General Letters Hebrews

The New Covenant Is Superior

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 660 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ጥቂት ስለ ሊቀ ካህኑ አዉርተናል ዛሬም በዚያ ላይ በጥልቀት እናወራለን ፡፡ የዕብራዉያንን መፅኀፍ ማን እንደ ፃፈው አናዉቅም ነገር ግን በአሮጌዉ በሕግ ኪዳን ስር መኖራቸዉን እንዲያቆሙ ለማሰማን ለዕብራዉያን በዕብራዉይ የተፃፈ እንደ ነበር እናውቃለን ፡፡

ከዕብራዉያን ጥያቄ አካል የትኛዉ አምላክ የሚበልጥ ነው - አምላኬ ወይስ ኢየሱስ ? የሚል ነው ፤ ምዕራፍ 8 ከክርስቶስ ጋር በትስስር ስለመሆን እና መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ጠንካራ ለመናን/መጠይቅን ያደርጋል ፡፡ የመልዕክቱ ተቀባዮች መሲሁን ኢየሱስን ኢየሱስ ስለሚያመጣዉ ነፃነት፣ ኃይል እና መቀራረብ እና ስላደረገዉ አዲስ ኪዳን ሙሉ ለሙሉ የያዙ አይመስሉም ፤ አብዛኛው ኢየሱስ እንዴት የሚያስደንቅ እንደ ሆነ በሚገባ ማየት እንዳልቻሉት ከኢየሱስ ጋር እንደተቀላቀለ ብዙ የአለም አብለጭላጪ ነገር እንደ ነበራቸው ተቀባዮች የሆነ ነው ፡፡ ኢየሱስ የመስዋዕቱ በግ፣ የይሁዳ አንበሳ፣ ሊቀ ካህን፣ የህይወት እንጀራና ብዙ ነው ፤ እሱ ብዙ ነገር ነው ፡፡

ለዛሬ ሰዉ በመጠኑ በክርስቶስ አማኝ ወደ ሆኑ አማኞች በመሄድ “ ማንኛዉ አምላክ ይበልጣል - አምላኬ ወይስ ኢየሱስ ? “ በማለት የሚጠይቃቸዉን ይመስላል ፤ አብዛኞቻችን ምናልባትም በጣም ብዙዎቻችን በጊዜያት ዉስጥ ከኢየሱስ በላይ ያስቀመጣናቸዉ አማልዕክት ወይም ጣዖቶች አሉን …. ገንዘብ፣ ንብረት፣ ቤተዘብ እና ወ.ዘ.ተ ፤ በሌላ አነጋገር “ ለምን ወይስ ለምን እየተገዛሁ ነው ? “ ለህጉ ? ለአንድ ብርጭቆ ወይን ነዉስ ? ለገንዘብ ? መጀመሪያ “ እግዚአብሄር ምንድነዉ የሚያስበው “ ብለን መጠየቅ አለብን ፡፡ በዙሪያችን ባሉት የአለም በሆኑት ነገሮች ላይ ተደግፈናል ወይስ ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ፡፡

ትምህርት

ዕብራዉያን (7፡ 26-28)፡ እነዚህ ጥቅሶች ለሊቀ ቃህኑ እንደ ስራ ድርሻ ሊገለፁ ይችላሉ ፡፡ ቁጥር 26 በህጉ ስር ከነበሩት ሊቀ ካህናት ጋር ሲወዳደር እንደ ሊቀ ካህናችን የኢየሱስን ታላቅነት ያሳያል፣ “ ቅዱስ ነው፣ ንፁኅ ነው፣ አልቆሸሸም፣ ከኃጢዓተኞች የተለዬ ነው እና ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ነው “ ፡፡ ቁጥር 28 የሚይዘው መግለጫ ወደ ምዕራፍ 8 ይመራል ፡፡

ዕብራዉያን (8፡ 1-2)፡ ፀኃፊው በምዕራፍ 7 ላይ ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ እና በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ አንድ ሊቀ ካህን እንደ ነበር ያብራራል (ቁጥር 1) ፡፡ የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናቶች የስርየት መስዋዕትን የማድረግ ኃለፊነት ነበረባቸዉ ከአመት በኋላም የሚፈፀም ነበር ፡፡ ኃላፊነቱ በፍፁም አልተፈፀመም ነበር ፤ ያ ስራ አሁን በሊቀ ካህኑ በኢየሱስ መስዋዕትነት ተፈፅሟል ፤ ይህን በመፈፀም አርፏል ፡፡ እዉነተኛዉ ቅዱስ ካህን በሰማይ ያለዉ ብቻ ነው ፤ እግዚአብሄር የሰራው ፍፁም ነው ፡፡ የሰዉ ልጅ ነገሮችን ደግመዉ በመስራት ጥሩ፣ የሚያምር ወይም በስርዓት ሊያደርጉ ይችላሉ ነገር ግን እግዚአብሄር እንዴት ዉብ/መልካም አድርጎ ነገሮችን ከደረጋቸዉ ጋር በፍፁም አናመሳስላቸዉም (ቁጥር 2) ፡፡

ዕብራዉያን (8፡ 3-5)፡ ቁጥር 3 የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናቶች መስዋዕት አድርገዋል ነገር ግን ሊሰዋ የሚችል ነገርን አግንተዋል ፡፡ በብሉይ ኪዳን ካህናት ከሌዊ ነገድ መጥተዋል ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ መጣ በፍፁም በምድር ላይ እንደ ሊቀ ካህን ሊያገለግል አይችልም (ቁጥር 4) ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመከተል ለእግዚብሄር የማደሪያ ስፍራ ድንኳንን (የታቦቱ ማደሪያን) በመስራት መልካም ስራን አደረገ ፤ ነገር ግን ሙሴ ያደረገዉ ሁሉም ነገር በሰማይ የእግዚአብሄር ማደሪያ ስፍራ ምን እንደሚመስል ጥላ ነበር (ቁጥር 5) ፤ ከአንዱ እዉነተኛዉ እግዚአብሄር ጋር የምንነጋገርበት ነው ፡፡ ስለ ሰማይ ምን እናዉቃለን ? በBlueLetterBible.org ላይ ፀኃፊው ዶን ስቴዋርት ሰማይ እንዴት ከምድር እንደሚለይ አስቀምጧል ፤ በሰማይ ሞት የለም (ራዕ 20፡ 14), ለቅሶ የለም (ራዕ 21፡ 4)፣ ርኩሰት የለም (21፡ 7) እንዲሁም ጨለማ የለም (ራዕ 22፡ 5) ይላል ፡፡ በተጨማሪም በጌታ ፊት ለፊት እንሆናለን (ራዕ 21፡ 3) እንዲሁም በእርሱ መገኘት ፊትም እንሰግዳለን እንዘምራለንም ፡፡

ዕብራዉያን (8፡ 6-7)፡ ኢየሱስ ለካህናት መተኪያ/ምትክ ብቻ አይደለም ከዚያም የሚበልጥ እጂ ፤ የመስዋዕቱ ምትክ/መተኪያ ነው ፤ የአሮጌዉ ኪዳን መተኪያ ነው (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ የካህን መተኪያ ነው ፤ የቤተ መቅደሱ ምትክ ነው ፡፡ ኢየሱስ ህጉን ሊፈፅም መጣ ፤ ሕጉ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ነበር ፤ እነዚህን ሁሉ ፈፀማቸው - መስዋዕቱን፣ በዓላቱን እና ስርዓቶቹን ሁሉ ፈፀማቸው ፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በኢየሱስ የተፈፀመ አላማ ነበራቸው ፡፡ በኢየሱስ በኩል እግዚአብሄር ወደ እርሱ እንድንሄድ ከመጠበቅ ይልቅ ሊያገኘን ወደ እኛ መጣ ፤ ስለዚህ ኢየሱስ የሚበልጥ/የላቀ አገልግሎት አለው በተሻለ ተስፋ ለታላቁ ኪዳን መካከለኛ ነው (ቁጥር 6) ፡፡ ይህ ሁሉ የላቀ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር ስራዉን ስለሚሰራው እና ስለምንካፈል ፡፡ ዕብራዉያን የመጀመሪያዉ ኪዳን የሚጠብቃቸዉን ነገሮች ማሟላት የቻሉ ስላልነበሩ አዲስ ኪዳን ተደረገ ፡፡ የመጀመሪያዉን ኪዳን መጠበቅ ችለዉ ቢሆን ኖሮ ሌላ አዲስ አይስፈልጋቸዉም (ቁጥር 7) ፡፡

ዕብራዉያን (8፡ 8-11)፡ አዲሱ ኪዳን ከኤር (31፡ 31-34) በመጥቀስ በቁጥር (8-12) የተጠቀሰ ነው ፡፡ አዲሱ ኪዳን በብዙ ከቀድሞዉ ኪዳን የተሸለ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሕጉን በአይምሮአቸዉ እንደሚያስቀምጥ እና በልባቸዉ እንደሚፅፍ ተናገረ (ቁጥር 10) ፡፡ አብዛሀኛዉ ሰው የትኛዉ ትክክል እና የትኛዉ ደግሞ ትክክል እንዳልሆነ ዉስጣዉ እዉቀት አላቸው ፤ ስህተት የሆነ ነገር በምናደርግ ጊዜ እናዉቃለን ፡፡ እንደ አማኝ ወደ እግዚአብሄር ተፈጥሮአዊ የሖነ ዝንባሌ አለን ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በምነብ ጊዜ የሚታወቀዉ/የሚያስተጋባው ትክክሉ ምንድን ነው ፤ በልባችንም ላይ የተፃፈበት ምክንያት ለዚያ ነው ፡፡ ያውቀናል የእርሱም ህዝቦች ነን ፤ እግዚአብሄርን እናውቀዋለን (ቁጥር 10-11) ፡፡ ቀድሞ ሕዝቡ ሕጉን እንዴት አገኙት ? እግዚአብሄር ሕጉን ለሙሴ በድንጋይ ፅላት ላይ ሰጠው በፅላቱም ላይ የተፃፉትን ቃላት ያደምጡ/ይሰሙ ነበር ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ እግዚአብሄር ሙሴን ሕዝቡን እንዲነግራቸዉ ነግሮታል ፤ አሁን ግን እግዚአብሄር ሕጉን በቀጥታ በአይምሮአችን ዉስጥ እና በልባችን ላይ አስቀምጧል ፡፡ አዲስ ኪዳንን በምናነብ ጊዜ በልባችን ስላለዉ ነገር ማረጋገጫ ነው ፤ መፅኀፍን ስናነብ ከልባችን ጋር ይህን ግንኙነት /ትስስር ያደርጋል - ያስተጋባል/ይታወቃል ፡፡

ዕብራዉያን 98፡ 12-13)፡ በቁጥር 12 የዕብራዉያን ፀኃፊ በኤርምያስ 31 እግዚአብሄር ስለ ሰጠዉ ተስፋ አድማጮቹን እያስታወሳቸው ነው ፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር ኃጢዓታቸዉን አያስብም ፤ በሰማይ በእግዚአብሄር ፊት ቆማችሁ ከዚህ በኋላ ኃጢዓታችሁን እንደማያስብ ስታዉቁ አስቡት ፡፡ ልክ እንደ ዕብራዉያን መስራት የምናቆምበት ጊዜ ነው - በሚገባ በቂ ለመሆን መሞከርን፣ ማድረግን ማቆም ከዚያ ይልቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነትን፣ ፀጋን፣ ምህረትን እና የእግዚአብሄርን ይቅርታ መቀበል ፡፡ በአዲሱ ኪዳን የቀድሞዉ/አሮጌዉ ኪዳን አልፏል (ቁጥር 13) ፤ ተተክቷል ፡፡

ሁሉም የህጉ መስፈርቶች ከዚህ በኋላ አይኖሩም ፡፡ በእናንተ እና በጌታ መካከል ግንብ እንዲኖር ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በመተው ርቀዉ እንዲጠፉ መፍቀድ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ገነባናቸዉ እንኳን የማናስተዉላቸዉን እኛን ከእግዚአብሄር የሚያርቁ አማልዕክትን እንፈጥራለን ፤ ማድረግ በማንችለው ላይ ወይም ደግሞ በእኛና በእግዚአብሄር መካከል በምናብ በምናየዉ ነገር ፍርኃትን እናስቀምጣለን ፡፡ አሁንም ለእግዚአብሄር መስዋዕትን ማድረግ እንፈልጋለን - ስለተሸከምነዉ ጥፋተኝነት ለመክፈል ፡፡ በአዲሱ ኪዳን ኑሩ ፤ መጋረጃዉ ተቀዷል ፤ በመሲሁ በኩል ከአብ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረትን ሊኖረን ችሏል ፡፡

በሐዋ (3፡ 1) ጴጥሮስ እና ዮሐንስ 3ሰዓት ላይ ሊፀልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ ፤ ይህ የመሰዋዕቱ ጊዜ ከሆነዉ ከ2፡ 30 በፊት ነበር ፡፡ በመስዋዕቱ መጨረሻ ላይ “ ተፈፀመ “ የሚለዉ ቃል ተነግሯል ፤ ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ወይኑኑ ከወሰደ በኋላ “ ተፈፀመ “ በማለት እንደ ተናገረ አስታዉሱ ፤ መስዋዕትነቱ አብቅቷል/አልቋል ፡፡ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ለመስዋዕት ሳይሆን ከጌታ ጋር በፀሎት ለመገናኘት ነበር ወደ ቤተ መቅደስ የሄዱት ፤ የአዲሱ ኪዳን ተግባርን ተረድተዋል ፡፡

በአሁኑ ጊዜ አማኞች ሊጠነቀቁባቸዉ የሚያስፈልጉ ነገሮች ወይም ህጋዊነትን/ስርዓትን የሚፈጥሩ ነገሮች አሉ፡

  1. ቤተ ክርስቲያን፡ የምገኘዉ/የምሳተፈው ቤቱን ለማረጋገጥ ነዉ ወይስ ከጌታ ጋር ለመገናኘት እና ለማምለክ ነዉ የምገኘው ?
  2. ፀሎት፡ የሌሎችን ፀሎት እጠቀማለሁ ወይስ በፀሎት ግላዊ/ትስስራዉ ጎን እዝናናለሁ ?
  3. መፅኃፍ ቅዱስ፡ በተለመደ/በህጋዊነት በኩል ነዉ የማነበዉ ወይስ በመሲሁ በኢየሱስ ላይ በታኮረ ግንኙነት መንፈሳዊነት በኩል ነዉ የማነበው ?

መደምደሚያ

ልባችሁን እና ኃሳባችሁን የእግዚአብሄር ቃል እንዲቀይረዉ ፍቀዱለት ፤ አማልዕክቶቻችሁ የሚሆኑ የተቀመጡ ስርዓቶችን/ሕጎችን ከመከተል ይልቅ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር በትስስር/የተቀራረበ እንዲሆን ፍቀዱለት ፡፡ ያለ ትስስር/ያለ ቅርርብ የስርዓትን መብት ለማግኘት በመሞከር ጊዜአችሁን በመጨረስ ከእርሱ ጋር ቅርርብነቱን ሙሉ ለሙሉ ታጡታላችሁ/ትስቱታላችሁ ፡፡

  1. Don Stewart, What Will It Be Like in Heaven?; available at https://www.blueletterbible.org/faq/don_stewart/don_stewart_148.cfm..

ጥያቄዎች

  1. በስራ የሚያምኑ ሰዎች ኢየሱስን ለማወቅ በጠየቁአችሁ ጊዜ ምን አይነት ማስረጃ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ ? (ዕብ 8፡ 7, 11-12)
  2. ከአዲሱ ኪዳን አሕዛቦች እንዴት ይጠቀማሉ/ጥቅም ያገኛሉ ? አይሁዶች ኢየሱስን እንደ መሲህ ተቀብለዉት እና ይዘዉት ቢሆን እግዚአብሄር ለአሕዛብ መዳንን ያቀርባል ብላችሁ ታምናላችሁ ? (ዘፍ 18፡ 18, 22፡ 18, 26፡ 4, ሮሜ 1፡ 16, 2፡ 9-11, 3፡ 29-30, 11፡ 11-17, ገላ 3፡ 8)
  3. እግዚአብሄር እንዴት የአንዳንድ ሰዎችን አለመታዘዝ ለሌሎች እድልን ለማምጣት እንደሚጠቀምበት አስቡ ፤ እግዚአብሄር ነፃ ፍቃድ ለምን እንደሰጠን ምን ታስባላችሁ ? ያለዚህ/ያለ ነፃ ፍቃድ አለም እንዴት የተለየት ትሆናለች ?
  4. በዕብራዉያን 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hebrews 8:1–2

“Now the main point of what is being said is this: We have this kind of high priest, who sat down at the right hand of the throne of the Majesty in the heavens, a minister of the sanctuary and the true tabernacle that was set up by the Lord and not man.”

የዕብራውያን ጸሀፊ በዋናነት ለተደራሲያኑ ስለዚህ ስለ አዲሱ ኪዳን ያወራላቸዋል ይህም ፡- ሰዎች በኢየሱስ ምክንያት ይህን የተሻለ ፣ የበለጠና እና በደንብ አስተማማኝ የሆነ ኪዳን ማግኘት እንደቻሉ ነው ፡፡ ኢየሱስ አሁን ታላቅ ሊቀ ካህን ነው በሰማይም በአብ ቀኝ ተቀምጧል ፡፡ እርሱም በሰው ሳይሆን በራሱ በእግዚአብሔር በተሰራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አምልኮን ይመራል ፡፡ ሰዎች የቀረበላቸውን እድል ማወቅና ወደ ዘላለማዊው ሊቀ ካህናት ወደ ኢየሱስ መቅረብ ያስፈልጋቸዋል ፡፡

በብሉይ ኪዳን ላይ ተጠምዳችኋልን ? በራሳችሁ በጎ ስራ ለራሳችሁ ድነትን ለማግኘትና ኃጢአታችሁን ለመስሻር ትጥራላችሁን ? አስታውሱ ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችሁ መስዋዕት ሆኗል ፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል ፡-“ዓመፃቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም ፡፡ “ ኢየሱስ እርሱ ታላቁ ሊቀ ካህናችሁ ነው ፤ እናንተም በየቀኑ በእያንዳንዷ ደቂቃ ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላችሁ ፡፡ እርሱ እንዲሁ እንዳላችሁ ይወዳችኋል ፡፡ እናንተ እርሱን በየቀኑ እያከበራችሁ ትኖሩ ዘንድ እርሱ ከእናንተ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ፡፡ ይሄ ጥሩ ነገር ስለማድረግ ወይም ትክክል የሆኑትን “ የክርስቲያን ተግባራት “ ስለመፈጸም አይደለም ፡፡ በክርስቶስ እናንተ በቂ ናችሁ ፡፡ ዛሬ በእግሮቹ ስር እረፉ ፣ ለእርሱም ንገሩት እናም እርሱን አዳምጡት ፡፡ ይህንን ማድረግ ስላለባችሁ አይደለም ይልቁንም ከአዳኛችሁና ከዘላለማዊው ሊቀ ካህናችሁ ጋር ህብረት እንድኖራችሁ ስለምትፈልጉ እንጂ ፡፡

“ ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው ፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን ፤ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው ፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት ። “

  • ዕብራውያን 8፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤርምያስ 31:31 — “ እነሆ ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “

ዕብራውያን 8:6 — “አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል ። “

ዕብራውያን 8:12 — “ ዓመፃቸውን እምራቸዋለሁና ፥ ኃጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም ። “