Evangelism Of Submission
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Living Hope 1 Peter 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በአጠቃላይ መልዕክት (በአዲስ ኪዳን በጳዉሎስ ባልተፃፉት መልዕክቶች) ላይ ጉዞአችንን ቀጥለናል ፡፡ እስካሁን ዕብራዉያንን እና ያዕቆብን አጥንተናል አሁን ደግሞ በ 1ጴጥሮስ ላይ ነን ፡፡
ጴጥሮስ ከስደቱ/ከመከራዉ የተነሳ ተበትነዉ ለነበሩት ጊዜአዊ ነዋሪዎች ይናገራል ፤ አብዛኛዉ 1 ጴጥሮስ መከራን ስለ አያያዝ ሲሆን የመፅኀፉ ጥብጥ ደግሞ ሕያዉ ተስፋ የሚል ነው (1ጴጥ 1፡ 3) ፡፡
ትምህርት
1-ጴጥሮስ (3፡ 1-6)፡ “ በተመሳሳይ መንገድ/እንዲሁም “ (ቁጥር 1) የሚለዉ ሐረግ በ 1ጴጥ (2፡ 13-15) እንዴት ዜጎች መንግስት እና ቀጣሪዎች ከተቀጣሪዎቻቸዉ ጋር እንዴት ይገናኙ በነበረዉ ላይ ይገነባል ፡፡ ኮንስታብል “ መታዘዝ የሑሉም ክርስቲያን ባህሪይ/መገለጫ መሆን አለበት ፤ (ለመታዘዝ) ሆፑታስ የሚለዉ የክሪክ ቃል በምንም አይነት የሰዉ የበታችንት ሳይሆን የእግዚአብሄርን ፍቃድ ስርዓት የመጠበቅ እይታ እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡ መታዘዝ በክርስትና ሕይወት በቅደም ተከተል መቀመጥ/መሆን ማለት እንጂ ወንድን ወይም ሴትን ማሳነስ ማለት አይደለም፡፡ ይህ የማያምኑ ወንዶችን አግብተዉ የነበሩ ሚስቶች ከሚስቶቻቸዉም ተግባር የተነሳ ባሎቻቸው ወደ ወንጌል የተሳቡ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሚደርስ/የሚናገር ነው ፡፡
ኮንስታብል መታዘዝ አራት ነገሮችን እንደሚያካትት ያጋራል ፤ “ መጀመሪያ አመለካከትን ለእግዚአብሄር በማስገዛት ይጀምራል (2፡ 23-25) ፤ የህይወታችን ትኩረት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መሆን አለበት ፡፡ ሁለተኛው መታዘዝ የሚያከብር ባህሪን ይፈልጋል (ቁጥር 1-2) ፤ ጭቅጭቅ የማክበር ባህሪይ አይደለም ፡፡ ሰዎስተኛ መታዘዝ እግዚአብሄራዊ የሆኑ ባህሪያት በማሳደግ ዉስጥ ይከናወናል (ቁጥር 3-5) ፡፡ አራተኛ መታዘዝ ትክክል የሆነዉን ማድረግን ያካትታል (ቁጥር 6) ፡፡ “
ከሚስት አንፃር መታዘዝ በባል መሪነት እና ቁጥጥር ስር ራስን ማስቀመጥ ነው ፡፡ በሚስት የመታዘዝ ኑሮ ዉስጥ ባል ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ኑሮ የሚፈተን ነው ፤ ይህም የወንጌል አካል ነው ፡፡ ምናልባትም ይህ በመፅኃፍ ላይ መፅኃፍ ቅዱስ ስለ እምነታችን እንዳንናገር ከዚያ ይልቅ እንድንመላለስበት የሚያዘን ብቸኛዉ ስፍራ ይሆናል ፡፡ ይህ ሌሎችን “ በፍርኃት ያለዉን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው” (ቁጥር 1-2) ፡፡
ዋይርስቤ ለመታዘዝ ሰዎስት ቁልፎቻችንን ያመለክታል፡ “ መታዘዝ ግዴታ ነው (ቁጥር 1) “፣ “ መታዘዝ እድል ነው (ቁጥር 1-2) “ እና “ መታዘዝ ጌጥ ነው (ቁጥር 3-6) “ ፡፡ ቁጥር (3-4) ዉበት ከዉጫዊ ጌጣጌጥ እንደማይመጣ ነገር ግን በዉስጥ ለእግዚአብሄር ካለ ልብ እንደሚመጣ ይገልፃል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የይበላሽ ጥራት “ (ቁጥር 4) የሚለዉን ሐረግ “ ልክ እንደ ሜካፕ፣ እንደ ጌጥ እና እንደ ልብስ በሚደበዝዝ ወይም በሚበሰብስ ላይ ሳይሆን በዉስጠኛው ጥራት ላይ እንዲሚሳተፍ “ ይገልፃል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ ክርስቲያን ሚስቶች የግል መብትን የማይጠይቁ አመለካከቶችን፣ የተረጋጋ እና የሚያረካ እንጂ የሚረብሽ እና የሚጎዳ አመለካከት ማሳየት እንዳልነበረባቸው “ ይናገራል ፡፡ በዉስጣዉ ማንነታችን በምንሰራ ጊዜ እግዚአብሄር ለሚስቶች በወንጌል ከዚህ አለም ጋር በተለይም ከባሎች ጋር መገናኘት እንዲችሉ ይከፍትላቸዋል ፡፡
ቁጥር 5 መልሶ ከመፅኃፉ ጭብጥ ኢየሱስ ህያዉ ተስፋ ነዉ ከሚለዉ ጋር ይገናኛል፡ “ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሄር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመዉ ነበርና “ ፡፡ እግዚአብሄር ክርስቶስን ለትዳር ባዘጋጀዉ /በሰራው ስርዓት በትዳር ዉስጥ እንዲያሳይ ሰዉን ሰራው ፡፡ ጴጥሮስ ጰሳራን እና የአብርኃምን ማሳያ ሰጠ - ሳራ ለእርሱ አክብሮታን ለማሳየት አብርኃምን እንደ “ጌታዋ “ እንደምትጠቅሰው ፡፡ ለባለቤቶቻቸው መታዘዝን በማሳየት ሚስቶች የሳራ ልጆች እንደ ነበሩ አሳይተዋል (ቁጥር 6) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ በመታዘዝ መከራን እንዴት እንደሚደርስ ብዙ ምሳሌዎችን ይሰጣል፡
- ሳራ ሚስት ለባልዋ ልጅ በመዉለድ መስጠት እንዳለባት ይህን ኃላፊነት በራሷ ላይ ወሰደች ( ዘፍ 16፡ 2-4) ፤ ምንም እንኳን የእግዚአብሄር እቅድ ባይሆንም አብርኃምን ለማገልገል በዚህ መሪነትን ወሰደች ፡፡
እሱ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ቢወስዳትም ሳራ አብርኃምን ተከተለችዉ (ዘፍ 12፡ 15, 20፡ 2) ፤ በመታዘዝ ለአብርኃም አክብሮቷን እና ለእግዚአብሄር መመሪያ መታመኗን አሳየች ፡፡
ለባሏ ራሷን የምታስገዛ ሚስት መመልከት አንድን ባል በተመሳሳይ ራሱን ለክርስቶስ ለማስገዛት እንዲፈልግ ይመራዋል ፡፡
1-ጴጥሮስ (3፡ 7)፡ ይህ ጥቅስ እግዚአብሄር ለእርሱ መታዘዛቸዉን እንዴት እንደሚባርክ ለባሎች ሊያረጋግጥ ይችላል ፤ ጴጥሮስ በቁጥር (1-2) ሚስቶችን እንዳዘዘዉ “ በተመሳሳይ መንገድ “ ለባሎች ትዕዛዝን በመስጠት “ ደካማ ተፈጥሮአቸዉን በመረዳት የህይወትን ፀጋ እንዲካፈሉ አክብሮትን እንዲያሳዩአቸዉ “ አዘዛቸው ቁጥር 7) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ አንድ ክርስቲያን ባል በኃይለኛዉ በመቅረብ የሚስቱን ፍላጎት፣ ጥንካሬዋን እና ድክመቷን፣ አላማዋን እና ምኞቷን ማወቅ አለበት ፤ በተሻለ መንገድ ለእርሷ ምላሽ ለመስጠት በተቻለ መጠን በሚገባ ስለ እርሷ ማወቅ አለበት “ ፡፡ ጴጥሮስ ሴቶችን እያዋረደ አልነበረም ነገር ግን የተወደዱ እንዲሆኑ ለባሎቻቸዉ እንዲገዙ አደረጋቸው ፤ ይህ ስለ መቆጣጠር አይደለም በጌታ ሚስቶቻቸዉን ስለ ማክበር ነዉ እንጂ ፡፡ በቁጥር 7 መሰረት ሚስቶች የማያከብሩ እና የማያገለግሉ ከሆኑ የባሎች ፀሎት የተከለከለ ይሆናል ፤ ሚስቶች በመንግስቱ እንደ አብሮ ወራሽ ሲታዩ እግዚአብሄር የባሎችን ፀሎት ያከብራል /ይመልሳል ፡፡ ጴጥሮስ በሚገባ ለቤተሰቦቻቸዉ አባላት የሚጠነቀቁ በእግዚአብሄር መንግስት ላይ ሌላ ኃላፊነትን መዉሰድ እንደሚችሉ ወደሚለዉ ኃሳብ የሚሳብ ይመስላል ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ ማብራሪያዉን ከባለቤቶቻችን ጋር ስለ ግንኙነታችን በጥናት ጥያቄዎች ይደመድማል፡
አጋሮች ነን ወይስ ተፎካካሪዎች ?
በተሻለ መንፈሳዊ ለመሆን እርስ በእርስ እየተረዳዳን ነው ?
በዉጫዊዉ ወይስ በዘላለማዊዉ ላይ የተደገፍን ነን ? በእዉነተኛዉ ወይስ በአርቲፊሻል ? በተሻለ እርስ በእርስ እንረዳዳለን/እንግባባለን ?
ለእያንዳንዳችን ስሜት እና ኃሳብ እንተሳሰባለን፣ አንድኛችን ለአንድኛችን ዋስትናስ እንወስዳለን ?
እግዚአብሄር ፀሎታችንን ሲመልስ ስናይ እንተያያለን ?
ከትዳራችን የተነሳ በልፅገናል ወይስ የእግዚብሄርን በረከት እርስ በእርስ እንዘራረፋለን ?
መታዘዝ ለእግዚአብሄር ራሳችንን ከማሳመን/ከመታመን አመለካከት ይጀምራል ፤ ያም በክርስቶስ ማን እንደሆንን በሆነዉ ማንነታችን ላይ የተደገፈ ነው ፡፡ በእርሱ ካልሆንን በቀር በፍፁም የጋብቻን መታዘዝ/መገዛት ቀጣዩን እርምጃ መዉሰድ አንችልም ፡፡ የክርስቶስ በሆንን ጊዜ ከባለቤታችን ጋር ከበሬታ የሞላበት ግንኙነት ይኖረናል ፤ በመለኮታዊነት ስለሚሆን የእግዚአብሄራዊ ባህሪያት ማደግን ያካትታል ፡፡ እዉነተኛ መታዘዝ እንዲሆን ትክክል የሆነን ማድረግ አስፈላጊ ነው ፡፡
መታዘዝ ሆን ተብሎ እግዚአብሄራዊ በሆኑ ባህሪያት ላይ መስራትን ይጠይቃል ፤ ከዚያ ዉጪ ሊሆን አይችልም ፡፡ ያንን በክርስቶስ ባለን ሕያዉ ተስፋ ብቻ ማድረግ እንችላለን ፡፡
Gerhard Delling, Theological Dictionary of the New Testament, s.v. “hypotasso”, 8 (1972 ): 44; referenced in Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): 1 Peter, p. 64; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1peter.pdf.
Constable, pp. 66-67; adapted from Family Life Conference (Little Rock, AR: Family Ministry, 1990), pp. 105–106.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1 Peter (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), pp. 408–409.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1683.
Nelson’s Commentary, p. 1683.
Nelson’s Commentary, p. 1683.
Nelson’s Commentary, p. 1684.
Nelson’s Commentary, p. 1683.
Wiersbe, p.411.
ጥያቄዎች
-
1ጴጥ (3፡ 1-2) ሲታነቡ ለቃሉ የማይታዘዝ ባል እንዴት የተሸነፈ/የሚታዘዝ ይሆናል ?
-
1ጴጥ (3፡ 3) ሚስቶች ፀጉራቸዉን መሰራት ወይም የወርቅ ጌጣጌጥ ማድረግ ወይም በደዚህ መንገድ መልበስ የለባቸዉም እያለ ነው ? አይደለም ካላችሁ ምን እያለ/ማለቱ ነው ?
-
በ 1ጴጥ (3፡ 5-6) መሰረት ሚስቶች በፍርኃት ለባሎቻቸዉ ታዛዥ መሆን ያለባቸዉ ለምንድን ነው ? የባል/የሚስት ግንኙነት ምን መምሰል አለበት፣ ግንኙነቱስ እንዴት ጴጥሮስ የጠቀሰዉን ፍራት እንዴት ያጠፋዋል ? (ኤፌ 5፡ 25-33)
-
በ 1ጴጥ (3፡ 8-13) ጴጥሮስ የሆነ ነገርን ሰበከ/ተናገረ ፤ ያለዉ/የተናገረዉ ነገር እንዴት ወደ አንድነት እና የተበሳጨ/የተናደደ ወደ አለመሆን ያመለክታል ?
-
በ 1ጴጥ (3፡ 14-17) ስለ ፅድቅ ስንል መከራን እንዴት እንታገሳለን/እንይዛለን ? (ሐዋ 5፡ 41)
-
በእናንተ ዉስጥ ስላለዉ ተስፋ ምላሽ ለመስጠት ራሳችሁን እንዴት ታዘጋጃላችሁ ? (1ጴጥ 3፡ 15)
-
በ 1ጴጥሮስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Peter 3:4
“Instead, it should consist of what is inside the heart with the imperishable quality of a gentle and quiet spirit, which is very valuable in God’s eyes.”
ጴጥሮስ አማኞች በመከራ ጊዜያት በኢየሱስ ህያው ተስፋ ላይ ጸንተው እንድቆሙ መከራቸው ፡፡ እርሱም በመጀመሪያ በክርስቶስ ዘንድ እነርሱ ማን እንደሆኑ አስረግጦ ከነገራቸው በኋላ ስለ መታዘዝ ጻፈላቸው ፡፡ እነርሱ በክርስቶስ የተመረጡ ነበሩ ፤ የእግዚአብሔር አሳብ ያለባቸው ደግሞም በትልቁ የእግዚአብሔር ንብረት ተብለው የተጠሩ ነበሩ ፡፡ ይህንን እንደ መነሻ በመጠቀም ፣ ጴጥሮስ አማኞችን ጥሪያቸውን በመልካም ባህሪና በቅድስና እንድፈጽሙ ይጠይቃቸዋል ፡፡ ጴጥሮስ በዓለም ያሉት ለክርስቶስ ተሰብከው ሳይሆን ንጹህና ፍርኀት የሞላበትን የአማኞች ባህሪ አይተው እንድሸነፉ ፈልጎ ነበር ፡፡ “ በፍቅራችን ክርስቲያን መሆናችንን ያውቃሉ “ እንደሚለው መዝሙር ማለት ነው ፡፡
ከክርስቶስ ጋር ስትመላለሱና በእርሱ ስትኖሩ በህይወታችሁ መንፈሳዊ ፍሬ ይበቅላል ደግሞም በራሱ ጊዜ ቅድስና በህይወታችሁ ይታያል ፡፡ ለእግዚአብሔር የልባችሁ ሁኔታና ጤንነት ከአለባበሳችሁ ፣ ከጸጉር ስታይላችሁ ወይም ከጌጣጌጥ ምርጫችሁ በላይ አስፈላጊ ነው ፡፡ በእርግጠኝነት ዓለም ውጫዊውን ውበታችሁን የበለጠ ማራኪ ለማድረግ እንድትሰሩ ይገፋፋችኋል ፡፡ እናም ደግሞ እንዲሁ እናንተ በክርስቶስ በሆናችሁት ማንነት በድፍረት ስትመላለሱ ፣ ሰዎች በእናንተ ውስጥ ወዳለው ወደ ክርስቶስ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ክርስቶስ ያላችሁ፣ ሁለ ነገራችሁ እንድሆን ፍቀዱ እናም ራሳችሁን በእርሱ ውስጥ ደብቁ ፡፡ እናም ከዚያ የእርሱ ውብ የሆነ ፍቅርና ጸጋ በህይወታችሁ ይደምቃል !
“ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።”
- 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 4:23 — “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።”
ዮሐንስ 1:12 — “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ፡፡ “
ዮሐንስ 13:35 — “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።