Growing In Faith
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Master of Truth 2 Peter 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁለተኛ ጴጥሮስ ለ 1ጴጥሮስ ክትትል ነው ፡፡ ለ 1ጴጥሮስ ቃላችን/ሐረጋችን በመከራ/በችግግር መካከል ላይ ሕያዉተስፋ የሚል ነበር ፡፡ በ 2ጴጥሮስ በኃሸተኛ አስተማሪዎች ላይ እንመለከታለን ለመፅኃፉም ሐረጋችን የእዉነት ጌታ የሚል ነው ፡፡ በ 2ጴጥሮስ (2፡ 1) ጴጥሮስ “ ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ “ በማለት ፅፏል ፡፡ እነዚህ አስተማሪዎች በድብቅ የሚያጠፋ ትምህርት/ኑፋቄን በማምጣት የእዉነትን ጌታን ኢየሱስንም ይክዳሉ ፡፡ እነዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ በተቃራኒ የሚሄዱ ነገሮች ነበሩ ፤ በእነዚህ በኑፋቄዎች ፊት ጴጥሮስ አንባቢዎቹን በእዉነት ጌታ ላይ የተጣበቁ እንዲሆኑ ነገራቸው ፡፡
የ 2ጴጥሮስ ፀኃፊ ከ 1ጴጥሮስ ፀኃፊ ጋር ተመሳሳይ ነበር - በ 1ጴጥሮስ (1፡ 1) ራሱን የለየዉ ስምዖን ጴጥሮስ ፤ በ 2ጴጥ (3፡ 1) ጴጥሮስ ፅፏቸዉ ከነበሩት ይህ ሁለተኛ መልዕክቱ እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡ 2ጴጥ (1፡ 14) እንዴት እንደሚሞት ኢየሱስ እንደነገረዉ ይናገራል (ዮሐ 21፡ 18-19) ፡፡ በቁጥር (16-18) ስምዖን ጴጥሮስ ኢየሱስ በተለወጠበት ተራራ ላይ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበር ይገልፃሉ ፤ እነዚህ ሁሉ የጴጥሮስ የፀኃፊነቱ የዉስጣዊ ማስረጃዎች እያሉም እንኳን ማክአርቱር፡
“ በ 2ጴጥሮስ ፀኃፊ ላይ እና ከሌሎቹ ከአዲስ ኪዳን መፅኃፍት በላይ በመፅኃፍ ሕግ በትክክለኛ ስፍራ ስለመቀመጡ ትችቶች ብዙ ሙግትን/ንትርክን አስነስቷል ፤ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተቀባይነታቸዉን ለመስጠት የዘገዩ ነበሩ ፡፡ 2ጴጥሮስን በስም ኦርጊን ሰዎስተኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እስኪቀርብ ድረስ ማንም የቤተ ክርስቲያን አባት 2 ጴጥሮስን አልጠቀሰም ፡፡ የቀድሞ የቤተ ክርስቲያን ባለታሪክ እሱቤስ ብቻ 2 ጴጥሮስን ከአከራካሪ መፅኀፍቶች ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከ 2ዮሐንስ እና ከ 3ዮሐንስ ጋር በማካተት ዘርዝሮታል “ በማለት ይገልፃል ፡፡
ስለ ፀኃፊው ከሚያወዛግበዉ አካል 1 ጴጥሮስ እና 2ጴጥሮስ የተለያዬ የአፃፃፍ ስልት ስለተጠቀሙ ነው ፡፡ ጴጥሮስ የመጀመሪያ መልዕክቱን በፀኃፊዉ በናሲሞስ አፃፈ ፤ ይሁን እንጂ ጴጥሮስ ሁለተኛዉን መልዕክቱን ራሱ ፅፏል ወይም ደግሞ ሌሌች ፀኃፊዎችን ተጠቅሟል ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ጴጥሮስ በሐዋሪያት ስራ በስብከቱ ላይ የተጠቀመባቸዉን ያልተለመዱ ቃላቶች በ 2ጴጥሮስ ተጠቅሟል ፤ ለምሳሌ “ አገኘ/ታደለ “ የሚለዉን ቃል ጥቅም በ 2ጴጥ (1፡ 2) እና በሐዋ (1፡ 17)፣ “ እግዚአብሄርን መፍራት/መምሰል “ የሚለዉን ቃል ጥቅም በ 2ጴጥ (1፡ 3) እና በሐዋ (3፡ 12) እና “ የዓመፅ ደሞዝ “ የሚለዉን ቃል ጥቅም በ 2ጴጥ ( 2፡ 13) እና ሐዋ (1፡ 18) አወዳድሩ ፡፡
ሌላዉ የሚጋጨዉ/ግራ የሚያጋባዉ ኃሳብ የጴጥሮስ መልዕክቶች ስለ ተለያዩ ጭብጦች ማዉራቱ ነው ፤ ለምሳሌ “ አንዱ መልዕክት ሁለተኛ ምፃቱ/መምጣቱ እንደ ቀረበ ሲያስተምር አንዱ ስለ መዘግየቱ ይናገራል ፤ አንደኛ ጴጥሮስ በተለይም በክርስቲያኖች መከራ ክርስቲያኖችን እንደ ማበረታቻነት የክርስቶስ መምጣት አይቀሬነት ላይ በማትኮር ያገለግላል ፡፡ ሁለተኛ ጴጥሮስ የማይቀረዉ የክርስቶስ ተመልሶ መምጣት ለምን እስካሁን እንዳልሆነ በማብራራት ስለ ዉሸት/ሾፍ ያወራል “ ፡፡ አንዳንድ የ 2ጴጥሮስ ተቺዎች በማስመሰል ሐሰተኛ አስተማሪዎች እንኳን እንደፃፉት ያመለክታሉ ፡፡
የመፅኃፉ ቀን/የተፃፈበት ቀን ከክርስቶስ ሞት 68 በኋላ የኔሮ ሞት ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ የቀደሙት ሰዎች/ታሪኮች ጴጥሮስ በኔሮ የክርስቲያኖች ማሳደድ ጊዜ እንደሞት ከያዙ ምናልባትም ጴጥሮስ 2ጴጥሮስን ከክርስቶስ ሞት (67-68) በኋላ መካከል ፅፎታል ፤ ምናልባትም ጴጥሮስ ከእስር ቤት ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ እያለ ከሮም ፅፎታል ፡፡ ተደራሲያኑ በ 2ጴጥሮስ ይ የተለዩ/የተጠቀሱ ባይሆኑም ግምቱ በ 1ጴጥሮስ (1፡ 1) ተጠቅሰዉ/ተለይተዉ ለነበሩት ተመሳሳይ ተደራሲያን የተፃፈ እንደ ነበር ነው ፡፡
ትምህርት
2-ጴጥሮስ (1፡ 1-3)፡ በቁጥር 1 ጴጥሮስ ራሱን ለክርስቶስ እንደ ባሪያ እና በግላቸዉ ከክርስቶስ ጋር ካገለገሉት ጋር አንድ ሐዋሪያ እንደ ሆነ ለይቷል ፡፡ “ በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነት ላገኙ “ አማኞች ፃፈ ፡፡ እንደ አማኝ የመጀመሪያዎቹ ሐዋሪያት እንዳገኙት ተመሳሳይ ክብር አግኝተናል ፡፡ ቁጥር 2 የተለመደ የክርስቲያን ሰላምታ ነው ፡፡ ኮንስታብል ቁጥር (3-11) “ እንደ ክርስቲያን ሁኔታ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ቁጥር 3 እግዚአብሄር ለእኛ እንደ እግዚአብሄር ኃሳብ እንድንኖር የሚያስፈልገንን ሁሉንም ነገር እንደሰጠን ይገልፃል ፤ በእግዚአብሄር ኃይል በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስፈልገን ሁሉም ነገር አለን ! የክርስቶስ የትንሳኤ ኃይል የሚያስፈልገን ነው (ኤፌ 1፡ 19-20, ፊል 3፡ 10) ፡፡
2-ጴጥሮስ (1፡ 4-7)፡ እዚህ ጋር በእግዚአብሄር መለኮታዊ ኃይል እና በክርስቶስ ትንሳኤ የተሰጠን ኃብት ተሰጥቶናል ፡፡ በመለኮታዊዉ ተፈጥሮ በመጋራት ከአለም መከራ እንድናመልጥ የሚፈቅድልንን ታላቅ እና ዉድ የሆነ ተስፋዎች ተሰጥተዉናል ፡፡ እነዚህ ዉድ ተስፋዎች የኢየሱስን ተልሶ መምጣት እና በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን ያካትታሉ ፤ ያ ማለት አማኞች በመከራ/በችግር ጊዜያት ዉስጥ አያልፍም ማለት አይደለም ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት ዉስጥ ስናልፍ የሚያፀና ሀብት/ምጭ አለን ማለት ነው ፡፡ መጀመሪያ እዉነቱን ካላወቅን የሐሰት ትምህርቶችን መጋፈጥ አንችልም ፡፡ ከዚህም የተነሳ ጴጥሮስ አማኞቹን በበጎነት በመኖር እምነታቸዉን እንዲደግፉ ከዚያም አንዱን በሌላዉ ላይ መንፈሳዊ ባህሪያትን መጨመርን እንዲቀጥሉ ነገራቸው (ቁጥር 5-7) ፡፡ በሜንዲ ስዕል እነዚህ “ ድጋፎች “ በቢራቢሮዎች ዉስጥ የታዩ ናቸው - እምነት በበጎነት፣ በእዉቀት፣ ራስን በመግዛት፣ በትዕግስት፣ እግዚአብሄርን በመምሰል፣ በወንድማማች መዋደድ እና ፍቅር ሊጠነክር ይችላል ፡፡ ኮንስታብል እነዚህን አጋዦች፡
- እግዚአብሄርን መምሰል የሞራል ልቀት ሲሆን አላማችንን ወይም ስራችንን ለመፈፀም የሚደረጉ ነገሮችን በክርስቶስ በትክክል ማድረግን ያካትታል ፡፡
- እዉቀት በቃሉ ዉስጥ የተገለጠዉን መረጃ ማግኘት/ማወቅ ነው ፡፡
- ራስን መግዛት ራስን መቆጣጠር ጭዋ መሆን፣ ሀሳብን እና ፍላጎትን መቆጣጠር መቻል ነው ፡፡
- መጽናት ወይም መትጋት በችግር/በመከራ/በተቃዉሞ ዉስጥ ፀንቶ የመቆም ችሎታ ነው ፡፡
- እግዚአብሄርን መምሰል የእግዚአብሄርን ባህሪይ ማንፀባረቅን/ማሳየትን ያመለክታል ፡፡
- የወንድማማችነት መዋደድ የህብረቱን አማኞች በመልካም አስተሳሰብ ማሰብ/መመልከት ነው ፡፡
- ፍቅር እግዚአብሄር እኛን በወደደን አይነት ከፍተኛ ፍቅርን ያመለክታል (ዮሐ 3፡ 16) ፡፡ በማለት ይገልፃቸዋል፡፡
2-ጴጥሮስ (1፡ 8-11)፡ ይህ ሂደት ታላቅ እምነት እንዲኖረን ይመራናል ፡፡ ይህ እያንዳንዳቸዉን እነዚህን አጋዦች በመዉሰድ ወደ ሌላ አጋዥ መሄድ ከመቻላችሁ በፊት የህይወታችሁ አካል ማድረግ እንዳለባችሁ ይመስላል ፡፡ ይህ የእምነት እድገት አማኞችን ጥቅም የሌላቸዉ ከመሆን ወይም ለክርስቶስ የማያፈሩ ከመሆን ይጠብቃቸዋል (ቁጥር 8) ፡፡ ጴጥሮስ በኑሮአቸዉ እነዚህ ነገሮች የሚያሳድጉትን አማኞች ክርስቶስ በሞቱና በትንሳኤው ከኃጢዓትአት እንዳነፃቸው የረሱ እንደ እዉር እና የሩቁን ማየት የማይችል በማለት ገልፆአቸዋል (ቁጥር 9) ፡፡
መደምደሚያ
ፈተናዎች ወይም መከራዎች ቢኖሩም እንኳን አንተ በኑሮአችን እንዳለህ መመላለስ እንድንችል ጌታ ሆይ እምነታችንን ጨምር ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1924.
MacArthur, p. 1924.
MacArthur, p. 1924.
MacArthur, p. 1925.
MacArthur, p. 1925.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 2 Peter, p. 13; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2peter.pdf.
Constable, pp. 20-21.
ጥያቄዎች
-
እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሕይወትን ለመኖር የሚያስፈልጋችሁ ሁሉም ነገር እንዳላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? ጴጥሮስን ይህን እርሱን ወደ ማወቅ በመጣን ጊዜ እንደተቀበልን ፅፏል (2ጴጥ 1፡ 3) ፤ በግል አስተያየታችሁ ከእነዚህ ነገሮች ዉስጥ ጥቂቶቹ ምን ይሆናሉ ?
-
በ 2ጴጥ (1፡ 5-7) ጴጥሮስ በፀጋ እንድናድግ ሊረዱን የሚችሉ ስምንንት ነገሮችን ዘርዝሯል ፤ እነዚህ ስምንት ነገሮች ምንድን ናቸው፣ እያንዳንዶቹንም እንዴት ትገልፁቸዋላችሁ ?
-
በ 2ጴጥ (1፡ 11) ላይ በማንበብ አሰላስሉት ፤ አዲሱ ሕያዉ ትርጉም “ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግስት መግባትበሙላት ይጣችኋል “ ይላል ፡፡ ያ መፅኃፍ ለእናንተ እንዴት ይናገራችኋል ?
-
በ 2ጴጥ (1፡ 19) ላይ የተጠቀሰዉ የንጋት ኮኮብ ማነዉ ወይስ ምንድን ነው ? በመፅሃፍ ላይ ኢየሱስ እና ሰይጣን ሁለቱም ለምን የንጋት ኮኮብ ተብለዉ ተጠቀሱ ? እንዴት የሚለያዩ ናቸው ? እንደሚያበራ የንጋት ኮኮብ የተጠቀሰው ማንኛዉ ነው ? (ራዕ 22፡ 16)
-
በ 2ጴጥሮስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Peter 1:3–4
“His divine power has given us everything required for life and godliness through the knowledge of Him who called us by His own glory and goodness. By these He has given us very great and precious promises, so that through them you may share in the divine nature, escaping the corruption that is in the world because of evil desires.”
ጴጥሮስ አማኞችን በአዲስ ኪዳን በህግ ሳይሆን በእምነት እንዴት መኖር እንደሚገባቸው መምከሩን ቀጠለ ፡፡ እርሱም የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኋይል ለህይወትና እርሱን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደሰጣቸው አስታወሳቸው ፡፡ ሁሉንም ነገር ! የእግዚአብሔር ተስፋ አማኞች ከክፉ ምኞት ከሚመጣው ጥፋት አምልጠው የመለኮት ባህርይ ተካፋይ እንድሆኑ ያስችላቸዋል ፡፡ ጴጥሮስ አማኞች በእምነታቸው እንድጠነክሩ በመሻት እንዴት እምነታቸውን እንደሚያጠነክሩ አዘዛቸው ፡፡
ምናልባትም የዛሬዋን ጠዋት ልክ እንደ ሌሎች አማኞች ሁሉ እናንተም በኢየሱስ ላይ በመታመን ተነስታችሁ ይሆናል ፡፡ እና አሁን ከተነሳችሁ በኋላ ምንድን ነው የምታደርጉት ? በውስጣችሁ ስላስቀመጠው ኋይል ደግሞም ለህይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ስለሰጣችሁ በጸሎት አመስግኑት ፡፡ በሰማይ የዘላለምን ህይወት ፤ ይመራችሁም ዘንድ የእርሱን ቅዱስ መንፈስ ፤ ለእናንም ያለውን ፍቅር ፤ ሁልጊዜም ከእናንተ የማይለየው ህልውናው እናም ብዙ…. የእግዚአብሔርን ገደብ አልባ የተትረፈረፉ ተስፋዎችን ተቀብላችሁ በእነርሱ ውስጥ እረፉ ፡፡ በማየት ሳይሆን በእምነት በመመላለስ እየጸናችሁ እግዚአብሔር እምነታችሁን በእነዚህ በረከቶች ፡- በበጎነት ፣ በእውቀት ፣ በራስን መግዛት ፣ በመጽናት ፣ እግዚአብሔርን በመምሰል ፣ በወንድማማች መዋደድ እንድሁም በፍቅር እንድደግፍ ጸልዩ ፡፡ እግዚአብሔር በእምነታችሁ እንድታድጉ ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህም ዛሬ በእምነታችሁ ጽኑ ! እግዚአብሔር የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ሰጥቷችኋል !
“ የመለኮቱ ኃይል ፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን ፥ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን ። “
- 2ኛ ጴጥሮስ 1፡3-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ፊልጵስዩስ 3:10 — “ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ ፥ በመከራውም እንድካፈል ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ ። “
ዕብራውያን 11:6 — “ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና ። “
2ኛ ጴጥሮስ 1:5–8 — “ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና ፡፡“
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።