Inheriting The Promise
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዕብራዉያን 6 የጠፋ/የሚፈለግ መልዕክት አለው ፡፡ በዕብራዉያን 5 ፀኃፊው የመንፈሳዊነት አለማደግ ምልክቶችን ለይቷል ፡፡ የዕብራዉያን መፅኀፍ የተፃፈበት ጊዜ ምናልባት ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ ከክርስቶስ ሞት 70 አመት በኋላ ከመፍረሱ በፊት ነበር ፡፡ የዕብራዉያን የተለዩት አንባቢዎች/ተደራሾች ለቃሉ ሰነፎች እና ስልቹዎች ነበሩ ፤ ሕዝቡ ቃሉን ለማጥናት ፍላጎት አልነበረው ፡፡
ፀኃፊው እነዚህ አማኞች የእግዚአብሄርን ቃል ማስተማር እንደሚገባቸው ነገር ግን ያንን ለማድረግ በሚገባ በመንፈሳዊነት እንዳልጠነከሩ አስተያየት ሰጥቷል ፡፡ እንዴት የሰለጠኑ እንደሚሆኑ ወይም በክፉዉ እና በመልካሙ መካከል ያለዉን ልዩነት እንዴት የለዩ እንደሚሆኑ ሀሳቡ/እዉቀቱ አልነበራቸውም ፤ ያልጠነከሩ/የማያስተዉሉ አማኞች ነበሩ ፡፡ ስለ መሲሁ የጠለቀ መረዳት አልነበራቸውም ፤ መሰረታዊ ከሆነዉ ቀላል ስለሆነዉ ሞት፣ ቀብር እና የክርስቶስ ትንሳኤ መረዳት በላይ መቀጠለ/መሄድ አስፈለጋቸው ፡፡ ወደ መንፈሳዊ ጥንካሬ /እድገት ላይ መግፋትን ይጠብቁ ነበር ፤ መንፈሳዊ ለዉጥ እንዲኖራቸው የዕብራዉያን ፀኃፊ ካሉበት መቀጠል የሚያስፈልጋቸዉን ስድስት ነገሮች ዘርዝሯል ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (6፡ 1-20)፡ እግዚአብሄር “ በእድገት/ብስለት እንድንሄድ ! “ ጠርቶናል (ቁጥር 1) ፡፡ ፀኃፊዉ አማኞች ወደ ፊት መቀጠል /መጓዝ እንደሚያስፈልጋቸዉ እየመከረ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 6 ለመንፈሳዊ ብስለት እና ለመንፈሳዊ ህይወት እንደ ግብዣ በመጥራት ይለየዋል፡
ሐዋ (20፡ 21) ወደ እግዚአብሄር በንስኃ ስለመመለስ እና በክርስቶስ ስለማመን ይናገራል፣ እነዚህ ሁለት ነገሮች ለአንድ ሰዉ እምነት ወሳኝ ናቸው ፡፡ በዕብራዉይና ቁጥር (1-6) ፀኃፊው አማኞች ሊከተሏቸዉ የሚገቧቸዉን ስድስት የመጀመሪያ የክርስቶስ መርሆችን ዘርዝሯል፡
- “ ከሞተ ስራ ንስኃ መግባት “ (ቁጥር 1) ፡፡
- “ በእግዚአብሄር ማመን “ (ቁጥር 1) ፡፡
- “ ስለ ኃይማኖታዊ ጥምቀቶች/መታጠቦች ትምህርቶችን “ (ቁጥር 2) ፡፡
- “ እጅን ስለ መጫን “ ያለ ትምህርትን (ቁጥር 2) ፡፡
- “ ስለ ሙታን ትንሳኤ “ ያለን ትምህርት (ቁጥር 2) ፡፡
- “ ስለ ዘላለም ፍርድ “ የሆነን ትምህርት (ቁጥር 2) ፡፡
የእምነት እና ንስኃ የመግባት መርሆች ለአማኞች የተሰጡና አላማቸዉ ከእነዚህም በላይ የሚሄዱ ናቸው ፡፡ ከዚያም ሁለተኛዉ ነገር የብሉይ ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን ማስተሳሰሪያ የነበረዉ የኃይማኖታዊ መታጠብ ወይም ጥምቀት ይሆናል ፡፡ ሉቃስ (24፡ 50) እንደ በረከት ከእግዚአብሄር ጋር ስላለን ግንኙነት እና ከሌሎች ጋር ስላለን ግንኙነት ይናገራል ፡፡ ጥምቀት እና እጅ መጫን “ የአንድ ሰዉ ግንኙነት በአካባቢዉ ካለዉ ጉባኤ አማኞች ጋር ይደረጋል “ ፡፡ ሐዋ (19፡ 6) ጳዉሎስ እጁን በአማኞች ላይ ሲጭን መንፈስ በእነርሱ ላይ እንደ መጣ የመዘገበ ነው ፡፡
የሙታን ትንሳኤ እና የመጨረሻዉ የዘላለማዊዉ ፍርድ “ በሚመጣዉ ዘመን የሚሆኑ ናቸው “ ፤ እነዚህ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ነገሮች ከሚመጣዉ ዘመን ጋር የሚገናኙ ናቸው ፡፡ ሐዋ (24፡ 14-15) የሙታን ትንሳኤን ይጠቅሳል /ያመለክታል ፤ ሐዋ (17፡ 30-31) የመጨረሻዉን ፍርድ ይጠቅሳል ፡፡ ፍርድ እንደ ሊቀ ካህ በተሦመዉ በክርስቶስ በአለም ላይ ይመጣል ፡፡
ዋይርስቤ መንፈሳዊ እድገትን ከልጅነት ጋር ያወዳድራል፡ “ ሀለመ እያላችሁ በመቁጠር ስለተማራችሁ ቃላትም፣ ዓ.ነገርን እና መፅኃፍትን ታነባላችሁ - በእርግጥም በፅኁፍ ማንኛዉንም ታነባላችሁ ፤ ነገር ግን መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን እየተማራችሁ አትቀጥሉም ፤ ወደ ተሻለ ነገር ለመሄድ መሰረታዊዉን ነገር ትጠቀማላችሁ “ ፡፡ ከመሰረታዊ መንፈሳዊ ነገሮች በኋላ ወደ ፊት በመሄጃ/በመቀጠያ ጊዜ የተማሩ ናቸው ፤ አድማጮቹ ወደቀድሞዉ የመጀመሪያ ነገር መሄድ ከቻሉ የመበሰል ሌሎች ነገሮችን/ጉዳዮችን እና ንስኃ መግባት ለመድረስ ዝግጁ ናቸዉ ማለት ነው ፡፡
በቁጥር 4 ፀኃፊው አንዴ በእዉነቱ ተምረዉ የነበሩትን እና አንዴ ድነዉ የነበሩትን ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሄር ዞር ያሉትን አማኞች ደረሳቸዉ/ተናገራቸው ፡፡ ማጣቀሻው አንዴ የዳኑት አሁን ደግሞ ተመልሰዉ የነበሩት ከንስኃ በላይ እንደ ነበሩ ያመለክታል ፡፡ ቁጥር 4 ተመርምሮ ከነበር ዞር ብሎ የነበረ ግለሰብ ወደ ክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የሚያስችል መንገድ እንዳማይኖር የሚል ይመስላል ፡፡ ቁጥር 5 ድነትን ቀምሰዉ ስለ ነበሩት ከዚያም በንቀትም እንደ ክርስቶስ ነቃፊነት ስለሆኑት ያወራል ፡፡
ዕብራዉያን (6፡ 1-3) ለአንባቢዎች ምንም ችግር አይፈጥርም ምክንያቱም እነዚህ ጥቅሶች አማኞች በእምነታቸው በብስለት እንደሚያድጉ እንደሚጠበቅ ስለሚናገር ፡፡ ዕብ (6፡ 4-6) እነዚህ መፅኀፍት አምነዉ እንደ ገና ላፈገፈጉት ንስኃ የለም ወደ ሚለዉ ኃሳብ ሲያመክቱ የተለያዩ እይታዎችን ይጠይቃል ፡፡
በመሰረታዊነት በዘላለማዊ ደህንነት ላይ ሁለት አመለካከቶች አሉ፡ 1) ሮሜ (8፡ 35-39) ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ሊለየን እንደማይችል ይናገራል፣ 2) ዕብ (6፡ 4) “ አንዴ የዳነ ሰዉ በክርስቶስ ላይ ጀርባዉን ቢያዞር ወደ ድነት ተመልሶ ሊመጣ እንደማይችል ይናገራል “ ፤ አስቸጋሪዉ ነገር በድነታችን እንዴት እንሰራለን/እንመላለሳለን ነው ፡፡ ዮሐ (6፡ 39) ማንም እንደማይጠፋ ይናገራል ፤ ዮሐ (10፡ 27-29) ማንም ከእግዚአብሄር እጅ አማኝን ማንም መንጠቅ እንደማይችላ ይናገራል የዘላለም ደህንነትንም ያመለክታል ፡፡ ሮሜ (8፡ 28-30) ስለ ዘላለማዉ ደህንነት ሂደት ይናገራል ፤ አንድ ግለሰብ ከዳነ በዚህ ዉስጥ እንዲሰራ /እንዲመላለስ ይጠብቃሉ ፡፡
ድነት ወደ መስተካከል ሲመራ መስተካከል ደግሞ ወደ ፅድቅ ይመራል ፤ ፅድቅ ደግሞ ወደ ክብር ይመራል ፡፡ የዕብራዉያን የመጀመሪያዉ ማስጠንቀቂያው የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያከብሩ ነበር ያ ከሆነ አማኝ ወደሌላ ስለማይሳብ ፡፡ ድነታችን በስራችን ላይ የተመሰረተ አይደለም ነገር ግን ወደ እግዚአብሄር የቀረብን ለመሆን ባለን ፍላጎት እና ወደ እግዚአብሄር በመቅረብ ስናድግ በቃሉ መቆየታችን/መቀመጣችን ላይ እንጂ ፡፡
ቁጥር (7-8) ወንጌልን በመስማት በእምነት ምላሽ የሰጡት የተባረኩ እንደ ሆኑና ወንጌልን በመስማት ያልተቀበሉት የተረገሙ እንደ ሆኑ ይናገራል ፡፡ ወንጌልን በእምነት የሚቀበሉት የተባረኩ ሲሆኑ በመጨረሻም የጌታ ያልሆኑት የህይወት ነገሮች ይጠፋሉ ፡፡ የዕብራዉያን ፀኃፊ ሰዎቹ እንዲያምኑ የሚያስፈራ አይነት ነገር ለመፍጠር እየሞከረ ነበር ፤ በቁጥር 9 ፀኃፊው ሊሆን ስለሚችለዉ ነገር አማኞችን አስጠነቀቃቸው ፡፡ ይሁን እንጂ እምነት ላላቸው እግዚአብሄር መልካም ስራቸዉን አይረሳም ፡፡
በቁጥር 11 እና በሚቀጥሉት ፀኃፊው የእግዚአብሄርን ተስፋ በማግኘት አብርኃምን ጠቅሶታል ፤ እግዚአብሄር ተስፋዉን ለአብርኃም በመኃላ ሰጠው ፡፡ ቁጥር 19-20 እንደ ሊቀ ካህናችን በክርስቶስ ሁሉንም የተስፋ መልዕክት ያቀርባል ፡፡
መደምደሚያ
የዕብራዉያን ማበራሪያ አይናችንን በክርስቶስ ላይ እንድናደርግ ነው ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ሊቀ ካህናችን በክርስቶስ መልህቅ እንዳለን አረጋግጦልናል ፡፡ እሱ ተስፋችን፣ ኪዳናችን እና ህይወታችን ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary, Vol. II, (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 295.
Wiersbe, p. 295.
Wiersbe, p. 295.
Wiersbe, p. 296.
Wiersbe, p. 295.
Wiersbe, p. 296.
ጥያቄዎች
-
ዕብ (6፡ 4-6) ስታነቡ በክርስቶስ ላይ ራሳቸዉን እንዳዞሩ ሰዎች ወደ አይምሯችሁ ዉስጥ ማን ይመጣል ? በግል አስተያየቶቻችሁ ለእነርሱ ተስፋ አላቸው ? አዎ ከሆነ እንዴት አይደለም ከሆነ ደግሞ ለምን ?
-
በመፅኃፍ ላይ የዕብ (6፡ 7-8) ምሳሌ ሌላ የትላ ሊገኝ ይችላል (ማቴ 13፡ 1-8) ? ተመሳሳይ ነገር እየገለፁ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በዕብ (6፡ 15) ጳዉሎስ “ በትዕግስት ታገሰ “ የሚለዉን ቃል ተጠቅሞታል ፤ እንደ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ተስፋዉ እስኪፈፀም ድረስ በትዕግስት ትጠብቃለች/ትታገሳለች?በራሳችሁ ህይወት ለተስፋችሁ በትዕግስት ትጠብቃላችሁ ?
-
በዕብራዉያን 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 6:19
“We have this hope as an anchor for our lives, safe and secure. It enters the inner sanctuary behind the curtain.”
ኢየሱስ ለህይወታችሁ መልህቅ ሆኖ ዘላለማዊ ተስፋን አቅርቦላችኋል ፡፡ የእርሱ ተስፋ አስተማማኝና የጸና ነው ፡፡ በዙሪያችሁ ምንም ነገር ይፈጠር ፡- ወጀብ ፣ ልፋት ወይም በሽታ ፣ ነገር ግን አንድ እውነት አለ ፡- በኢየሱስ ስታምኑ ትድናላችሁ የዘላለም ህይወትም ይኖራችኋል ፡፡ ስለዚህም ምንም ነገር ማየት በማትችሉበት ጊዜም ጭምር በተስፋ እረፉ ፡፡ በጨለማ ውስጥ ተስፋ ማድረግ ትችላላችሁ ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ ወጀቡ እያለ ተስፋ ማድረግ ትችላላችሁ ፡፡ በምስቅልቅሉ በአመጹ ውስጥ ተስፋ ማድረግ ትችላላችሁ ፡፡
ጌታ እንደሚያበረታችሁ ይናገራል ፡፡ ጌታ ጥበቃን እንደሚያደርግላችሁ ይናገራል ፡፡ ጌታ መገኘቱን ከእናንተ ጋር እንደሚያደርግ ይናገራል ፡፡ ጌታ ስለታማኝነት ይናገራል ፡፡ ስለዚህም በእርሱ ላይ መጣበቅ መሟጨጭ ትችላላችሁ ፡፡ ኢየሱስን መልህቃችሁ በማድረግ ተስፋ ስታደርጉ ፣ ፈጽማችሁ አትናወጡም ፡፡ በእርሱ ላይ ተጣበቁ ፡፡ ጠላት ያስታችኋል ወይም በዚህ መንገድ ወይም በዚያ መንገድ ሂዱ እያለ ይፈትናችኋል ሆኖም ግን ጽኑ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብርቱ ነውና ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እርሱ መልህቃችሁ እንደሆነ ንገሩት ፡፡ እስኪ በአዕምሯችሁ እንዲህ አስቡ ወገባችሁን ተስፋ ታጥቃችሁ እናም ያ ተስፋ ከኢየሱስ እንዳትሄዱ አድርጎ አስሮ ሲይዛችሁ ፡፡ በክርስቶስ ደህንነታችሁ የተጠበቀ ይሆናል ደግሞም ትጸናላችሁ ፡፡ ዛሬ ማድረግ ትችላላችሁ ፡፡ ነገን መጋፈጥ ትችላላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር ኃይላችሁና መሸሸጊያችሁ ነው ተስፋችሁም በእርሱ ዘንድ የተጠበቀ ነው ፡፡ አትናወጡም ፡፡
“ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው ፡፡ “
- ዕብራውያን 6፡19
ተጨማሪ ጥቅስ
ፊልጵስዩስ 3:12 — “ አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም ፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ ። “
2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 — “ ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው ። “
1ኛ ዮሐንስ 5:13 — “ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።