A Call To Good Works
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Living Hope 1 Peter 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አንደኛ ጴጥሮስ በአዲስ ኪዳን ከአጠቃላይ መልዕክቶች ዉስጥ አንዱ ነው ፡፡ ጴጥሮስ በቤተ ክርስቲያን አጀማመር ዉስጥ አንዱ ትልቅ ስዕል/ማሳያ ነበር ፡፡ በተደጋጋሚ ኢየሱስ ጴጥሮስን እንዴት እግዚአብሄርን በመታዘዝ ማድረግ እና መከተል እንዳለበት አቅጣጫን ሰጥቶታል ፡፡ በተለይም ምንም እንኳን ለክርስቶስ የቀረበ ደቀ መዝሙር ቢሆንም እና ከክርስቶስ ጋር የጠበቀ/የቀረበ ግንኙነት ቢኖረዉም ጴጥሮስ ይህን ከመያዙ እና ከመረዳቱ በፊት መልዕክቱ ሰዎስት ጊዜ ሊሰጠዉ አስፈለጎት ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ጴጥሮስ (2፡ 1-25)፡ ጴጥሮስ ብዙ አይቷልም ብዙ ትምህርቶችንም ተምሮ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ብዙ ስህተቶችን አድርጓል ነገር ግን አሁን ስለ መከራ/ስለ ስደት ለአማኞች እየተናገረ ነበር ፡፡ ሮም ተቃጥላ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ በተለያዩ በሮም አዉራጃዎች ዉስጥ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያም፣ በእስያ እና በቢታንያ ጨምሮ ለተበተኑት አማኞች እየፃፈ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ እነዚህን አማኞች እንዲጠነክሩ እን በእምነታቸዉ እንዲቀጥሉ አበረታታቸው ፡፡ ሐዋሪያት ልክ እንደ ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ስደትን/መከራን ቀምሰዉ ስለ ነበር ለአማኞች በአስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ ለመትጋት ምን ያስፈልግ እንደ ነበር ያውቃሉ/ተረድተዋል ፡፡
ጴጥሮስ የተሰደዱትን አማኞች ህያዉ ተስፋ እንደ ነበራቸዉ እያስታወሳቸዉ ነበር ፡፡ ህያዉ ተስፋ በክርስቶስ ትንሳኤ እና እንደ አማኝ በአዲስ ዉልደት ይመጣል ፡፡ ግፊቱ/ጫናዉ ሲካሄድ እነዚህ አማኞች በተግባራዊ ቅድስና ለመመላለስ የተበረታቱ ነበሩ ፡፡ ለክርስትና ቅድስና እና ለብስለት/ለእድገት ጥሪ ነበር ፡፡
በቁጥር 1 ጴጥሮስ ሰዎችን ክፋትን ሁሉ እንዲያስወግዱ ተጣራ ፡፡ ማክጊ፡ “ ክፋት ምን ማለት ነው ? “ የሚለዉን ጥያቄ አነሳ ፤ እኔ ያገኘሁት ምርጡ ትርጓሜ የተደበቀ ብስጭት የሚል ነው ፤ ይህ ማለት ይቅር የማይለ መንፈስ መኖር ማለት ነው “ ፡፡ መጀመሪያ ጴጥሮስ አማኞችን ተንኮልን፣ ግብዝነትን፣ ቅንዓትን፣ ክፋትን እና ዉሸትን እንዲስወግዱ ይጣራል ፡፡
የአማኝ ፍላጎት በማደግ የእግዚአብሄርን ቃል መፈለግ አለበት ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ አገላለፅ “ ፍላጎት/ምኞት ሁሉም ነገር ያለዉን ለሆነ ነገር መናፈቅ እንጂ ዝም ብሎ የሆነ ነገር መፈለግ ማለት አይደለም “ ፡፡ ያፍላጎት/ምኞት በክርስቶስ በሆነዉ ድነት ምክንያት ይመጣል ፤ አማኞች ስለዳኑ ስለ ጌታ የሚበልጥ ነገር ለማወቅ ይፈልጋሉ ፡፡
ሮሜ (15፡ 4) “ ..ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን እንደ ተፃፈ “ ይናገራል ፤ ተስፋ ከመፅኃፍት መጽናት እና ማበረታታት ይመጣል ፡፡ በቃሉ በመኖር ተስፋ የአማኞ አካል በመሆን በደንብ የተመሰረተ ይሆናል ፡፡
በቁጥር 4 “ ሕያዉ ድንጋይ “ ክርስቶስን ያመለክታል ፡፡ በዚህ ፅኁፍ ላይ እንደ አለት ተተርጉሞ የነበረዉን የጴጥሮስ ስምን እና ሕያዉ ድንጋይ የተባለዉን ክርስቶስ የማወዳደር ፍላጎት ምንድን ነው ፡፡ ሕያዉ ድንጋይ በሰዎች የተገፋዉ ነበር ፤ እንደ ዮሐ (3፡ 18) አገላለፅ ሕያዉ ድንጋይ የተናቀ ከነበር በእግዚአብሄር ልጅ ስላላመኑ አላማኞች ይፈረድባቸዋል ፡፡ ክርስቶስን ያልተቀበሉት ምንም ይቅርታ አይኖራቸዉም በሮሜ (1፡ 18-23) መሰረት የእግዚአብሄር ቁጣ ይደርስባቸዋል ፡፡
በቁጥር 5 አማኞችም እንደ ሕያዉያን ድንጋዮች ተለይተዋል ፤ ስለዚህም ከነቢያቶች እና ከሐዋሪያቶች ጋር የቤተ ክርስቲያን ህንፃ አካል ናቸው ፤ የግንባታዉ ክፍሎች ሲሆኑ ክርስቶስ ደግሞ የማዕዘኑ ድንጋይ ነው ፡፡ አማኞች ወደ ህያዉ ቤተ መቅደስነት ወደ መንፈሳዊ ቤትነት የተገነቡ የሚሆኑ ናቸው ፡፡
አማኞች ወደ ቤተ መቅደስ የመጡትን ምስጋናችንን፣ ንብረታችንን እና ራሳችንን ጨምሮ መንፈሳዊመስዋዕት የሆኑ ህያዉ ቤተ መቅደስ ናቸው ፡፡ ሁሉም ነገር በመዓዘን ድንጋዩ ዙሪያ መሰረት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በምሳሌአዊነት አነጋገር እግዚአብሄር እያንዳንዳቸዉን ከሌሎች ጋር በማጣመር እና እያንዳንዳቸዉን ከክርስቶስ ህይወት ጋር በማጣመር ሁሉንም አማኞች በተገቢዉ ስፍራ በማስቀመጥ መንፈሳዊ ቤት እየሰራ እንደ ሆነ ( ኤፌ 2፡ 19, ዕብ 3፡ 6) “ ፅፏል ፡፡
ቁጥር 6 አማኞች “ ህያዉ ተስፋ “ እንዳላቸዉ ይናገራል ፡፡ ጴጥሮስ ኢሳ (28፡ 16) ጠቅሷል ፤ በኢሳይያስ ያለዉ ማጣቀሻ እንደ ማዕዘን ድንጋይ ወደ መሲሁ አመልክቷል ፡፡
የህያዉ ድንጋይ ሚና ቅዱስነትን፣ በመንፈሳዊ ቤት መገንቢያ መሆንን እና ቅዱስ የክህነት አገልግሎትን ያካትታል ፤ እነዚህ ሁሉ እንደ ማዕዘን ድንጋይ በክርስቶስ ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ብሉይ ኪዳን ካህናት እና የአዲስ ኪዳን አማኞች ካህናት፡ ሁለቱም በልዩ መብት ተመረጡ፣ ሁለቱም ከኃጢዓት የነፁ ናቸው፣ ሁለቱም ለአገልግሎት የለበሱ ናቸው፣ ሁለቱም ለአገልግሎት የተዘጋጁ ናቸው፣ ሁለቱም ለመታዘዝ የተመረጡ ናቸው፣ ሁለቱም የእግዚአብሄርን ቃል የሚያከብሩ ናቸው፣ ሁለቱም በእግዚአብሄር ቃል የሚመላለሱ ናቸው፣ ሁለቱም ሁለቱም ለኃጢዓተኞች ተፅዕኖ የተደረገባቸዉ ናቸው፣ ሁለቱም የእግዚአብሄር መልዕክተኞች የሚሆኑ ናቸው “ በማለት ተናግሯል ፡፡ እነዚህ ህያዋን ድንጋዮች ከሆኑት አማኞች የሚጠበቁ ተስፋዎች ናቸው ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ በቁጥር 7 “ የግሪኩ በደንብ በስትክክል ሲነበብ ክብሩ ለምታምኑ ለእናንተ ነው ፤ የምናገኘዉ ክብሩ ወይም መብቱ/እድሉ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙት የማናፍርበት (ቁጥር 6) ከእርሱም የተነሳ አንሰናከልም (ቁጥር 8) “ በማለት ይገልፃል ፡፡
ቁጥር 9 አማኞች “ የተመረጠ ትዉልድ፣ የንጉስ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ እና ለርስቱ የተለዬ ሕዝብ “ እንደ ተደረጉ ይናገራል ፡፡ ማክጊ እነዚህ አማኞች ከአዲስ ዉልደት/ልደት የተነሳ የተመረጠዉ ሕዝብ አባል እንደ ሆኑ ይናገራል ፡፡
አማኞችን ምን ቅዱስ ሕዝብ አደረጋቸዉ በክርስቶስ ያላቸዉ ስፍራቸዉ እና አቋማቸው ነው ፤ ለርስቱ የተለዩ ሕዝቦች ናቸው ፡፡ ማክጊ “ እንግዲህአዲስ ሕዝቦች ሳይሆኑ በዚህ አለም ያሉ ነገር ግን የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች በዚህ ኃሳብ ለምን እንደሚፈሩ አላውቅም ፤ ያ ማለት በባህሪይ ልዩ እና እንግዳ የሆንን ነን ማለት ሳይሆን የእርሱ የሆንን ነን ማለት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡
መደምደሚያ
ሰዎች ወደ ክርስቶስ በሚመጡ ጊዜ ስለሚይዛቸው የተመረጠዉ ህዝብ የቅዱስ ሕዝቡ አካል ይሆናሉ ፤ እንደ አማኝ ሚናቸዉ የተመረጠ ትዉልድ፣ የንጉስ ካህናት እና ቅዱስ ሕዝብ መሆን ነበር ፡፡ አማኞች የእርሱን ምስጋና የሚናገሩ የራሱ የተለዩ ሰዎች ሲሆኑ ክርስቶስ ደግሞ በሂደቱ ዉስጥ የሚጠብቀን ነው ፡፡
Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Peter, p. 11; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1peter.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publisher, 1999), p. 1680.
J. Vernon McGee, Thru the Bible, 1 Corinthians–Revelation, v. 5 (Nashville, Thomas Nelson Publisher, 1983), p. 689.
Nelson’s Commentary, p. 1680.
McGee, p. 692.
MacArthur, p. 1907.
MacArthur, p. 1908.
Nelson’s Commentary, p. 1681.
McGee, p. 693.
McGee, p. 693.
ጥያቄዎች
-
በ 1ጴጥ (2፡ 6) ላይ የተጠቀሰዉ የማዕዘን ድንጋይ ማነው ? ህያዋን ድንጋዮችስ እነማን ናቸው ? እንደ ቅዱስ ካህናት የተጠቀስነዉ ለምንድን ነው ? (ኤፌ 2፡ 20-21, 1ጢሞ 3፡ 15, ራዕ 1፡ 6)
-
ክርስቲያኖች ባይሆኑም እንኳን እግዚአብሄር መሪዎቻችንን እንድናከብራቸዉ እና እንድንታዘዛቸዉ ይፈልጋል ? የማትታዘዙባቸዉ ሁኔታዎች አሉ ? አዎ ካላችሁ ጥቂቱን ጥቀሱ ፤ በምን እንደምንታዘዛቸዉ እና በምን እንደማንታዘዛቸዉ እንዴት ታውቃላችሁ (ዕብ 13፡ 17) ?
-
አገልጋዮች ለጌቶቻቸዉ እንዴት መስራት/ማድረግ እንዳለባቸዉ ጴጥሮስ ምን አለ ? ይህን ለምን አለ (1ጴጥ 2፡ 19-22) ? በአሁኑ ጊዜ ይህ በእኛ ላይ እንዴት ይተገበራል/ይሰራል ?
-
1ጴጥ (2፡ 16) በነፃ የሚያገለግልን ይጠቅሳል ፤ በነፃ የማገልገል ባርነትን ትርጉሙ ምንድን ነው፣ ጴጥሮስስ አማኞችን ለምን እንደ ነፃ አገልጋይ ጠቀሳቸው ?
-
በ 1ጴጥሮስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Peter 2:9
“But you are a chosen race, a royal priesthood, a holy nation, a people for His possession, so that you may proclaim the praises of the One who called you out of darkness into His marvelous light.”
ጴጥሮስ ስደትን እየተቀበሉ ላሉት አማኞች ህያው ድንጋይ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ያስታውሳቸዋል ፡፡ አዎን ኢየሱስ ይከተሉትና እንደ ጽኑ መሰረት ይቆሙበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ የማዕዘን ድንጋይ ነው ፡፡ ስለዚህም ህይወታችሁን ህያው ድንጋይ በሆነው በኢየሱስ ላይ መስርቱ ፡፡ እርሱ የእርሱን ስም ብቻ እንድታወድሱና እንድታመሰግኑ መርጧችኋል !
ስለማንነታችሁ እውነቱን ተቀበሉ ፡፡ ስራችሁ ፣ ልጆቻችሁ ፣ ያላችሁ ንብረት ወይም የተቀበላችሁት መከራ እናንተ ማን እንደሆናችሁ አይገልጹም ፡፡ ዛሬ በዚህ እውነት መመላለስ ያስፈልጋችኋል ፤ ይህም እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ፡፡ ተመርጣችኋል ፡፡ ለታላቅ የክህነት ስራ ተጠርታችኋል ፡፡ እናንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱስ ናችሁ ፡፡ የእግዚአብሔርን ምስጋና የሚያወራ መሳሪያ ትሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ተመረጣችሁ ፡፡ ህይወታችሁን ህያው ድንጋይ በሆነው በኢየሱስ ላይ ገንቡ ፡፡ በእርሱ ዘንድ ካላችሁ ማንነት የተነሳ አትናወጡም ፡፡ የእግዚአብሔርን መልካምነት ደግሞም በህይወታችሁ ያለውን ምህረቱን እንድሁም ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን ጥሪ አወድሱ ፡፡ እርሱ እናንተን በአለማ መርጧችኋል ፈጥሯችኋልም ፡፡ ከጠላት የምትሰሙትን የትኛውንም አይነት ውሸት አራግፉ ፡፡ ዛሬ የሚመጣው ምንም ነገር ይሁን ፣ እንደተመረጡ የእግዚአብሔር ልጆች ተመላለሱ ፡፡
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ ፡፡ “
- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 2:7–9 — “ ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን ። ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር ፤ ነገር ግን ፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። “
2ኛ ጢሞቲዎስ 1:9 — “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥ “
1ኛ ጴጥሮስ 2:4 — “ በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።