A High Priest
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመስቀላ ላይ በኢየሱስ ሞት፣ የተቀበረ በመሆኑና ወደ ህይወት ተመልሶ በመምጣቱ ወደ አባቱ የመጋባት እድል ተሰጥቶናል ፡፡ ከክርስቶስ አስደናቂ መስዋዕትነት የተነሳ የመግባት እድል ተሰጥቶናል ፡፡ ምዕራፍ 5 እንደ ሊቀ ካህን ስለ ክርስቶስ ስራ/ተግባር ያወራል ፤ ኢየሱስ ከመለዓክት ይበልጥ ነበር፣ የኢየሱስ መልዕክት ከመለዓክት መልዕክት ይበልጥ ነበር እንዲሁም ኢየሱስ ከሙሴ ወይም ከአሮን ይበልጥ ነበር ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (5፡ 1-14)፡ የታላቁ ካህን ስራ በስርየት ቀን ለኃጢዓት ይቅርታ ስጦታንና መስዋዕትን ማቅረብ ነበር ፡፡ እንደ ዮሐንስ ማክአርቱር አገላለፅ “ የመጀመሪያዉ ዙር (ስጦታ) በብሉይ ኪዳን ስር ለምስጋና ወይም ለመቀደስ ይሰጥ የነበረውን በተለይም የእህል ቁርባን/መስዋዕትን ያመለክታል ፤ ያም ለኃጢዓት ስርየት የሚሰዋዉን ደም ለማመልከት ለሁለተኛዉ ዙር (መስዋዕት) ይለቅቃል (ዘሌ 1-5) “ ፡፡ ሊቀ ካህኑ ስለ ሁሉም ሰዎች ሲል ወደ ጌታ መጥቷል ፤ ለእግዚአብሄር በአገልግሎቱ ተሾሞአል ነገር ግን የተመረጠዉ ከሰዉ ነበር ፡፡
ቁጥር 2 ታላቁ ካህን ድክመት ቢኖርበትም እንኳን በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ለነበሩት/ኃጢዓት እያደረጉ ለነበሩት በእርጋታ ማስተሰረይ ይችል ነበር ፤ ይህ በብሉይ ኪዳን እንደ ተገለፀዉ የታላቁ ካህን ተግባር ነበር ፡፡ ቁጥር 3 ታላቁ ካህን ለራሱና ለሰዎቹ የኃጢዓት መስዋዕት ማቅረብ ይጠበቅበት ነበር ምክንያቱም ሰዉ ስለ ነበርና ኃጢዓትን ስለሰራ በማለት ይናገራል (ቁጥር 3-4) ፡፡
እነዚህ ጥቅሶች/ቁጥሮች ቁጥር 5 ያመቻቻሉ/ግልፅ ያደርጋሉ ፡፡ ማክአርቱር ዕብራዉያን 5 “ በህዝቡ ላይ እና ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እንዳተኮረ (ዕብ 5፡ 1)፣ ለደካሞች እና ላልተማሩት እንደሚራራ (ዕብ 5፡ 2)፣ ስለ ኃጢዓት መስዋዕት ማቅረብ እንደሚገባው (ዕብ 5፡ 3) እና በእግዚአብሄር በዚህ ተግባሩ ከተጠራ ይልቅ ማንም ራሱን እንደማይሾም (ዕብ 5፡ 4) እንደ አንድ ካህን እዉነተኛም መሪ እንደሚገልፅ “ ይገልፃል ፡፡ ስለዚህም አሁን እንደ ሊቀ ካህን በክርስቶስ ላይ እነዚህን መርሆች በመዉሰድ መተግበር አስፈላጊ ነበር ፡፡ በጥሪ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ሚና/ተግባር ከእግዚአብሄር ጋር ትስስር መኖር ነበር ከዚህም ተግባር ጋር የተጠሩት ግለሰቦች ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚያገናኙ ይጠበቁም ነበሩ ፤ ተግባሩም ቸርነትን ለማሳየት ነበር ነገር ግን ከኃጢዓት ይጠራል/ያስወጣል ፡፡ እነዚህን ተግባራት የመፈፀም ምክንያት እግዚአብሄር በግለሰብ ህይወት ላይ ይህን ጥሪ አድርጎ ስለ ነበር ነበር ፡፡
ቁጥር 5 ለብሉይ ኪዳን ፅሁፎች ማጠቀሻን ይይዛል ፡፡ ማክአርቱር “ በመዝ (2፡ 7) እና (110፡ 4) ፀኃፊው የክርስቶስን ልጅነት እና የክህነት አገልግሎት ሁለቱም በመለኮት ሹመት የተሰጠ እንደ ነበር እንደሚያሳይ “ ይናገራል ፡፡
በቁጥር 6 ክርስቶስ “ በአብርኃም ዘመን የሰላም ንጉስ እና የልዑል እግዚአብሄር ካህን እና በተጨማሪም አንድ የንጉስ ካህን እንደ ነበረው (ዘፍ 14፡ 18-20) “ በመልከ ጼዴቅ እንደ ሊቀ ካህናት የተለዬ ነበር ፡፡ የዕብራዉያን ፀኃፊ ማብራሪያ በመልከ ጼዴቅ ተርታ ከክርስቶስ ላይ እንደ ንጉስ ከመልከ ጼዴቅ ተርታ እንደ ሊቀ ካህን በክርስቶስ ላይ ነበር ፡፡ አድማጮቹ በሕጉ እየታገሉ ነበር ፡፡ ዕብራዉያን 5 ኢየሱስ ከሰዉ ጳጳሳት/ካህናት የበለጠ ስለመሆኑ ነበር ፤ ኢየሱስ ሰዎችን ነፃ ለማዉጣት መጥቶ ነበር ፡፡
ቁጥር (1-4) ከሰዉ ካህናት ጋር ስለ ኢየሱስ ንፅፅሮች ናቸው ፤ ቁጥር 5 እና የሚከተሉት እንደ ሊቀ ካህን ስለ ክርስቶስ ተግባር ናቸው ፡፡
ማክአርቱር በቁጥር 7 “ የሚቀጥለዉ አዉድ ይህ በቁጥር አምስት ዋና ባለቤት በነበረዉ ክርስቶስ ላይ ተመልሶ በመጥቀስ ግልፅ ያደርገዋል ፤ በጌቴሴማኔ ኢየሱስ በማዘን አለቀሰ ነገር ግን ሞት የሚያመጣበትን የመከራ ፅዋን ተስፋ በማድረግ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ ራሱን አስገዛ (ማቴ 26፡ 38-46, ሉቃ 22፡ 44, 45) “ በማለት ያመለክታል ፡፡ ኢየሱስ ምን እየመጣ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ማክአርቱር፡
“ የኃጢዓትን የፍርድ ሸክም እንደሚሸከም ተስፋ በማድረግ ኢየሱስ በሙሉ ስቃይ እና ኃዘን ወደቀ (ኢሳ 52፡ 14, 53፡ 3-5, 10) ፤ ስለሆነም በዝምታ ቅጣቱን ተሸከመ ከዚያ ዉስጥም ራሱን ለማዉጣት አልፈለገም (ኢሳ 53፡ 7)፣ ፍፁም ቅዱስ እና ታዛዥ በሆነዉ ሰዉ በእርሱ ላይ በፈሰሰዉ በእግዚአብሄር ቁጣ ኃይል ከስቃይ ጮኸ/አለቀሰ (ማቴ 27፡ 46, 2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ኢየሱስ በሞት ሳይቀር የዳነ እንዲሆን ጠየቀ ማለትም እንዲነሳ ጠየቀ (መዝ 16፡ 9, 10) “ ይናገራል ፡፡ መዝሙር 16 የመሲሁ ትንሳኤ እንዲሚሆን የተናገረ ትንቢታዊ እና መሲሀዊ መዝሙር ነበር ፡፡
ቁጥር 8 ስለ መታዘዝ ነበር ፤ ማክአርቱር “ ክርስቶስ ማናኛዉን አለመታዘዝ ለመያዝ እና ለማስተካከል መከራን መቀበል አላስፈለገውም ፤ በአምላክነቱ (እንደ እግዚአብሄር ልጅ) ሙሉ ለሙሉ መታዘዝን ተረድቷል ፤ እንደ ተመሰከረለት ጌታ ለመማርም ራሱን ዝቅ አደረገ (ሉቃ 2፡ 52) ፡፡ ፈተናን ለመሸከም በተመሳሳይ ምክንያት መታዘዝን ተመራ፡ ትህትናዉን እና በሙሉነት መከራዉን መቅመሱን ያረጋግጣል (በ2፡ 10፣ ሉቃ 2፡ 52, ፊል 2፡ 8 ላይ የተፃፈውን እዩ ) “ በማለት ይናገራል ፡፡ ክርስቶስ ይህን ሁሉ በግዜ ዉስጥ ተማረ በዚህም አደገ ፤ ክርስቶስ በዚህ ልምምድ ዉስጥ እንዲመላለስ የተሾመ እንደሆነ ያውቃል ፡፡
ክርስቶስ በመከራ መታዘዝ የታሰረ ፍፁም ነበር ፤ የእግዚአብሄር እቅድ ወደ ፍሬ የመጣ ነበር ፡፡ ከፍፁሙ ከእግዚአብሄር እቅድ ስለ ኃጢዓታችን መስዋዕቱን ጨምሮ በኋላ ኢየሱስ የድነት ምንጭ ሆነ ፡፡
ዋይርስቤ በቁጥር 11 እና በሚቀጥሉት የመንፈሳዊነት አለመብሰልን አመልካችቾ እንዳሉ ያመለክታል “ ፀኃፊው ስለ ሰማያዊዉ የክህነት አገልጋይ በክርስቶስ ገለፃ የጀመረ ነበር ነገር ግን አንባቢዎቹ ለሚያስተምረዉ ነገር ዝግጁ እንደ ነበሩ እርግጠኛ አልነበረም “ ያመለክታል ፡፡ የመንፈሳዊነት አለማደግ ምልክቶች ዝርዝር የሚያካትቷቸው፡ ስለ ቃሉ ስልቹ መሆን፣ ለመናገር/ለማጋራት ብቁ አለመሆን፣ “ የህፃን ልጅ ምግብ “ መመገብ እና ቃሉን በመጠቀም ብቁ አለመሆን “ ፤ የዕብራዉያን ፀኃፊ ተስፋ አማኞች እምነታቸዉን እና ቃሉን ለማጋራት ሊችሉ እንደሚገባቸዉ ነበር ፡፡ እነዚህ ምልክቶች አማኞች ከጌታ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት የት ስፍራ እንዳሉ ያሳያሉ ፡፡
መደምደሚያ
አኗኗራችን፣ ቃላችን እና ድርጊታችን ጠንካራ ምግብ እንደምንመገብ ማሳየት አለበት ፤ ይህ በጌታ እንድናድግ እና እንድንጠነክር ያስፈልገዋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1846.
Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1643.
MacArthur, p. 1847.
MacArthur, p. 1847.
MacArthur, p. 1847.
MacArthur, p. 1847.
MacArthur, p. 1847.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament, vol. 11 (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 294.
Wiersbe, p. 294
ጥያቄዎች
-
ከዕብ (5፡ 2) ጋር ትስማማላችሁ ? ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ላላቸዉ ሰዎች ትልቅ ቸርነት /ርህራሄ ኖሯችሁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታገኙትም ?
-
በዕብ (5፡ 10) የተጠቀሰዉ መልከ ጼዴቅ ማን ነበር (ዘፍ 14፡ 18-20, ዕብራዉያን 7) ? ለምን ተጠቅሶ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
ዕብ (5፡ 11-14) በምታነቡ ጊዜ እነዚህ ጥቅሶች ሊገልፁአቸዉ የሚችሉአቸዉ ሰዎችን ታውቃላችሁ ? በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት መንፈሳዊ እንደሆናችሁ የት ይሰማችኋል ? እንዴት ልታድጉ ትችላላችሁ ? ሌላ ሰዉስ እንዲያድግ እንዴት ልትረዱት ትችላላችሁ ?
-
በዕብራዉያን 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 5:7–8
“During His earthly life, He offered prayers and appeals with loud cries and tears to the One who was able to save Him from death, and He was heard because of His reverence. Though He was God’s Son, He learned obedience through what He suffered.”
ጌታ ስለ እናንተ የሆነ ሊቃ ካህናት ነው ፡፡ ኢየሱስ ስጋን ለብሶ በሰዎች መካከል ሲኖር ጸለየ ወደ እግዚአብሔርም በፍርሀት ጮኸ ፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር አብ ከሞት ሊያድነው እንደሚችል ያምን ስለነበር እግዚአብሔርን ፍቃዱ ቢሆን እንድያድነው ለመነ ፡፡ ሆኖም ግን አግዚአብሔር ኢየሱስ መከራ እንድቀበልና እንድሞት ፈቀደ ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ እንኳ በመከራው መታዘዝን ተማረ ፡፡
ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናት በመከራው መታዘዝን ተማረ ፡፡ እግዚአብሔር መከራን እንደምትቀበሉ ይናገራል ፣ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ ሁሉ እናንተም በእነዚህ የመከራ ጊዜያት ነው መታዘዝን የምትማሩት ፡፡ መከራ ትዕግስትን ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን ያደርጋል ፡፡ ባህሪው ጡሩ ባለመሆኑ ምክንያት እርሱን ለማስተካከል ሲባል ከሌሎቹ ተለይቶ የተቀመጠ ልጅ እንደተበደለ እንደተጎዳ ይሰማዋል ፡፡ሆኖም ግን በዚህ ክልከላው በሚያስከትለው ህመም ውስጥ ነው ያ ልጅ ለቤተሰቦች መገዛትና በመታዘዝ ማደግን የሚማረው ፡፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ በመከራችሁ ጊዜ ፣ ወደ እግዚአብሔር ስትቀርቡ ከእርሱ መገለጥን ትቀበላላችሁ በህይወታችሁም ውስጥ ያለውን የእርሱን ስራ ታወድሳላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር በፍቅሩ ወደ አዲስ ጥልቀት ይወስዳችኋል እናንተም አብልጣችሁ ለእርሱ መታዘዝን ትማራላችሁ ፡፡ ዛሬ በመከራችሁ ወደ ጌታ ቅረቡ ፡፡ ከእርሱ ጋር አብራችሁ ስትራመዱ ፣ እግዚአብሔር ይመራችኋል ደግሞም በመታዘዝ ያሳድጋችኋል ፡፡
“ እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት ፤ ምንም ልጅ ቢሆን ፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ ፡፡ “
- ዕብራውያን 5፡7-8
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 119:71 — “ ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ ። “
ሮሜ 5:3–4 — “ ይህም ብቻ አይደለም ፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን ፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፡፡ “
1ኛ ዮሐንስ 2:17 — “ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።