Trials, Testings, And Maturity
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Perfect Law James 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ የያዕቆብ መፅኃፍ ጥናታችንን እንጀምራለን፡፡ መፅኃፉ በፀኃፊው የተሰየመ ነው (1፡ 1) ፡፡ ማክአርቱር በአዲስ ኪዳን ስማቸዉ ያዕቆብ የነበሩ አራት ሰዎች ነበሩ ነገር ግን ሁለቱ ብቻ ለፀኃፊነት በእዉነተኛነት እጩነት እንደሆነ አመልክቷል ፤ የዘብድዮስ ወንድ ልጅ ያዕቆብ እና የኢየሱስ የእናቱ ወንድም ናቸው ፡፡ የዘብድዮስ ልጅ ያዕቆብ (ወዲያዉኑ የታወቀዉ ያዕቆብ) በተፃፈዉ ደብዳቤ ፊት ተሰዉቶ/ተገድሎ ስለ ነበር ፀኃፊው የኢየሱስ የእናት ልጅ እና የይሁዳ ወንድም ያዕቆብ ይሆናል ማለት ነው (ማቴ 13፡ 55, ማር 6፡ 3, ዮሐ 7፡ 5) ፡፡ ያዕቆብ ኢየሱስ ለእርሱ እና ለደቀ መዛሙርቱ እስኪታይ ድረስ አላመነም ነበር (1ቆሮ 15፡ 7) ፡፡ በጊዜው ያዕቆብ በኢየሩሳሌም በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ አንዱ ዋና ሰዉ ሆነ (ሐዋ 12፡ 17) ፤ እንደ ተከበረ መሪ ያዕቆብ በኢየሩሳሌም ኮሚቴ ላይ በክርክሩ ጭብጥ ላይ ነበር (ሐዋ 15፡ 13) ፡፡
ያዕቆብ “ ለተበተኑት ለአስራ ሁለቱ ነገዶች “ ፅፏል (1፡ 1) ፤ እነዚህ ከእስጢፋኖስሰማዕትነት ኃዘን በኋላ ወይም በሄሮድስ አግሪጳ መከራ በኢየሩሳሌም በመከራ ተበትነዉ የነበሩ የአይሁድ አማኞች ነበሩ (ሐዋሪያት ስራ 12) ፡፡ መፅኃፉ ምናልባትም ከክርስተስ ሞት (44-49 በኋላ) መካከል (በሐዋሪያት ስራ 12 እና 15) መካከል የተፃፈ ነበርምክንያቱም የኢየሩሳሌም ጉባኤ ከክርስቶስ ሞት በ49 በፊት ከመገናኘቱ በፊት የተፃፈ ነበር ፡፡ ክርስቶስን ተቀብለዉ/ይዘዉ ለነበሩት አይሁዶች የተፃፈ ነበር፡፡
ዋይርስቤ የያዕቆብን መፅኃፍት የሚያጠቃልሉ አራት አስፈላጊ ጭብጦችን አመልክቷል፡
- ዳግም መወለድ አለብን ፡፡
- በእግዚአብሄር ቃል ብርኃን ራሳችንን መፈተን/መመርመር አለብን ፡፡
- ምንም ያክል ዋጋ ቢያስከፍልም እግዚአብሄር የሚያስተምረንን ማክበር/መታዘዝ አለብን ፡፡
- ለተጨማሪ/ለሚበልጥ ፈተናዎች እና መከራዎች የተዘጋጀን መሆን አለብን ፡፡
በያዕቆብ መፅኃፍት ለክርስቶስ ሐረጋችን/ቃላችን ፍፁም ሕግ የሚል ነው (ያዕ 1፡ 25) ፡፡ ነፃነታችን ወደ ቤተ መቅደስ፣ ወደ ኃይማኖታዊ ስርዓት እና በመስዋዕት ላይ በመመልከት ሳይሆን በኢየሱስ ፍፁም በሆነዉ ሕግ ላይ በመመልከት ይመጣል ፡፡ ማቴዎስ ፍፁሙ ሕግ ክርስቶስ እንደሆነ ፅፏል (ማቴ 5፡ 17, ገላ 2፡ 4, ዕብ 10፡ 1) ፡፡
ትምህርት
ያዕቆብ (1፡ 1-8)፡ ያዕቆብ ራሱን “ የእግዚአብሄር እና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ “ በማለት ያስተዋዉቃል በሁሉም በአእስራኤል 12 ነገዶች አማኞች እንደ ነበሩ አመለከተ (ቁጥር 1) ፡፡ ቁጥር (2-4) ንግግሩን በፈተናዎች እና በመከራዎች ላይ ይጀምራል ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር (2-5) ለመግለፅ እነዚህን ቁልፍ ቃላቶች እና ኃሳቦች ይጠቀማል፡
መቁጠር (ቁጥር 2)፡ በመከራ ዉስጥ በምናልፍ ጊዜ እንደ ደስታ መቁጠር ወይም የደስታ ኃሳብ ሊኖረን ይገባል ፡፡ ዋይርስቤ መቁጠር የሚለዉን ቃል “ እንደ መዉሰድ/መመዘን “ በመግለፅ በኑሮአችንን በመመዘን/በመመርመር ዉስጥ ነገሮች ከእግዚአብሄር የመጡ ስለሆኑ በማለት በዚያ መልኩ መቁጥር እንደምንችል ይገልፃል ፡፡
ማወቅ (ቁጥር 3)፡ በፈተናዎች ዉስጥ በምናልፍ ጊዜ ብስለትን እና ትዕግስትን እንማራለን እምነታችንም ይጠነክራል ፡፡ የአይሁድ አማኞች በመከራዎች ዉስጥ ሲያልፉ በጌታ በጥበብ ያድጋሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እግዚአብሄር የሚሰጠዉ ጥበብ ከችግሩ እንዴት እንደሚወጣ የሚያስፈልግ ማስረጃ ሳይሆን ከንድ አስቸጋሪ ነገር እንዴት እንደሚቻል ማስተዋል እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡
መፍቀድ (ቁጥር 4)፡ ይህ እድገት ፍቃዳችንን ለእርሱ ለማስገዛት ፍቃደኞች በምንሆን ጊዜ ይሆናል ፡፡
መጠየቅ (ቁጥር 5-8)፡ ያዕቆብ ስለ ጥበብ አንባቢዎቹን ጥበብ ጎድሏቸዉ ከነበረ እግዚአብሄር በልግስና እንደሚሰጣቸዉ ተስፋ በመስጠት እግዚአብሄርን እንዲጠይቁት በመናገር ቀጠለ (ቁጥር 5) ፡፡ ይሁን እንጂ ሳይጠራጠሩ መጠየቅ እንደ ነበረባቸዉ አስጠነቀቃቸው ምክንያቱም ተጠራጣሪ በፍፁም እግዚአብሄር ማንኛዉንም ነገር ይመልስልኛል ብሎ አይጠብቅም (ቁጥር 6-7) ፡፡ ያዕቆብ ተጠራጣሪ አማኞችን “ የተገፋ እና የተነቃነቀን የባህር ማዕበል እንደሚመስል “ ይገልፃል ፡፡
ቁጥር (2-3) የሚሉትን ለማጠቃለል ፈተና እና ችግር ትዕግስትን ያመጣል ፡፡ ያ ማለት አሁንም ፈተናን እና መከራን መጠበቅ እንችላለን ምክንያቱም ያ ዕድገት የሚቀጥል ሂደት ስለሆነ እና ያ ትዕግስት ደስታን ስለሚያመጣ ፡፡ ሂደቱ እድገት/ብስለትን እና ጥበብን ያመጣል ነገር ግን ጥበብ ከሌለ መጠየቅ ይቻላል ፡፡ ይሁን እንጂ እምነት የሌላቸው አይጠይቁ ምክንያቱም እግዚአብሄር በዚያ ስለማይከብር ፡፡ ቁጥር 8 አንድ የሚወላዉል ሰው ሙሉ በሙሉ ያልተረጋጋ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህን “ ሁለት ኃሳብ ያለው “ እንደ መሆን ወይም ቃል በቃል “ ሁለት ነፍስ “ ያለዉ በማለት ይገልፃል ፤ ያ ማለት “ የሰዉ አንዱ አካል በእግዚአብሄር ላይ ሲሆን ሌለኛዉ አካለ ደግሞ በአለም ላይ በመሆኑ በዉስጡ የማያቋርጥ ግጭት ይኖራል “ ማለት ነው ፡፡
ያዕቆብ (1፡ 9-11)፡ ቁጥር (9-11) በእነዚህ መከራዎች ዉስጥ የባለፀጋን እና የድኃን ሁለት ማሳያዎች ይሰጣሉ ፡፡
ያዕቆብ (1፡ 12-18)፡ ያዕቆብ መከራዉን የሚታገስ የተባረከ እንደሚሆን እና እግዚአብሄር ተስፋ ገብቶት የነበረውን የህይወት አክሊል እንደሚቀበል ገልፆአል (ቁጥር 12) ፡፡ ቁጥር (13-18) “ እንዴት ፈተና እንደሚሸነፍ/እንደሚያዝ “ ይገልፃል ፤ ፈተና ከእግዚአብሄር አይመጣም (ቁጥር 13) ፡፡ ፈተና ከሰዉ ከራሱ ክፉ ምኞት በመምጣት ወደ ኃጢዓት ቀጥሎም ወደ ሞት ይመራል (ቁጥር 14-15) ፡፡
ያዕቆብ (1፡ 19-27)፡ ፈተናዎች የተለያዩ እና ከእግዚአብሄርም ስለሚመጡ በእግዚአብሄር ፊት ፃድቅ ሆነን ለመገኘት “ ለመስማት የፈጠንን ለመናገር እና ለመቆጣት የዘገየን “ መሆን አለብን (ቁጥር 19-20) ፡፡ ስለዚህ የስነ-ምግባር ቆሻሻን እና ክፋትን በማስወገድ በዚህ ፋንታ በትህትና የእግዚአብሄርን ቃል በምንቀበል ጊዜ ወደ ክርስቶስ ስለሚያመለክት ሊያድነን ይችላል (ቁጥር 21) ፡፡ አንዴ ቃሉን ከሰማን ቃሉንም አድራጊዎች መሆን አለብን (ቁጥር 22) ፤ አድራጊዎች ካልሆንን በራሳችን ላይ እና በስጋዊ ፍላጎቶቻችን ላይ ብቻ የምንመለከት ነን ማለት ነው (ቁጥር 23) ፡፡ ነገር ግን ወደ ክርስቶስ ሕይወት እና ወደ እግዚአብሄር ቃል በጥንቃቄ የሚመለከት/የሚያደርግ በሚያደርገዉ የተባረከ/ች ይሆናል (ቁጥር 25) ፡፡
ስለዚህ ምን እናድርግ ? አንደበታችንን ስንገዛ ኃይማኖታችን ጥቅም የሌለዉ አይሆንም እንዲሁም ደግሞ ራሳችንንም አናታልልም (ቁጥር 26) ፡፡ “ ንጹሕ የሆነ ነዉርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሄር አብ ዘንድ ይህ ነው ፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች፣ ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰዉነትን መጠበቅ ነው “ (ቁጥር 27) ፡፡
መደምደሚያ
የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ቁጥሮች እምነታችንን እንዴት እንደምንኖረዉ በጣም ተግባራዊ የሆኑ ትዕዛዞች ናቸው - ለራሳቸዉ ስለማያስቡ/ስለማይጠነቀቁ ለባልቴቶች እና ወላጅ ለሌላቸዉ ልጆች መጠንቀቅ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1879.
MacArthur, p. 1879.
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: Hebrews (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 336.
Wiersbe, p. 337.
Wiersbe, p. 338.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 1663.
Wiersbe, p. 339.
Wiersbe, p. 340.
Nelson’s Commentary, p. 1663.
Nelson’s Commentary, p. 1663.
Wiersbe, p. 341.
ጥያቄዎች
-
የያዕቆብን መፅኃፍ ማን ፃፈው የታቀዱት ተደራሲያንስ እነማን ነበሩ ?
-
12 ነገዶች የተበታተኑበት አንዱ ምክንያት ምን ነበር ? (ሐዋ 7፡ 54 – 8፡ 1, 11፡ 19)
-
ብዙ መከራ በሚደርስባችሁ ጊዜ ያዕቆብ ሁሉንም እንደ ደስታ ቁጠሩት ለምን ይላል (ያዕ 1፡ 2) ? ደስታን ለማግኘት የሚቻል የማይመስል አስቸጋሪ መከራ ደርሶባችሁ ያውቃል ወይስ እየደረሰባችሁ ነው ? በኃይለኛ/በአስቸጋሪ መከራ ላይ እንዴት አመለካከታችሁን መቀየር ትችላላችሁ ? (ያዕ 1፡ 3-4, 1ጴጥ 5፡ 10)
-
ለመናገር ቀላል የሆነዉ በመከራ ዉስጥ በሚታለፍ ጊዜ ደግሞ የማይባለዉ ነገር ምንድን ነው (ያዕ 1፡ 13)? ፈተና ከየት ነዉ የሚመጣው ? ወደ ፈተና የመግባት ዉጤቶቹ ምንድን ናቸው ?
-
ቃሉን በሚሰማ እና ቃሉን በሚያደርግ መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ?
-
በያዕቆብ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin James 1:5–6
“Now if any of you lacks wisdom, he should ask God, who gives to all generously and without criticizing, and it will be given to him. But let him ask in faith without doubting. For the doubter is like the surging sea, driven and tossed by the wind.”
ጌታ በምድር ፈተናና ችግር እንደሚገጥማችሁ ይናገራል ፡፡ እነዚህ ፈተናዎች በእናንተ ዘንድ ትዕግስትን ያስገኛሉ ፡፡ ልክ የድንገተኛ አደጋ የስልክ ጥሪ ሲደርሳችሁ ፣ የህክምና ምርመራ ውጤት ሲደርሳችሁ ፣ በግንኙነት ውስጥ ያለው ጉዳት ሲደርስባችሁ ወይም ደግሞ ተስፋ ስትቆርጡና ቀጣዩን እርምጃ መራመድ ሲያቅጣችሁ ፣ ስለ ትዕግስታችሁ መጠንከር መብዛት ምንም ትዝ ላይላችሁ ላታስቡ ትችላላችሁ ፡፡ ነገር ግን ያዕቆብ አማኞችን በፈተና ውስጥ እንኳ ሆነው ይህን እንደ ትልቅ ደስታ እንድቆጥሩት ይመክራቸዋል ፡፡ ይህንን አስታውሱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ሊሆን ፣ ከእናንተ ጋር ሊራመድ ደግሞም ቀና ሊያደርጋችሁ ቃል እንደገባ ፡፡
በክፉ ቀናት ውስጥ ማለፍ ትችሉ ዘንድ ጥበብና ኋይል ስለሚያስፈልጋችሁ፣ በእምነት እግዚአብሔርን በመፈለግ ጥበብን እንድሰጣችሁ ጠይቁት ፡፡ እግዚአብሔርን ከመጠየቃችሁ በፊት ሁሉም ነገር እንድኖራችሁ አያስፈልግም ፡፡ እርሱ ያለምንም ማንገራገርና እናንተን ሳይተች በልግስና እንደሚሰጣችሁ ተናግሯል ፡፡ እርሱ ከወጀቡ ይጠብቃችኋል ስለዚህም የዚህ ዓለም ጭንቀቶች ፍርሀቶች እናንተን አያናውጧችሁም ፡፡ እግዚአብሔር በጣም ይወዳችኋል ደግሞም ችግሮቻችሁን ያያል ፡፡ እግዚአብሔር ጥበብ ይሰጣችሁ ዘንድ ጠይቁት እርሱም ይመልስላችኋል ፡፡
“ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ፥ ለእርሱም ይሰጠዋል ። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን ፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና ። “
- ያዕቆብ 1፡5-6
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 25:9 — “ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
ዕብራውያን 11:6 — “ ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል ። “
ያዕቆብ 1:2–3 — “ ወንድሞቼ ሆይ ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።