The Role Of The Elders
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Living Hope 1 Peter 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ የጴጥሮስን የመጀመሪያዉን መልዕክት በመጨረስ ወደ ሁለተኛዉ መልዕክቱ እንሄዳለን ፡፡ ለ 1ጴጥሮስ የሜንድ ስዕል ለምዕራፍ 5 የሚያስደንቅ እይታ ነው ፡፡ ጴጥሮስ በክርስቲያን ስደት በመላዉ አካባቢ/ክልል ዉስጥ ተበትነዉ ለነበሩት አማኞች እየፃፈ ነበር ፤ ጴጥሮስ የተሰደዱትን ክርስቲያኖች በነበሩበት ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን መጀመር የሚችሉ አቅም እንዳላቸዉ ቤተ ክርስቲያን ተከይ አያቸው ፡፡ አሳድደዋቸዉ/መከራ ባደረሱባቸዉ የሚደክሙትን/የሚታመሙትን አማኞች በህያዉ ተስፋችን በክርስቶስ ላይ አይናቸዉን እንዲያደርጉ አበረታቸው ፡፡
ትምህርት
1-ጴጥሮስ (5፡ 1-4)፡ ጴጥሮስ በእነዚህ በተተከሉት ቤተ ክርስቲያን ራሱን ከቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጋር በማስቀመጥ ከሐዋሪያነት ይል ራሱን የህብረቱ ሽማግሌ በማድረግ ጠቀሰ (ቁጥር 1) ፡፡ በመጀመሪያ የመሲሁ መከራ ምስክር እንደሆነ እዉቅና በመስጠት “ ሊገለጥ ካለዉ ክብር ተካፋይ የሚሆን እንደ ነበር “ ተናገረ (ቁጥር 1)፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እንደ አንድ ተካፋይ ጴጥሮስ “ በሚመጣው መንግስት በክርስቶስ ዘመን ስለ መካፈል እንደ ተናገረ “ ይገልፃል ፡፡ የጴጥሮስ ትኩረት በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ላይ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቃል በቃል ስማቸው “ ሽማግሌ “ ተብሎ ሊተረጎም ስለሚችለዉ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች የስራ ዘርፋቸዉን ያቀርባል ፡፡ ሽማግሌ ባለ ራዕዮችን እና ጳጳሳትንም ሲያመለክት ኃላፊነታቸው የሚያካትታቸው፡
- ቤተ ክርስቲያንን መመገብ ወይም ደግሞ መጠበቅ (ሐዋ 20፡ 28, 1ጴጥ 5፡ 2)፡ “ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች የእግዚአብሄርን ሕዝብ በተመሳሳይ መንገድ ይመራሉ፡ በግድ ሳይሆን በዉድ/በደስታ…..ይመግባሉ፣ ይጠብቃሉ እንዲሁም ይመራሉ “ ፡፡
- በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ላሉት ሰዎች እንደ አግዚአብሄር ሀሳብ በመኖር ምሳሌ መሆን (1ጴጥ 5፡ 3)፡ “ ክርስቲያን መሪዎች እግዚአብሄር እንዲጠነቀቁላቸዉ ለሾማቸው የአለቃን ሳይሆን የአገልጋይነት ሚና/ስራ ማድረግ/መስራት ያስፈልጋቸዋል “ ፡፡
- ቤተ ክርስቲያንን ማስተዳደር (1ጢሞ 5፡ 17, ቲቶ 1፡ 5) ፡፡
- መስበክ እና ማስተማር (ኤፌ 4፡ 12, 1ጢሞ 3፡ 2, 5፡ 17) ፡፡
- ቤተ ክርስቲያንን መወከል (ሐዋ 20፡ 17) ፡፡
- ለታመሙት መፀለይ (ያዕ 5፡ 14) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ከ 1ጢሞቴዎስ ለሽማግሌነት/ለመሪነት መስፈርቶቹን ያስቀምጣል፡ “ እንከን የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ መልካም ፀባይ ያለዉ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣ የማይሰክር፣ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፣ ገንዘብን የማይወድ፣ የማይጣላ፣ ቤቱን በመልካም የሚያስተዳድር፣ ታዛዥ/ጨዋ ልጆች ያሉት፣ ጀማሪ ያልሆ/አዲስ ክርስቲያን ያልሆነ፣ መልካም ምስክርነት ያለው “ ፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ/መሪ ለመሆን እና ቤተ ክርስቲያንን ለመወከል ትልቅ ጉዳይ ነው ፡፡
ኢየሱስም “ እንደ እረኛ (1ጴጥ 2፡ 25)፣ እንደ መልካም እረኛ (ዮሐ 10፡ 11, 14) እና እንደ ታላቅ እረኛ (ዕብ 13፡ 20) “ የተጠቀሰ ነበር ፤ እረኛዉ መንጎቹን/በጎቹን ያውቃል እነርሱም ድምፁን ያውቁታል ስለ እነርሱም በፍቃዱ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል ፡፡
በቁጥር 4 ጴጥሮስ አለቃዉ/ዋናዉ እረኛ (ክርስቶስ) በሚመለስ ጊዜ ሽማግሌዎቹ የማይጠፋዉን የክብርን አክሊል እንደሚቀበሉ አሳሰባቸው ፡፡ ኮንስታብል አማኞች ሊቀበሏቸዉ የሚችሉአቸዉን አምስት አክሊሎችን አስቀምጧል፡
የማይጠፋ አክሊል - ስርዓት ያለዉ ህይወት ለሚመሩ (1ቆሮ 9፡ 25) ፡፡
የደስታ አክሊል - ስለ ወንጌላዊያን እና ደቀ መዛሙርነት (1ተሰ 2፡ 19) ፡፡
የጽድቅ አክሊል - ለሚወዱት የጌታ መገለጥ ለሚወዱ (2ጢሞ 4፡ 8) ፡፡
የህይወት አክሊል - መከራን ለሚታገሱ (ያዕ 1፡ 12, ራዕ 2፡ 10) ፡፡
የክብር አክሊል - የእግዚአብሄርን መንጋ በታማኝነት ለጠበቁት (1ጴጥ 5፡ 4) ፡፡
እነዚህ አካላዊ አይደሉም ነገር ግን ምሳሌያዊ አክሊል ናቸው ፡፡ ሽማግሌዎች በእነዚህ ሁሉ ምሳሌ መሆን አለባቸው ፡፡
1-ጴጥሮስ (5፡ 5-11)፡ ጴጥሮስ ወደ ጎበዛዝት ሰዎች በመሄድ ለሽማግሌዎች እንዲገዙ አዘዛቸው ፡፡ ሁሉም አማኞች ራሳቸዉን ትህትናን በማልበስ (ቁጥር 5) ከእግዚአብሄር ስር ራሳቸዉን ያስገዛሉ/ያዋርዳሉ (ቁጥር 6) ፡፡ ኮንስታብል “ መልበስ ተብሎ የተተረጎመዉ የግሪክ ቃል አገልጋዮች በዘወትር ልብሳቸዉ ላይ የሚያስቀምጡትን ሽርጥ ከሚያመለክት ቃል የመጣ ያልተለመደ ነው ፤ ይህ ልብስ እነርሱን ለስራ/ለአገልግሎት እንደሚያዘጋቸዉ “ ይገልፃል ፡፡ ጴጥሮስ ጎበዛዝቶችን ክርስቶስ ስለ እነርሱ ስለሚያስብ የሚያሳስባቸዉን በእርሱ ላይ እንዲጥሉት አበረታታቸው ፡፡
ጴጥሮስ “ ..ዲያብሎስ የሚዉጠዉን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ስለሚዞር “ (ቁጥር 8) የተጠነቀቁ እና የነቁ እንዲሆኑ አስጠነቀቃቸው ፡፡ መንቃት እና መጠንቀቅ ሩሱን የሚገዛ መሆን በማለት ወይም “ በስትክክል የሚያስብ ሞኝ/ተላላ ያልሆነ ራሱን የሚገዛ “ እና ሁልጊዜ ንቁ የሆነ ወይም “ በህይወታችን ለመንፈሳዊ ወጥመዶች/መሰናክሎች መንቃት እና እንደማናሰናክል እርግጠኛ የሚያደርጉንን ትክክለኛ እርምጃዎች መዉሰድ “ በማለት ሊተረጎሙ ይችላሉ ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ ሰይጣን ብልጥ እና ጨካኝ ሁለቱንም እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ኮንስታብል አማኞች የሰይጣንን ኃይል አስተዋይ መንፈስ ያላቸዉ ሆነዉ በማክበር ሊቋቋሙት እንደሚችሉ አጠንክሮ ይናገራል ፡፡ ምንም እንኳን ሰይጣን አማኞች በጌታ ሲመላለሱ ለማሳሳት የሚችለዉን ሁሉ ቢያደርግም ጴጥሮስ መከራ ከደረሰባቸዉ በኋላ እግዚአብሄር “ እንደሚያድሳቸዉ፣ እንደሚያቆማቸዉ፣ እንደሚያበረታቸዉ እና እንደሚደግፋቸው “ ተስፋን ሰጠ (ቁጥር 10) ፡፡
መከራን ለመቀበል መጠበቅ እንችላለን ነገር ግን አሸናፊነት/የበላይነት የእግዚአብሄር ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለእግዚአብሄር ቃል አሜን በማለት ምላሽ መስጠት ሁሉም ተናግረዉት የነበረዉ እዉነት እንደ ነበርና ያንንም እዉነት ሰሚዎቹ በተግባር እያስቀመጡ ይፈፅሙት እንደ ነበር የአይሁዶችን የአዋጅ ልምምድ እንደሚያስተጋባ “ ይገልፃል ፡፡
1-ጴጥሮስ (5፡ 12-14)፡ ጴጥሮስ መልዕክቱን መልዕክቱን በስልዋኖስ አፅፎት እንደ ነበርና እነርሱን ለማበርታት እዉነተኛ የእግዚአብሄር ፀጋ እንደ ነበር በመግለፅ አጠቃለለ (ቁጥር 12) ፡፡ በክርስቶስ ፀጋ እንዲቆሙ አበረታቸው ፡፡ “ በባቢሎን ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን “ ምናልባትም በሮም ለነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን የኮድ ስም ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ጴጥሮስ ማርቆስ ዮሐንስን እንደ መንፈሳዊ ልጁ አቀረበው ፡፡ እርስ በእርሳቸዉ በፍቅር ሰላም እንዲባባሉ በማዘዝ አበቃ ፤ እንዲሁም የክርስቶስ ሰላም ከእነርሱ ጋር ይሁን በማለት ጨረሰ ፡፡
መደምደሚያ
ሰዎች በመከራ ጊዜ ዉስጥ በሚያልፉ ጊዜ ሰላም አስፈላጊ ነገር ነው ፡፡ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ እና በአይምሯችሁ እንደ አዲስ ሲያርፍ በሕያዉ ተስፋ ላይ ትጣበቃላችሁ/አጥብቃችሁ ትይዛላችሁ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1688.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Nelson’s Commentary, p. 1689.
Nelson’s Commentary, p. 1689.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 1 Peter, pp. 104-105; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1peter.pdf.
Constable, p. 105.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Nelson’s Commentary, p. 1688.
Constable, p. 108.
Nelson’s Commentary, p. 1690.
Nelson’s Commentary, p. 1690.
ጥያቄዎች
-
በ 1ጴጥሮስ 5 መሰረት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንዴት መስራት አለባቸው ? ለማን ጥቅም ?
-
እግዚአብሄር ስለ ትዕቢት እና ስለ ትህትና ምን ይላል ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ትዕቢትን የት ታዩታላችሁ ?
-
በ 1ጴጥ (5፡ 8) ላይ ዲያብሎስን ከአንበሳ ጋር ለምን እንዳወዳደረዉ ምን ታስባላችሁ (መዝ 17፡ 12, ሕዝ 19፡ 6, አሞ 3፡ 4) ? ይህ እንደ ይሁዳ አንበሳ ከተጠቀሰዉ ከኢየሱስ እንዴት የተለዬ ነው ? (ሆሴ 5፡ 14-15, ሚክ 5፡ 7-9, ራዕ 5፡ 5)
-
በ 1ጴጥሮስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Peter 5:5b–7
“And all of you clothe yourselves with humility toward one another, because God resists the proud but gives grace to the humble. Humble yourselves, therefore, under the mighty hand of God, so that He may exalt you at the proper time, casting all your care on Him, because He cares about you.”
ልክ እግዚአብሔር ክርስቶስን ራሱን ትሁት እንድያደርግና በህይወታችሁ ላይ ዋና እረኛ እንድሆን እንደጠራው ሁሉ እናንተንም ራሳችሁን ትህትና እንድታለብሱና እርሱን እንድታምኑት ይጠራችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ራሳቸውን ከሌሎች እንደሚበልጡ አድርገው የሚያስቡ ፣ በትዕቢት የሚመላለሱ ሰዎችን ይቃወማል ፡፡ ነገር ግን እናንተ በትህትና ስትመላለሱ እግዚአብሔር ጸጋን ይሰጣችኋል ፡፡ ጴጥሮስ አማኞች ራሳቸውን ትሁት እንድያደርጉ ይመክራቸዋል ፡፡ በትህትና በመራመድ ጭንቀቶቻችሁን ሁሉ ለጌታ ስጡትና በእርሱ ፍቅር ውስጥ እረፉ ፡፡
ትህትና እና እምነት ፡፡ ሰይጣን እምነታችሁንና በትህትና የመራመድ ጥረታችሁን ያጠፋ ዘንድ እንደሚያገሳ አንበሳ ዙሪያችሁን ይዞራል ፡፡ እርሱ እንድትታበዩ እና በራሳችሁ እንድትመኩ ፣ እንድትጨነቁና እንድትፈሩ ይፈትናችኋል ፡፡ ስለዚህም በእምነታችሁ መጽናት ይገባችኋል ፡፡ አታስመስሉ ፡፡ በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቁሙ ፤ ምንም ነገር ሳታዩም በእግዚአብሔር ታመኑ ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደሆነ ደግሞም እርሱ ትላንት እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ነገም ሉዓላዊ እንደሆነ እመኑ ፡፡ በትህትና ስትራመዱ ፣ የድያብሎስን ሽምገላ ትቃወሙ ዘንድ እግዚአብሔር ጸጋንና ኃይልን ይሰጣችኋል ፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ ፡፡ በራሳችሁ ራሳችሁን ከፍ ለማድረግ እንዳትሞክሩ ራሱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል ፡፡ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ በእግዚአብሔርም ታመኑ ፡፡
“ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። “
- 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5b-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 3:5–6 — “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”
ሉቃስ 14:11 — “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
1ኛ ጴጥሮስ 5:8–9 — “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።