Run The Race With Endurance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዕብራዉያን ዉስጥ እንደቀጠልነው ፀኃፊው አንባቢዎቹን አሮጌዉን ኪዳን መከተል አቁመዉ አዲሱን ኪዳን መከተል እንዲጀምሩ ሲነግራቸው አይተናል ፡፡ በመቀጠልም በምዕራፍ 11 የታዋቂዎቹን የእምነት ዝና ተመልክተናል፡፡
ምዕራፍ 12 ክርስቶስ ለእርሱ እንድንኖርለት የሚፈልገዉን አይነት ኑሮ ወደ ሚመሩን ባህሪያት በስፖርት ምሳሌነት በማስመሰል በማመልከት ይጀምራል ፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በልባችን ስለሚያስተጋባዉ የእግዚአብሄር ቃል ተናግሬአለሁ ፤ ለስፖርት ካለኝ ፍቅር የተነሳ ይህ ፅሁፍ በእኔ ዉስጥ የሚያስተጋባ/የሚሰማ ነው ፡፡ ምስያዉ/ማመሳሰሉ ፀኃፊው በምዕራፍ 11 እንዳሉት የእምነት ምሳሌዎቻችን እንድናስብ መልክ/ቅርፅ እንድንይዝ ሲሞክር በመላዉ ምዕራፉ ዉስጥ ሊጠቀመዉ/ሊመስልበት ይችላል ፡፡ እንዲሁም በምዕራፍ 11 የእምነት ስብስቡ ሌላ የስፖርት ማጣቀሻ ነው ፡፡ በእምነት በምንመላለስ ጊዜ ይህ ስለ ህይወት ዘላለማዊነት እና በዚህ በምድር ላይ የተትረፈረፈ ዘላለማዊ ህይወትን ስለ መኖር ነው ፡፡
ወደ ፅኁፉ ከመግባታችን በፊት ለምዕራፉ የስፖርት አገባቦችን/አገላለፆች አይነቶችን እናስቀምጥ/እንለይ ፤ ስፖርት አለማቀፋዊ ቋንቋ እና በሁሉም ባህል የሚገኝ ነው ፡፡ ማመሳሰሉ/መግለጫዉ በሩጫ ዉድድር ስፖርት ላይ የተመሰረተ ነው ፤ በቀድሞዉ በኦሎምፒክ ጨዋታ ሩጫ የመጀመሪያዉ ውድድር ነበር ፡፡ በጫዎታወች የእርምጃ ዉድድር በአሁኑ ዘመን ከዋና፣ ከመስመር እና ከመስመር ወጪ ካሉ ውድድሮች እና ከእግር ኳስ ጋር ተመጣጣኝ/ተመሳሳይ ትልቅ ዉድድር ነበር ፡፡ የመጀመሪያዉ/የቀደመዉ የኦሎምፒክ ስታድዮም ወይም “ ስታድዮን “ በብዛት ወጥ የሆነ ሜዳ ነበር ሯጮችም ከአንድኛዉ የስታድዮም ጫፍ ወደ ሌለኛዉ ይሮጣሉ ፤ ርቀቱ 180 ሜትር ወይም 590 ጫማ ያክል ማትም ሁለት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ወይም አንድ ከግማሽ የእግር ኳስ ሜዳን ያክል ነበር ፡፡ በጊዜ ብዛት/ከጊዜ በኋላ ሯጮች ዉድድሩን ለማጠናቀቅ ወደ ሜዳዉ ጫፍ በመሄድ ቋሚዎቹን በመዞር ወደ ጀመሩበት መስመር ተመልሰዉ በመሄድ ይሮጧሉ ፡፡
ለሯጮቹ ብዙ ፈተናዎች ነበሩባቸው ፤ የመጀመሪያው የመሮጫዉ ሜዳ የተሰራው ከአሸዋ ስለ ነበር ሩጫዉ በጣም አስቸጋሪ ነበር ፤ ሁለተኛው ሯጮቹ የሚፎካከሩት ያለ ልብስ ነበር ፤ ሰዎስተኛው ዉድድሩ/ክስተቱ እያደገ ሲመጣ ዉድድሩን ለመቀጠል ሯጮቹ በቋሚዎቹ ለመዞር ሲሞክሩ በእያንዳንዱ ጫፍ ላይ መጨናነቅ ይሆናል ፡፡ ስለሆነም ዉድድሩ አንዱ መታገስ/መጨከን/መጠንከር ነበር ፡፡ ፅሁፉን ስታነቡ ይህን መግለጫ በአይምሯችሁ ዉስጥ አስቀምጡ ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (12፡ 1)፡ በምዕራፍ 11 ስለ መታመን አዉርተናል ፡፡ በቁጥር 1 የተጠቀሱት ብዙ ምስክሮች ናቸው ፡፡ ምስክር የሚለዉ ቃል በኃይለኛዉ ለሚያምነዉ/ለምታምነው ነገር በፍቃደኝነት ከሚሞተዉ ሰዉ ከምናገኘው ሰምዓት ከሚለዉ የተገኘ የግሪክ ቃል ነው ፡፡ ምስክር በሆነ ጊዜ የሆነ ሰዓት/ደረጃ ላይ ስለተፈጠረ እዉነታ የግል መግለጫን መስጠት የሚችል ሰው ነው ፤ በምዕራፍ 11 ስላሉት የእምነት ከዋክብት አስቡ - ብዙ ምስክሮች፣ ብዙ ምስክርነቶች እንዲሁም ብዙ የታገሱ አሉ ! መታገስ (መቋቋም/መቻል) የሚለዉ ቃል እንደ ነበረ መቆየት/መኖር ማለት ነው ፡፡ ታጋሽ/ቻይ ለመሆን በዉድድሩ ዉስጥ ብዙ ነገሮች ነበሩ - አሸዋዉ፣ ሙቀቱ፣ መጨናነቁ/የተወዳዳሪዉ ግፊያ እና ድካሙ ፡፡ ቁጥር 1 ሁሉንም ሸክም እና ኃጢዓት ወደ ጎን እንድንጥል እና እንድናስወግድ ይናገራል ፡፡ ሸክሙ እንቅፋት ነው ፤ በመንገድ ላይ የሚገኝ ነገር ነው ፡፡ ኃጢዓት(ልክ እንደ ሹራብ) በነፃነት መሮጥ ቀላል እንዳልሆነ አጥብቆ ይይዛል ፡፡
ዕብራዉያን (12፡ 2)፡ ይህ ጥቅስ አይናችንን በኢየሱስ ላይ እንድናደርግ ያስጠነቅቀናል ፡፡ ሯጮቹ በመወዳደሪያ መስመሩ ላይ ውድድሩን ለመጨረስ አይኖቻቸዉ ከፊት ለፊታቸዉ ላይ ያተኮሩ ነበሩ ፡፡ በኑሮአችን ዉድድሩን በምንሮጥ ጊዜ የእምነታችን ጀማሪ እና ፈፃሚ በሆነዉ በኢየሱስ ላይ በማትኮር መቆየትን እንፈልጋለን ፡፡ አይናችን ወደ ሚሄድበት ሰዉነታችን ይከተላል ፡፡ ኢየሱስ ዉድድሩን/ሩጫውን ታገሰ - ስደቱን/መከራውን፣ ቅጣቱን፣ ሕመሙን እና ከእርሱ በኋለ ለነበረዉ ደስታ መስቀሉን ታገሰ ፡፡ ኢየሱስ አይኑን በእግዚአብሄር ላይ በማድረግ ለመፈፀም መጥቶ በነበረዉ ነገር ላይ በቀጥታ ወደ ፊት አተኮረ ፤ ምንም ነገር ደርሶበት ቢሆንም በመታገስ ስራችን ስለሰራልን በደስታ ሩጫችንን መሮጥ የምንፈልግ ያደርገናል ፡፡
ዕብራዉያን (12፡ 3-5)፡ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ስለሰራው በድካም አናድግም ፤ ይህ የተሸነፋችሁ በሆናችሁበት ሁሉንም ሰዉ የማዳን የኃሳብ ጥንካሬን/መታገስን ያሳያል ፡፡ እዚህ የትግል ስፍራ አልተገኘንም ፤ የትም ስፍራ ብንሆንም ክርስቶስ ያን ትግል ያውቀዋል (ቁጥር 4) ፤ በተጨማሪም የእግዚአብሄር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ስለ ሆንን (ቁጥር 5) ከእግዚአብሄር ቅጣትን (ስልጠናን) መጠበቅ እንችላለን (ኤፌ 6፡ 4, 2ጢሞ 3፡ 16) ፡፡
ዕብራዉያን (12፡ 6)፡ ቅጣት/ተግሳፅ ከቤተሰብ እና ከልጆች አንፃር ልጆች መሄድ በሚገባቸዉ መንገድ ማሰልጠን ማለት ነው ፤ በቅጣት ግራ ማጋባት ማለት አይደለም ፡፡ ጌታ የሚወደዉን ይቀጣል (ቁጥር 6) ፡፡ ለምሳሌ ሚስቴ ኢሪክ ሁልጊዜ ማለዳ ፀሎት እንድትጀምር በእግዚአብሄር 11፡ 45 እንድትነቃ ተጠይቃ ነበር ፤ የማለዳ/በጥዋት የምትነሳ ሰዉ አይደለችም ነገር ግንየተቀጣችች ስትሆን በ11፡ 45 በእያንዳንዷ ማለዳ ጀመረች ፤ ከዚያም እግዚአብሄር 11፡00 እንድትነቃ ነገራት ፤ አላርም በመቅጠር ሞከረች ነገር ግን ሁልጊዜ ስኬታማ አልነበረችም ፤ ይሁን እንጂ የአንድ አመት ከግማሽ ወንድ ልጃችን ሁል ጊዜ ማለዳ 11፡00 አካባቢ ጀምሮ እስከ ማለዳ ድረስ ማልቀስ ጀመረ ፤ በአላርሟ በሚገባ በምትነቃ/በምትነሳ ጊዜ አይነቃምም በጥዋት አይነሳም ፡፡ ሁለታችንም እግዚአብሄር በዚህ በፀሎት ሕይወታ በመገሰፅ እያስተማራት እንደ ነበር አመንን ፡፡
ዕብራዉያን (12፡ 7-13)፡ እግዚአብሄር የሚወዳቸዉን ስለሚቀጣ ቅጣቱን መታገስ አለብን (ቁጥር 7) ፡፡ ሌላዉ ሁሉም የሚቀበለዉን የእግዚአብሄርን ቅጣት የማትቀበሉ ከሆነ ልጆቹ አይደላችሁም (ቁጥር 8) ፡፡ በአባቶቻችን እንደተቀጣነው እና አሁንም እንደምናከብራቸው አባታችንም በፍቅር ይቀጣናል (ቁጥር 9) ፤ እግዚአብሄር ለመልካም ነገር ስለሚቀጣን ከቅድስናዉ መካፈል እንችላለን (ቁጥር 10) ፡፡ እዉነታው የተለመደ እስኪሆን እና የተፈጥሮ አካል እስኪሆን ድረስ ቅጣት እንደ ሕመም ብቻ ነዉ የሚሰማው (ቁጥር 11-12) ፡፡ “ እጆችን መጣል/መዛል እና የደከመ ጉልበት “ አካላዊ ደካማ የመሆን ማሳያ ናቸው ፡፡ ጉልበታችሁን በማቅናት/በማጠንከር ቀጥ ባለ መስመር በመሮጥ ጉዳትን ለማስወገድ ሁሉንም ነገር በስፍራዉ መጠበቅ (ቁጥር 13) ፡፡ ስለዚህም ዉድድሩን ስንሮጥ በመንፈሳዊ ኑሮአችን በሚገባ የጠነከርን መሆን አለብን ፡፡
ዕብራዉያን (12፡ 14-17)፡ እንደ አማኝ በመንፈሳዊነት ጠንካራ ለመሆን በዉድድሩ/በሩጫዉ የታገሰ ለመሆን የአማኝ ሰዉነት አባላትም አስፈላጊ ነው ፤ በመታገስ ለሰላም እና ለቅደስና ስንተጋ ሌሎች እግዚአብሄርን ያዩታል (ቁጥር 14-15) ፡፡ ቁጥር (16-17) ቅድስና ከማጣቱ የተነሳ ሳዖል እንዴት እንደተናቀ ይገልፃሉ ፡፡ መንፈሳዊ ጥንካሬ በግል ደረጃ ሊጎዱን የሚችሉ ነገሮች እና የአማኞችን ሰዉነት የሚጎዱ ነገሮች ከማድረግ እንድንቆጠብ ይረዳናል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ አማኞች ሰላምን እና ፅድቅን በማይከታተሉ ጊዜ የሚሆኑትን ሰዎስት አደጋዎች ያመለክታል፡
- “ ከእግዚአብሄር ፀጋ በአጭር መዉደቅ - ያም የክርስቶስን የከበረ የድነት አቅርቦት እና የሚያስፈልጋቸዉን ስጦታ ችላ ማለት ነው “ ፤ በሕጉ ፍርድ እና ሸክም ስር አትኑሩ ፡፡
- “ በጉባኤአችሁ መራር ስር እንዲበቅል ይፈቅዳል - ምናልባትም በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የጣዕት አምላኪዎች እንዲኖሩ ይፈቅዳል “ ፤ በህይወታችሁ ምሬት በማመርቀዝ መንፈሳዊ በሽጻን ይፈጥራል ፡፡ ለመሮጥ መንፈሳዊ ዉድድር በሚኖርበት ጊዜ ለምሬት ክፍተት/ቦታ አይኖርም ፡፡
- “ በወሲብ ስርዓት አልበኛ እና ኃይማኖታዊ ያልሆነ መሆን “ ፤ ተገቢ/ልክ ያልሆነ/ስብዕና የጎደለው ወሲብ ለጥፋተኝነት፣ ለእፍረት፣ ለዉርደትከኃጢዓት እና ከጨለማ ጋር አጋር ለመሆን ምክንያት ይሆናል ፡፡ ትክክል/ፀያፍ ከሆነ የወሲብ ግንኙነት እንሽሽ ፡፡
“ በስታድዮም “ በሮማን በአንድ ጥሩ ሯጭ መግለጫ ማብራሪያው በሚገባ የተመጣጠነ ስለ መሆን ነበር ፤ በጣም ረጅም አለመሆን ምክንያቱም ረጅም ሰዎች መረጋጋት/በደንብ መቆም ሊያጥራቸዉ ስለሚችል እና በጥሩ የሯጭ እግር፣ ደረት እና ትካሻ መመጣጠን ለመስፈንጠር ጥሩ አቋም መኖር ያስፈልጋል ፡፡ ሁሉም ነገር ከመጠኑ ዉጪ ከነበር ሯጩ ተጨማሪ ክብደትን/ሸክምን ይሸከማል ፡፡
መደምደሚያ
ቁጥር (28-29) መንግስቱ ስለማይናወጥ የእግዚአብሄርን ፀጋ እንያዝ በማለት ያጠቃልላል ፤ በመታገስ እግዚአብሄርን ደስ በማሳኘት በአምልኮ ፍርኃጽ እና በማስደነቅ ማገልገል እንችላለን ምክንያቱም እግዚአብሄር የሚባላ እሳት ነው ፡፡ ይህ በፊታችን ለሚወድቀዉ አካላዊ ዉጊያ ስለ ሚያዘጋጀን አይናችንን ሳንነቅል በኢየሱስ ላይ ማትኮር እንችላለን ፡፡ የቀድሞዉን ኪዳን ወደ ጎን በማስቀመጥ ከፊታችን ላለዉ ሩጫ እንዳዘጋጀን አይናችንን በኢየሱስ ላይ በመክፈት በእምነት እንመላለስ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Hebrews (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1657.
Nelson’s Commentary, p. 1657.
Nelson’s Commentary, p. 1657.
ጥያቄዎች
-
ዕብ (12፡ 1) “ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢዓት እንድናስወግድ “ ያዘናል ፤ በፅናት እንዳትሮጡ የሚያደርጋችሁ/የሚከለክላችሁ ሸክም ምንድን ነው ?
-
በዕብ (12፡ 2) መሰረት አይናችንን በኢየሱስ ላይ ማድረግ የእግዚአብሄርን ፍቅር ለእኛ ያሳያል ፤ በተግባራዊነት ሲነገር ይህ እንዴት ይሰራል ?
-
የእግዚአብሄር ቅጣት ለእኛ ያለዉን ፍቅር እንዴት ያሳያል (ዕብ 12፡ 6) ? በሚያሳድጓቸዉ ቤተሰቦቻቸው ያልተቀጡ ሰዎችን ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን ይመስላል ?
-
በዕብ (12፡ 10-11) መሰረት በእግዚአብሄር ቅጣት የሚፈለገዉ ዉጤት ምንድን ነው ? “ በሰላም እና በፅድቅ ፍሬ ማለት “ ምና ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ
-
በዕብ (12፡ 14) የሚለው ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ሮሜ 6፡ 19, 2ቆሮ 7፡ 1, 1ተሰ 4፡ 7)
-
በዕብራዉያን 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 12:1–2
“Therefore, since we also have such a large cloud of witnesses surrounding us, let us lay aside every weight and the sin that so easily ensnares us. Let us run with endurance the race that lies before us, keeping our eyes on Jesus, the source and perfecter of our faith, who for the joy that lay before Him endured a cross and despised the shame and has sat down at the right hand of God’s throne.”
በእምነት መመላለስ አስቸጋሪ ተግዳሮት የበዛበት ሊመስል ይችላል ፡፡ ልክ ማራቶን ለመሮጥ እንደሚደረገው ዝግጅት እንድሁ እናንተም ቀለል ያሉ የእምነት እርምጃዎችን በመራመድ ትጀምሩና ቀስ በቀስ ከኢየሱስ ጋር ትልልቅ የእምነት እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስፈልገውን ትዕግስት ትገነባላችሁ ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችሁ ፣ ጌታ በእምነት ለመራመድ ትችሉ ዘንድ ትዕግስትን ሊያስተምራችሁ ይወዳል ፡፡ እናም እንድሁ የሰማዩ አባታችሁ ሊያጠነክረው የሚፈልገው የህይወት ክፍል ሲኖር ፣ እርሱ ይቀጣችኋል ፡፡ ከባድ ሊሆን ይችላል ፡፡ ቅጣቱ እንድታለቅሱ ሁሉ ሊያደርጋችሁ ይችላል ፡፡ ለማቆም ለመተውም ትፈልጉ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን በእምነት በርቱ ፤ የማታዩትን በማመን ጽኑ ፤ እግዚአብሔርም በህይወታችሁ እየሰራ እንዳለ እመኑ ፡፡ በቅጣትና ስልጠና የሰላምንና የጽድቅን ፍሬ ታፈራላችሁ ፡፡
በርግጥም ከእግዚአብሔር የሆነ ቅጣትና ስልጠና አስፈላጊ ነው ፡፡ እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ ፈውስ የሚያስፈልገውን ይፈውሳል ፡፡ በዚህ የቅጣትና ስልጠና ጊዜ ውስጥ ስታልፉ ፣ አይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ አድርጉ ፡፡ ግራ የሚያጋቧችሁን የሚከቧችሁን ክፋትን ፣ ቅንዓትን ፣ ሸክምንና ሌሎች ኋጢአቶችንም ጭምር ተው ፡፡ ሰላምን ያዙ ፡፡ በፈተና ውስጥ እንኳን ሆናችሁ በእግዚአብሔር ላይ ያላችሁ እምነት አይናወጥም ፡፡ የምትራመዱት በጠንካራ ፣ በማይናወጥ ዓለት ላይ ነው ፡፡ ጸጋው በፈተና ውስጥ ይሸከማችሁ ዘንድ ይችላል ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያጠፋ እሳት ነው ፡፡ እርሱ ህይወታችሁን ያበራል ፡፡ ወደ እርሱ ፍቅር በመሮጥ በርቱ ጽኑ ፡፡
“ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን ፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን ፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን ፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና ። “
- ዕብራውያን 12፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
ዕብራውያን 12:7 — “ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው ? “
ዕብራውያን 12:28–29 — “ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና። “
ያዕቆብ 1:2–3 — “ ወንድሞቼ ሆይ ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።