Worshipping The Shadow Or The Reality
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ወደ እግዚአብሄር ቃል በጥልቀት ስንቆፍር/ስናጠና ሁልጊዜ መፅኃፍት እንዴት በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ወደ እኛ እንደሚመጣ ማስብ መላካም ነው ፤ ከዚህም የተነሳ ስናጠና ለእኛ በመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት አስፈላጊ ነው ፡፡ ዕብራዉያን 10 የምዕራፍ (8-9) ቀጣይ ክፍል የሚቀጥል ነው ፡፡ ምዕራፍ 10 ኢየሱስ ከህጉ የላቀ እና የተሻለ በሆነዉ እዉነት ላይ ያተኮረ ነው ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (10፡ 1-4)፡ ፀኃፊው ሕጉን “ ሊመጣ ያለዉ የበጎ ነገር እዉነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለዉ በማለት “ ይገልፀዋል (ቁጥር 1) ፡፡ ጥላ በብርኃን የሚፈጠር ወይም በብርኃን መንገድ የሚገኝ ነገር ነው ፤ የሆነ ነገር ጥላንካልፈጠረዉ ጥላ አይሆንም /አይመጣም ፡፡ ካህናቱ በየዕለት መስዋዕታቸው ሁልጊዜ በሚያደርጉ ጊዜ ሁሉም ያዩት ነው - እዉነት የነበረዉን ጥላ ፤ ተደርጎ የነበረዉ ሁሉም መስዋዕት/ቁርባን ይመጣ ስለ ነበረዉ ነገር ጥላ ነበር፡፡ ጥላ እየፈጠረ የነበረዉን በፍፁም ኢየሱስ ክርስቶስን አላዩት ፡፡
ሕጉ የእዉነተኛዉ ነገር ምሳሌ/ሞደል ነው ፤ ከእዉነተኛዉ ነገር ኃይል የተነሳ ኃይል አለው ፡፡ ሕጉን በመጠበቅ ለኃጢዓታቸዉ መስዋዕትን አቅርበዋል ጊዜአዊ ስርየትም ተሰጥቷቸዋል ፤ ኃይለኛ/ኃያል ነበር ነገር ግን ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንዳደረገው ኃይለኛ/ታላቅ አልነበረም ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኑሮአችን የክርስቶስን ጥላ በማየት እዉነታዉን ከማምለክ ይልቅ ጥላዉን እናመልካለን ፡፡
ለምሳሌ አንድ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ እድገት ዉስጥ ስለሆነች ትልቅ የማምለኪያ ስፍራን ለመፍጠር አቅርቦቶቹን/ስፍራዎቹን እንደ ገና መስራት አስፈለጋት ፤ አርክቴክቱ ቀድሞ መሰዊያዉ እነበረበት ስፍራ ላይ የልጆቹን ቦታ ማስቀመጥ ፈለገ ፤ በቤተ ክርስቲያኗ ዉስጥ ያሉት ሰዎች ያ እንዲሆን አይፈቅዱም ምክንያቱም ያ ስፍራ የክርስቶስን አዳኝነት የተቀበሉበት ስፍራ ስለ ነበር ፤ ስፍራዉ ለእነርሱ ጣዖት ሆኖባቸዋል ምክንያቱም በስፍራዉ ሳይሆን በኢየሱስ በኩል ብቻ ስለዳኑ ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ በዚያ ሰዎቹ ያሸንፋሉ ፡፡ ክርስቶስን ያገኛችሁበትን ጊዜ የሚወክል - ለምሳሌ የተለዬ መዝሙር - በሌላ የማምለኪያ የሙዚቃ አይነት እንዳታመልኩ የሚከለክላችሁ ለእናንተ ጥላ የሆነ ነገር ሊኖራችሁ ይችላል ፡፡
ይህን አስተዉሉ፡ እግዚአብሄር በሕይወታችሁ ያደረገላችሁን የመጨረሻዉን ምስክርነት ካደረጋችሁ እና በዚያ ካመለካችሁ ምን ያክል ጊዜ ሆናችሁ ?
ዕብራዉያን (10፡ 5-18)፡ እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስን እንደ ሊቀ ካህን እና እንደ ተሰዋ ያሳያሉ ፤ በፍፁም እንደ ገና መቅረብ የማያስፈልገዉን ሙሉ የነበረዉን መስዋዕት ለሁሉም አንዴ ካደረገዉ ከመስዋዕትነቱ በኋላ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ እጅ ተቀመጠ ፡፡ ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የመሬት መናወጡ የቤተ መቅደሱ ከላይ ወደ ታች ወደ ሁለት የተቀደደ እንዲሆን ምክንያት ሆነ ፡፡ እግዚአብሄር የቤተ መቅደሱን መሰረት እንዲሁም እምነቶች እና ተጣብቀዉ የነበሩትን ልምምዶችን እያናወጠ እንደ ነበር አምናለሁ ፡፡ ከዚያም የቀድሞዉ ኪዳን መጥፋት ጀመረ አይሁዶችም መጋረጃዉን በመጠገን ወይም በመተካት ቀድሞ እንደሚያደርጉት ሁልጊዜ መስዋዕትን ማቅረባቸዉን ቀጠሉ ምናልባትም ኢየሱስ ከሞት በተነሳበትም ቀን ጭምር እና ከዚያም በኋላ ሁልጊዜ ፡፡
ዕብራዉያን (10፡ 19-25)፡ ክፍሉ “ እንግዲህ “ በሚለዉ ቃል ይጀምራል ፤ በመሰረቱ በዕብራዉያን መፅኃፍት ዉስጥ አስራ አምስት ጊዜ እንግዲህ የሚለዉ ቃል ጥቅም ላይ ዉሏል ፤ እያንዳንዱ አስፈላጊ ነው ፡፡
ዕብራዉያን (3፡ 1)፡ ወደሌላ እንዳትሳቡ አይናችሁን በእግዚአብሄር ላይ አድርጉ ፤ ዕብራዉያን (4፡ 1) በእርሱ እረፍትን ለማግኘት የእግዚአብሄርን ተስፋ እንዳትስቱ ፤ ዕብራዉያን (4፡ 7) እግዚአብሄር “ እንደ ገና “ ዘመንን ስለሚያስቀምጥ በእርሱ ላይ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ ፡፡ ዕብ (4፡ 11) “ ስለዚህ “ በእግዚአብሄር ለማረፍ ሁሉንም ጥረት እናድረግ ፡፡
በሁሉም በአስራ አምስቱም ካለፍኩኝ በኋላ እንግዲህ (እንደ ገና ወይም ስለዚህም) የሚለዉን ቃል በመጠቀም ሁለት ጭብጦችን አግኝቻለሁ ፤ መጀመሪያው ምክሩ በኢየሱስ ላይ በማትኮር እንድንቆም ነበር ፤ ሁለተኛው ደግሞ በአጭር ላለመዉደቅ የተጠነቀቃሁ እንድትሆኑ ነው ፡፡ በሁሉም በአስራ አምስቱም ዉስጥ ማስጠንቀቂያ ወይም ትኩረት ነበር ፡፡
በቁጥር 19 “ እንግዲህ “ የሚለዉ ቃል አንባቢዎቹን በኢየሱስ ላይ በማትኮር ኢየሱስ ለእኛ ካደረገዉ ነገር የተነሳ የተወሰነ ነገር ማድረግ እንዳለብን ወደ ማስጠንቀቂያዎች ለመምራት ይጣራል ፤ ሁልጊዜ እነዚህ ነገሮች “ እንቅረብ/እንተያይ/እንጠብቅ “ በሚለዉ ቃል ይጀምራል (ቁጥር 22, 23, 24) ፡፡
- በእምነታችን በሙሉ እርግጠኝነት ወደ እግዚአብሄር እንቅረብ (ቁጥር 22) ፤ ያለ ምንም መሰናክል ወደ እግዚአብሄር መገኘት መሄድ እንችላለን ፡፡
- በክርስቶስ ባለን ተስፋችን በመያዝ ባለመነቃነቅ እንጠብቅ (ቁጥር 23) ፡፡
- በፍቅር እና በመልካም ስራ እርስ በእርስ እንተያይ (ቁጥር 24) ፤ ይህ ሰዎስተኛው የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ መጀመሪያ የኑሮአችን አካል ካልሆኑ መፈፀም/መደረግ አይችልም ፡፡
- በህብረት እና በአምልኮ በአንድ ላይ እንሰባሰብ (ቁጥር 25) ፡፡
- እርስ በእርስ መበረታታችንን/መመካከራችንን እንጠብቅ (ቁጥር 25) ፡፡
እነዚህን ነገሮች ከተዉን/ችላ ካልን የወንጌልን ኃይል እናጣለን ፡፡
ዕብራዉያን (10፡ 26-39)፡ ይህ ክፍል ጠንካራ ማስጠንቀቂያን ይዟል ምናልባትም በመፅኃፍ ላይ ጠንካራዉን ማስጠንቀቂያ፡ “ የእዉነትን እዉቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአትን ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢዓት መስዋዕት አይቀርልንምና ፤ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለዉ የእሳት ብርታት አለ “ (ቁጥር 26-27) ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ክርስቶስ ለእናንተ ባደረገዉ ያቀረበላችሁን የድነት እድል ችላ በማለት ከነገሩ ዞር በማለት ለእርሱ ካልኖራችሁ ፍርድ ይመጣባችኋል ማለት ነው ፡፡
በሚያናድድ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴት ስለ ክርስቶስ የቆሙ ሰዎችን፣ የሚሰብኩ እና ድነቱን እና የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስተምሩ ሰዎችን እይተናል ነገር ግን አሁን ስለ እርሱ የቆሙት ሁሉንም ነገር የሚቃወሙ ናቸው ፡፡
ከእግዚአብሄር የተቀበልነዉ ይህ እወቀት የጠለቀ/የቀረበ/ሚስጥር የሆነ እዉቀት ነው ፤ ታላቅ /ኃይለኛ እዉቀት ነው፡፡ እዚህ ጋር ያለዉ ማስጠንቀቂያ በኃይማኖት ዙሪያ ከሳታችሁ፣ በጥላዉ ዙሪያ ከሳታችሁ ጥላዉ ሊያጠፋችሁ አይችልም የሚል ነው ፡፡ በጥላዉ ዉስጥ ኃይል የለም ፤ ነገር ግን ስለ ተሰዋዉ ስለ ክርስቶስ ስታወሩ ከዚህ በኋላ ዋና ኃይል ስለሆነው ስለ እግዚአብሄር ልጅ እንጂ ስለ ድንኳኑ (ስለ ቤተ መቅደሱ) አታወሩም ማለት ነው ፡፡ ወደ እርሱ ከቀረባችሁ፣ በእርሱ ላይ ከፀናችሁ አብሮ በህብረተ እና በአምልኮ አብሮ በመገናኘት እርስ በእርስ ትተያያላችሁ ያ ካልሆነ እና ሆን ብላችሁ ይህን ሁሉ ችላ የምትሉ ከሆነ በዚያ ለመሆን አስቸጋሪ ስፍራ ይሆናል ፡፡
ይህ አስፈሪ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሆን ብለን ወደ እርሱ ብንቀርብ እና በእርሱ ላይ በንፀና ምን ይሆናል ? ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር መገናኘት ባንፈልግም ሆን ብለን ከሌሎች ጋር ብንገናኝ ምን ይሆናል ? እነዚህን ነገሮች ካደረግን በኑሮአችን የእግዚአብሄር የሚያስደንቅ ኃይል እንቀምሳለን/እናገኛለን ፡፡ ይህ የማስጠንቀቂያው የኃሳብ ጎን ነው ፤ በጥላ ዉስጥ ኃይል የለም ፤ ጥላው ኢየሱስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ የሰራዉን ትክክለኛ ስራ ያመለክታል ፡፡
መደምደሚያ
በጥላዉ ላይ ተይዛችኋል ? ከራሱ ከአምልኮዉ በላይ በይበልጥ በአስፈላጊነት በስፍራ ወይም በመዝሙር በኩል ወይም በአንዳንድ ፓስተሮች በኩል እርሱን ለማምለክ ተይዛችኋል ? ዛሬ ወደ ኢየሱስ ኃይል በመቅረብ እና በህይወታችሁ ለኃይሉ በመፍቀድ ለእናንተ አዲስ ምስክርነት እንዲያመጣ እንድትነኩት ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዕብ (10፡ 9) ፀኃፊዉ ምን ማለቱ እንደሆነ ግለፁ ፤ “ የመጀመሪያው “ ምን ነበር “ የሁለተኛውስ “ ምንድን ነው (ዕብ 8፡ 13) ? በዕብ (10፡ 10) “ በመስዋዕት የተቀሰደ መሆን “ ምን ማለት ነው ?
-
በዕብ (10፡ 16) ጌታ እንዴት አድርጎ “ በልባቸዉ ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸዉም እጽፈዋለሁ “ ?
-
በዕብ (10፡ 19) ፀኃፊው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስንገባ ድፍረት እንዳለን ይናገራል ፤ እንዲህ አይነቱ ድፍረት ምን የሚመስል ነው ?
-
በግል አስተያየታችሁ ዕብ (10፡ 25) ምን እያለ ነው ? ይህ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ነዉ ? ሌላ ምን ምሳሌ ይሆናል ?
-
ትዕግስተኛ መሆን/መታገስ ምን ያክል አስቸጋሪ ነው ? ዕብ (10፡ 36) የእግዚአብሄር ፍቃድ ከተፈፀመ በኋላ ተስፋዉን መቀበል እንደሚሆን ይናገራል ፤ ተስፋዉ ምንድን ነው ? (ዮሐ 3፡ 16, ዕብ 10፡ 16-17, ያዕ 1፡ 12)
-
በዕብረዉያን 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 10:19–22
“Therefore, brothers, since we have boldness to enter the sanctuary through the blood of Jesus, by a new and living way He has opened for us through the curtain (that is, His flesh), and since we have a great high priest over the house of God, let us draw near with a true heart in full assurance of faith, our hearts sprinkled clean from an evil conscience and our bodies washed in pure water.”
የኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት የቤተ መቅደሱን መጋረጃ ቀደደው ፣ እናንተንም ወደ እርሱ ጸጋ ፣ ምህረትና ፍቅር ትገቡ ዘንድ አስቻላችሁ ፡፡ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ለሚያምኑት ሁሉ ፣ በመላው የእግዚአብሔር ቤት ላይ ታላቅ ሊቀ ካህናት በመሆን ያገልግላል ፡፡ ወደ እርሱ መቅረብ ትችላላችሁ ፡፡ ወደ ኢየሱስ በእርግጠኝነት በእምነት ኑ ትድኑማላችሁ ፡፡
ኢየሱስ ወደ እርሱ እንድትቀርቡና በእርሱ ላይ እንድትጣበቁ ይፈልጋል ፡፡ ጸልዩ ፡፡ እርሱን ፈልጉ ፡፡ ተስፋን ፣ ህይወትን ወይም ድልን ለማግኘት ስትሉ ሌላ አምላክ ለራሳችሁ እንዳትሰሩ ወይም ወደ ጣዖት ዘወር እንዳትሉ ፡፡ የሚያስፈልጋችሁ ኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡ በኢየሱስ እንድሁም በእርሱ ኃይልና በቃሉ ላይ ተጣበቁ ፡፡ እርሱ በጥበብ ይሞላችኋል ፡፡ እርሱ ብቻ ርሀብና ጥማችሁን ያረካል ፡፡ እናንተ በእርሱ ላይ ስትጣበቁ ፣ እርሱ ልክ እናንተ እርሱን እንደምትሹት ሁሉ ሌሎችም እርሱን እንድሹ እንድትመክሩ ያዛችኋል ፡፡ በአንድ ላይ ተሰባሰቡ ደግሞም እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ ፡፡ ፍቅርንና በጎ ስራንም አጠንክሩ ፡፡ ከባድ በሆነው ጊዜ እንኳን ሳይቀር እርስ በእርሳችሁ ተበራቱ ፡፡ ተስፋም አትቁረጡ ፡፡ ጽኑ ፣ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ እርስ በእርሳችሁ ተመካከሩ ፡፡ ኢየሱስ እናንተ ለእርሱ ከሌሎች ተለይታችሁ ብቻችሁን እንድትኖሩ አይፈልግም ፡፡ ዛሬ ማን ይሆን የምታስቡለት ? ዛሬ ሂዱና በአዳኛችሁ በኢየሱስ ኃይል የሆነን ሰው ውደዱ ፡፡
“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ ፡፡ “
- ዕብራውያን 10፡19-22
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ቆሮንቶስ 4:1 — “ ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም ። “
1ኛ ተሰሎንቄ 5:17 — “ ሳታቋርጡ ጸልዩ ፡፡ “
ዕብራውያን 10:23–25 — “ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ፤ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው ፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።