Living Hope
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Living Hope 1 Peter 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሐዋሪያዉጴጥሮስ 1ኛእና 2ኛጴጥሮስንሁለቱንምፃፈ፡፡ ጴጥሮስ በግልፅ የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር ፤ መቼም ቢሆን አዲስ ኪዳን ሐዋሪያቱን በሚዘረዝር ጊዜ ጴጥሮስ ሁልጊዜ ከዝርዝሩ መጀመሪያ ላይ ይገኝ ነበር (ማቴዎስ 10, ማርቆስ 3, ሉቃስ 6, ሐዋሪያት ስራ 1) ፡፡ በመጀመሪያ ጴጥሮስ ስምዖን ተብሎ ይታወቅ ነበር፡ “ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው ፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ስጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ “ (ማቴ 16፡ 17) ፡፡ የጴጥሮስ ቤተሰቦች በቅፍርናሆም በገሊላ ባህር ላይ አሳ አጥማጆች ነበሩ ፡፡ አሳ አጥማጅነት ከጉልበት ሰራተኝነት ጋር የሚስተካከል ነበር ፡፡ ጴጥሮስ ከዘመኑ ከኃይማኖት ሊሂቃን አልመጣም ፡፡
ማክአርቱር ጴጥሮስ መጀመሪያ በኢየሱስ አገልግሎት እንደ ደቀ መዝሙር የተጠራ እንደ ነበር ያመለክታል፡ “ ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው ድዉዮችንም ሊፈዉሱ አጋንትንም ሊያወጡ ስልጣን ይሆንላቸው ዘንድ 12 አደረገ ፤ ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው “ (ማር 3፡ 14-16) ፡፡ እንደ ጥሪዉ አካል ኢየሱስ የጴጥሮስን ስም ትርጉሙ “ አለት “ ወደሚል ቀየረው ፡፡ በወንጌላት ዉስጥ ኢየሱስ ያለማቋረጥ ትምህርቶችን እንዲማር ጴጥሮስ ነጥሎ ወስዶታል ፡፡
እንደ ኢየሱስ ሐዋሪያ ራሱን ጴጥሮስ ብሎ ከለዬ በኋላ ጴጥሮስ የአነስተኛዉ እስያ ሰሜናዊ ክፍል ተብለዉ ለሚታሰቡት ለአምስት ለተወሰኑ ስፍራዎች መልዕክቱን ደርሷል ፤ ብዙ አሕዛቦችን ቢደርስም የጴጥሮስ ተደራሲያኖች ጥቂት አይሁዶችንም የያዙ ናቸው ፡፡
ማክአርቱር የሮም ቃጠሎ ዜጎቿን እንዳጠፋ ፅፏል፡ “ ታላቅ ቤተ መቅደሶቻቸው፣ የተቀደሱ ስፍራዎቻቸዉ እና የቤት ዉስጥ ጣዖቶቻቸው ተቃጥለዉ ነበር ፤ ይህ ትልቅ ኃይማኖታዊ ትርጓሜ ነበረው “ ፡፡ ከዚያ በኋላ የሮም ሰዎች ተስፋ እንደሌላቸዉ እና የሚረዳቸዉ እንደሌለ ተረዱ ፤ ከዚህም የተነሳ ኔሮ እሳቱን በክርስቲያኖች ላይ በማመካኘት ማሳደዱ ተጀመረ ፡፡ ስደቱ/መከራው ከሮም ጴጥሮስ ይህን መልዕክት ወደ ፃፈበት ክልል ወደ ሰሜን ተስፋፋ ፡፡ ይህ መልዕክት ሮም ከተቃጠለች በኋላ ግን ጴጥሮስ ከመሰዋቱ ቢያንስ ከጥቂት አመታት በፊት ምናልባትም ከክርስቶስ ሞት 64 በኋላ አካባቢ ተፃፈ ፡፡
ለ1 ጴጥሮስ ቃላችን/ሐረጋችን ለሁለት ምርጫዎች መጣ ፤ የመጀመሪያው የእረኞች አለቃ ነበር፡ “ የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈዉን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ “ (1ጴጥ 5፡ 4) ፡፡ ስደት/መከራ በሚጨምር ጊዜ መልካሙ እረኛ ከአጠገባችሁ/አጋዣችሁ እንደሆነ ለማወቅ መልካም ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ለ 1ጴጥሮስ ሐረጋችን ህያዉ ተስፋ ነው፡ “ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ለሕያዉ ተስፋ…….እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ “ (1ጴጥ 1፡ 3-4) ፡፡ ለአማኞች ስደት ሲገጥማቸው በክርስቶስ ባለዉ ተስፋቸው መፅናትን ማስታወስ አስፈላጊ ነበር ፡፡
ጴጥሮስ ይህን መልዕክት በመፃፍ ዋጋ የተሰጠዉ ቢሆንም ስልዋኖስ በፅኁፍ ይህን መልዕክት ፃፈ፡ “ እየመከርኋችሁ የምትቆሙባት ጸጋ እዉነተኛ የእግዚአብሄር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ የታመነ ወንድ እንደሆነ በቆጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ “ (1ጴጥ 5፡ 12)! ጳዉሎስ ይህን ተመሳሳይ መፃፍን የመስጠት ዘዴን ተጠቅሞበታል ፡ “ ይህን መልዕክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ “ (ሮሜ 16፡ 22) ፡፡
ትምህርት
1-ጴጥሮስ (1፡ 1-2)፡ ጴጥሮስ አንባቢዎቹን እንደ “ ጊዜአዊ ነዋሪ/መፃተኛ “ ይደርሳቸዋል ፡፡ አማኞች የራሳቸዉ ባልነበሩ ምድሮች ላይ በምድር ላይ እንግዶች ነበሩ ፡፡ “ እግዚአብሄር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው “ (ቁጥር 1-2) በሂደቱ ዉስጥ ኃይማኖታዊ ተጓዥ ነበሩ ፡፡ ማክአርቱር ቀድሞ እንዳወቃቸዉ/ቀድሞ ማወቅ የሚለዉን “ በእግዚአብሄር እዉቀት ቀድሞ እንደ ተወሰነዉ ግንኙነት “ በማለት ገልፆታል ፡፡ እግዚአብሄር አማኞች ለድነት የተመረጡ ከመሆናቸዉ በፊት አቅዷል ፡፡ እግዚአብሄር “ ቀድሞ አስቧል ቀድሞ ወስኗል ወይም እያንዳንዱን ድነት ቀድሞ ደርሷል/ወስኗል “ ፤ ያ ማለት “ ለመታዘዝ ተለይተናል “ (ቁጥር 2) ማለት ነው ፡፡ የተቀደስን ስለምንሆን ይህ አለም ቤታችን አይሆንም ፡፡
1-ጴጥሮስ (1፡ 3-9)፡ ከእግዚአብሄር ታላቅ ምህረት የተነሳ አማኞች “ አዲስ ልደት “ አላቸው / እንደ ገና የተወለዱ ናቸው ፡፡ ዕብ (6፡ 19) “ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ፅኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ዉስጥ የገባ ነው “ ይላል ፡፡ ይህ መልሕቅ በኑሮአችን ዉስጥ ስለ ክርስቶስ የታተመ ነው ፡፡ ስደት/መከራ ሲመጣ አማኞች “ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ “ (ቁጥር 3) ህያዉ እና የሚሰራ ተስፋ ነበራቸው ፡፡
ማክአርቱር በአማኞች ሕይወት ዉስጥ የሕያዉ ተስፋን አስር አንድምታን አስቀምጧል፡
- ከእግዚአብሄር የመጣ ነው - “ ነፍሴ ሆይ ለምን ታዥኛለሽ ? ለምንስ ታዉኪኛለሽ ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነዉ ዘንድ በእግዚአብሄር ታመኚ “ (መዝ 43፡ 5) ፡፡
የፀጋ ስጦታ ነው - “ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሄር አባታችን “ (2ተሰ 2፡ 16) ፡፡
በመፅኀፍ የተገለፀ ነው - “ በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድአስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና “ (ሮሜ 15፡ 4) ፡፡
ምክንያታዊ የሆነ እዉነታ ነው - “ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት ፡፡ በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ “ (1ጴጥ 3፡ 15) ፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት/ትንሳኤ የተረጋገጠ ነው - “ ኢየሱስም ፡- ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያዉ ይሆናል ፤ ሕያዉ የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም ፤ ይህን ታምኚያለሽን ? አላት “ (ዮሐ 11፡ 25-26) ፡፡
በአማኞች ዉስጥ በመንፈስ ቅዱስ የተረጋገጠ ነው - “ የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ “ (ሮሜ 15፡ 13) ፡፡
ክርስቲያኖችን ከሰይጣን ጥቃት ይከላከላል - “ እኛ ግን ከቀን ስለሆንን የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋእንደ ራስ ቁርእ የለበስን በመጠን እንኑር “ (1ተሰ 5፡ 8) ፡፡
በመከራ የተረጋገጠ ነው - “ ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን “ (ሮሜ 5፡ 3) ፡፡
ደስታን ያደርጋል/ይፈጥራል - “ የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋዉም በአምላኩ በእግዚአብሄር የሆነ ሰዉ ምስጉን ነው “ (መዝ 146፡ 5) ፡፡
በክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የሚፈፀም ነው - “ የተባረከዉን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን….” (ቲቶ 2፡ 13) ፡፡
መደምደሚያ
ለአማኞች የመጣዉ ይህ ህያዉ ተስፋ “ ዘላለማዊ፣ የማይበላሽ እና የማይጠፋ ነው “ (ቁጥር 4) ፡፡ አማኞች በክርስቶስ ተመልሶ መምጣት ለመገለጥ በተዘጋጀው “ በእምነት በእግዚአብሄር ኃይል “ (ቁጥር 5) የተጠበቁ ናቸው፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1899.
MacArthur, p. 1899.
MacArthur, p. 1900.
MacArthur, p. 1903.
MacArthur, p. 1903.
MacArthur, p. 1904.
ጥያቄዎች
-
ጴጥሮስ ይህንን መልዕክት ለማን ፃፈ ? ጴጥሮስ ይህን መልዕክት ለምን ፃፈ ? በግል አስተያየታችሁ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለዉ ስደት/መከራ ከአሁን ከክርስቲያኖች መከራ/ስደት እንዴት ይለያል ? እንዴትስ ይመሳሰላል ?
-
ጴጥሮስ ስለ መከራ ምን አለ (1ጴጥ 1፡ 6-7) ? ይህ በህይወታችሁ መቼ እዉነት ሆኖ እንደምታገኙት በጊዜ አንፀባርቁት
-
ጴጥሮስ መከራ/ስደት ደርሶበታል (ሐዋ 4፡ 1-3) ? ስለ እምነታችሁ መከራ/ስደት እንደ ደረሰባችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በአሁኑም ጊዜ ልክ እንደ አንዳንድ ክርስቲያኖች ወይም ደግሞ እንደ መጀመሪያዋ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን መከራ እንደሚገጥማችሁ ታስባላችሁ ? አዎ ከላችሁ እንደ አንድ የክርስቶስ ተከታይ ለዚህ ነገር የተዘጋጃችሁ ናችሁ ?
-
1ጴጥ (1፡ 16) “ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተፃፈ “ ይላል ፤ ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው ? እግዚአብሄር ቅዱስ እንደ ሆነው ቅዱስ መሆን ቀላል ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን ቀላል አይደለም ? እንዴት አንዱ ቅዱስ ማድረግ ይችላል (1ጴጥ 1፡ 19) ?
-
1ጴጥ (1፡ 25) ምን ለዘላለም ይኖራል ይላል ? ይህ ስላላችሁ ነገር እና በምድር ላይ ስለምታደርጉት ነገር እንዴት እይታችሁን/አመለካከታችሁን ይቀይረዋል ?
-
በ 1ጴጥሮስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Peter 1:3–4
“Praise the God and Father of our Lord Jesus Christ. According to His great mercy, He has given us a new birth into a living hope through the resurrection of Jesus Christ from the dead and into an inheritance that is imperishable, uncorrupted, and unfading, kept in heaven for you.”
ጴጥሮስ ይህን መልዕክት መከራን እየተቀበሉ ላሉ አማኞች ጽፏል እናም ስለ እምነታቸው እየደረሰባቸው ባለው መሳደድ ውስጥ ለክርስቶስ ጸንተው እንድቆሙ ይመክራቸዋል ፡፡ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንኳን ሆነው ሳሉ ጴጥሮስ እግዚአብሔርን እንድያመሰግኑ ይመክራቸዋል ፡፡ ጴጥሮስ በኢየሱስ ክርስቶስ በተገኙ በረከቶች ላይ ትኩረቱን አድርጓል ማለትም ፡- ስለ ታላቅ ምህረቱ ፣ ህያው ወደ ሆነ ወደ ማይጠፋ ተስፋ ዳግም መወለድ ፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለው መስዋዕትነት ደግሞም በሰማይ ስለተዘጋጀው ርስት ነው ፡፡ እርሱም በሰማይ የተዘጋጀውን ርስት የማይጠፋ ፣ እድፍም የሌለበት ደግሞም የማያልፍ በማለት ገልጦታል ፡፡
እናንተ ወይም እናንተ የምታውቁት ሰው አሰቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥማችሁ አይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ አድርጉ ፡፡ በመከራ በህመም ውስጥ እንኳን ሳላችሁ ስሙን አመስግኑ ፡፡ አስቸጋሪው ፈታኝ የሆነው ሁኔታ በዙሪያችሁ እያለ አይኖቻችሁን ጨፍኑና በእግዚአብሔር ስጦታዎችና በረከቶች ላይ አሳባችሁን አድርጉ ፡፡ ኢየሱስ በዓለም ሳላችሁ መከራ እንዳለባችሁ ተናግሯል ፣ ነገር ግን ተስፋ እንዳትቆርጡ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ስለሚበልጥ ፡፡ ኢየሱስ ህያው ተስፋችሁ ነው ደግሞም እርሱ ለእናንተ ዘላለማዊ መኖሪያን በሰማይ እያዘጋጀ ነው ፡፡ ኢየሱስ ያበረታችኋል ፡፡ እርሱ ለበጎ ስራ ሁሉ ያበረታችኋል ፡፡ በየቀኑ ጊዜ እየወሰዳችሁ ህያው ተስፋችሁን ኢየሱስን አመስግኑ!
“ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ ፡፡ “
- 1ኛ ጴጥሮስ 1፡3-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 5:3–4 — “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፡፡”
1ኛ ተሰሎንቄ 5:16–18 — “ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ ፤ በሁሉ አመስግኑ ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። ”
2ኛ ተሰሎንቄ 2:16–17 — “ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።