General Letters Hebrews

A Greater Priesthood

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 659 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዕብራዉያን ቃላችን ሊቀ ካህን የሚል ነው፡ “ እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ስላለን ጸንተን ኃይማኖታችንን እንጠብቅ “ (ዕብ 4፡ 140 ፡፡ ብሉይ እና አዲስ ኪዳን በአንድ ላይ ታስረዋል ፤ ከኢየሱስ የተነሳ አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን መፈፀም ነው ፡፡ ኢየሱስ ከሕጉና ከካህናቱ ይበልጣል ፤ እንዲሁም ኢየሱስ ከዘፍጥረት በመምጣት በዚህ ምዕራፍ ላይ ብዙ ትኩረት ከተሰጠው ከመልከ ጼዴቅም ይበልጣል ፡፡ ከዚህም ዕብራዉያን ፀኃፊው ኢየሱስ ከሁሉም ነገር እንደሚበልጥ ለማመልከት በጥልቀት ስለሚጓዝ የድግግሞሽ ስሜት ይሰማል ፡፡ በእርግጥም ከምዕራፍ 7 የዕብራዉያን ጭብጥ “ ኢየሱስ ከምንም ነገር የተሻለ ነው “ የሚል ሊሆን ይችላል ፡፡

ትምህርት

ዕብራዉያን (7፡ 1-3)፡ ዋይርስቤ ኢየሱስ በታሪክ የተለዬ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ መልከ ጼድቅ በሁለት ነገሮች የታወቀ ነበር - በአብርኃም ዘመን ንጉስ እና ካህን ነበር (ቁጥር 1) ፤ አብርኃምም የስሙ ትርጓሜ “ የፅድቅ ንጉስ “ እና የሳሌም ንጉስ ስለ ነበረም በተጨማሪም “ የሰላም ንጉስ “ የሚል ስም ለተሰጠው ለመልከ ጼዴቅ ከዉጊያ ገድል ከሁሉም አስራትን ሰጠው (ቁጥር ) ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ መልከ ጼዴቅ የዘር ግንድ የለዉም ፤ ዉልደቱ እና ሞቱ አልተመዘገበም ፤ ከዚህም የተነሳ መልከ ጼዴቅ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ፡፡

ግን ለምን ? መልከ ጼዴቅ በምን ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? በስሙ ትርጉም ብቻ በቀላሉ የክርስቶስ ጥላ ነው ? ወይስ የመልከ ጼዴቅ ስርዓት(ክህነት) ለዘላለም ይቆያል ተብሎ በተፃፈው በክህነቱ ዘላለማዊነት ነው (መዝ 110፡ 4)?

ዕብራዉያን (7፡ 4-14)፡ በታሪክ መልከ ጼዴቅ ታላቅ ሰዉ ነበር ፡፡ ታላቅነቱን እዉቅና በመስጠት(በማስተዋል) አብርኃም ከዘረፈዉ ነገር ሁሉ አስራትን ሰጠው (ቁጥር 4) ፤ በብሉይ ኪዳን ሌዋዊያን ከህዝቡ አስራትን እንዲቀበሉ ታዘዉ ነበር ፤ ነገር ግን የአብርኃም ልጆች ስለሆኑ በአብርኃም በኩል ለመልከ ጼዴቅ አስራት እንደተከፈለ የተረዱ ሊሆኑ ይችላሉ (ቁጥር 9-10) ፡፡ ይህ እዉነት መባረክ ከታላቁ ለትንሹ እንደሚነገር በመናገር መልከ ጼዴቅ ቆይተው ከመጡት ሌዋዊያን የክህነት አገልጋዮች እንደሚበልጥ በማሳየት አቀናጅቷል/ያሳያል ፡፡

ከመልከ ጼዴቅ አንፃር ዮሐንስ ማክአርቱር “ ክህነቱ በሌዋዊያን የክህነት አገልግሎት ላይ ስልጣን ከነበረዉ ከህጉ በላይ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ በክህነት ላይ ያለ ለዉጥ ከህጉ መለወጥ ጋር የሚስማማ/የሚጣጣም ነው (ቁጥር 12) ፤ ስለሆነም የክህነት ለዉጥ/ሂደት ከመልከ ጼዴቅ ወደ ሌዋዊያን ክህነት ከዚያም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኢየሱስ ክህነት ሄዷል ፡፡ እንደ ሊቀ ካህን የኢየሱስ መቀመጥ የህጉ መፈፀም እንጂ መጥፋት አይደለም፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ (ማቴ 5፡ 17) ፡፡

ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ የመጣ ነው (ቁጥር 14) ፤ ይህ “ በመሰዊያው “ እንዲያገለግሉ በሕጉ ከታዘዘዉ ነገድ “ የተለዬ “ ነበር (ቁጥር 14) ፡፡

ዕብራዉያን (7፡ 15-19)፡ የዕብራዉያን ፀኃፊ በክህነት ይህ የመቀየር መልክ ሌላ ካህን ከመልከ ጼዴቅ በተመሳሳይ ቢከሰት ግልፅ እንደሚሆን ፅፏል ፤ ጸኃፊው እያለ ያለዉ በመልክ ስለ መጣበት ሁኔታ በዘር ግንዱ ሳይሆን “ በማይጠፋ ህይወት ኃይሉ “ የአንድ ካህን ስራን በማሰብ ካህን ማለት ነው (ቁጥር 16) ፡፡ ማክአርቱር “ የማይጠፋ ህይወት “ ማለት “ ማብቂያ የሌለዉ ህይወት “ በማለት ተርጉሞታል ፡፡ኢየሱስ ክህነትን በህግ ሳይሆን በአምላክነቱም እንዳገኘዉ አብራርቷል ፤ ከእግዚአብሄር ቀጥሎ እንደ ሁለተኛ የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት መጨረሻ ስለሌለዉ የተሸለ ነው ፡፡

ቁጥር 17 መዝ (110፡ 4) ይጠቅሳል ፤ “ የምታደክመዉ/የማትጠቅመዉ “ “ የቀድሞዋ ትዕዛዝ “ የብሉይ ኪዳን ሕግ ነበር (ቁጥር 18) ፡፡ ማክአርቱር “ ሊያድን ስላልቻለ እና በሰዉ ዉስጥ ዉስጣዉ ለዉጥን ስለማያመጣ “ ሕጉ “ ደካማ “ እና “ የማይጠቅም “ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ አሁን በክርስቶስ በኩል “ ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ እንድንሳብ “ የሚፈቅድ “ የተሸለ ተስፋ “ አለን (ቁጥር 19) ፡፡ ማክአርቱር ይህ ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ የመሳብ ሀሳብ “ ከሌዋዊያን ስርዓት ጋር ሲወዳደር የክርስትና ሁኔታ/ስርዓትን እንደሆነ “ አጉልቶ ያሳያል ፡፡

በብሉይ ኪዳን ካህናቱ በጌታ ፊት ከመምጣታቸዉ በፊት በዝግጅት ዉስጥ ራሳቸዉን ያነፁ ነበር፡ “ ወደ እግዚአብሄርም የሚቀርቡት ካህናት ደግሞ እግዚአብሄር እንዳያጠፋቸው ራሳቸዉን ይቀድሱ አለው “ (ዘጸ 19፡ 22)፡፡ ቢየሱስ ሞት “ እነሆም ወዲያዉኑ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ ምድርም ተናወጠች ዓለቶችም ተሰነጠቁ “ (ማቴ 27፡ 51) ፡፡ መጋረጃው ሰዎችን ከእግዚአብሄር መገኘት ለይቷል ፤ በሕጉ ካህናቱ ብቻ በአካል ወደ እግዚአብሄር መገኘት የነበራቸዉ ሰዎች ብቻ ነበሩ ይህም ደግሞ ለአንድ ለተወሰነ ቀን ለስርየት ቀን ጊዜ ብቻም ነበር ፡፡ አሁን ከኢየሱስ ስራ የተነሳ በማንኛዉም ጊዜ አማኞች ወደ እግዚአብሄር መገኘት መምጣት ይችላሉ ፤ የኢየሱስ ክህነት የተሻለ ነው ፡፡

ዕብራዉያን (7፡ 20-22)፡ ከሌዋዊያን ክህነት አንፃር የኢየሱስ ክህነት ከእግዚአብሄር በመኃላ የመጣ ነው ፡፡ እንደ ገና የዕብራዉያን ፀኃፊ ኢየሱስን ለዘላለም የሚቀጥል ካህን ለማድረግ የእግዚአብሄርን መኃላ አጉልቶ ለማሳየት መዝሙር 110 ጠቅሷል ፡፡ ከዚህም የተነሳ “ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆናአል “ (ቁጥር 22) ፤ በመልከ ጼዴቅ መስመር እንደ ካህን ኢየሱስ የአዲሱ ኪዳን መካከለኛ ሆኗል ፡፡ ማክአርቱር “ ኢየሱስ ራሱ የመዳን የአዲሱ ኪዳኑ ስኬት ዋስ እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡

ኢየሱስ የአዲሱ ኪዳን ዋስትና እንደሆነ መፅኀፍ ለሌሎች ዋስትና የሆኑ የሌሎች ሰዎች ምሳሌን ይይዛል ፤ ጳዉሎስ ፊልሞናን መልሶ ወደ ቤቱ ሲልከው ለፊልሞን ዋስ ሆኗል (ፊል 18-19) ፡፡ ይሁዳ ዮሴፍ ወንድሞቹ ምግብ ለመቀበል ሲመጡ ቢንያምን እንዲያመጡ በፈለገ ጊዜ ስለ ቢንያም ህይወት ዋስ ሆኗል (ዘፍ 43፡ 8-9) ፡፡ ኢየሱስም በእኛ ስፍራ ራሱን በማስቀመጥ የመጨረሻው ዋስ ነበር ፡፡

ዕብራዉያን (7፡ 23-28)፡ እያንዳንዳቸዉ ካህናት ስለሞቱ ብዙ ሌዋዊያን ካህናት ነበሩ፣ ኢየሱስ የክህነት አገልግሎቱን ለዘላለም ይዟል (ቁጥር 23-24) ፡፡ “ ስለዚህም ወደ እርሱ የሚመጣዉን ማንኛዉንም ሰው ማዳን የሚችል ነው “ (ቁጥር 25) ፤ ኢየሱስ ለሁሉም መስዋዕት የመጨረሻዉ ስለ ነበር በተደጋጋሚ መስዋዕት ማቅረብ አያስፈልገዉም (ቁጥር 27) ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር ኢየሱስ ሊቀ ካህን እንደ ሆነ አረጋግጧል ፡፡ የተሻለ ኪዳን የሚያመጣ ከሁሉ የሚበልጥ ካህን ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2007), p. 299.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 1853.

  3. MacArthur, p. 1853–1854.

  4. MacArthur, p. 1854.

  5. MacArthur, p. 1854.

  6. MacArthur, p. 1854.

ጥያቄዎች

  1. መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ ከመገለጡ በፊት እንዳለዉ መልክ አይነት ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ? በመፅኃፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ መልከ ጼዴቅ ተጠቅሷል ለምን ? (ዘፍ 14፡ 17-20, መዝ 110፡ 4, ዕብ 5፡ 6, 10)
  2. በዕብ (7፡ 18-19) መሰረት አዲስ ክህነት ያስፈለገዉ ለምን ነበር ? አዲሱ ኪዳን ከአሮጌዉ ኪዳን እንዴት እንደሚሻል ግለፁ ? በግል አስተያየታችሁ ሕጉን መከተል ወይስ በፀጋ መዳን ነዉ የሚከብደው ? ለምን ?
  3. በግል አስተያየታችሁ መሲሁን ለመላክ ለእግዚአብሄር ለምን ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ምን ታስባላችሁ ? ዛሬም እንደ ገና ተመልሶ መምጣቱን ለምን እንጠብቃለን ?
  4. በዕብራዉያን 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hebrews 7:22–25

“So Jesus has also become the guarantee of a better covenant. Now many have become Levitical priests, since they are prevented by death from remaining in office. But because He remains forever, He holds His priesthood permanently. Therefore, He is always able to save those who come to God through Him, since He always lives to intercede for them.”

ኢየሱስ የተሻለ ኪዳን ዋስ ነው ፡፡ የተሻለ ተስፋ ፡፡ የተሻለ ክህነት ፡፡ ከህጉም የላቀ ፡፡ እርሱ ህግን ሊሽር አልመጣም ፣ ይልቁንም ሊፈጽም እንጂ ፡፡ ኢየሱስ ለዓለም ኋጢአት ዘላለማዊ መስዋዕት ሆኖ ነው የመጣው ፡፡ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ለሁለት ሲሰነጠቅ ፣ አማኞች ወደ ዘላለማዊ ካህናቸው ወደ ኢየሱስ መግባት ሆነላቸው ፡፡ ኢየሱስ ሁልጊዜም እርሱን አዳኛቸው አድርገው ያሚያምኑትን ያድናቸዋል ኢየሱስ ስለ እናንተ ሁልጊዜ ይማልዳል ፡፡ ሁልጊዜ ፡፡ ለዘላለም አስተማማኝ ነው ፡፡ አዎን በርግጥም ኢየሱስ የተሸለው ሊቀ ካህናት ነው እርሱም ስለ እናንተ ኃጢአት መስዋዕት በመሆን ሞቷል ፡፡

ዛሬ ይህ እንዴት ነው ከእናንተ ህይወት ጋር የሚገናኘው ? እናንተ ቅዱስ የሆነው ሊቀ ካህናት ፣ ንጹህ የሆነው ፣ የማይሻረው ፣ ከኃጢአት የተለየው ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ ያለውን ኢየሱስን የማግኘት ሙሉ የሆነ መብት አላችሁ ፡፡ እናንተ ከኃጢአት ነጻ መውጣት እንድትችሉ ኢየሱስ ሞተ ፡፡ እርሱ ተስፋችሁ ነው የተሻለው ተስፋችሁ ፡፡ ስለዚህም ዛሬ ቀናችሁ ምንም ነገር ይዞባችሁ ይምጣ ፣ በተስፋ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ፡፡

“እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ። “

  • ዕብራውያን 7፡22-25

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 5:17 — “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም ። “

ዕብራውያን 7:18–19 — “ ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና ፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች ፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል ። “

ያዕቆብ 4:8 — “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል ። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ ። “