Personal Responsibility For Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዕብራዉያን 13 አጠቃላይ የዕብራዉያን መፅኀፍ መደምደሚያ ምዕራፍ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ግላዊ ማሳያዎችን ያደረገባቸው የሮሜ 16፣ የ 1ቆሮንቶስ እና የ 2ቆሮንቶስ ትዝታ ነው ፡፡ የእብራዉያን ፀኃፊ ባይታወቅም በምዕራፍ 13 የመደምደሚያው አስተያዬት/ሀሳብ ስለ ፀኃፊዉ ጥሩ ነገርን ይገልፃል ፡፡ ለምሳሌ በምዕራፉ ዉስጥ እያንዳንዱ ቁጥር አጭር እና እጥር ምጥን ያሉ ናቸው ፤ እያንዳንዳቸው (በቲዊተር፣ በማህበራዊ ሚዲያ) ላይ መፃፍ የሚችሉ ናቸው ፡፡ ጳዉሎስ ለምን ፀኃፊዉ እንዳልሆነ ይህ እንድ ፍንጭ ነዉ ምክንያቱምስለ ጳዉሎስ ፅኁፍ እጥር ምጥን ያለ ስለሌለ ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (13፡ 1-3)፡ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቁጥሮች ተገቢ ስለሆኑ ግለሰባዊ ጉዳዮች ላይ ያወራሉ ፤ በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ ልንወዳቸዉ የሚገቡ ሰዎስት አይነት ሰዎች አሉ፡
- ሌሎች አማኞች፡ ቁጥር 1 “ የወንድማማችነት መኖር ይኑር/ይቀጥል “ በማለት ይናገራል ፤ እዚህ ጋር ለመዉደድ የተጠቀመዉ የግሪክ ቃል ፊሊያ ሲሆን ካገኘነዉ ከወንድማማች መዋደድ ጋር ተመሳሳይ ቃል ነው ፡፡ ቀጥሉ/ይኑር የሚለዉ ቃል አታቋርጡ ወይም ፅኑ ማለት ነው ፤ እንደ ሐዉልት/መታሰቡ ከምንተረጉመዉ የግሪክ ቃል የመጣ ነው ፤ ስለዚህም ጥቅሱ “ የፍቅራችሁ መታወቂያ/መታሰቢያ አንዱ ሌላዉን በመዉደድ “ ይሁን በመባል ሊነበብ ይችላል ፡፡ ስለ ብሉይ ኪዳን እና ስለ አዲስ ኪዳን የምታዉቁት ሁሉም ነገር በፍቅራችሁ የሚኖር ነው ፡፡
እንግዶች፡ እዚህ ጋር ለፍቅር ያለዉ ቃል ፍቅርን ለእንግዶች ማሳየት የሚል ትርጉም ካለው ፊሊያን ከሚለዉ ቃል የመጣ ነው (ቁጥር 2) ፡፡ አማኞች ለእንግዶች ማሰባቸዉን እና እንክብካቤ ማድረግን መርሳት ወይም ችላ ማለት የለባቸውም - ይህን ማድረግ እንዳለባቸዉ ራሳቸዉን ማሳሰብ አለባቸው ! እንግዳ ተቀባይነት አንዳንድ ጊዜ ለመለዓክት ሊሆን ችሏል ፡፡
እስረኞች፡ “ ከእነርሱ ጋር በእስር ቤት እንዳላችሁ “ የሚለዉ ፅኁፍ/ሐረግ “ ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደታሰራችሁ “በማለት ሊተረጎም ይችላል (ቁጥር 3) ፡፡ በእስር ቤት እስረኛን ከጎበኛችሁ በፍፁም አትረሱትምም አታገኙአቸዉም ፡፡ በእስር ቤት አገልግሎት የሚሳተፉ ብዙ ጊዜ ለዚህ ነገር በኃይል የተሰጡ ናቸዉ ምክንያቱም ፍሬዉን ስለሚያዩ ፡፡ በእስር ቤት ካሉት አንዳንዶቹ በዚያ የሆኑት ባላደረጉት ነገር ነው ፤ ከደቀ መዛሙርቱ አብዛኛዎቹ ወንጌልን በመስበካቸዉ በእስር ቤት ተቀምጠዉ ነበር ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 4)፡ እዚህ ጋር ፀኃፊው ወደ ጋብቻ በመሄድ ጋብቻን በሁሉም ዘንድ “ የተከበረ እንደሆነ “ ማለትም ለሁሉም የሚያስደንቅ ዋጋ/ክብር እንዳለዉ ይገልፃል ፡፡ የመኪናን ሞተር ስራ በመረዳት ላይ ጠበብት የሆኑ ወይም ደግሞ የአጋዘንን ደብዛ/ስርዓት መረዳት ላይ ጠበብት የሆኑ ሰዎች አሉ ፡፡ ሰዉች በሌሎች ነገሮች እንደሚያደርጉት ሁሉ ስለ ባለቤታቸዉ እና ስለ ትዳራቸው በሚገባ ቢያዉቁ ትዳር/ጋብቻ የሚያስደንቅ ዋጋ እንዳለዉ ይታያል ፡፡
ሁልጊዜ ሰዎችን ስለ ጋብቻ/ትዳር ሁለት ጊዜ እመክራለሁ ፤ የመጀመሪያው እርስ በእርስ ያልተዋወቁት ነገር እንዳለ ማስተዋል ባልቻሉበት ጊዜም እንኳን ቢሆን ከሰርጋቸዉ በፊት ነው ፤ ሁለተኛው በትዳር ዉስጥ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ በማይሄዱበት ጊዜ ነው ፡፡ ከእነዚህ ዉጪ ሰዎችን ለመምከር ጥሩ ጊዜዎች አይደሉም ፡፡ ጋብቻ/ትዳር ሁለቱም አካላት አስበዉ ስራቸዉን እንደሚሰሩት በጋብቻቸዉ ላይም ጠንክረዉ ለመስራት በሚወስኑ ጊዜ ልምላሜ ይሆንበታል ፡፡ ጋብቻ የተሰራበት ሊሆን፣ የተከበረ ሊሆን እና ዋጋ የተሰጠዉ ሊሆን ይገባዋል ፤ በሆነ ነገር ላይ በምትሰሩ ጊዜ ካከበራችሁት ከአለዉ በላይ ይበልጥ ወደ ዋጋ ትመጣላችሁ ፡፡
ቁጥር 4 “ ጋብቻ በሁሉም የተከበረ መሆን አለበት የጋብቻም/የትዳር መኝታም ንፁህ መሆን አለበት “ ተብሎ መነበብ እንዳለበት አስባለሁ ፤ ልክ ያልሆነ ወይም ወሲባዊ ብልግና የሚለዉ ቃል ፖርኖግራፊ ከሚለዉ የምናገኘዉ የግሪክ ቃል ነው ፡፡ አመንዝራዎች በጋብቻ/በትዳር ዉስጥ ያሉ ከጋብቻ ዉጪ ወሲባዊ ግንኙነት ያላቸዉ ናቸው ፡፡ በእነዚህ በሁለቱም ላይ ጥበቃችንን/ጥንቃቄአችንን መቀጠል አለብን ፡፡ ይህ ሁሉ ስራን ይወስዳል/ይፈልጋል !
ዕብራዉያን (13፡ 5)፡ በቁጥር 5 ምክሩ/ተግሳፁ “ ብርን ስለመዉደድ “ ስለሆነዉ የግሪክ ቃል ፊላጊሪየስ አይደለም ፤ ያ ከእግዚአብሄር ጋር ካላችሁ ግንኙነት የተነሳ ባላችሁ ደስተኞች እና የረጋችሁ በመሆናችሁ የተፈፀመ ነው ፡፡ በህይወታችሁ ምንም ነገር ቢፈጠር አይተዋችሁም አይጥላችሁም ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 6)፡ ቁጥር 6 መዝሙር 118 በመጥቀስ “ እግዚአብሄር ረዳቴ ነው “ በማለት ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር መከታችሁ/ጋሻችሁ ነው ፤ ለሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ እግዚአብሄር በቂ ስለሆን መፍራት አያስፈልጋችሁም ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 7-8)፡ በማህበረሰቡ ዉስጥ ስለሚደረጉ ነገሮች ያወራል ፤ መጀመሪያ አስባችሁ/ሆን ብላችሁ ወደ ክርስቶስ የመሯችሁን መሪዎች በማስታወስ ኑሮአቸዉን በመመልከት እምነታቸዉን መምሰል (ቁጥር 7) ፡፡ ኢየሱስ ትናትና፣ ዛሬ እና ለዘላለም ተመሳሳይ ነው ስለሆነም አስተማሪዎች/ሰባኪዎችም ተመሳሳይ መሆን አለባቸው፡፡ የሚያስተምሩ እና ክርስቶስን የሚከተሉ ተመሳሳይ ቅንነት እና እርግጠኝነት እንዲሁም ደግሞ በእርሱ ላይ የተደገፉ መሆን ሊኖራቸዉ ያስፈልጋቸዋል ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 9-10)፡ በመቀጠል የእግዚአብሄርን ቃል በማያንፀባርቅ እንግዳ ትምህርት ላይ እንዳንወሰድ የፀናን መሆን (ቁጥር 9) ፡፡ የትምህርት አንዱ አደገኛዉ ነገር ከዚህ በፊት ተሰምቶ በማይታወቅ የተለዬ በሆነ ትምህርት ለመምጣት መሞከሩ ነው ፤ ይሁን እንጂ ሙሉ የሖነዉ የእግዚአብሄር ቃል የተነገረ/የታወጀ ስለ ሆነ እንደ ምናስተምረው መደገፍ እንችላለን ፡፡
የዕብራዉያን ፀኃፊ ቀድመዉ በቤተ ክርስቲያን ሰርገዉ የነበሩትን አንዳንድ እንግዳ የሆኑ ትምህርቶችን እና የግል ጉዳዮችን ይገልፃል ፡፡ ምንም እንኳን አማኞች ከዚህ በኋላ በሙሴ ሕግ ክልከላ የተያዙ ባይሆኑም አንዳንዶች በመሰዊያዉ ላይ ተቀምጦ የነበረዉን የበዓላት ምግብ እንዳይበሉ እያስተማሩ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ሌሎች ትምህርቶች ደግሞ ምንም እንኳን አሁን አማኞች ካህናት እንደ ነበራቸዉ ተመሳሳይ መብት ቢኖራቸውም ካህናቱ ማድረግ ከሚችሏቸዉ ነገሮች ልክ ተሰዉቶ ከነበረዉ ነገር መብላት አይነትን የተከለከሉ መሆንን ያካትታሉ (ቁጥር 10) ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 11-14)፡ በመቀጠል ፀኃፊው ኢየሱስ ለእኛ እንዴት ተሰዉቶ እንደ ነበርና በመዋረድ ከከተማዋ ዉጪ እንዴት እንዲሞት ተደርጎ እንደ ነበር ይገልፃል (ቁጥር 11-12) ፡፡ ስለዚህም አማኞች ኢየሱስ ወደላበት በመሄድ የምትመጣዉን ከተማን በመጠበቅ ነቀፌታዉን እንሸከማለን (ቁጥር 13-14) ፡፡ ይህ ምድር ቤታችን አይደለም ፤ ቤታችን በእግዚአብሄር መንግስት በሰማይ ነው ፡፡
ዕብራዉያን (13፡ 15-17)፡ ቁጥር 15 በመፅኃፉ በመጨረሻ እንግዲህ በሚለዉ ቃል ይጀምራል ፡፡ ጥቅሶቹን ከማጠቃለላችን በፊት የእግዚአብሄርን ስም የሚያወድስ መስዋዕትን ማቅረብ አለብን ፤ ይህ መልዕክት በአይሁድ እምነት ላይ መሳተፍ እየናፈቁ ለነበሩት ነበር ፡፡ ከዚህ በኋላ የደም መስዋዕታቸዉ አያስፈልግም ምክንያቱም ኢየሱስ መስዋዕት ስለነበር እና እግዚአብሄር የኛን ምስጋና ስለሚፈልግ ፡፡
መስዋዕትነት የሆነ ነገርን ያሳጣናል/ያስከፍለናል - ገንዘብን፣ ጊዜን እና ጉልበትን ፡፡ ምስጋና/ማመስገን ለመጨረሻ ጊዜ የሆነ ነገር ዋጋ ያስከፈላችሁ መቼ ነው ? ምስጋናን ለማቅረብ ከራሳችሁ መንገድ ላይ የወጣችሁት መቼ ነው ? ለሌሎች መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ ምክንያቱም እግዚአብሄር በመስዋዕቶቹ ስለሚደሰት (ቁጥር 16) ፡፡ ስለ ራሳቸዉ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ስለ እናንተም ነፍስ ኃላፊነት ስላለባቸዉ መሪዎችን በማመን ትታዘዙአቸዋላችሁ (ቁጥር 17) ፡፡
አስቡ/ተመልከቱ፡ ለመመራት ደስታ በመሆን በሚፈጥር አይነት መንገድ እንኖራለን ፤ በአንድ ስፍራ ዉስጥ በምትመላለሱ ጊዜ የሚመሯችሁ ያበሩላችኋል/ብርኃን ይሆኑላችኋል ? ይህን እንደ ደስታ ወይስ በዙሪያችሁ ስለሆኑ እንደ ሸክም ይቆጥሩታል ?
ዕብራዉያን (13፡ 18-19)፡ በመጨረሻም ፀኃፊው ለአንባቢዎቹ የታደሰ መሆን እንዲችል እንዲፀልዩ ይጠይቃል ፡፡ በህይወቱ ለእርሱ የሚፀልዩለትን ሰዎች እየሰበሰበ ነበር (ቁጥር 18-19) ፡፡
መደምደሚያ
“ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነዉን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊት ደስ የሚያሰኘዉን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ስራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን ፤ አሜን “ (ዕብ 13፡ 20-21) ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዕብ (13፡ 5) ላይ ያለዉ የእግዚአብሄር ቃል ከገንዘብ ፍቅር ነፃ በመዉጣት ደስታን ያገኝን እንድንሆን እንዴት ያግዘናል ?
-
በዕብ (13፡ 9) ፀኃፊው በእንግዳ ትምህርት የተሳብን እንዳንሆን ያስጠነቅቀናል ፤ እነዚህ ትምህርቶች በዙሪያችን ሲንቀሳቀሱ ምን ይመስላሉ ? እነዚህ ትምህርቶች ምን እንደሚሆኑ ሌላ አስተምሮ አለ ? (ገላ 1፡ 6-9, 2ጢሞ 4፡ 3-4)
-
ሌሎች እናንተን በዕብ (13፡ 14) ላይ የተገለጠችዉን ነገር ግን እስካሁን ያልመጣችዉን ከተማ እንደሚፈልግ አይነት ሰዉ እንደሚያዩአችሁ ታስባላችሁ (ዕብ 11፡ 9-10, 13-16) ? ለምን ወይስ ለምን አያዩአችሁም ?
-
በዕብ (13፡ 15-16) የተዘረዘሩት ሰዎስት መስዋዕቶች ምንድን ናቸው ? እነዚህ የመኖር አካላት እንደሆኑ ታስባላችሁ ሮሜ (12፡ 1) ? ለምን ?
-
ዕብ (13፡ 7 እና 17) በነፍሳችሁ ላይ ስለተሸሙት/ጥበቃ ስለሚያደርጉት መሪዎች ስለ መታዘዝ እና ማክበር ይጠቅሳል ፤ በሕይወታችሁ ያ መሪ ማነው ? በሚገባ እንዴት ተገዙላቸዉ እና ትታዘዙላቸዋላችሁ ?
-
በዕብራዉያን 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 13:15
“Therefore, through Him let us continually offer up to God a sacrifice of praise, that is, the fruit of our lips that confess His name.”
የዕብራውያን ጸሀፊ በዋናነት ይህን አሳብ ያጸናል ፡- ኢየሱስ ከህግ ይሻላል ፡፡ ከዚያም ሲቀጥል እንዴት በክርስቶስ እንደ አዲስ ኪዳን አማኝ መኖር እንደሚገባ ይናገራል ፡፡ ይህም እርስ በእርስ በመዋደድ ፣ በመተዛዘን ፣ የታሰሩትን በማሰብ በመጠየቅ ፣ ያለ ነቀፋ በመሆን ትዳርን በማክበር እናም እርሱ በቂ ስለሆነ በክርስቶስ በመርካት ነው ፡፡ ቤታችሁ በዚህ ምድር አይደለም ፣ ዘላለማዊ ነው ፡፡ ስለዚህም ከእንግድህ ወዲያ በቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕትን አታቀርቡም ነገር ግን ይልቁንም የምስጋና መስዋዕት ዘወትር በአፋችሁ ይሁን ፡፡
ከኢየሱስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ውስጥ ምስጋና አስፈላጊ ነው ፡፡ ልክ የትዳር አጋራችሁን ፣ ልጃችሁን ወይም ጓደኛችሁን ማበረታታት ማመስገን እንዳለባችሁ ሁሉ እንዲሁ የኢየሱስን ስም ማመስገን አለባችሁ ፡፡ ምስጋና አምልኮ ነው ፡፡ ምስጋና መስዋዕት ነው ፡፡ ምስጋና የውጊያ ድምጻችሁ ነው ፡፡ የአምላካችሁን እግዚአብሔርን ስም በምስጋና እና በውዳሴ ከፍ አድርጉት ጥሩት ! እንደ ክርስቶስ አማኝ ቀናችሁን እግዚአብሔርን በማመስገንና በማክበር ጀምሩ ፡፡ ልባችሁን አፍስሱለት፣ አመስግኑት ፡፡ በአምልኮ ወደ እግዚአብሔር ቅሩቡ እናም ልክ እናንተ ልባችሁን ለኃያሉ ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስትሰጡ በህወታችሁ ውስጥ ያሉ ሌሎች ጉዳዮች ይስተካከላሉ! ፈጽሞ የማይተዋችሁንና የማይጥላችሁን ረዳታችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፡፡ ዛሬ እርሱ ብቻ ያርካችሁ !
“ እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ፥ በእርሱ እናቅርብለት ። “
- ዕብራውያን 13፡15
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 34:1 — “ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው። “
መዝሙር 113:3 — “ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን። “
ዕብራውያን 13:5–6 — “ አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን ፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና ፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።