General Letters 1 Peter

Following Christ While Suffering

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Living Hope 1 Peter 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 674 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጴጥሮስ በጊዜዉ ከኢየሱስ ጋር በብዙ ነገር ዉስጥ አልፏል እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን መሪዎችም እንደ አንዱ ተከስቷል ፡፡ የሐዋሪያት ስራ የመጀመሪያዉ ግማሽ ስለ ጴጥሮስ ሲሆን ሁለተኛዉ ግማሽ ደግሞ ስለ ጳዉሎስ ነው ፡፡ በ 1ጴጥሮስ ጴጥሮስ ከመከራዉ የተነሳ ተበትነዉ የነበሩትን አማኞች ለማበረታታት ፃፈው ፡፡

ትምህርት

1-ጴጥሮስ (4፡ 1-5)፡ ዋይርስቤ ጴጥሮስ “ አንድ ክርስቲያን ህይወቱን ሁሉ እግዚአብሄር የሚፈልገዉ አይነት ለማድረግ ከፈለገ በሕይወት ዘመኑ መለማመድ እንደሚችል “ የገለፀዉን አራት አመለካከቶች ያጠቃልላል ፡፡

የመጀመሪያዉ አመለካከት/አስተሳሰብ “ በኃጢዓት ላይ የተዋጊነት አመለካከት “ ነበር (ቁጥር 1-3) ፤ ጴጥሮስ አንባቢዎቹን ስለ ኃጢዓት የተጠነቀቁ እና የተዘጋጁ እንዲሆኑ ነገራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ጴጥሮስ ክርስቶስ በስጋ መከራን ተቀብሎ እንደ ነበር ነገር ግን ኃጢዓት የሌለበት ሆኖ እንደቆዬ አብራራ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በሰዉ ተፈጥሮ ተቀብሎ ስለ ነበር የክርስቶስ መከራ እዉነት እንደ ነበር “ ያመለክታል ፡፡

ክርስቶስ የኃጢዓትን መያዣ ስላሸነፈው ከሞትን በኋላ ኃጢዓት በእኛ ላይ መያዣ አይኖረዉም ፡፡ ይህ አስተሳሰብ በኃጢዓት ላይ ከእግዚአብሄር ፍቃድ ይልቅ በሰዋዊ ፍላጎታቸዉ ቁጥጥር ስር ከመሆን ይጠብቃቸዋል (ቁጥር 2) ፡፡ ጴጥሮስ ክርስቶስን ሰዎስት ጊዜ ከመካድ ይህን የስጋ ፈተና/ትግል ያውቀዋል ፡፡ ጴጥሮስ ልክ እንደ ጣዖት አምላኪዎች ባልተገባ ባህሪይ እንዳይኖሩ ነገራቸው (ቁጥር 3) ፡፡

1-ጴጥሮስ (4፡ 6)፡ሁለተኛዉ አመለካከት/አስተሳሰብ “ ስለ ጠፉት የታካሚ አመለካከት ነበር “ (ቁጥር 4-6) ፡፡ ጴጥሮስ ልቅ የሆነ ህይወት የሚኖሩት ከእነርሱ ጋር የተለዬ ኑሮ ዉስጥ ባለመግባት የተለዬ ኑሮ በሚኖሩት ላይ እንደሚያሾፉ ተናገረ (ቁጥር 4) ፡፡ ልቅ የሆነ ኑሮን የሚኖሩት፣ የሚያስደስታቸዉን ሁሉ ለማድረግ ነፃ እንደሆኑ የሚያስቡት በእግዚአብሄር ፊት ተጠያቂ ይሆናሉ (ቁጥር 5) ፤ እነርሱን መዳኘት የአማኞች አይደለም ፡፡

በቁጥር 6 ጴጥሮስ “ አሁን ሙታን ስለሆኑት “ ተናግሯል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህ እነማን እንደ ነበሩ አራት የሚሆኑ ማብራሪያዎችን ያቀርባል፡

  1. አንዳንዶች ይህን ፅሁፍ በ 1ጴጥ (3፡ 19-20) የክርስቶስ አዋጅ ከሆነዉ ጋር በማገናኘት “ ይህ ጥቅስ ከክርስቲያን ዘመን በፊት ለኖሩት የክርስቶስ የድነት መስዋዕት እንደሚሆን ይረዳሉ “ ፤ ይህ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የወደቁት መለዓክት ድነትን እንደተቀበሉ እንደሚያመለክት ኃሳብ ያቀርባሉ ፤ ይህንን የሚደግፍ መፅኃፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የለም ፡፡

ሌሎች ደግሞ ይህን ፅሁፍ በ 1ጴጥ (3፡ 19-20) የክርስቶስ ንግግር ከሆነዉ ጋር በማገናኘት ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ፃድቃን ለነበሩት ሰብኳል የሚለዉን ሀሳብ ይቀበላሉ ፡፡

ሌሎች ደግሞ ጴጥሮስ የኢየሱስን ስብከት ሰምተዉ የነበሩትን ነገር ግን አሁን ሞተዉ ስለ ነበር በሰማይ የነበሩትን እያመለከተ እንደ ነበር ያምናሉ ፡፡

ሌሎች ደግሞ አሁንም ጴጥሮስ በመንፈሳዊ ነገር ሞተዉ የነበሩትን እያመለከተ እንደ ነበር ያምናሉ ፤ ምናልባትም የመጨረሻው ትርጓሜ በደንብ ተገቢ ትርጓሜ ነው፡ “ ወንጌል ለእነርሱ ተሰብኮላቸዉ ስለ ነበር በመንፈስ ወደ ህይወት ሊመጡ ቻሉ “ ፡፡

1-ጴጥሮስ (4፡ 7)፡ሰዎስተኛዉ አመለካከት/አስተሳሰብ “ ስለ ክርስቶስ ተስፈኛ የሆነ አመለካከት ነበር “ (ቁጥር 7)፡፡ ጴጥሮስ የዘመኑ መጨረሻ ስለቀረበ የተጠነቀቁ እና ስርዓት ያላቸዉ እንዲሆኑ ፃፈ (ሮሜ 13፡ 12, 1ተሰ 1፡ 10, ያዕ 5፡ 7-8, 1ዮሐ 3፡ 3, ራዕ 22፡ 20) ፡፡ ክርስቶስ በማንኛዉም ጊዜ ሊመጣ ስለሚችል ተጠንቅቀን የተቀመጥን መሆን ያስፈልገናል ፡፡

1-ጴጥሮስ (4፡ 8-9)፡አራተኛዉ አመለካከት/አስተሳሰብ “ ስለ ቅዱሳን ከፍ ስላለ የፍቅር ግንኙነት ነበር “ (ቁጥር 8-11) ፡፡ ጴጥሮስ አንባቢዎቹን ፍቅር ብዙ ኃጢዓትን ስለሚሸፍን እርስ በእርሳቸዉ ከፍ ያለ ፍቅር እንዲኖራቸዉ አዘዛቸው (ቁጥር 8) ፡፡ ሌሎች ቅዱሳን እንኳን በቅድስና ባይሆኑም አማኞች አሁንም ይቅርታ ሊያደርጉላቸዉ እና ሊወድዷቸዉ የተጠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ሁልጊዜ ለማድረግ ቀላል አይደለም (ምሳ 10፡ 12) ፡፡ ጥላቻ ፀብን ታስነሳለች ፍቅር ግን ፀብን ሁሉ መሸፈን ትችላለች ፡፡ ጳዉሎስ እንግዳ ተቀባይነትን ሌሎችን ከልብ የመዉደድ አንዱ መንገድ በማድረግ አካትቶታል (ቁጥር 9) ፡፡

1-ጴጥሮስ (4፡ 10-11)፡ ይህም ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ዉስጥ አንዱን እንግዳ ተቀባይነትን ይጠቅሳል ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች በሮሜ (12፡ 3-9)፣ 1ቆሮንቶስ 12 -14 እና ኤፌ (4፡ 1-16) የተጠቀሱ ናቸው ፡፡ ጴጥሮስ አማኞች ማንኛዉንም ስጦታ ይቀበሉ ሌሎችን ለማገልገል ሊጠቀሙባቸዉ እንደ ነበር ጽፏል (ቁጥር 10) ፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ስጦታዎች በኑሮአችን የእግዚአብሄር ፀጋ ምስል ናቸው ፡፡ በቁጥር 11 ላይ ጴጥሮስ በስጦታዎች ላይ መፃፉን በመቀጠል አማኞች እግዚአብሄር ለሰጣቸዉ ስጦታዎች ባላደራ እንደ ነበሩ ያብራራል ፡፡

መደምደሚያ

የምዕራፉ የቀረዉ ክፍል በመከራ መካከል ዉስጥ እንዴት ክርስቶስን መከተል እንዳለ ትዕዛዝን ይሰጣል ፡፡ እግዚአብሄር በምናደርገዉ ሁሉም ነገር ይከብራል ፤ የተሰጡን እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች በክርስቶስ ለእግዚአብሄር ክብርን ያመጣሉ ፡፡

  1. Warren W Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians–Revelation (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 419.

  2. Wiersbe, p. 419.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1686.

  4. Wiersbe, p. 420.

  5. Nelson’s Commentary, p. 1686.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1686.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1686.

  8. Nelson’s Commentary, p. 1686.

  9. Wiersbe, p. 421.

  10. Wiersbe, p. 422.

ጥያቄዎች

  1. 1 ጴጥ (4፡ 1) አንብቡ ፤ “ በስጋ መከራን የተቀበለ ኃጢዓትን ትቶአልና “ የሚለዉን ፅሁፍ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ይህ እግዚአብሄር ለእኛ እንዴት አሳዬ ? (ሮሜ 5፡ 8)
  2. በመጨረሻዉ ዘመን ክርስቲያኖች እና ክርስቲያን ያልሆኑት ሁለቱም በእግዚአብሄር ይዳኛሉ/ይፈረድባቸዋል ? ስላደረጋችሁት ሁሉም ነገር እና ስላላደረጋችሁት ስለ ሕይወታችሁ መግለጫ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ ?
  3. በ 1ጴጥ (4፡ 5-6) ጴጥሮስ ስለ ማን እያወራ ነበር (1 ተሰ 4፡ 13-17) ? ይህ ከእናንተ በፊት አረፍዉ/ሞተዉ ስለ ነበሩት እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል ? ይህ የምትኖሩበትን መንገድ እና አሁን ለክርስቶስ መልስ አሰጣጣችሁን እንዴት ይቀይረዋል ?
  4. የነገሮች ሁሉ መጨረሻ እንደቀረበ አድርገን እንዴት እንኖራለን/እነሰራለን (1ጴጥ 4፡ 7-11) ? ለምን ?
  5. እግዚአብሄር ለእናንተ ምን ስጦታን ሰጣችሁ ? እንዴትስ እየተጠቀማችኋቸዉ ነዉ ለራሳችሁ ጉዳይ ነዉ ወይስ ለሌሎች ጥቅም ?
  6. በ 1ጴጥሮስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Peter 4:7–8

“Now the end of all things is near; therefore, be serious and disciplined for prayer. Above all, maintain an intense love for each other, since love covers a multitude of sins.”

ጴጥሮስ በቀጥታ ፡- የነገር ሁሉ መጨረሻው ቀርቧል በማለት ይናገራል ፡፡ ኢየሱስ አዳኛችሁ ይመጣል ፡፡ በመጠን ለመኖርና በጸሎት ለመትጋት ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ከሁሉም አብልጣችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ፡፡ ፍቅር የኋጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ፡፡ በመጨረሻም ጸልዩ ሌሎችንም ውደዱ ፡፡ ለምንድን ነው ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በፊት ምንም የሚባክን ትርፍ ጊዜ የሌለው ?

መጸለይ እንዳለባችሁ ማወቅ ቀላል ነገር ነው ፡፡ ነገር ግን በትክክል ያለማቋረጥና በትኩረት መጸለይ ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው ፡፡ ዓለም ብዙ የሚያዋክቡ ጉዳዮች አሏት አይደል ? “ውይ ይህን መልዕክት መላክ አለብኝ ፤ ቶሎ ብዬ ልብስ ማጠብ አለብኝ ፤ ቆይ ይሄን መልዕክት ላረጋግጥ ፤ አሁን እኮ ልጅ ወለድኩኝ ልክ እሷ መዋለ ህጻናት ስትገባ የጸሉት ቡድኑን እቀላቀላለሁ! ” ጓደኞቼ ምንም አይነት ምክንያት አያስፈልግም ፡፡ ቆፍጠን ለማለት ለመወሰን ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ወደ ጌታ ፊታችሁን መልሱና ጸልዩ ፡፡ በጸሎታችሁም ሌሎችን አብዝታችሁ መውደድ እንድትችሉ ኃይልን እንድሰጣችሁ ለምኑ ፡፡ ጥልቅ ፍቅር የሚገኘው ከክርስቶስ ጋር በመኖር ነው ፡፡ አዎን መጀመሪያ የሚያስፈልጋችሁ ፍቅሩን መቀበልና በፍቅሩ ማረፍ ነው ፡፡ ከዚያ ሌሎችን መውደድ ፣ ሌሎችን ይቅር ማለት እናም ሌሎችን ያለምንም ስስትና ራስወዳድነት ማገልገል ትችላላችሁ ፡፡ እናም ፍቅር ይህ ዓለም የሚያስፈልገው ነገር ነው ፡፡ እናም እርሱ ፈጥኖ ስለሚመለስ ዛሬ ይህን አይነቱን ፍቅር መኖር ትችሉ ዘንድ ኃይል እንድሰጣችሁ እርሱን በጸሎት ለምኑ ፡፡ በቂምና በትንንስ ጉዳዮች ላይ ለመባከን ምንም ጊዜ የለም ፡፡ በመጠን ኑሩ ጸልዩም ፡፡ እርስ በእርሳችሁም ተዋደዱ ፡፡

“ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፥ ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ ። “

  • 1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤፌሶን 6:18 — “ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ ፡፡“

1ኛ ጴጥሮስ 4:11 — “ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።

ራዕይ 22:20 — “ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።”