥፋትን የማስወገጃ መንገድ እድል እንደ ነበር ለሰዎች ለማሳሰብ ነበር ፡፡ ያ መንገድ በንስኃ ወደ ጌታ በመምጣት ክርስቶስን መቀበል ነበር ፡፡
2-ጴጥሮስ (3፡ 5-18)፡ በ 2ጴጥሮስ 3 የሚመጣ የሌላ ጥፋት ማሳሰቢያ ነበር ፡፡ በቁጥር 7 ጴጥሮስ ይህ ቀጣዩ ጥፋት በእሳት እንደሚሆን ይናገራል ፡፡ ፍርድ በሐሰተኛ አስተማሪዎች እና በማያምኑት ላይ እየመጣ ነበር ፤ እግዚአብሄር በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች እዉነቱን በመያዝ ንስኃ እንዲገቡ ይፈልጋል በማያምኑት ላይ ግን በእግዚአብሄር ጊዜ ጥፋት ይመጣባቸዋል ፡፡ የጌታ ቀን በእግዚአብሄር ጊዜ ይከናወናል ፡፡
ሐሰተኛ አስተማሪ ይህ ጥፋት በፍፁም አይሆንም ይላል ፤ እዉነተኛ አስተማሪ ለክርስቶስ መመለስ ሰዎችን ያዘጋጃል፡፡
በሐዋሪያት ስራ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደበት መንገድ ተመልሶ ወደ ምድር የሚመጣበት መንገድ እንደሚሆን ተነግሯቸዋል ፡፡ የጌታ ቀን እንዲከናወን በኢየሩሳሌም ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ ይገነባል ፡፡ የሰላም ሰባት አመታት ይኖራሉ ፤ ከሰባቱ አመታት ዉስጥ ግማሹ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ራሱን በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በማስቀመጥ አምላክ እንደ ሆነ ያውጃል ፡፡ ሰባቱ አመት መከራ ይሆናል ፤ ምንም እንኳን የምድር ቀጣዩ ጥፋት ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ የሚመጣ ቢሆንም ከሰባቱ አመታት መከራ ዉጪ አይመጣም ፡፡
ስለ ታላቁ መከራ ሰዎስት አመለካከቶች አሉ ፤ ከመከራዉ በፊት የሚለዉን እምነት የያዙት አማኞች ከጥፋቱ በፊት እንደሚነጠቁ ያምናሉ ፤ መከራዉ መካከል ላይ የሚለዉን እምነት የሚይዙት ደግሞ አማኞች ከመጨረሻዎቹ ሰዎስት አመት ከግማሽ ከመከራ አመት በፊት በሰባት አመቱ መካከል ላይ እንደሚነጠቁ ያምናሉ ፡፡ ከመከራዉ በኋላ የሚለዉን አመለካከት የያዙት ደግሞ ከሰባት አመቱ መከራ በኋላ ቤተ ክርስቲያን የተወገደች እንደምትሆን ያምናሉ ፡፡ ታላቁ መከራ የእግዚአብሄር ፍርድ ከሆነዉ ከጌታ ቀን በፊት ይሆናል ፡፡
የጌታ ቀን በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን የተገለፀ ነው ፡፡ ማክአርቱር በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ሁሉንም “ የጌታን ቀን ማጣቀሶች “ ለይቷቸዋል፡ “ የጌታ/የእግዚአብሄር ቀን ፤ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ የጌታ ቀን በግልፅ አስራ ዘጠኝ ጊዜ ተጠቅሷል፡
1. አብድዩ 15 | 6. ኢዩኤል 3:14 | 11. ኢሳይያስ 13:6 | 16. ሕዝቅኤል 13:5 |
2. ኢዩኤል 1:15 | 7. አሞፅ 5:18 | 12. ኢሳይያስ 13:9 | 17. ሕዝቅኤል 30:3 |
3. ኢዩኤል 2:1 | 8. አሞፅ 5:18 | 13. ሶፎንያስ 1:7 | 18. ዘካሪያስ 14:1 |
4. ኢዩኤል 2:11 | 9. አሞፅ 5:20 | 14. ሶፎንያስ 1:14 | 19. ሚልክያስ 4:5 |
5. ኢዩኤል 2:31 | 10. ኢሳይያስ 2:12 | 15. ሶፎንያስ 1:14 |
ማክአርቱር በአዲስ ኪዳን ዉስጥ የጌታ ቀን አራት ጊዜ እንደተጠቀሰ ይናገራል፡ “ አራት ግልፅ የሆኑት የጌታ ቀን መጠቀሶች በአዲስ ኪዳን ዉስጥ፡
1. ሐዋ 2:20 | 2. 1 ተሰሎንቄ 5:2 | 3. 2 ተሰሎንቄ 2:2 | 4. 2 ጴጥሮስ 3:10 |
በቁጥር 11 ጴጥሮስ አማኞችን ለክርስቶስ መምጣት የተዘጋጁ እንዲሆኑ ያበረታታል ፤ የጌታን ቀን መምጣት መፈለግ አለባቸው ፤ እግዚአብሄርን መምሰላቸው ክርስቶስን የሚያንፀባርቅ እና የሚያዘጋጃቸው መሆን አለበት ፡፡
መደምደሚያ
አማኞች በጥንቃቄ እንዲሁም ደግሞ በክርስቶስ ፀጋ እና እዉቀት ያደጉ መሆን አለባቸው ፡፡ አማኞች ዝም ብለዉ ብቻ አይጠብቁም ክርስቶስን መከተላቸዉንም ይቀጥላሉም እንጂ ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ኋላ አላፈገፈገም ፤ እኛ ቤተ ክርስቲያኖች የተዘጋጀን መሆን አለብን ! የእርሱን መምጣት በትህትና በመጠበቅ መፈለግ አለብን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1937.
MacArthur, p. 1942.
3 MacArthur, p. 1942
ጥያቄዎች
-
በ 2ጴጥሮስ 3 መጀመሪያ ላይ ሁለቱንም መልዕክት ጴጥሮስ የፃፈበት ምክንያት ምን ነበር ? ነቢያት የተናገሩት ከእግዚአብሄር እንደ ነበር እንዴት ታዉቁታላችሁ ? (2ጴጥ 1፡ 19-21)
-
በመጨረሻው ዘመን ዘባቾች የሚሉት ነገር ምንድን ነው ? ምን ያደርጋሉ ? እንደ መፅኃፍ ቅዱስ ለዘባቾች እንዴት ትመልሱላቸዋላችሁ ? ( ማቴ 9፡ 28, 24፡ 27, ራዕ 20፡ 4-6)
-
ስለ ክርስቶስ መመለስ ጴጥሮስ ችላ ስላልተባለዉ ነገር ምን አብራራ (2ጴጥ 3፡ 8-9) ? ጌታ ተመልሶ ለመምጣት የሚታገሰዉ ለምንድን ነው ? ጌታስ ወንጌልን ለማን እንድታጋሩት ይጠይቃችኋል ?
-
በ 2ጴጥ (3፡ 11-18) የክርስቶስን ተመልሶ መምጣት ስለ መጠበቅ ስለ ጴጥሮስ ምክር ምን ትላላችሁ ? ( 2ጴጥ 1፡ 5, 10, 15)
-
ክርስቲያኖች በትጋት ሊያደርጓቸዉ የሚገቡ ጴጥሮስ የተቀሳቸዉ ሰዎስት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (2ጴጥ 3፡ 11-18)
-
በ 2ጴጥሮስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Peter 3:17–18
“Therefore, dear friends, since you know this in advance, be on your guard, so that you are not led away by the error of lawless people and fall from your own stability. But grow in the grace and knowledge of our Lord and Savior Jesus Christ. To Him be the glory both now and to the day of eternity. Amen.”
ጴጥሮስ መልዕክቱን ለወንድሞች ስለ ሀሰተኛ ነቢያት በማስጠንቀቅና በሌላ በኩል ደግሞ ጌታ ስለሚመጣበት ቀን በመናገር ይቋጫል ፡፡ ብዙ ሰዎች የገዛ ምኞታቸውን ይከተላሉ ሆኖም ግን አማኞች በጌታ ላይ ካላቸው መሰረት ወደ ውድቀት ሊመሯቸው ከሚችሉ መረን ከሆኑ ሰዎች መጠንቀቅ አለባቸው ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ ለኢየሱስ መምጣት መዘጋጀትና በእውነቱ ላይ መቆም ያስፈልገዋል ፡፡ ጌታ ከመምጣት አይዘገየም ይልቁንም ስለ እናንተ እየታገሰ እንጂ ፡፡ እርሱ ማንም እንድጠፋ አይፈልግም ይልቁንም ሁሉም ንስሀ እንድገቡ እንጂ ፡፡
በርግጥም ጌታ ይመጣል ፡፡ የእርሱንም መምጣት ስትጠባበቁ ፣ በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቁሙ ፡፡ በዙሪያችሁም ያሉትን ሀሰተኛ መምህራን የሚያዩ አይኖች ይኑሯችሁ ፡፡ በእርሱ ላይ በመታመን ኑሩ ! በንጹህ አሳብና በበጎ ህሊና እርሱን ለማወቅ ትጉ ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም ለመኖር የሚገባችሁን ሁሉ አድርጉ ፡፡ በኢየሱስ ስም የሆነ ነገር ማለት እንዳለባችሁ ከተሰማችሁ ፣ በፍቅሩ ኋይል በሉት ፡፡ እድሉንም እንዳታጡ ደፋሮች ሁኑ ፡፡ እውነቱንም ስለምታውቁት በውጭ ባሉት ሀሰተኛ መምህራን ምክንያት እንዳትፈሩ ፡፡ እውነቱንም በማወጅ ሌሎችን ለዘላለም ታደጉ ፡፡ ስለዚህም ዛሬ በእርሱ የጸና የእውነት መሰረት ላይ ቆማችሁ ፣ ለኢየሱስ መምጣት ዝግጁ ሆናችሁ ኑሩ ፡፡
“ እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። “
- 2ኛ ጴጥሮስ 3፡17-18
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤፌሶን 5:15–16 — “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።”
2ኛ ጴጥሮስ 3:8–9 — “እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”
2ኛ ጴጥሮስ 3:13–14 — “ ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።