Comparing The Old And New Covenants
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዕብራዉያን መፅኀፍት አዲሱ ኪዳን ከአሮጌዉ ኪዳን የተሻለ መሆኑን ማሳየቱን ይቀጥላል ፡፡ የመፅኃፉ ፀኃፊ ለዕብራዉያን ምንም እንኳን ነገሮችን ከእግዚአብሄር ጋር በአንድ መንገድ እንዲሆኑ እየተጠቀሙ የነበሩ ቢሆኑም ቀድሞ ለምደዉት ከነበረዉ ነገር ኢየሱስ የሰጠዉ ነገር የተሸለ እንደ ሆነ ለማሳየት ምሳሌዎቹን መስራቱን ይቀጥላል፡፡ በክርስቶስ በኩል የሆነዉ አዲሱ ከማንኛዉም ነገር ያስቡት ከነበረዉም እንኳን የተሻለ ነው ፡፡
በምዕራፍ 9 የመጀመሪያዎቹ አስር ቁጥሮች አሮጌዉን/ያለፈዉን ኪዳን ሲሸፍኑ የምዕራፉ የቀሩት ቁጥሮች ደግሞ ስለሚሻለዉ አዲሱ ኪዳን ያወራሉ ፡፡ አሮጌዉ አይቆይም ነገር ግን አዲሱ ለዘላለም ይቆያል ፤ ዕብራዉያንን ለመረዳት በአንዳንድ መንገድ የሁለት ስፍራዎች ዜጋ መሆናችንን መረዳት አለብን፡ የዚህ አለም እና የእግዚአብሄር መንግስት ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (9፡ 1-10)፡ ዋይርስቤ አሮጌዉ ኪዳን የበታች/ያነሰ/የማይሻል የነበረበትን አምስት ምክንያቶች ያቀርባል፡
- “ የምድራዊ መቅደስ ነበረው (ቁጥር 1) “
- በሰዉ የተሰራ ነበር (ዕብ 8፡ 2) ፡፡
- የተከፈለዉ በሰዉ ነበር ፡፡
- ጥገናና መልሶ ግንባታን ይፈልጋል ፡፡
- መኖር በሚችልበት በአቀማመጥ/በመልከዓ ምድር የተወሰነ ነበር ፡፡
“ የሚበልጥ/የተሻለ ነገር አይነት ነበር (ቁጥር 2-5) “
ምን ይመጣ እንደ ነበር አንስቷል/ጠቅሷል ፡፡
መብራትን ለመስጠት የወርቅ መቅረዝ አስፈልጎታል ኢየሱስ ግን የአለም ብርኃን ነው (ዮሐ 8፡ 12)፡፡
በእያንዳንዱ ሳምንት የአስራ ሁለቱ ቂጣ/እንጀራ ዉክልና በማስቀመጥ የእግዚአብሄርን መገኘት ይወክላል ፤ ኢየሱስ ግን የዘላለም የህይወት እንጀራ ነው (ዮሐ 6፡ 35) ፡፡
ሁልጊዜ የወርቅ መሰዊያዉ በማሳያነት በቅዱሱ ስፍራ/በቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ ይታያል (ዘጸ 30፡ 6, 40፡ 5) በፀሎትም ለመማለድ ሁሉጊዜ በጥዋት ዕጣን በላዉ ላይ ይቃጠልበት ነበር (መዝ 141፡ 2) ፡፡
ሮሜ (8፡ 33-34) ኢየሱስ በእግዚአብሄር ፊት ስለ እኛ እንደሚማልድ ይናገራል ፡፡
“ ለሕዝቡ የማይገኝ/የማይታይ ነበር (ቁጥር 6-7) “
የቅድስተ ቅዱሳኑ የኪዳኑ ታቦት እና የስርየት መቀመጫዉ ቤት ሲሆን በአመት በስርየት ቀን ብቻ በሊቀ ካህኑ ሊገባበት የሚቻል ነው ፡፡
ሊቀ ካህኑ ለራሱ ኃጢዓት እና እንዲሁም ደግሞ የሕዝቡን ኃጢዓት ያስተሰረያል ፡፡
እንደ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ለእኛ ብቻ እንጂ ለራሱ ኃጢዓት አላስተሰረየም ፡፡
“ ጊዜያዊ ነበር (ቁጥር 8) “
ካህናቱ ሲያገለግሉ ሕዝቡ ከኋላ ይጠብቅ ነበር እንጂ ራሳቸዉ ወደ እግዚአብሄር መገኘት መግባት አይችሉም ፤ ከሁሉም በተሻለ ጊዜአዊ ነበር ፡፡
መንፈስ ቅዱስ ስራዉን እየሰራ ነበር ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ እግዚአብሄርን እንዲቀርቡት ለሰዎች መንገድን አልከፈተም ነበር ፡፡
“ አገልግሎቱ ዉስጣዊ ሳይሆን ዉጫዊ ነበር (ቁጥር 9-10) “
መስዋዕቱ የአምላኪዎቹን አስተሳሰብ መቀየር አልቻለም ፤ ዉጫዊዉን ነገር ብቻ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡
ዕብራዉያን (9፡ 11-28)፡ በተጨማሪም ዋይርስቤ አዲሱ ኪዳን ለምን የላቀ እንደ ሆነ አምስት ምክንያቶችን ያቀርባል፡
“ ሰማያዊ ነው (ቁጥር 11) “
በሰዉ እጅ የተሰራ ስላልሆነ በሰዉ መጠገን/መልሶ መሰራት አይችልም ፡፡
“ ኃጢዓት ለማንፃት አገልግሎቱ የተሳካ/ዉጤታማ ነው (ቁጥር 12-15) “
የኢየሱስ ሞት በሚገባ ስለ ሁሉ አንድ ጊዜ ኃጢዓትን አስወግዷል/ወስዷል ፡፡
“ አገልግሎቱ በጣም ዋጋ በሚያስከፍል መስዋዕትነት ላይ የተመሰረተ ነው (ቁጥር 16-23) “
ፀኃፊው አንድ ሰው ለመሞት ፍቃደኝነትን ባደረገ ጊዜ ዉጤቱን ብቻ በመዉሰድ የፍቃደኝነቱን ትዕዛዝ በማብራራት እንደ ማሳያነት ፍቃድን (በሞት ላይ የሰዉዬዉን ንብረት ለማከፋፈል ትዕዛዝ የሚሰጠዉን ማስረጃ) ተጠቅሟል ፡፡ አሮጌዉ ኪዳን ዉጤትን መዉሰድ ከመቻሉ በፊት ደም ማፍሰስ ያስፈለገዉ ለዚያ ነው ፡፡
ደም ሳይፈስስ ስርየት/ይቅርታ የለም
ዋይርስቤ የመጀመሪያዉ/የቀድሞዉ መቅደስ በእንስሳት ደም ነፅቷል ነገር ግን እኛ የእግዚአብሄር ልጅ ደም በመርጨት በሰማያዊ መቅደስ በእግዚአብሄር ተቀባይነት ያገኘን መሆን እንችላለን ፡፡
“ አገልግሎቱ መፍፀምን/ፍፃሜን ይወክላል (ቁጥር 24) “
በቁጥር (24-28) ተገልጧል የሚለዉ ቃል ሰዎስት ጊዜ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡
ኢየሱስ ስለ እኛ ኃጢዓታችንን በማስወገድ በአባቱ ቀኝ በሰማይ ነው ፡፡
“ አገልግሎቱ የመጨረሻ እና ማብቃያ ነው (ቁጥር 25-28) “
ኢየሱስ ኃጢዓትን ሊያስወግድ ተገለጠ (ቁጥር 25) ፡፡
ኢየሱስ እርሱን ለሚጠብቁት ድነትን ለማምጣት ለሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል (ቁጥር 28) ፡፡
መደምደሚያ
እነዚህ ሁሉ አዲሱ ኪዳን ከቀድሞዉ/ከአሮጌዉ ኪዳን የሚሻልበት፣ የሚበልጥበት እና የላቀበት ምክንያቶች ናቸው ፤ ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ አድርጓል ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary, Vol. II, (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 309-310.
Wiersbe, p. 311-312.
ጥያቄዎች
-
በአሮጌዉ/በቀድሞዉ ኪዳን ስር ሊቀ ካህኑ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ምን ያደርጋል ለማድረግስ እንዴት አድርጎ ይሄዳል ? (ዘሌ 16፡ 32-34)
-
መንፈስ ቅዱስ ስለ ቅደስተ ግልፅ እያደረገ የነበረዉ ምንድን ነበር ? ለአሁኑ ጊዜስ እንዴት ምልክት ይሆናል (ዕብ 9፡ 8-9) ? ወደ እግዚአብሄር የሚስገባዉ ብቸኛዉ መንገድ ማነው ? (ዮሐ 14፡ 6)
-
ኢየሱስ የሊቀ ካህንን ስራ/ተግባር እንዴት እንደፈፀመ ግለፁ ፡፡
-
በአዲሱና በአሮጌዉ ኪዳን በሁለቱም የደም ተግባር በጣም አስፈላጊ የነበረዉ ለምን ነበር (ዘሌ 16፡ 5-10, ዕብ 9፡ 22, 13፡ 12) ? ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ደም በጣም ለምን እንደሚያወሩ ለሚጠይቋችሁ አላማኞች ምን ትሏቸዋላችሁ ?
-
ዛሬ/በዚህ ዘመን አማኞች ከእግዚአብሄር ጋር ለማዉራት ለምን ሊቀ ካህን አላስፈለጋቸውም (1ጢሞ 2፡ 5) ? በብሉይ ኪዳን እንዳሉት ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ብዙ መስዋዕት ማድረግ ለምን አላስፈለገውም ? (ዕብ 7፡ 27, 9፡ 24-26, 10፡ 11-12)
-
በመፅሀፍ ላይ ለዕብ (9፡ 27) ብርቅ የሆኑት ተስፋዎች ምንድን ናቸው (ዘፍ 5፡ 24, 2ነገ 2፡ 11, ዮሐ 11፡ 43-44, 1ተሰ 4፡ 17) ? በአማኞች ፍርድ እና በማያምኑት ፍርድ መካከል ልዩነቱ ምን ይሆናል (2ቆሮ 5፡ 10, ራዕ 20፡ 11-15) ? በየትኛዉ ፍርድ ዉስጥ ትሆናላችሁ ? ቤተሰቦቻችሁ፣ ጓደኞቻችሁ እና የስራ ባልደረቦቻችሁ በየትኛዉ ፍርድ ዉስጥ ይሆናሉ ?
-
በዕብራዉያን 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 9:11–12
“But the Messiah has appeared, high priest of the good things that have come. In the greater and more perfect tabernacle not made with hands (that is, not of this creation), He entered the most holy place once for all, not by the blood of goats and calves,but by His own blood, having obtained eternal redemption.”
የዕብራውያን ጸሀፊ አዲሱ ኪዳን ማለትም የኢየሱስ አገልግሎት እንዴት ከአሮጌው ኪዳን ፡- ከህጉ እንደሚሻል ይገልጻል ፡፡ አዲሱ ኪዳን ታላቅ የሆነ ፣ ፍጹምም የሆነ ቤተ መቅደስ አለው ፡፡ ይህ በምድራዊ ነገሮች የተሰራ አይደለም ነገር ግን ልክ እናንተ ወደ እግዚአብሔር መገኘት ስትገቡ በቀጥታ ይሄ ራሱ ሰማይ ነው ፡፡ በአዲስ ኪዳን ቤዛነትን የምታገኙት በየአመቱ ከሚደረግ የእንሰሳት ደም መስዋዕት አይደለም ነገር ግን ከኢየሱስ መስዋዕት እንጂ ፡፡ እርሱ ስለ ዓለም ኃጢአት አንድ ጊዜ ለሁሉም ሞተ ፡፡ የእርሱም በሞት መታዘዝ ለእናንተ ዘላለማዊ ድነትንና ቤዛነትን አስገኘ ፤ ይህም እናንተ ኢየሱስን እንደ ጌቶች ጌታና እንደ ነገሥታት ንጉሥ እንድታከብሩት አደረጋችሁ ፡፡
በኢየሱስ ስለሆነው አዲስ ኪዳን አመስግኑ ፤ አስተውሱ ከእርሱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት በልማድ ወይም ለእግዚአብሔር የሆነን ነገር በመስጠት ላይ የተመሰረተ አይደለም ፡፡ ይህ ድነታችሁን በበጎ ስራ ማግኘትም አይደለም ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና መጸለይ ለእግዚአብሔር ያላችሁን ፍቅር ያሳያል ፡፡ እነዚህን ተግባራት ወይም ትምህርቶች የምትፈጽሙበትም ምክንያት እነዚህ ወደ እግዚአብሔር ልብ ስለሚያቀርቧችሁና በህይወታችሁም መገኘቱን ስለሚያፋጥኑ ነው ፡፡ እስኪ ዛሬ ራሳችሁን እንዲህ ጠይቁ ፡- ወደ ጌታ እየቀረብኩኝ ያለሁት ወደ እርሱ መቅረብ እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው ወይስ እርሱን ለማምለክ ስለምፈልግና መገኘቱን ስለምሻ ነው ? ጌታ በፍቅሩ በነጻነት እንድትኖሩ ይፈልጋል ፡፡
“ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም ። “ - ዕብራውያን 9፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሮሜ 6:8-11 — ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን ፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና ። መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና ፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል ። እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ ። “
- ገላትያ 5:1 — “ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ ። “
- ዕብራውያን 9:13–14 — “ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ ፥ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን ? “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።