General Letters 2 Peter

The Judgement Of False Teachers

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Master of Truth 2 Peter 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 677 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጴጥሮስ ለተበተኑት አማኞች ፃፈ ፤ በመከራ/በችግር ዉስጥም ሲያልፉ በሕያዉ ተስፋ በክርስቶስ ላይ እንዲፀኑ አበረታቸው ፡፡ አማኞቹ ተበታትነዉ ስለ ነበር ሐሰተኛ አስተማሪዎች ዘልቀዉ/ሰርገዉ ገብተዋል ፡፡

ኢየሱስ እንደ እዉነት ጌታ ሊገለጥ ችሏል ፡፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች በድብቅ የሚያጠፉ ኑፋቄዎችን እና የእዉነትን ጌታን እንኳን ሳይቀር በመካድ ይመጣሉ ፤ ጴጥሮስ አማኞቹን በአካባቢያቸው ሐሰተኛ አስተማሪዎች በመምጣት በእዉነት ላይ ለመጠየቅ እንደሚሞክሩ መጠበቅ እንዳለባቸዉ ነገራቸው ፤ እነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ጥፋትን ለማምጣት እየሞከሩ ነበር ፡፡

ትምህርት

2-ጴጥሮስ (2፡ 1-2)፡ ጴጥሮስ አማኞች ምን እንደሚመስሉ እንዲያዉቋቸዉ የሐሰተኛ አስተማሪዎችን ባህሪይ አጋራ ፡፡ በ ዮሐ (14፡ 14፡ 6) የተለዬዉ እዉነት ክርስቶስ ነበር ፤ ኢየሱስ “ እኔ መንገድና እዉነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም “ አለ ፡፡መስፈርታቸዉ ኢየሱስ ነበር ፡፡

ዋይርስቤ “ የተጠነቀቅን እንድንሆን እኛን ለማስጠንቀቅ ጴጥሮስ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የእነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች መለያ ሰዎስት እይታዎችን/መለያዎችን እንዳቀረበ “ ይገልፃል ፤ ሐሰተኛ አስተማሪዎችን የሚለዩት ሰዎስቱ መለያዎች ማታለል፣ መካድ እና ስሜታዊነት ነበሩ ፡፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች የአማኞችን ጥቅም በመዉሰድ ሚስጥራዊ ነገሮችን ይጨምራሉ ፤ እነዚህም ትምህርቶች አጥፊዎች ነበሩ ፡፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ሰዎችን ወደ ራሳቸዉ ኃሳብ ለመሳብ ይሞክራሉ ፤ ጴጥሮስ ግን ክርስቶስ እንጂ ሌላ እዉነት እንደሌለ ደግሞ ተናገረ ፡፡

የሐሰተኛ አስተማሪዎች የአስተምሮ ስህተት ክርስቶስን መካድ ነበር ፤ ክህደታቸው በመስቀል ላይ የክርስቶስን መሞት ያካትታል ፤ በተጨማሪም ክርስቶስ ማን እንደ ነበር ይክዳሉ ፡፡ የጴጥሮስ ማስጠንቀቂያ የተጠነቀቁ እንዲሆኑ ነበር ፡፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎቹ ወደ ሰዎቹ ለመድረስ የተደበቀ አቀራረብ ነበራቸው እንዲሁም በግልፅ የተሳሳተም አስተምሮ ነበራቸው ፡፡ የሐሰት ትምህርትን ለመለየት ብቸኛዉ መንገድ እኔ ክርስቶስን ክጃለሁ ? የሚለዉን ጥያቄ የሚጠይቅ መነፅርን መጠቀም ብቻ ነበር ፡፡

ሐሰተኛ አስተማሪዎች ከእዉነት ወደ ክርስቲያኞች ማህበረሰብ የሚያጨናግፍ መዳረሻን ያቅዳሉ ፤ በእዉነቱላይ በዉሸት መጨመርን ይወዳሉ ፡፡

2-ጴጥሮስ (2፡ 3)፡ በቁጥር 3 ሐሰተኛ አስተማሪዎች የተከታዮቻቸዉን ጥቅም በመዉሰድ ከእነርሱ እያተረፉባቸዉ ነበር ፤ የትምህርታቸዉ መሰረት ስስት ነበር ፡፡ ጴጥሮስ እዉነት በሆነዉ በክርስቶስ መነፅር ትምህርቱን ስላልዳኙት ሕዝቡ ለሐሰተኛ አስተማሪዎች እየሰጠ እንደ ነበር አመለከተ ፡፡ ከስስታቸዉ የተነሳ የሐሰተኛ አስተማሪዎቹ ጥፋት እየመጣ ነበር ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ይመጣባቸዋል ፡፡ አማኞች በጌታ ሲያድጉ የአማኞች የመለየት ስሜት/ችሎታ ያድጋል ፡፡ እዉነቱን ማጥናት አስፈለጋቸው የሐሰት ትምህርትን የመለየት ችሎታቸዉ ይጨምራል ፡፡

2-ጴጥሮስ (2፡ 4-8)፡ በቁጥር (4-10) ጴጥሮስ የፍርድ ሰዎስት ምሳሌዎችን ሰጥቷል ፡፡ ኮንስታብል በኃጢዓት ላይ እነዚህን ሰዎስት የፍርድ ማሳያዎችን አቅርቧል፡

  • “ የመጀመሪያዉ ምሳሌው ኃጢዓትን ያደረጉ መለዓክት ሲሆኑ (ቁጥር 4) ይህ ክፉዉ እንዴት እንደሚሰራ ምሳሌ ነው ፤ ሁለተኛዉ ምሳሌዉ የኖኽ ዘመን አለም ሲሆን ይህ ደግሞ የአለም ምሳሌ ነው ፤ ሰዎስተኛዉ ምሳሌ ደግሞ የሰዶምና የጎሞራ ወደ አመድነት መቀየር ሲሆን (ቁጥር 6) የስጋ ምሳሌ ነው “ ፡፡

እግዚአብሄር ባለፉት ዘመናት ፍርድን እና ጥፋትን ስላመጣ ጴጥሮስ ወደ ፊት ምን ሊመጣ እንደሚችል አንባቢዎቹን እነዚህን ማሳያዎች በመጠቀም አስጠነቀቀ ፡፡ ኮንስታብል ያን በሰዎስተኛዉ ምሳሌ ይገልፀዋል፤

“ ሎጥ እንደ ፃድቅ ሰዉ የተገለፀ ነው ፡፡ የዘፍጥረት መግለጫ ሎጥን በአለም ነገር ተፅዕኖ እንደ ተደረገበት የሚያሳይ ይመስላል ፤ እዚህ ላይ ለክፋት የሎጥ ምላሽ ተነግሮናል፡ በክፋዎች ቆሻሻ ባህሪይ እና በክፉ ድርጊት አመፃቸዉ ተጨንቆ ነበር “ ፡፡

2-ጴጥሮስ (2፡ 9-11)፡ በቁጥር 9 ጴጥሮስ እግዚአብሄር እንዴት እግዚአብሄርን በመምሰል የሚኖሩት እንደሚያድን እንደሚያዉቅ ይናገራል ፡፡ በክርስቶስ መልዕክት ላይ በክፋት በሚናገሩ ጊዜም እንኳን የሐሰተኛ አስተማሪዎች ባህሪይ እንደማያስጨንቃቸዉ አመለከተ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ፡

“ ለፍርድ ሁለት የተለዩ ቡድኖች የተለዩ ናቸው፡ በርኩሰት ምኞት የሚኖሩት እና ስልጣንን በንቀት የሚይዙት ፡፡ በራሱ ፍላጎት የሚሰራ፣ የራሱን ፍቃድ የሚያሟላ፡ እነዚህ ቃሎች የሐሰተኛ አስተማሪዎችን ዘዴ እና ባህሪይ ይገልፃሉ ፡፡ ድርጊታቸዉ በድፍረት የታወቀ/የሚደረግ ሲሆን እግዚአብሄርን እና ሰዉን ሁለቱንም በግዴለሽነት ይቃወማሉ “ ፡፡

ሐሰተኛ አስተማሪዎቹ መንገዳቸዉ ትክክል እንደ ነበር የሚያስቡ ይመስላሉ ፡፡

2-ጴጥሮስ (2፡ 12-22)፡ በቁጥር 12 ጴጥሮስ ሐሰተኛ አስተማሪዎችማሰብ ከማይችሉት እንስሳቶች ጋር ያወዳድራቸዋል ፡፡ ስምን በማጥፋት ይናገራሉ በመጨረሻም የጠፉ ይሆናሉ ፡፡ መፅኃፍ እዉነትን እንደ ማይረዱ ይናገራል ፡፡ በቁጥር 13 ጴጥሮስ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለድርጊታቸዉ እንደ ክፍያን መከራ/ችግር ይደርስባቸዋል ፤ በተደበቀ ንግግር በመቅረብ በኢየሱስ ላይ በመናገር ተደስተዋል ፤ ፅድቅ የሌለዉን ተግባራቸዉን በአደባባይ ስፍራ አሳይተዋል ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 4 የጴጥሮስን ቃል፡

“ የሐሰተኛ አስተማሪዎች አይኖች በአመንዝራነት የተሞሉ ነበሩ ፤ ሴቶችን በዝሙት ተመለከቱ ፡፡ ከኃጢዓታቸዉ ማቆም አልቻሉም ምክንያቱም ምኞታቸዉ/ተግባራቸው ልምድ ሆኖ ስለ ነበር ፤ ከዚህም የተነሳ በቤተ ክርስቲያን ያልፀኑትን ነፍሳት አመንዝራነት ተቀባይነት ያለዉ የክርስቲያን ባህሪ እንደ ሆነ በማሳመን ትክክለኛ ወዳልሆነ ወሲባዊ ግንኙነት ሳባቸው “ ፡፡

ፍሬ ኃሳቡ/ጭብጡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ሴቶችን እና ገንዘብን የሚከተሉ እንደ ነበሩ ነበር ፡፡ እዉነትን እና የእዉነት ጌታን የኢየሱስን መንገድ የተዉ ነበሩ ፤ ሐሰተኛ አስተማሪዎች የበለዓምን መንገድ የተከተሉ ነበሩ ፡፡

መደምደሚያ

ሐሰተኛ አስተማሪዎች ባዶ ናቸው ፤ ዉኃ የሌለዉን ምንጭ የሚመስሉ ናቸው ፡፡ ፍርድ ለእነርሱ በተለዬ ይመጣላቸዋል ፤ ይህን የሚመስል ተመሳሳይ ፍርድ እንዳይገጥመን ለማስወገድ ያልተቀደሱ ትምህርቶችን የመለየት ጥበብ ለማግኘት በቃሉ መሆን ያስፈልገናል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament, vol. 2, (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 447.

  2. Wiersbe, pp. 447–448.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 2 Peter, p. 45; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2peter.pdf

  4. Constable, p. 47.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1697.

  6. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, p. 1698.

ጥያቄዎች

  1. 2 ጴጥ (2፡ 1-3) ሐሰተኛ ነቢያቶችን ይገልፃል ፤ ሐሰተኛ ነቢይ አግኝታችሁ ወይም ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ወደ እነርሱ መናገር ችላችሁ ነበር ? አዎ ከሆነ መልሳችሁ ዉጤቱ ምን ነበር ?
  2. በፍቃደኝነት በኃጢዓት ዉስጥ እየኖረ እግዚአብሄር የፍቅር አምላክ ስለሆነ አሁን ሰማይ እሄዳለሁ የሚል ሰዉ ታውቃላችሁ ? 2 ጴጥ (2፡ 4-6) ከዚያ የኃሳብ ሂደት ጋር እንዴት ይጣረሳል /ይጋጫል ?
  3. በ 2ጴጥ (2፡ 9) እንደ ተጠቀሰው እግዚአብሄር እናንተን ከመከራ የታደገባችሁ ጊዜ አለ ? እንዴት አዳናችሁ ?
  4. 2 ጴጥ (2፡ 22) በመፅኃፍ ሌላ የት ስፍራ ይገኛል (ምሳ 26፡ 11) ? ይህን ጥቅስ ለማያምን ሰዉ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  5. በ 2ጴጥሮስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Peter 2:1–2

“But there were also false prophets among the people, just as there will be false teachers among you. They will secretly bring in destructive heresies, even denying the Master who bought them, and will bring swift destruction on themselves. Many will follow their unrestrained ways, and the way of truth will be blasphemed because of them.”

ጴጥሮስ ለአማኞች ሀሰተኛ ነቢያት እንደሚነሱ አስጠነቀቀ ፡፡ ጠላት ማሳቻ መንገዶች አሉት ሀሰተኛ መምህር እስከመሆንም ድረስ ራሱን ይቀያይራል ፡፡ አስታውሱ ኢየሱስ ብቸኛው መንገድ ፣ እውነትና ሕይወት ነው ፡፡ እርሱ ብቻ ነው እውነተኛው መንገድ ፣ ጠባቡ መንገድ እንድሁም ዘላለማዊ ወደ ሆነው ህይወት የሚወስደው መንገድ ፡፡

ሀሰተኛ መምህራን እናንተን በማሳት ደስ ይሰኛሉ ፡፡ ምንዝረኛ አይናቸውም ወደ ኃጢአት ይመለከታል ፡፡ ስስት በሞላበትም ልብ ያባብሏችኋል ያስጎመጇችኋልም ፡፡ ሆኖም ግን ኢየሱስ እንዲህ ብሏል ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ ነው ፣ የሚያልፉበትም ብዙዎች ናቸው ፡፡ ወደ ህይወትም የሚወስደው መንገድ ጠባብ ነው ጥቂቶችም ያልፉበታል ፡፡ ስለዚህም አይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ በማድረግ ፣ ነቅታችሁም ቁሙ ፡፡ ነገር ግን ሀሰተኛ መምህራንን እንዳትፈሩ ምክንያቱም እናንተ በኢየሱስ ኋይል አሸናፊ ስለሆናችሁ ፡፡ እርሱም ይመራችሁ ፣ ያስተምራችሁና በመረዳት ያበረታችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ሰጥቷችኋል ፡፡ አትፍሩ ፣ ነገር ግን ንቁ ፡፡ ወደ ጌታ ቅረቡ እርሱም በመንገዱ ይመራችኋል ፡፡

“ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል ። “

  • 2ኛ ጴጥሮስ 2፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 7:13–14 — “በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ። “

ዮሐንስ 14:6 — “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”

2ኛ ጴጥሮስ 2:13b–14 — “በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዓይኖች አሉአቸው ፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው ። “