General Letters Hebrews

Living By Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 663 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዕብራዉያን (1-10) የቀደመዉን ከአዲሱ ጋር በማወዳደር ተመልክተናል ከባድ ጥናትም ነው ፡፡ ኢየሱስ አይሁዶች ያዉቋቸዉ ከነበሩት ሊቀ ካህናቶች የሚበልጥ ነው፤ አዲሱ ኪዳን ካለፈዉ/ከአሮጌዉ ኪዳን የሚልቅ ነው ፡፡ ሰማያዊዉ መቅደስ በምድር ላይ ከተሰራዉ መቅደስ የተሸለ ነው ፡፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ (1-6) “ ስለ ላቀዉ ሰዉ “ ስለ ኢየሱስ ሲሆኑ ምዕራፍ (7-10) “ ስለ ላቀዉ ክህነት “ ሲሆኑ ምዕራፍ (10-14) “ ስለ ሚበልጠዉ/ስለ ላቀዉመርህ ስለ እምነት “ እንደ ሆኑ ይናገራል ፡፡ ዕብ (11፡ 6) “ ያለ እምነት ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና “ ፡፡ እንደ አማኝ በእምነት የምንሰራ ካልሆነ በፍርኃት፣ በስጋ እና በኃሰተኛ እምነት እየሰራን ነው ፡፡ ምዕራፍ 11 በአጠቃላይ በመፅኃፍ ላይ በእምነት ስለ ተመላለሱ ሰዎች ነው ፡፡

ትምህርት

ዕብራዉያን (11፡ 1-3)፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ቁጥሮች እምነትን ይገልፃሉ ፡፡ እምነት “ እዉነት “ ወይም የሚጨበጥ ነገር፣ “ ማረጋገጫ “ ወይም ማስረጃ እና “ የታዬ “ ወይም የተረጋገጠ ማለት ነው (ቁጥር 1) ፡፡ እዉነታው/እዉነቱ ሊታዩ ስለቻሉት ወይም በተጨባጭ ሊነኩ ስለቻሉት ነገሮች ይናገራል ፡፡ ጄ.ኦስዋልድ ሳንደርስ “ እምነት የሚያምንን ነፍስ የወደፊቱን ነገር አሁን እንዳለ እና የማይታየዉን እንደ ታዬ እንዲያስብ የሚያስችል እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ጥቅሶች ሊመመጡት የታመኑ ስም ዝርዝሮች እና ዕብ (12፡ 1) “ እንደ ታላቅ የደመና ምስክሮች “ ብሎ ለጠቀሳቸዉ ደረጃን ያስቀምጣሉ ፤ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄር እቅድ እንዲከናወን በፈቀደ መንገድ በእምነት ተጓዙ ፡፡ ኖህ በፍፁም ቀድሞ ዝናብን አላዬም ነገር ግን ለአመታት መርከብን በመገንባት ሰራ ፤ ያም የማይረባ የቅንዓት/የሞኝነት ወይም ደግሞ የእምነት የመታዘዝ ድርጊት ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍርኃት በመፍራት ወይም ሞኝ መምሰል ነገሮችን በእምነት ከማድረግ ያስቆመናል ፡፡

ቁጥር 2 የአይሁድ አባቶች /አያቶቻቸው በእምነታቸዉ የእግዚአብሄርን አድናቆት አሸንፈዉ እንደ ነበር ይናገራል ፤ ይህ ድርጊታቸዉን ሳይሆን እግዚአብሄር የተመለከተዉ እምነታቸዉ ነበር ፡፡ በኑሮአችን የእግዚአብሄርን አድናቆት ለመወሰን እናዘነብላለን ምክንያቱም የቁጥር 1 ያክል እንኳን መቅረብ ስለማንፈልግ ፡፡ በእምነት እግዚአብሄር አለምን እና ሁሉን ነገር ሊታይ ከማይችለዉ ነገር እንደፈጠረ መረዳት እንችላለን (ቁጥር 3) ፡፡ ሁላችንም የሆነ ደረጃ ያክል በእምነት እንሰራለን ፤ በእግዚአብሄር እስከ አለማመን የእምነት ንግግር ድረስ - እግዚአብሄር ሊኖር አይችልም ብሎ እስከ ማመን አለዉ እምነተ ድረስ ፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገው በእኛ ዉስጥ መታየት በሚችልበት መንገድ በእምነት ስንሰራ ነው ፡፡

ዋይርስቤ በምዕራፍ 11 የተዘረዘሩት ሁሉም ሰዎች በእምነታቸዉ አራት ነገሮችን እንዳጋሩ ይገልፃል፡ “ 1) እግዚአብሄር በቃሉ በኩል ተናገራቸው፣ 2) ዉስጣቸው በተለያየ መንገድ የተነሳ ነበር፣ 3) እግዚአብሄርን ታዘዋል እና 4) ስለ እነርሱ ምስክሮችን አሸክሟል/አኑሯል “ ፡፡ ዉጤቱን ምንም እንኳን ባያዩም ጌታ ምን እየሰሩ እንደ ነበሩ አረጋግጧል ፡፡

እምነት መታዘዝን ይፈልጋል ፤ ያ ማለት መታዘዝ ቀላል ነዉ ማለት አይደለም ፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት በመስራት በሁለት አመት ዉስጥ 730 ክፍልን ለማስተማር/ለመመዝገብ ስንወስን ቀላል እንደማይሆን እናውቃለን ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር እንድንሰራዉ ጠርቶን ለነበረዉ ነገር በመታዘዝ ነበር ፡፡ በእምነት መመላለስ፣ በጠባቡ መንገድ መመላለስ በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ ወዳጆቻችሁን እና ቢዝነሳችሁን ያሳጣል ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች አናዳጅ/ተቃራኒ ሆነዉ ስለሚገኙ ፡፡

ዕብራዉያን (11፡ 4-40)፡ እንዴት እምነትን ተመላልሰዉበት እንደ ነበር ማሳያዎቹ በቀሪዉ በምዕራፍ 11 ዉስጥ ቀርበዋል ፡፡ ዕብራዉያን 11 የክርስቶስ ተከታይ እንደሆናችሁ በሚገባ እዉነታዉን የሚያረጋግጥ ነው ፤ ይህ ቤተ ክርስቲያን ስለ መገኘት አይደለም በእምነት ስለ መመላለስ ነው እንጂ ፡፡

  • ከእምነቱ የተነሳ እግዚአብሄር የአቤልን መስዋዕት አደነቀው/ወደደው (ቁጥር 4) ፤ የአቤል እምነት በአምልኮዉ ዉስጥ የታዬ ነበር ፡፡ ያደረገዉም ነገር ሁል ጊዜ በመፅኀፍት ዉስጥ ተቀምጧል ፤ ዋይርስቤ “ ከእምነቱ የተነሳ አቤል ፃድቅ ሰዉ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡
  • በቁጥር 5 የሄኖክ እምነት በእምነት ሲመላለስ የታዬ ነበር ፡፡ እንደ ገና ቁጥር 6 በማንበብ በመቀጠል ራዕ (22፡ 12) አንብቡ ፡፡
  • የኖህ እምነት መረዳት ስላልቻለዉ ነገር ለአንድ መቶ አመታት በሚሰራበት ጊዜ የታዬ ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ ከመጀመሩ በፊት ኖህ አናፂነት ቢያዉቅም እንኳን ትደነቁበታላችሁ ፤ ጎሬቤቶቹ/ወዳጆቹ ኖህን ሲሰራ ሲመለከቱ ምን ሊያስቡ እንደሚችሉ አስቡት ፡፡
  • የአብርኃም እምነት እግዚአብሄር በነገረዉ መሰረት በፍፁም ወዳላየዉ ስፍራ ሲቀይር እና ለርስቱ ወራሽነት ከሳራ ልጅ እንደሚኖረዉ ለአመታት በመጠበቁ የታዬ ነበር (ቁጥር 8-12) ፡፡ ቁጥር 9 መሰረት ወደ ነበራት በእግዚአብሄር ወደ ተሰራችዉ እና ተገንብታ ወደ ነበረችዉ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ወደፊት እየተመለከተ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡

መደምደሚያ

በዕብራዉያን 11 ያላገኘናቸዉን ሁሉንም ሰዎች ተመልከቱ፡ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ሙሴ፣ ረዓብ፣ ጌድዎን፣ ባራቅ፣ ሳምሶን፣ ዮፍታሄ፣ ዳዊት፣ ሳሙኤል እና ነቢያቶች እንዲሁም ስማቸዉ ያልተጠቀሰዉ ሌሎች ነበሩ ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእምነት እየተጓዙ የነበሩ ነበሩ ፤ እነዚህ ሁሉ ከእምነታቸዉ የተነሳ የእግዚአብሄርን አድናቆት ተቀብለዋል፡፡

በጌታ በእምነታችን ላይ በምንመላለስ ጊዜ ይህንን ህይወት እየኖርን ተስፋ የገባዉን የምናይበት ምንም ዋስትና የለም (ቁጥር 39) ፤ ነገር ግን እንደሚያይ መስራት /ማድረግ አለብን ፤ ያ የእምነታችን ማስረጃ እና እንዴት እንደተመላለስን የሚወስን ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary, Vol. II, (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 275.

  2. J. Oswald Sanders; quoted in Wiersbe, p. 318.

  3. Wiersbe, p. 318.

  4. Wiersbe, p. 318.

ጥያቄዎች

  1. ለአንድ ለማያምን ሰው ዕብ (11፡ 1) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? አንዳንድ የእምነት ምሳሌዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ ?
  2. በዕብራወያን 11ከተጠቀሱት በተጨማሪ በጌታ ላይ ታላቅ እምነትን ያሳየው ሌላው ማነው ? እንዴት አሳዬ ወይም አሳዬች ?
  3. እግዚአብሄርን ያለ እምነት ማስደሰት ለምን እንዳልተቻለ ምን ታስባላችሁ ? ሰዉ እንዴት እምነቱን ሊጨምር ወይም ልትጨምር ትችላለች ? (ሉቃ 17፡ 5-10, ሮሜ 10፡ 17)
  4. በዕብራዉያን 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hebrews 11:1–2

“Now faith is the reality of what is hoped for, the proof of what is not seen. For our ancestors won God’s approval by it.”

የተሻለውን የአዲስ ኪዳኑን የኢየሱስ አገልግሎት ካብራራ በኋላ የዕብራውያን ጸሀፊ እንዲህ ይላል ፡- “እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም ። “ ይህ እምነት ምንድን ነው ? “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው ። “ እምነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማመን ብቻ አይደለም ፣ ይልቁንም ወደ እርሱ በመቅረብ ለእርሱ በመታዘዝ ምላሽ ይሰጣል እንጂ ፡፡ ይህም እግዚአብሔር እንድታደርጉ ያዘዛችሁን ነገር ማድረግን ፣ እግዚአብሔርን ብቻ ማምለክን ፣ በኢየሱስ ላይ ባላችሁ እምነት ጸንታችሁ መቆምን ወይም በእምነት መታገስን ወይም ደግሞ አለመቸኮልን ያካትታል ፡፡

በእምነት ልትኖሩት የሚገባ ነገር አለን ? ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በእምነት እርምጃን ትወስዳላችሁ ፡፡ ተናጉሩ ፡፡ መልዕክት ልካችሁ ጠይቁ ፡፡ ለውጥ አድርጉ ፡፡ እምነት እግዚአብሔርን እንድታምኑ ፤ ሀላፊነትን አሳልፋችሁ ለእርሱ እንድትሰጡ እና እምነት ትንስ ወጣ ያለ ያልተለመደ እንደሆነ ልትረዱ ያስፈልጋል ፡፡ ኖህ ምንም አይነት የዝናብ ጠብታ እንኳ ሳያይ መርከብ መስራቱን አስባችሁታል ? ነገር ግን በእምነት ኖህ መርከቡን ሰራ እናም ከዚያ ዝናቡ መጣ ፡፡ እግዚአብሔር የጻፈው ታሪክ ምን እንደሆነ አታውቁም ፡፡ እናንተ የምታውቁት እርሱ እንድትወስዱ ያዘዛችሁን እርምጃ ነው ፡፡ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ፡፡ ዛሬ ፈቃዳችሁን ለእርሱ አስገዙ ፡፡ ለማይታየው ለእርሱ እሺ በሉ ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡

“ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና ። “

  • ዕብራውያን 11፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 3:5–6 — “ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን ፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “

ዕብራውያን 10:39 — “ እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም ። “

ዕብራውያን 11:6–7 — “ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና ። ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ ። “