Controlling The Tongue
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Law James 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የያዕቆብ ፀኃፊ በብዛት የሚመስለዉ የኢየሱስ የእናት ልጅ ነበር ፡፡ ያዕቆብ በኢየሩሳሌም በመጀመር በሌሎች ስፍራዎች ተስፋፍቶ ከነበረዉ መከራ/ስደት የተነሳ በሚታወቀዉ አለም ተበትነዉ ለነበሩት አማኞች ፃፈ ፡፡
በያዕቆብ 3 ፀኃፊው አንደበታችን በዙሪያችን ያሉትን እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያሳድርባቸዉ ስለ አንደበት ስድስት ምሳሌአዊ አነጋገሮችን ሰጥቷል ፡፡ ዋይርስቤ ያዕቆብ የአደገ/የጠነከረ ክርስቲያን ለመሆን ምን እንደሚወስድ እንደገለፀ ያመለክታል፡ “ በመከራ የታገሰ (ያዕቆብ 1) እና እዉነትን ተግባራዊ የሚያደርግ (ያዕቆብ 2) ፤ በዚህ ምዕራፍ (በምዕራፍ 3) …. በአንደበቱ ላይ ስልጣን ያለዉ/የሚገዛ “ ፡፡
ትምህርት
ያዕቆብ (3፡ 1-8)፡ ዕብራዉያን (5፡ 11-14) አማኞች ሁሉ አማኞች የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ ያዕቆብ ብዙዎቹ አስተማሪዎች እንዳይሆኑ ፅፏል ምክንያቱም በባሰዉ ፍርድ ስር የተያዙ ስለሚሆኑ (ቁጥር 1) ፤ የእግዚአብሄርን እዉነት ቢናገሩም በኑሮአቸዉ ስለማይኖሩበት (ቁጥር 2, 1ዮሐ 2፡ 20, 27) ፡፡ ማክአርቱር ይህ የባሰ ፍርድ “ የሚመጣዉን የወደፊቱን ፍርድ ያመለክታል፡ 1) በሁለተኛዉ መምጣቱ ላይ ለማያምኑት የኃሰት አስተማሪዎች (ይሁዳ 14, 15) እና 2) በክርስቶስ ፊት በሚሸልምበት ጊዜ ለአማኞች (1ቆሮ 4፡ 3-5) “ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ይህ የባሰ ፍርድ የመጠራትን አስፈላጊነት የአቅም አስተማሪዎችን የሚያስጠነቅቅ እንጂ ለማስተማር የተጠሩትን ተስፋ የሚያስቆርጥ ማለት አይደለም ፡፡ ማክአርቱር ማሰናከል የሚለዉን ቃል “ እንደ ኃጢዓት መስራት ወይም የእግዚአብሄርን ሰው እንደ ማወክ “ ያብራራዋል ፡፡
ያዕቆብ በትምህርታቸዉ እና በኑሮአቸዉ ግብዞች የነበሩትን አስተማሪዎች - አንድ ነገር እያስተማሩ ሌላ ነገር የሚያደርጉትን - በፍርድ እንደሚያዙ/እንደሚፈረድባቸው ያብራራል ፡፡ የሚያስፈልገው መላዉ ሰዉነትን ስለመቆጣጠር/ስለ መግዛት ነው (ቁጥር 2) ፡፡ መፅኃፍ አንደበት ምክንያት ሊሆንባቸዉ የሚችሉ ብዙ ክፉ ነገሮችን አካትቷል (መዝ 5፡ 9, 34፡ 13, 39፡ 1, 52፡ 4, ምሳ 26፡ 28, 28፡ 23) ፡፡ ማክአርቱር “ አንደበት በኃጢዓት፣ በስህተት እና አግባብ ባልሆነ መልኩ ለመናገር ትልቅ ኃይል እንዳለው “ ይናገራል ፡፡
ዋይርስቤ አንደበት “ የማዘዝ ኃይል “ እንዳለዉ ይገልፃል ፡፡ ቁጥር (3-5) ማሳያዎችን ይሰጣል፡ በአንድ ፈረስ ዉስጥ ያለች ትንሽ ልጓም ሁሉንም ፈረሶች እንደምትመራ (ቁጥር 3)፣ ትንሽ መሪ ምንም እንኳን በታላቅ ነፋስ ቢገፋም ትልቁን መርከብ እንደምትቆጣጠረው (ቁጥር 4) እና አንዲት ትንሽ እሳት በመላው ደን/ጫካ ዉስጥ እንደምትስፋፋ (ቁጥር 5) ፡፡ አንደበትም “ የማጥፋት ኃይል “ ያላት ትንሽ ነገር ናት ፡፡
ዋይርስቤ በ1871 የቺካጎን ታላቁን እሳት ምሳሌ ተጠቅሟል ፡፡ በኦሌሪይ በረት የጀመረዉ እሳት በቺካጎ በመስፋፋት 100,000 ሰዎችን ቤት አልባ አደረገ፣ 17,500 ሕንፃዎች ወደሙ/ፈረሱ፣ 300 ሰዎች ሞቱ በተጨማሪም ከ400,000,000 ዶላር በላይ ጠፋ ፡፡ አንደበትም ሰዉነትን ሁሉ መበከል የሚችል እሳት ነው ፡፡ “ በገሀነምም/በሲዖል በእሳት ይቃጠላል “ (ቁጥር 6) (ምሳ 26፡ 20-21) ፤ ማክአርቱር ሲዖል የሚለዉ ቃል ገሀነም (የእሳት ሸለቆ) ከሚለዉ የግሪክ ቃል እንደመጣ ይገልፃል ፡፡ “ በክርስቶስ ዘመን በኢየሩሳሌም ቅጥር ደቡብ ምዕራብ የሚገኘዉ ይህ ሸለቆ እንደ ከተማዋ ቆሻሻ መጣያ ያገለገለ እና በማያቋርጥ በሚነድድ እሳት የሚታወቅ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ያን ስፍራ የዘላለም የቅጣት እና የስቃይ ስፍራን ለመወከል ተጠቅሞበታል (ማር 9፡ 43, 45) “ ፡፡ ይህ ማለት አንደበታችሁ ሰዉነታችሁን የሚቆጣጠር ከሆነ የአንደበታችሁ ክፋት እግዚአብሄር ለእናንተ አቅዶላችሁ ከነበረዉ መንገድ በተለዬ መልኩ ይልካችኋል ማለት ነው ፡፡ ይህ አንደበታችንን ካልተቆጣጠርን ጠላት እንዲቆጣጠረን እንደምንሰጥ ያመለክታል ፤ ይህ ወደ ቀጣዩ ማሳያ ይመራል - ሰዉ በምድር ላይ ያለዉን ፍጥረት ሁሉ ሊገዛተምሯል ክፉ እና በካይ ከሆነዉ ከአንደበቱ ዉጪ (ቁጥር 7-8) ፡፡
ያዕቆብ (3፡ 9-12)፡ ዋይርስቤ አንደበት “ የማስደሰት ኃይል “ እንዳለዉ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄርን በአንደበታችን እናከብራለንበእግዚአብሄር አምሳል የተተሰራዉንም ሰው እንረግማለን (ቁጥር 9)፣ ማክበር እና መርገም ሁለቱም ከተመሳሳይ አፍ ዉስጥ ይወጣሉ (ቁጥር 10) ፡፡ ያዕቆብ አንድ አይነት ዉኃ ብቻ ሁለቱንም ሳይሆን ጣፋጭ ወይም መራር መስጠት የሚችልን የምንጭ ምሳሌ ተጠቀመ (ቁጥር 11) ፤ በተጨማሪም እንዴት አንድ የወይን ዛፍ የወይንን ፍሬ ብቻ ማፍራት እንደሚችል እና ወይራን ማፍራት እንደማይችል የበለስን ዛፍ ምስል ተጠቀመ (ቁጥር 12) ፡፡ ይህ ተመልሶ የምናምነው ከእኛ ዉስጥ የሚታየዉ እና የሚሰማዉ እንደሆነ ከሚያወራው ከያዕቆብ 2 ጋር መልሶ ያስተሳስረዋል ፡፡
በእያንዳንዱ ቀን አንድ ግብ በመኖር ሌሎችን እንዴት ተፅዕኖ ማድረግ እንደሚቻል አስቡ - በሌሎች ዉስጥ ክርስቶስን እና ሕይወትን በመናገር ፡፡
ያዕቆብ (3፡ 13-18)፡ ያዕቆብ በየዕለት ከዕለት አኗኗር ላይ ስለሚኖር ጥበብ ቀጠለ (ቁጥር 13) ፡፡ መራራ ቅንዓት እና የራስ ወዳድነት ፍላጎት ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ያልሆነ እና አጋንንታዊ ነው (ቁጥር 14-15) ነገር ግን “ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና ፡፡ ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት በኋላም ታራቂ ገር እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላበት ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት “ (ቁጥር 16-17) ፡፡ ይህ ሁሉ ከጽድቅ ፍሬ ይመጣል - እኛም ሰላምን አድራጊዎች እንሆናለን (ቁጥር 18) ፡፡
መደምደሚያ
በእርሱ እምነት በሚኖረን ጊዜ በዚህ እንመላለሳለን ፤ እርሱንም በመምሰል እንደ እርሱ እንመላለሳለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 357.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1889.
MacArthur, p. 1889.
MacArthur, p. 1889.
MacArthur, p. 1889.
Wiersbe, p. 358.
Wiersbe, p. 359.
Wiersbe, p. 339.
MacArthur, p. 1889.
Wiersbe, p. 360.
ጥያቄዎች
-
ያዕቆብ 3 አንደበትን ስለ መግታት የሚላቸዉ ብዙ አሉት ፤ ይህ አንደበታችንን ለማስለመድ ለምን አስፈላጊ ነው ? (መዝ 141፡ 3, ማቴ 12፡ 36-37, ሮሜ 3፡ 13-14, ያዕ 1፡ 26, 3፡ 1-12)
-
ያዕ (3፡ 1) አንደበትን ስለማስለመድ/ስለመግታት ጋር እንዴት ይተሳሰራል/ይገናኛል ? አስተማሪዎች ለምን የባሰን ፍርድ እንደሚቀበሉ ምን ታስባላችሁ ?
-
ያዕ (3፡ 8) ማንም አንደበትን መግታት አይችልም ይላል ፤ ማንም ሰዉ አንደበትን መግታት የማይችል ከሆነ አንደበታችንን እንዴት እናስለምደዉ/እንገታዋለን ?
-
ያዕ (3፡ 9-12) እንዴት በተመሳሳይ እንደበት እግዚአብሄርን እንደሚባረክ እና በእርሱ አምሳል የተሰራውን ሰዉ እንደሚረግም ያወራል ፤ ቀጣዩ ቁጥሮች ከላይ የመጣዉን ጥበብ በምድር ካለዉ ጋር ያነፃፅራሉ ፤ በጥበብ ላይ የሚያወሩት ጥቅሶች ከቀደመዉ ስለ መባረክ እና መርገም ከሚያወሩት ጥቅሶች ጋር እንዴት ይገናኛል ?
-
ጥበብ በያዕቆብ ዉስጥ ብዙ ጊዜ የሚታይ አንድ ጭብጥ ነው ፤ ያዕ (1፡ 5-8) ጥበብ እንዴት ማግኘት እንዳለብን ያወራል ? በያዕ (3፡ 17) የጠገለፀው ከላይ የመጣዉ ጥበብ እንዴት ነው ? መራራ ቅናት እና አድመኝነት እንዴት ተፅዕኖ ያደርሱብናል ያስ ጥበብ ከየት የመጣ ነው ?
-
በያዕቆብ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin James 3:5–6a
“So too, though the tongue is a small part of the body, it boasts great things. Consider how large a forest a small fire ignites. And the tongue is a fire.”
እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችሁን ጠይቅ ፡- ከአንደበቴ የሚወጣው ንግግር ሌሎችን ያንጻል ? የምናገረው የሚፈውሱ የሚያንጹ ቃላትን ነው ወይስ ትርጉም የሌላቸውን ? ያዕቆብ አንደበትን የሰውነት ትንሽ የሆነ አካል ክፍል ነገር ግን በትልልቅ ነገሮች ላይ ጭምር የሚመካ አድርጎ ይገልጸዋል ፡፡ ልክ መቅዘፊያ ጀልባን እንደሚቆጣጠር ሁሌ አንደበት በአንድ ጊዜ በጎም ይሁን አሉታዊ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም አለው ፡፡ ልክ ትንሽ እሳት ጫካውን ሙሉ እንደሚያቃጥል ፣ ጥቂት የሆነውም የአንደበት ቃል ትልቅ የሆነ አወንታዊ ተጽዕኖ ማሳደር ወይም ጥፋትን ማምጣት ይችላል ፡፡ ልክ ልጓም የፈረስን የጉዞ መስመር እንደሚቀጣጠር ሁሉ አንደበታችሁም የእናንተን የህይወት መስመር ይቆጣጠራል ፡፡
ምናልባት አንደበታችሁን መቆጣጠር የማይቻል ከባድ የሆነ ሀላፊነት ሊመስል ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር እንድያግዛችሁ ለምኑ ፡፡ እናንተም በእርሱ ስትኖሩ ፣ በእርሱ ስታርፉና ከእርሱ ጋር ስትመላለሱ ፣ እርሱ በጸጋ እና በኋይል ያበረታችኋል ፡፡ በቃሉ ላይ ብዙ ጊዜን ባሳለፋችሁ ቁጥር ፣ የእርሱንም እውነት ወደ ልባችሁ ባስገባችሁ ቁጥር እርሱ ደግሞ አብልጦ አንደበታችሁን ትገዙ ዘንድ ራስን በመግዛት ያበረታችኋል ፡፡ በስጋችሁም ሳይሆን በእርሱ መንፈስ ትመላለሳላችሁ ፡፡ በእግዚአብሔር ስትኖሩ የእርሱ መንፈስ የምትናገሩትን በጥበብ እንድትመርጡ ፣ ከመናገርም ይልቅ እንድታደምጡ ደግሞም በንግግራችሁ ፍቅርንና መልካምነትን በዙሪያችሁ ላሉ እንድታስተላልፉ ይመራችኋል ፡፡ ዛሬ አንደበታችሁን እንድትገዙ እግዚአብሔር እንድረዳችሁ እርሱን ለምኑ ፡፡ በኢየሱስ ሁሉም ነገር ይቻላል ፡፡
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዮሐንስ 15:5 — “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ።”
- ኤፌሶን 4:29 — “ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ ። “
- ያዕቆብ 1:19 — “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።