Waiting For The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Law James 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ በአንዱ በአጠቃላይ መልዕክት በያዕቆብ መፅኃፍ ዉስጥ የመጨረሻው ክፍል/ትምህርት ነው ፡፡ ያዕቆብ ለእስራኤል ለ12 ነገዶች እየፃፈ ነበር ፤ እነዚህ በኢየሱስ ያመኑ ከእያንዳንዱ ነገዶች ቅሬታ የአይሁድ አማኖች ነበሩ ፡፡ ተደራሲያኑ ጠንካራ በሆነ የአማኞች ማህበረሰብ የተከበቡ ስላልነበሩ ያለ ማቋረጥ ተፈትነዉ ነበር ፡፡ ማክአርቱር የያዕቆብን አስር ፈተናዎች ዘርዝሯል፡ 1) በመከራ ዉስጥ ተግቶ የመስራት ፈተና፣ 2) በምኞት የመወቀስ ፈተና፣ 3) ለቃሉ ምላሽ የመስጠት ፈተና፣ 4) የወገተኝነት ፍቅር ፈተና፣ 5) የጽድቅ ስራ ፈተና፣ 6) የአንደበት ፈተና፣ 7) የመዋረድ ጥበብ ፈተና፣ 8) የአለማዊነት ፍላጎት ፈተና፣ 9) የጥገኝነት ፈተና እና 10) በትግስት የመቻል ፈተና ፡፡
ያዕቆብ የፈተና መፅኀፍ ነበር ነገር ግን ፍፁሙ ሕግ በክርስቶስ በኩል ወደ ነፃነት ይመራል ፡፡ አማኞች ወደ ፍፁሙ ሕግ ከተመለከቱ ይባረካሉ ፡፡ በክርስቶስ በዚህ መንገድ ለመመላለስ ሁሉም ፍላጎት ይኖራሉ ፡፡
ትምህርት
ያዕቆብ (5፡ 1-20)፡ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያዎቹ 11 ቁጥሮች በማክአርቱር “ በትዕግስት የመታገስ ፈተና “ በመባል የተገለፁ ነበሩ ፡፡ ባለፀጋ የነበሩ ሰዎችም ተደርሰዋል ፤ ኃብታቸው፣ ንብረታቸዉ እና ልብሳቸው በብል እና በዝገት የሚጠፋ ነበር ፡፡ የሰዎች ኃብት የሚመጣ እና ከመጨረሻው ቀን/ዘመን በፊት ይሄዳል ፡፡
ኮንስታብል ከአለም አመለካከት አንፃር አስር የገንዘብ እይታዎችን ያስቀምጣል፡ “ 1) ገንዘብ ነፃነት ያመጣል፣ 2) ገንዘብ ደህንነትን ያመጣል፣ 3) ገንዘብ ሁሉን ነገር ነው፣ 4) ገንዘብ ኃይል ነው፣ 5) ገንዘብ ክብራችሁን/ዋጋችሁ ብቻ የሚሰራ ሳይሆን እንደ ሰው ክብራችሁን ይሆናል፣ 6) ገንዘብ ስኬታማ ያደርጋችኋል፣ 7) ገንዘብ ምርጫን ይሰጣችኋል፣ 8) ገንዘብ ደስታን ያመጣል፣ 9) ገንዘብ ዋጋችሁ/ሽልማታችሁ ነው ፤ ይህን በመያዝ በራሳችሁ ላይ አሳልፉት እንዲሁም 10) ገንዘብ ንብረታችሁ ነው ፡፡ በምትፈለጉት ላይ አሳልፉት “ ፡፡
ኮንስታብል በተጨማሪም ከቃሉ አንፃር አስር ተነፃፃሪ የገንዘብ እይታዎችን ሰጥቷል፡ “1) ክርስቶስ ብቻ እዉነተኛ ነፃነት ያመጣል፣ 2) እዉነተኛ ደህንነት እግዚአብሄርን በማወቅ እና በመታመን የሚገኝ ነው፣ 3) ክርስቶስ እና የእግዚአብሄር መንግስት ሁሉን ነገር ናቸው፣ 4) ኃይል በመንፈስ በመሞላት የሚመጣ ነው፣ 5) ዋጋችሁ የባንክ መዝገባችሁ የሚለዉን ሳይሆን እግዚአብሄር በሚላችሁ ላይ የተመሰረተ ነው፣ 6) ስኬት እግዚአብሄር የሚለዉን በማወቅ እና በማድረግ ይመጣል፣ 7) ምርጫ የሚሰጣችሁ የመጨረሻዉ እግዚአብሄር ነው፤ 8) ገንዘብ የሚሰጠዉ ደስታ አጭር ጊዜ የሚኖር ነው፣ 9) የምትችሉትን ያክል ስጡ፣ እና 10) ያላችሁ ሁሉ እርሱን የሚያስደስት የምታደርጉበት የእግዚአብሄር ነው “ ፡፡ ያዕቆብ ሁሉም ሰው ማስቀመጫቸዉን/ማጠራቀሚያቸዉን በእግዚአብሄር ላይ እንዲያስቀምጡ ፈለገ ፡፡
ቁጥር 4 የሰራተኞችን/የሌሎችን ደሞዝ ስለመያዝ ይናገራል ፡፡ በሌሎች ወጪ ላይ ኃብትን በሚያከማቹት ላይ ፍርድ ይመጣባቸዋል ፤ ማክአርቱር “ ለመታረድ እንደደረሰ የደለበ ጥጃ/ከብት ያዕቆብ እየወቀሳቸዉ የነበሩት ባለፀጎች እስከ ፍፃሜ እስኪደርሱ ራሳቸዉን እንደሚያዝናኑ “ ይናገራል ፡፡ በጣም ተንደላቀዉ/ተሞላቀዉ የነበሩት ያዕቆብ በዚህ መልዕክት እየደረሳቸዉ በነበራቸዉ ኑሮ ዉስጥ ይወድቃሉ ፡፡
ባለፀጎች ገንዘብን እያከማቹ እና ደሞዝን እየያዙ ነበሩ ፡፡ በቁጥር 6 ያዕቆብ በገንዘባቸዉ ፍርድን እየገዙ/እየቀየሩ እንደ ነበር ፡፡ ባለፀጎች እስከ መጨረሻው ድረስ ራሳቸዉን ያዝናኑ/ያሞላቀቁ ነበሩ ፡፡
ለአማኞች ትዕዛዙ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታጋሽ መሆን ነበር ፡፡ ማክአርቱር፡ “ በክርስቶስ ተልሶ መምጣት ላይ የሚጠብቅን ክብር ማስተዋል የአሁኑን ችግር እንዲታገሱ አማኞችን እንደሚያበረታታቸው ይገልፃል (ሮሜ 8፡ 18) “፤ ፤ ከዚያም በመቀጠል “ በጥቅምት እና በህዳር በእስራኤል ዝናብ ለመዝራት መሬቱን ለማለስለስ ይዘንባል ፤ የበኋላዉም ዝናብ እህሉ ከመሰብሰቡ በፊት ወዲያዉኑ በመጋቢት እና ማዚያ ይዘንባል ፤ ገበሬ እህሉን ለመሰብሰብ ከቀደመዉ ዝናብ እስከ ኋለኛዉ ዝናብ በትዕግስት እንደሚጠብቅ ክርስቲያኖችም የጌታን ተመልሶ መምጣት መጠበቅ አለባቸው (ገላ 6፡ 9, 2ጢሞ 4፡ 8, ቲቶ 2፡ 13) “ ብሎ በመግለፅ “ የመጀመሪያዉ ዝናብ እና የኃለኛዉ ዝናብ “ የሚለዉን ሐረግ ይገልፀዋል ፡፡ ክርስቶስ መጥቶ ስለ ነበር አሁን ለታላቁ መከረ በትዕግስት ይጠብቁታል ፡፡ በመጠበቁ ዉስጥ አማኞች እምነታቸዉን በገንዘባቸዉ ላይ ማስቀመጥ የለባቸውም ፡፡
የክርስቶስ አካልበትዕግስት የመጥተብቅ እንደሆነች ትጠበቃለች ፤ ነገር ግን በተተከሉ ጊዜ መጠበቅ እና ልባቸዉን ማጠንከር ያስፈልጋቸዋል ፡፡ የጌታ መምጣት ቀርቦአል ፤ ቅሬታ አያቀርቡም ወይም አያጉረመርሙም ፡፡ ዳኛው በአደባባዩ በር ላይ ቆሞ ነበር ፡፡
ያዕቆብ አነስ እንዳለ ምሳሌያው አነጋገር ነው ፤ ነቢያቶች በቁጥር 11 ላይ ሲጠቀሱ ኢዮብ በትዕግስት እንደሚጠብቅ ምሳሌ የተጠቀሰ ነበር ፡፡
ቁጥር 12 የእዉነተኝነት/ስለ መኃላ ንፈተና ይዳስሳል ፤ በፍርድ ስር እንዳይወድቁ አማኞች የሚሉትን እንደ ቀላል መዉሰድ የለባቸውም ነበር ፡፡
በቁጥር 13 ያዕቆብ ወደ ፀሎጽ ፈተና ዞረ ፤ በችግር ዉስጥ ለነበሩት ሌሎች ስለ እነርሱ ይፀልዩላቸው ፡፡ ማንም ሰዉ ቢታመም “ ለማበርታት፣ ለመርዳት እና ለመፀለይ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ይጠራሉ “ ፤ የእምነት ፀሎት የታመመዉን ሰዉዬ ያድነዋል፣ ያድሰዋልም ይፈዉሰዋልም ፤ ሰዉዬዉም ኃጢዓቶቹ ይቅር ይባሉለታል ፡፡ ኤልያስ ለፀሎት ኃይል እንደ ምሳሌነት ተጠቅሷል ፡፡
ቁጥር 19 ስለ እዉነተኛ እምነት ፈተና ነው ፡፡ ክርስቶስ አማኞችን ሙሉ ነፃነት መስጠት ይፈልጋል ፡፡ ከስህተት መንገድ ከኃጢዓት የሚመለሱ ህይወታቸዉን ያድናሉ ብዙ ኃጢዓትንም ይሸፍናሉ ፡፡ ነፍሳቸዉን ከሞት ያድናሉ (ቁጥር 20) ፡፡
መደምደሚያ
እንደ ፍፁም ሕግ ኢየሱስ ሙሉ ነፃነት ሊሰጠን ይፈልጋል ፤ አንድ ኃጢዓተኛ ከእግዚአብሄር የራቀ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ይህ ታላቅ/አስፈላጊ ነገር ነበር ፡፡ ክርስቶስ ከኃጢዓት ባርነት ነፃነት ሊሰጠን ፈለገ ፡፡ ፀሎት ሙሉ ነፃነትን ላይ እስኪደረስ ድረስ በዚህ ለመመላለስ አስፈለገ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1881–1895.
MacArthur, p. 195.
Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: James, pp. 93–94; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/james.pdf.
Constable, pp. 93-94.
MacArthur, pp. 1895–1896.
MacArthur, p. 1896.
MacArthur, p. 1897.
ጥያቄዎች
-
በያዕ (5፡ 2) ያዕቆብ ለመናገር እየሞከረ የነበረው መልዕክቱ ምን ነበር (ማቴ 6፡ 19-21) ? ንብረታችሁን የምታጠራቅሙት የት ነው ?
-
በያዕ (5፡ 9) ላይ እንዳለዉ ስለ ሰዉ ስታወሩ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ስለ ነገሩ ጌታ ገሰፃችሁ ወይስ እሰ ብቻ ፈራጅ/ዳኛ እንደ ሆነ አሳያችሁ ? አዎ ከሆነ በምን መንገድ ?
-
በያዕ (5፡ 10-11) እንዳለው በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ትዕግስት እንዲኖረን እና መከራ ሲደርስብን እንደ በረከታችን እንድንቆጥረው ተነግሮናል ( ዮሐ 16፡ 33) ? ችግር/መከራ ደርሶባችኋል ? አዎ ከሆነ በእነዚህ ጥቅሶች መፅናናትን አግኝታችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አላገኛችሁም ?
-
በያዕ (5፡ 15) ያዕቆብ በእምነት የሆነ ፀሎት እንደሚያድን እና ጌታም ያድሰዋል አለ ፤ ፀልያችሁ ፈዉስን አይታችሁ/ቀምሳችሁ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን ተፈጠረ ?
-
በሰዉ ላይ እጃችሁን በመጫን የእምነት ፀሎትን በመፀለይ ሲፈወሱ አይታችሁ ታውቃላችሁ ? አናውቅም ከሆነ ዛሬም ለፈዉስ ለሰዉ ለመፀለይ በእምነታችሁ በሚገባ ደፋር ትሆናላችሁ ?
-
በያዕቆብ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin James 5:17b–18
“The urgent request of a righteous person is very powerful in its effect. Elijah was a man with a nature like ours; yet he prayed earnestly that it would not rain, and for three years and six months it did not rain on the land. Then he prayed again, and the sky gave rain and the land produced its fruit.”
ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ሲጽፍ ፡- “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ፡፡“ አዎን በኢየሱስ ስታምኑ እርሱ ጻድቅ ብሎ ይጠራችኋል ፡፡ ጽድቅን ለማግኘት ልዩ የሆነ መስዋዕት ማቅረብ ወይም በጎ ስራን መስራት አይጠበቅባችሁም ፡፡ ያዕቆብ ሲጽፍ ፡- “የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች “ እርሱም ስለ እናንተ እያወራ ነበር ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆናችሁ ፡፡ በእርግጥም እግዚአብሔር እናንተ በፊቱ እንድትቀርቡና እንቆቅልሻችሁን እንድትነግሩት ይሻል ፡፡ እናንተም ልክ እንደ ኤልያስ ሁሉ ፣ እግዚአብሔርን ሁሉንም ነገር የመጠየቅ ስልጣኑ አላችሁ ፡፡
ወደ ጌታ ጸልዩ ፡፡ እርሱ እያንዳንዱን ጸሎት ይሰማል ፡፡ እርሱም እሺ በማለት ወይም አይሆንም አለበለዚያም ትንስ እንድትጠብቁ በመናገር ይመልሳል ፡፡ ወደ እርሱም ስትጣሩ ስትጸልዩ በእምነትና በእርግጠኝነት ጌታ ጸሎታችሁን እንደሚሰማ እመኑ ፡፡ እርሱን አመስግኑ ፡፡ የምትወዱትን ሰው እንድፈውሰው ፣ እንድረዳው ወይም ደግሞ ድነትን እንደድደርግት ለምኑት ፡፡ ሳታቋርጡ ጸልዩ ፡፡ ልክ ሁልጊዜ ሳያቋርጥ አባቱን እንደሚጠይቅ ልጅ እንድሁ እናንተም የሰማዩ አባታችሁን ጠይቁ ፡፡ ጸሎታችሁ ኃይልን ያደርጋል ፡፡ በእምነት የሚደረግ ጸሎታችሁ ተራራን ይነቅላል ፣ ዝናብን ያዘንባል ፣ በሽታን ይፈውሳል ደግሞም የጠፋውን ያስገኛል ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር ጸሎታችሁን እንደሚሰማ በማመን ጸልዩ ፡፡
“ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ ፡፡“
- ያዕቆብ 5:16b–18
ተጨማሪ ጥቅስ
- 1ኛ ነገሥት 18:41–42 — “ ኤልያስም አክዓብን ፦ የዝናቡ ውሽንፍር እጅግ ነውና ተነሥተህ ውጣ፥ ብላም ጠጣም አለው ። አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ ፤ ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጕልበቱ መካከል አድርጎ በግምባሩ ተደፋ ። “
- ሮሜ 10:9–10 — “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። “
- 1ኛ ዮሐንስ 5:14 — “ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።