General Letters James

Our Will and God's Will

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Law James 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 669 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በያዕቆብ ዉስጥ እነዚህ ክፍሎች ጳዉሎስ ባልፃፋቸዉ መልዕክቶች በአጠቃልይ መልዕክት ደብዳቤ ዉስጥ ናቸው ፡፡ ጳዉሎስ በአዲስ ኪዳን አብዛኞቹን መልዕክቶች ፅፏል ፡፡ ያዕቆብ ለአማኞች የተፃፈ ነበር በተለይም ከስደቱ/ከመከራዉ የተነሳ ተበትነዉ ለነበሩት የአይሁድ ሰዎች ፤ ያዕቆብ መልዕክቱን ለተበተኑት ለ12 ነገዶች በማለት አድርሷል ፡፡

ያዕቆብ አንባቢዎቹን ወደ ፈተና እና ወደ ሚገጥማቸዉ መከራ የተሰጡ እንዳይሆኑ ያበረታታቸዋል ፤ የፀኑ እንዲሆኑ እና እንዲታገሱ ነገራቸው ፡፡ ያዕቆብ እድገት እንደሚመጣ እና በመጨረሻም ልክ እንደ ክርስቶስ መተግበር፣ ልክ እንደ ክርስቶስ መናገር እና ክርስቶስን እንደሚመስሉ እየመከራቸዉ ነበር ፡፡ ትኩረቱ ስለሚቻሉ የማቻቻል አይነቶች ነበር ፤ ዋይሰርቤ እነዚህ ክርስቲያኖች “ እርስ በእርስ በጦርነት እንደ ነበሩ “ ተናግሯል ፡፡

ትምህርት

ያዕቆብ (4፡ 1-17)፡ ኢየሱስ ፍፁም ሕግ ተብሎ ተጠርቶ ነበር ፡፡ አማኞች አይኖቻቸዉን በክርስቶስ ላይ በሚያደርጉ ጊዜ በክርስቶስ ሕግ ተግተዉ ይሰራሉ፣ መልካም ስራን በሚያደርጉ ጊዜ አድርገዉት ስለ ነበረዉ ነገር የተባረኩ ነበሩ ፡፡ አይኖቻቸዉን በነፃነት ፍፁም ሕግ ላይ አይናቸዉን በማድረግ አንዱ በሌላዉ ላይ በጦርነት አይዘምትም ፡፡ ሊታዘዙት/ሊያከብሩት የሚገባዉ አንዱ ክርስቶስ ነበር ፡፡ ያዕቆብ ስለ ምን በጦርነት ላይ እንደ ነበሩ ወይምእርስ በእርስ ያልተስማሙት ስለምን እንደ ነበር ? በማለት ይጠይቃል ፤ በራሳቸዉ ጦርነትን ዘምተዋል ፤ ለአለመስማማታቸዉ ምክንያቱ በዉስጣቸዉ በነበረዉ በስጋ ሀሳብ ነበር ፡፡ በአብዛኛው በሌሎች ላይ ሳይሆን በራሳቸዉ ላይ አትኩረዋል ፤ ብዙ ነገር ስለሚፈልጉ ታገሉ ፡፡

አድማጮቹ/ተደራስያኑ ክርስቲያን አማኞች ነበሩ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ያዕቆብ እየደረሳቸዉ የነበሩትንተደራሲያን በመግለፅ ዉስጥ “ ስጋዊ ክርስቲያን “ የሚለዉን ቃል ተጠቅሟል ፡፡ በክርስቶስ የሚያምኑ ግለሰቦች ነበሩ ነገር ግንየእርሱን ተፈጥሮ/አኗኗር አላንፀባረቁም/አላሳዩም ፡፡ ማክአርቱር ሰዎቹ “ በክፉት የሚኖሩ በግል ደስታ እና በራስ ወዳድነት ምኞት የተነሳሱ “ እንደ ነበሩ ገልፆአቸዋል ፡፡ ለያዕቆብ ከቁሳዊነት የተነሳ ፀብ፣ ግድያ እና ጦርነት ነበር ፤ እነዚህ አማኞች ብዙ ነገር ፈለጉ ፡፡ 1ዮሐ (2፡ 15-16) የአለም የሆነዉ ሁሉም ነገር ከእግዚአብሄር ስላልሆነ ማንም አለምን እንዳይወድድ ተናግሯል ፡፡ በብዙ ነገር ላይ መታገል ክርስቶስን አያንፀባርቅም/አያሳይም ፡፡

ያዕቆብ አማኞች ይጠይቃሉ ነገር ግን አይቀበሉም ምክንያቱም በክፉ መሻት ይጠይቃሉና አለ (ቁጥር 3) ፡፡ እርስ በእርሳቸዉ እና በራሳቸዉ ዉስጥም በጦርነት ላይ ነበሩ ምክንያቱም ከክፉ አላማ እና ከክፉ መሻታቸዉ ስለጠየቁ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ያዕቆብ ለክፉ ነገሮች እየፀለዩ እንደ ነበር በማመልከት መለሰላቸው ፤ ለኃጢዓት ምኞታቸዉ ከመፀለይ ይልቅ ለእነርሱ ስለ እግዚአብሄር መልካም ፍቃድ መፀለይ አለባቸው ፤ አብዛኛዉን ጊዜ እግዚአብሄርን እንድ ሰዉ የፈለገዉን የማይሰጥበት ምክንያት በአጭሩ ለዚያ ሰዉ እንደማይጠቅመዉ ስለሚያውቅ ነው (ፊል 4፡ 19) “ በማለት ተናግሯል ፡፡

ያዕቆብ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር አልመለሰላቸዉም ምክንያቱም ጥያቄአቸዉ ከክፉ ምኞት የተነሳ ስለ ነበር እንደሆነ አብራርቷል ፡፡ ከጌታ ጋር ባለ የግል ግንኙነት ጥቅም ያላዉ ካልነበር የበለጠ ምቾት የሚያመጣ ነገር ይጠይቃል ነገር ግን ይህ ለረጅም ጊዜ/ለወደፊቱ እንደማይጠቅም ያውቃል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እግዚአብሄር ፀሎታችንን በአዎንታዊነት መመለስ እንደማይገደድ “ ያመለክታል ፡፡ በፀሎት ብንጠይቀዉም እንኳን እግዚአብሄር ከፍቃዱ በተቃራ በሆነ መንገድ አያደርግም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በፀሎት እግዚአብሄር ወደ እኛ ፍቃድ አያጎነብስም፣ ከዚያ ይልቅ ለኑሮአችን ለመልካም ፍቃዱ እንድንገዛ “ ተናግሯል ፡፡

በ12 ነገዶች ዉስጥ ያሉት አማኞች እየጠየቁ የነበሩትን ሁሉም ነገር በክፉ ምክንያት እየጠየቁ ነበር ፡፡ ለግል ጥቅም ብቻ የነበሩ ፀሎቶች የተመለሱ አልነበሩም ምክንያቱምበክርስቶስ ካለዉ የነፃነት ፍፁም ሕግ ላይ አይኖቻቸዉን ስለሚወስዱ/ስለሚያነሱ፡፡ ክርስቶስ ስለ እያንዳንዱ ሰዉ ያውቃል ፡፡

ዋይርስቤ ቁጥር (4-10) “ ከእግዚአብሄር ጋር ጦርነት ላይ የሆኑ “ ሰዎች በማለት ይለያቸዋል፡፡ ከክርስቶስ መንገድ ላይ ከማትኮር ላይ በመሳብ በአማኞች ኑሮ ላይ የሚንቀሳቅስ ኃይል የሚሆን ማንኛዉም ነገር የተወገደ መሆን አለበት ፡፡ ማንኛዉም የድርጊት እና የፍላጎት ጥያቄዎች መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ኑሮ የሚናገራቸዉ ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ትኩረቱ በነፃነት ፍፁም ሕግ ላይ መሆን አለበት ፡፡ ሰዎች የአለም ወዳጅ የሚያደርግ ትንሽ ነገርን ማድረግ የእግዚአብሄር ጠላቶች ያደርጋቸዋል ፡፡

ቁጥር 5 መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ዉስጥ እየሰራ/እየተንቀሳቀሰ እንደ ነበር አመልክቷል ፡፡ በአማኞች ሕይወት ዉስጥ አሮጌ ተፈጥሮ እና አዲስ ተፈጥሮ የሚያሳይ ምስል ነበር ፤ በአሮጌዉ ተፈጥሮ ያዘነበሉ ከሆኑ ከእግዚአብሄር እየራቁ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ሕዝቡ ቀናተኛ ነበር ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአማኞቹ ኑሮ ዉስጥ መንቀሳቀስ ስለፈለገ በኑሮአቸዉ መንፈስ ቅዱስ ለብዙ ነገር እየናፈቀ ነበር ፡፡

ያዕቆብ እግዚአብሄር ለትሁታን ታላቅ ፀጋን እንደሚሰጠ ገለፀ (ቁጥር 6) ፤ ምሳ (3፡ 34) እግዚአብሄር ለትሁታን ፀጋን እንደሚሰጠ ያመለክታል ፡፡ ምሳ (16፡ 18) የሰዉ ልጅ በትዕቢት በሚሰራ ጊዜ ለዉድቀት ማሳያ እንደሆነ ያብራራል ፤ ትዕቢት ከዉድቀት/ከጥፋት በፊት ይመጣል ፡፡ እስራኤላዊያን አይኖቻቸዉን ከእግዚአብሄር ላይ በማንሳት አካባቢያቸዉን ለመቆጣጠር ሞከሩ ፡፡

ቁጥር (7-10) ተጨባጭ የሆኑትን ትዕዛዝ ዝርዝር ይሰጣሉ ፤ እንደ ማክአርቱር ገለፃ አስሩ ትዕዛዝ ይካተታሉ፡

  1. ለእግዚአብሄር መገዛት (ቁጥር 7) ፡፡
  2. ክፉን መቃወም (ቁጥር 7) ፡፡
  3. ወደ እግዚአብሄር መቅረብ (ቁጥር 8) ፡፡
  4. እጆቻችሁን ማንፃት (ቁጥር 8) ፡፡
  5. ልባችሁን ማጥራት (ቁጥር 8) ፡፡
  6. መጨነቅ (ቁጥር 9) ፡፡
  7. ማዘን (ቁጥር 9) ፡፡
  8. ማልቀስ (ቁጥር 9) ፡፡
  9. ያለ ሳቅና ያለ ደስታ ማዘን (ከኃጢዓታችሁ የተነሳ) (ቁጥር 9) ፡፡
  10. ራሳችሁን አዋርዱ (ቁጥር 10) ፡፡

ያዕቆብ ይህን ሁሉ የገለፀው የነፃነትን ፍፁም ሕግ በማክበር እና የአማኞችን አይን በክርስቶስ ላይ ስለማድረግ ተግባራዊነት ነበር ፤ ይህ ዝርዝር ግለሰቦችን በእምነታቸዉ እንዲኖሩ ለመርዳት የያዕቆብ ጥረት ነበር ፡፡ በኔልሰን ማብራሪ መሰረት“ ይህ በመጀመሪያነት ከእግዚአብሄር ጋር የአንድን ሰው የመንፈሳዊነትን ግንኙነት ያመለክታል “ ፡፡ ቁጥር (11-12) ራስን ከፍ ከፍ ስለማድረግ በተመለከተ ናቸው ፡፡ ቁጥር (13-16) በራስ ስለመታመን/ስለ መመካት ናቸው ፡፡ ቁጥር 17 ማድረግ እያወቀ ነገር ግን ላላደረገዉ ሰዉዬ ኃጢዓት እንደ ነበር በመናገር ስለ መተዉ/ስለ አለማድረግ ኃጢዓት ይናገራል ፡፡

መደምደሚያ

በያዕቆብ ዉስጥ ለአማኞች ፀጋን ከመቀበል አንስቶ በእምነት እስከሚኖሩ ድረስ ሂደት ነበረው ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን በአሮጌዉ ተፈጥሮ/ማንነታቸዉ እንዲኖሩ አይፈልግም ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህ የአይሁድ አማኞች ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ፈለገ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 366.

  2. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson Publishers. 1999), p. 1669.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1892.

  4. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1669.

  5. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1669.

  6. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1669.

  7. Wiersbe, p. 368.

  8. MacArthur, p. 1894.

  9. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1670.

  10. Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: James, p. 88; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/james.pdf.

ጥያቄዎች

  1. ራሳችሁን ወይም ሌሎችንበዙሪያችሁ ካሉ ከሌሎች ጋር ሲጋጩ እና ሲጣሉ ብታገኟቸው ያዕ (4፡ 1-3) ምንጩ ምንድነዉ ይላል ? ማስተካከያዉስ ምንድን ነው (ቁጥር 6-7) ?
  2. ያዕ (4፡ 4) አንብቡ፡ የአለም ወዳጅ መሆንን የመረጡትን ያዕቆብ እንዴት ገለፃቸው ? የአለም ወዳጅ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ዮሐ 17፡ 14, 1ዮሐ 2፡ 15-16)
  3. ያዕ (4፡ 7) ለእግዚአብሄር እንድንገዛ ይነግረናል ፤ ያን እንዴት እናደርጋለን ? (መዝ 1፡ 1-2, ማቴ 11፡ 29, ኤፌ 5፡ 21, 1ጴጥ 2፡ 11-17, 5፡ 5)
  4. በሁሉም መንገዳችሁ ያልተረጋጋችሁ/ወላዋይ በመሆን ራሳችሁን ሁለት ሀሳብ (ያዕ 1፡ 8, 4፡ 8) ሆናችሁ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ይህን ለማስተካከል ምን ማድረግ ትችላላችሁ ? (ማቴዎስ 7፡ 24-27, ሉቃ 13፡ 24-27, ሮሜ 13፡ 11-14, ያዕ 1፡ 2-4)
  5. በያዕ (4፡ 11-12) እንዳለው በያዕቆብ ላይ የሚገኘዉ ሌለኛዉ ጭብጥ አንዱ በሌላዉ ላይ ስለመናገር እና ስለ መፍረድ ነውሰ ፤ በዚህ ትፈተናላችሁ/ትቸገራላችሁ ? አዎ ከሆነ ስለ ነገሩ ለሌላ ሰዉ ራሳችሁን እንዴት ተጠያቂ ታደርጋላችሁ ? (ያዕ 5፡ 16)
  6. በያዕቆብ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin James 4:11–12

“Don’t criticize one another, brothers. He who criticizes a brother or judges his brother criticizes the law and judges the law. But if you judge the law, you are not a doer of the law but a judge. There is one lawgiver and judge who is able to save and to destroy. But who are you to judge your neighbor?”

በሌሎች ላይ ትፈርድ ዘንድ አንተ ማን ነህ ? አንተ በእነርሱ ቦታ ላይ ቆመህ አታውቅም ፡፡ የእነርሱን ታሪክ አታውቅም ፡፡ እና ታዲያ እንዴት ነው አንተ ዳኛ ልትሆን የምትችለው ? ከአንተ የሚወጣው የትችት አስተያየት ማንንም ተጠቃሚ አያደርግም ፡፡ ስለዚህም ሌሎች እንዴት ልጆቻቸውን እንደሚያሳድጉ ፣ ምን እንደለበሱ ወይም ለምን መጥፎ አመለካከት እንዳላቸው እንኳ ጭምር አትፍረድ ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ታሪክ አለው ፡፡ የሆኑትን ሳታዳምጥ ታሪካቸውን ሳታውቅ በሌሎች ላይ መፍረድ የለብህም ፡፡

እግዚአብሔር በሌሎች ላይ መፍረድን ወይም ሌሎችን መተቸትን ስለ ሌሎች በመጸለይ መለወጥ እንድትችል እንድረዳህ ጸልይ ፡፡ እግዚአብሔር ለእርሱ እንድትገዛ ፣ ድያብሎስን ግን እንድታቃወም እርሱም ከአንተ እንደሚሸሽ ይናገራል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል ፡፡ ስለዚህም ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በጎረቤቶችህ ላይ ፈራጅና እነርሱን የሚተች የመሆንን ፈተና ተቃወም ፡፡ ጌታ ጎረቤቶችህን እንደ ራስህ እንድትወድ ያዝሃል ፡፡ እስኪ ራስህን ጠይቅ ፡- እንዴት ነው እንደ ጎረቤት መወደድ የምፈልገው ? አንተ ማየት የምትፈልገውን ፍቅር አሳይ ፡፡ እናም ምንም የምትለው መልካም ነገር ከሌለህ ፣ ምናልባትም ምንም መናገር አያስፈልግህም ! አንተ እርሱ ላይ በመፍረድ የምትፈተንበት ያ ሰው ከፍርዱ ይልቅ በጸሎትህና በመልካምነትህ በጣም ይጠቀማል ፡፡ ስለዚህም አንተም ልክ እንደ ኢየሱስ ለእነርሱ ፍቅርን እንዴት ማሳየት እንደምትችል እንድረዳህ እግዚአብሔርን በጸሎት ፈልግ ፡፡

“ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?”

  • ያዕቆብ 4፡11-12

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 2:1–3 — “ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።እንደዚህም በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን።አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?”

ያዕቆብ 2:8 — “ነገር ግን መጽሐፍ፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ ፡፡ “

ያዕቆብ 4:7–8a — “ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል ። “