General Letters James

Don't Show Favoritism

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Law James 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 667 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በያዕቆብ ዉስጥ እንደ ፍፁም ሕግ በኢየሱስ ላይ መመልከታችንን እንቀጥላለን(1፡ 25) ፡፡ ለሁሉም ለሪቫይቭ ት/ቤት ማጠቃለያዉ ጥቅስ ማቴ (5፡ 17)፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም ለመሻር አልመጣሁም “ ፡፡ ሕጉን በመፈፀም ኢየሱስ ፍፁም ሕግ ነው ፡፡ በያዕቆብ ዉስጥ ጥያቄው በክርስቶስ ይህ ነፃነት ካለን በነፃነታችን ምን እናድርግበት የሚል ነው ፡፡

ትምህርት

ያዕቆብ (2፡ 1-13)፡ ዋይርስቤ የመጀመሪያዎቹን አራት ቁጥሮች “ የክርስቶስ አምላክነት “ በማለት ያጠቃልለዋል ፡፡ የመጀመሪያውአማኞች እንዴት በክርስቶስ እምነት ለሌሎች አድሎን በማሳየት እንዴት እንደሚቻል (ቁጥር 1) ፤ ይህ ጥቅስ አንድ ምሳሌ ወይም ትንሽ ስብከት ነው ፡፡ ቁጥር (2-4) ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡን የሁለት ሰዎች ማሳያ ይሰጣሉ - የሀብታም እና የድሀ ሰዎችን ፡፡ ኃብታሙ/ባለፀጋው ሰዉዬ ወገንተኝነት ቢደረግለት እና ድኃዉ ሰዉዬ ትክክል ባልሆነ መንገድ ከታዬ አማኞች ድሀዉን ሰዉዬ በክፉ አስተሳሰባቸዉ ፈርደዉበት ነበር ፤ ያ ማለት በአይናችን በመመልከት በመልክ እና ለእኛ ሊያደርግልን በሚችለዉ መሰረት አንዱን ከሌላዉ የተሻለ እንደሆነ ወሰንን ማለት ነው ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ አማኞች አድሎ ማድረግ የሌለባቸዉን አራት ምክንያቶችን ይሰጣል፡

  1. እግዚአብሄር በሁኔታቸዉ ላይ ያለምንም ፍርድ ድሆችን ይቀበላል (ቁጥር 5) ፡፡

ባለፀጎች ሌሎችን በተለይም አማኞችን ለማስጨነቅ እድላቸዉን ይጠቀሙበታል (ቁጥር 6-7) ፤ “ መልካም ስም “ የሚለዉ በክርስቶስ ተጠምቀዉ የነበሩትን አማኞች ያመለክታል (ቁጥር 7) ፡፡

ወገንተኝነት ማሳዬት ሌሎችን መዉደድ የሚለዉን የእግዚአብሄርን ሕግ ይጥሳል (ቁጥር 8-11) ፤ “ የንጉስ ሕግ “ “ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ዉደድ “ የሚል ነው (ቁጥር 8) ፡፡ ኃብታሞችንም ድኃዎችንም ሁለቱንም እንድንወድድ ተጠርተናል ፤ ነገር ግን አድሎ የምናሳይ ከሆነ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት እናደርጋለን ፡፡ ቁጥር 10 አማኞችን በማንኛዉም መንገድ ሕጉን ሙሉ ለሙሉ መጠበቅ እንደማይችሉ አሳሰባቸው ፤ እንዲሁም የምንጠብቀዉን እና የምንጥለዉን ሕግ መምረጥ እና ማንሳት አንችልም ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ አንዳንድ ፈሪሳዊያን በዚህ ነገር ጥፋተኝነትን ጀምረዉ እንደ ነበር ይገልፃል፡ “ የሕጉን አንዳንድ መስፈሮትችን ለምሳሌም ሰንበትን መጠበቅን በጥንቃቄ በመመልከት ሌሎችን ለምሳሌም ቤተሰብ ማክበርን ችላ አሉ ፤ ኃጢዓት ሕግ ሰጪ የሆነዉን የእግዚአብሄር ፍፁም ቅድስናን መጣስ ነው “ ፡፡ ያዕቆብ በሚታወቀዉ አለም ዉስጥ ተበትነዉ ለነበሩት እና በነበሩበትም መከራ እየተከናወነ ለነበረበት አማኞች ሁሉ አደረሰ/መልዕክቱን አስተላለፈ ፤ ምናልባትም ከራሳቸዉ ላይ መከራን/ስደትን ለማስወገድ ለመሞከር ለኃብታም ወገንተኝነትን እያሳዩ ነበር ፡፡ ያዕቆብ የእግዚአብሄርን ፍቅር ለሌሎች ከማሳየት ይልቅ ለራሳቸዉ ለሚያስፈልጋቸዉ ነገር በመመልከት አማኞች ግብዞች እንዲሆኑ አልፈለገም ፡፡

የእግዚአብሄርን ሕግ የሚጥሱ/የሚተላለፉ በእርሱ ይፈረድባቸዋል (ቁጥር 12-13)፡ በኃብታም በመዳኘት ከመጨነቅ ይልቅ በእግዚአብሄር በነፃነት ሕግ ስር በተናገሩበት እና በአደርጉበት መንገድ ራሳቸዉን ይመለከታሉ (ቁጥር 12) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አማኞች የፍቅር ሕግ በሆነዉ በነፃነት ህግ ይዳኛሉ ፡፡ ወገንተኝነትን ተግባራዊ የማያደርጉ ነገር ግን ፍቅርን እና ምህረትን ተግባራዊ የሚያደርጉ አማኞች በድል ደስታ በፍርድ ይቀመጣሉ ፤ ምህረትን የማያደርጉ ምህረትን አይቀበሉም “ በማለት ይናገራል ፡፡ እዉነታው ለሁሉም ፍቅርን እና ምህረት ማሳየት እንዳለብን ነው ፡፡

ያዕቆብ (2፡ 14-19)፡ የፕሮቴስታንት/የወንጌል አማኞች ለዉጥ መሪ ከሆኑት ዉስጥ አንዱ ማርቲን ሉተር መዳናችን/ድነታችን በእምነት በኩል ብቻ ሊመጣ እንደሚችል የመዳንን/የድነትን አስተምሮ ተናግሯል ፤ ሉተርን በ1522 በአዲስ ኪዳን መግቢያዉ ላይ ያዕቆብን “ በገለባ የተሞላ መልዕክት “ ብሎ በመጥራት የያዕቆብን መፅኃፍ በመፅኃፉ ክፍል ዉስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ በማጣቀሻው ላይ አስቀመጠው ፡፡ ሉተርን የጳውሎስን የእምነት ፅኁፍ መረጠ (ሮሜ 3፡ 28) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ሉተርን በዚህ ስፍራ ምንም ምርጫ አልነበረውም ምክንያቱም “ መልካም ስራ ሊያድናቸዉ እንደሚችል በሚነገሩ ሰዎች ተከብቦ ስለ ነበር ፤ እግዚአብሄር ብቻውን በእምነት ብቻ ሊያድን እንደሚችል ስለሚያውቅ “ በማለት ይናገራል ፡፡

ያዕቆብ “ እምነት ከነበራቸዉ መልካም ስራ መስራት አያስፈልግም በሚሉት ስራ በሌለዉ እምነት ላይ ያሉትን ኢላማ በማድረግ እየወሰደ ነበር ፤ እዉነታው እምነት ካላችሁ መልካም ስራ በተፈጥሮ ዉጤት ይሆናል / ሆኖ ይመጣል “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ አማኞች በመልካም ስራ መዳን አይችሉም ማለት መልካም መስራትን ማቆም አለባቸዉ ማለት እንዳልሆነ ያመለክታል፡ “ ከምክንያቱ የሚመጣዉን ዉጤት መጠበቅ አትችሉም ፤ የአፕል ዛፍ የአፕል ፍሬ እንደሚያፈራ እምነትም መልካም ስራን ያመጣል/ያመነጫል/ያፈራል (ሉቃ 6፡ 43-44) “ ፡፡ እምነትን እና መልካም ስራን እንደ ጠላት ከማየት ይልቅ በአንድ ላይ መስራት እንደሚችሉ ማየት ይቻላል ፡፡ “ በእኛ ዉስጥ ሁለት የእግዚአብሄር ስራ ክፍሎች አሉ ፤ እምነት ሰዉን ወደ ድነት ሲያመጣው ያንን ሰው መልካም ስራ ደግሞ ወደ ሙሉነት ያመጣዋል ፡፡ እምነት ምክንያቱ ሲሆኑ ስራዎቹ ደግሞ ዉጤቶቹ ናቸው “ ፡፡

በቁጥር 14 ያዕቆብ ሰዉ እምነት ቢኖረው ነገር ግን ስራ ከሌለዉ ምን ይጠቅመዋል በማለት ጠየቀ ፤ ለተራቡ፣ ለበረዳቸው እና ለድሆች ምንም እርዳታ ሳይሰጡ ባዶ እዉቅና/አስተሳሰብ ቢሰጧቸው ምን ይጠቅማል (ቁጥር 15-16) ? ስለዚህም እምነት ያለ ስራ የሞተ/ከንቱ/ባዶ ሀሳብ ነው (ቁጥር 17) ፡፡ ቁጥር 18 ልዩነቱን ያነፃፅራል፡ “ ነገር ግን አንድ ሰው ፡- አንተ እምነት አለህ እኔም ስራ አለኝ ፤ እምነትህን ከስራህ ለይተህ አሳየኝ እኔም እምነቴን በስራዬ አሳይኃለሁ ይላል “ ፡፡

ቁጥር 14ማሪቲን ሉተርን የያዕቆብን መፅኃፍ እንዲተወዉ ያደረገዉን ቋንቋ ይጠቀማል - ድነት በመልካም ስራ በኩል ሊገኝ እንደሚችል የሚናገር ይመስላል ፡፡ ሀሳቡ ከዚያ ይልቅ እምነታችን በተጨባጭ በስራ መታየት አለበት የሚል ነው ፡፡ ጥያቄው የሚሆነው የአዋጅ/የንግግር አማኞች ያለ ስራ ይድናሉ ? አንዳንድ ጊዜበቀላሉ ስለምናዉቀዉ የሰዎች ድነት እንደነቃለን ምክንያቱም እምነታቸዉ በፍፁም በስራ ሲደረግ ስለማናይ ፡፡

ቁጥር 19 አጋንንትም በእግዚአብሄር እንደሚያምኑ እና እንደሚንቀጠቀጡ ይናገራል (ማር 3፡ 11-12, 5፡ 1-13, ሉቃ 8፡ 31) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አጋንንቶችም እንኳን በእግዚአብሄር የእዉቀት እምነት አላቸው ነገር ግንወደ ድነታቸዉ እንደማይወስዳቸው “ ይናገራል ፡፡ በእምነታችን በማንመላለስ ጊዜ ሰዎች ድነታችንን ሊያዩት ይችላሉ እዉነተኛ ድነትን እያገኘን/እየቀመስን ነዉስ ?

ያዕቆብ (2፡ 20-26)፡ ያዕቆብ እምነት ያለ ስራ ከንቱ/ጥቅም እንደሌለዉ በመናገር (ቁጥር 20) የአብርኃም እምነት በመታዘዝ ልጁን ነመሰዊያዉ ላይ ባቀረበ ጊዜ እንዴት እንደተረጋገጠ አመለከተ (ቁጥር 22) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እምነት በንድ ላይ ከስራ ጋር እንደሚሰራ እና በሁለቱም መካከል ግንኙነት እንዳለ ግንኙነታቸውም ስራ እምነትን ፍፁም እንደሚያደርገዉ ያም እድገት እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡ ቁጥር 24 በእምነት ብቻ ሳይሆንሰዉ በስራም እንደሚፀድቅ በመናገር ጥያቄን ይፈጥራል ፤ እዉነታው ሰዉ እምነቱን በስራ እንደሚኖርበት/እንደሚገልጥ ነው ፡፡ ቁጥር 25 ረዓብ በእምነቷ ሰራች “ ነገር ግን የዉስጥ መቀየሯን ለማረጋገጥ ድርጊት አስፈላጊ ነበር “

መደምደሚያ

ድነት/መዳን በእምነት በኩል ነው ነገር ግን እምነትን በስራችን ልንኖረዉ ይገባናል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 350.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p, 1665.

  3. Nelson’s Commentary, p. 1665.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1665.

  5. Nelson’s Commentary, p. 1665.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1665.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1666.

  8. Nelson’s Commentary, p. 1666.

  9. Nelson’s Commentary, p. 1666.

  10. Nelson’s Commentary, p. 1666.

  11. Nelson’s Commentary, p. 1666.

  12. Nelson’s Commentary, pp. 1666-1667.

  13. Nelson’s Commentary, p. 1668.

  14. Nelson’s Commentary, p. 1668

ጥያቄዎች

  1. አድሎ/ወገንተኝነት ለምን እንደ ኃዓት ይታያል/ይቆጠራል (ያዕ 2፡ 9) ? ኢየሱስ ስለ ወገንተኝነት/አድሎ እንዴት አስተማረ ? (ማቴ 23፡ 1-7, ሉቃ 14፡ 7-14)
  2. ኢየሱስ የሰዎች አክባሪ ያልሆነዉ እንዴት ነው (ማቴ 22፡ 16) ? ከዉጨኛዉ መልክ/ገፅታ ይልቅ ጌታ የትኛዉን የሰዉ አካል ይመለከታል (1ሳሙ 16፡ 7) ? በወንጌላት ላይ ኢየሱስ ልባቸዉን እንዲመለከቱ የመረጣቸዉ ጥቂት ምሳሌዎች እነማን ናቸው ? (ማቴ 9፡ 9-13, ሉቃ 21፡ 1-4)
  3. በክርስትና ዉስጥ እምነት ቁልፍ አስተምሮ የሆነዉ ለምንድን ነው (ሮሜ 14፡ 23, 2ቆሮ 5፡ 7, ኤፌ 2፡ 8-9, ዕብ 11፡ 6) ? እንደ ያዕቆብ አገላለፅ ያለ ስራ እምነት ብቻ መኖር መልካም ያልሆነዉ ለምንድን ነው (ያዕ 2፡ 14-18) ?
  4. በያዕ (2፡ 15-16) ሰዎችን በተግባራዊነት በሚያስፈልጋቸዉ ነገር ስለ መርዳት ምን ልትማሩ ትችላላችሁ ? ይህን ታላቅ እምነት ካለዉ ጋር እንዴት ይወራረዳል ?
  5. ያዕቆብ አብርኃምን እና ረዓብን በመጠቀም የሚያድን እዉነተኛ እምነትን እንዴት አሳዬ ? (ዘፍጥረት 15, 22, ኢያ 2, 6፡ 15-25)
  6. በያዕቆብ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin James 2:14–16

“What good is it, my brothers, if someone says he has faith but does not have works? Can his faith save him? If a brother or sister is without clothes and lacks daily food and one of you says to them, ‘Go in peace, keep warm, and eat well,’ but you don’t give them what the body needs, what good is it?”

እምነት በጎ ስራን እንድትሰሩ ያደርጋችኋል ፡፡ ይህ በስራ የተገለጠ እምነታችሁ ነው ፡፡ በጎ ስራዎች ውስጣዊ የሆነ እምነት የሚታዩ ምልክቶች ናቸው ፡፡ በርግጥ የዳናችሁት በኢየሱስ ላይ ብቻ ባላችሁ እምነት ነው ፡፡ እናንተም የእግዚአብሔር ፍጥረቱ ናችሁና ትሰሩት ዘንድ ቀድሞ ስራን አዘጋጅቷል ፡፡ ስለዚህም ለእግዚአብሔር መንግስት ደግሞም ይህን ለሚያዩ ሁሉ ለእግዚአብሔርና ለሌሎች ያላችሁን ፍቅር ትገልጹ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በጎ ስራን እንድትሰሩ ይቀሰቅሳችኋል ፡፡ በጎ ስራን ግዴታ ስላለባችሁ አትሰሩም ይልቁንም በኢየሱስ ላይ ያላችሁ እምነት መገለጫ ስለሆነ እንጂ ፡፡

ጎረቤቶቻችሁ የኤለክትሪክ ኃይል ቢጠፋባቸው ፣ እንደ እግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ አድርጋችሁ ምግብን በቤታችሁ አዘጋጅታችሁ ትጠሩዋቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሊያሳስባችሁ ይችላል ፡፡ እናንተም መንፈስ ቅዱስ በማጥፋት ፣ ባለማዳመጥ ጸጥ ያለ ምሽትን ማሰለፍ መምረጥ ትችላላችሁ ፡፡ ወይም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ያለምንም ስስት ጊዜያችሁን ፣ አቅማችሁን ደግሞም ሀብታችሁን በመስጠት እምነታችሁን ወደ ስራ ትለውጣላችሁ ፡፡ ጎረቤቶቻችሁን የምትወዱት በጎ ስራ መስራት ስላለባችሁ አይደለም ይልቁንም በኢየሱስ በማመን መመላለስ ፣ እምነታችሁን በፍቅር እንድትገልጹ ስለሚያደርጋችሁ እንጂ ፡፡ ዛሬ የእርሱን ፍቅር ለሌሎች በመግለጽ በኩል ይመራችሁ ዘንድ ጌታን ጠይቁ ፡፡

“ ወንድሞቼ ሆይ ፥ እምነት አለኝ የሚል ፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል ? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ ፥ ከእናንተ አንዱም ፦ በደኅና ሂዱ ፥ እሳት ሙቁ ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል ? “

  • ያዕቆብ 2፡14-16

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴውስ 22:36–39 — “ መምህር ሆይ ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት ? ብሎ ጠየቀው ። ኢየሱስም እንዲህ አለው ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች ፥ እርስዋም ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት ። “

ሮሜ 3:28 — “ ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና ። “

ኤፌሶን 2:8–10 — “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። እኛ ፍጥረቱ ነንና ፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ። “