General Letters Hebrews

Enter His Rest

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 656 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዕብራዉያን መፅኀፍ ቃላችን ሊቀ ካህን የሚል ነው ፡፡ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ሕግ ሊተካ የተሸለ ኪዳንን አመጣ ፡፡ ለዕብራዉያን መፅኀፍ የሜንዲ ስዕል በመስቀል ላይ የኢየሱስን ስራ በመወከል የመጋረጃዉ መቀደድን ያሳዉቃል ፤ በክርስቶስ ያለንን ነፃነት እና የሊቀ ካህኑን ስፍራ የሚወክሉ 12 ቢራቢሮዎች አሉ ፡፡ በብሉይ ኪዳን በሊቀ ካህኑ የደረት ኪስ እንደ ተደረደሩት ድንጋዮች የተገናኜ ቢራቢሮዎቹ የተደረደሩ ናቸው ፤ ከኢየሱስ ስራ የተነሳ ያለፈዉ የደረት ኪስ የሚያስፈልግ አይደለም ፡፡ ቢራቢሮዎቹ በክርስቶስ የአማኞችን ነፃነት በመወከል ከመጋረጃዉ ዉስጥ በመዉጣት እንደሚበሩ የታወቁ ናቸው ፡፡

ትናትና በዕብራዉያን 3 የእግዚአብሄርን ድምፅ ስላልሰሙ እና ልባቸዉን ስላደነደኑ እስራኤል ወደ እግዚአብሄር ረፍት ለመግባት እንዳልቻሉ ተምረናል ፡፡ ዕብራዉያን 4 እንዴት እዉነተኛን ነፃነት መለማመድ/ማግኘት እንደምንችል ያስቀምጣል ፡፡

ትምህርት

ዕብራዉያን (4፡ 1)፡ ምዕራፍ 4 አሁንም ቀላል ቢሆንም ወደ እግዚአብሄር ረፍት ለመግባት በተግሳፅ ይጀምራል ፡፡ ኮንስታብል ይህ ዕረፍት ምን እንደሚመስል አምስት ዕይታዎችን አስቀምጧል፡

  1. ሰማይ
  2. በክርስቶስ በኃብታችን ዕረፍት ይገኛል
  3. እግዚአብሄር እንድንደሰት በሚፈልገዉ ሁሉ በሚመጣዉ ዘመን መደሰት
  4. በሚመጣዉ ዘመን አንዳንድ መንፈሳዊ በረከቶች ማግኘት
  5. አሁን እንደ ክርስቲያን የሰላም ሕይወት መኖር

በየትኛዉም ጊዜ ቢሆን አማኞች ዕረፍትን ያገኛሉ ዋይርስቤም አሁንም“ የተሻለ ዕረፍት “ እንደሆ አስተካክሎታል ፡፡ ይህ ዕረፍት ከመለዓክቶች የተሻለ፣ ከሙሴ እና ከተስፋይቱ ምድር ዕረፍት እንኳን የተሻለ ነው ፡፡

ዕብራዉያን (4፡ 2-6)፡ ለቀድሞዎቹ ትዉልዶች የነበረዉ ዕረፍት አልጠቀማቸዉም ምክንያቱም የእግዚአብሄርን መልዕክት ስላላመኑ (ቁጥር 2) ፡፡ አሁን በእግዚአብሄር መልዕክት የሚያምኑ ወደ ዕረፍቱ መግባት ይችላሉ (ቁጥር 3)፡፡ ዋይርስቤ በአሁኑ እረፍት እና በቀድሞዉ እረፍት መካከል ዉጥረት/ልዩነት የሚመስለዉን ነገር አስቀምጧል፡ “ የመጀመሪያዉ የድነት እረፍት ነው፣ ሁለተኛው የመታዘዝ እረፍት ነው “ ፡፡

“ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ “ (ማቴ 11፡ 28) ፡፡

“ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜምቀሊል ነው “ (ማቴ 11፡ 29-30) ፡፡

በተጨማሪም ዋይርስቤ በሚገባየድነት ዕረፍትን እና የመታዘዝ ዕረፍትን ሁለቱንም መረዳት ሁለቱም ከእግዚአብሄር እና በእግዚአብሄር በሰላም እንደሚሆ ፅፏል ፡፡

የዕብራዉያን ፀኀፊ አለማትን ከፈጠረ በኋላ “ ስራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈፀም “ (ቁጥር 3) የሚለዉን ጉዳይ ለማድረግ የእግዚአብሄርን ዕረፍት ጠቅሷል (ዘፍ 2፡ 2) ፡፡ ሁሉም የእግዚአብሄር ስራ በመስቀል ላይ የኢየሱስን ሞት ጨምሮ “ ዕለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያበቃ እንደሚሆን “ ተናግሮ ነበር ፡፡ በፍጥረት በሰባተኛዉ ቀን ላይ እግዚአብሄር ለእርሱ የሚፈፅመዉ ምንም ነገር የቀረ ስላልነበር በእንቅስቃሴው ዉስጥ ለሁሉም ታሪክ ቀድሞ እቅድ አስቀምጦ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ወደ እረፍቱ የመግባት ግብዣን ሰዎች እንደማይቀበሉ ያውቃል ይሁን እንጂ ወደ እረፍቱ መግባት ለሰዎቹ አሁንም በጣም የዘገዬ እንዳልነበር እንዲያወቁ መለመኑን ቀጥሏል ፡፡ ማክአርቱር እንደፃፈው “ ወደ እግዚአብሄር እረፍት የመግባት እድል አሁንም ክፍት ነው ፤ አልረፈደም “ ፡፡

ዕብራዉያን (4፡ 7-9)፡ ኢያሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር በገባ ጊዜ የእግዚአብሄርን እረፍት እስከመጨረሻው አላገኘም ፤ ያ ዕረፍት በዚያን ጊዜ ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሄር በሚመጣዉ ዘመን ስለሌላ ቀን ዕረፍት አይናገርም ፡፡ በተስፋይቱ ምድር እስራኤል ያገኘችዉ/የቀመሰችዉ እረፍት ጊዜያዊ እና በኋለኛዉ ቀን በሊቀ ካህኑ በኢየሱስ የሚሰጠዉን የመጨረሻውን እረፍት የሚያመለክት ነበር ፡፡

ዕብራዉያን (4፡ 10-11)፡ ዋይርስቤ የእግዚአብሄርን ረፍት ለማግኘት መጀመሪያ የድነትን ዕረፍት ማግኘት እንዳለብን ይገልፃል ፤ አንዴ ያንን ካደረግን የመታዘዙን እረፍት ለመቅመስ ነፃ እንሆናለን ፡፡ የመታዘዝ ዕረፍቱን ለማግኘት ለእርሱ ለመገዛት ስንተጋ እረፍቱን ከማግኘት የሚያስቀረንን “ እንደዚያ አለመታዘዝ ምሳሌ ላለመዉደቅ እምቢ እንላለን “ (ቁጥር 11) ፡፡ በዘጸዓት ጊዜ እስራኤላዊያን ከሙሴ ጋር ካለመታዘዛቸዉ ስላልተማሩ የእግዚአብሄርን እረፍት አልቀመሱም/አላገኙም ፤ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላም አሁንም ካለመታዘዛቸዉ ያልተማሩ ስለ ነበሩ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን አላገኙም/አልቀመሱም ፡፡ ከላመታዘዙ የተነሳ ዳዊት በሚገባ የእግዚአብሄርን እረፍት አላገኘም ፡፡ የዕብራዉያንም ፀኃፊ “ ወደዚያ እረፍት ለመግባት እንትጋ “ (ቁጥር 11) በማለት የሚያብራራዉ ለዚያ ነው ፡፡

ዕብራዉያን (4፡ 12-13)፡ ለእኛ የተገኝን ዕረፍት እግዚአብሄር ጨርሷል ነገር ግን ወደ እረፍቱ ለመግባት ጥረት/ትጋት ማድረግ አለብን ፡፡ ዮሐ (1፡ 1 እና 14) “ በመጀመሪያዉ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሄር ነበር ፡፡ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነዉን ክብሩን አየን “ በማለት ይናገራል ፡፡ የእግዚአብሄርን እረፍት ማግኘት የምንፈልግ ከሆነ ኢየሱስን ማወቅ በማግኘት አግኝተነዋል ፤ ያንን ለማድረግ በመፅኃፍ/መፅኃፍ እንደሚለው መሆን አለብን ፡፡ በሚገባ በጌታ የምንመላለስ ከሆነ የተደበቀ ምንም ነገር አይኖረንም ፡፡

ዕብራዉያን (4፡ 14-16)፡ ኃጢዓት አልሰራም እንጂ ክርስቶስ የሚገጥመንን ፈተና ሁሉ ያውቀዋል ፤ ወደ እርሱም መቅረብ እንችላለን ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እኛን ወደ ድነት እረፍት እና ወደ መታዘዝ እረፍት የማመልከትን ስራ ስለሚሰራ “ እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ፀጋ መቀበል እንችላለን “ (ቁጥር 16) ፡፡ ይህ በጌታ ያለ የሚያስደንቅ የእረፍት መልክ ነው ፡፡

መደምደሚያ

በኑሮአችን ከክርስቶስ የተነሳ ወደ እግዚአብሄር ዙፋን መቅረብ እንችላለን ፡፡ ወደ እግዚአብሄር/ወደ አባቱ ክርስቶስ ብቸኛዉ መንገድ ነው ፤ ያንን ስናደርግ የእግዚአብሄርን ረፍት እናገኛለን/እንቀምሳለን ፡፡

  1. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Hebrews, p. 76; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/hebrews.pdf.

  2. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament: Hebrews (Colorado Springs: David C Cook, 1989), p. 287.

  3. Wiersbe, p. 287.

  4. Wiersbe, p. 287.

  5. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 1844.

  6. Wiersbe, p. 287.

ጥያቄዎች

  1. በዕብራዉያን 4 ዉስጥ “ የእግዚአብሄር ረፍት “ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰ ነው ፤ ይህ ማለት ምን አይነት ዕረፍት ነው ? (ዘጸ 31፡ 17, መዝ 95፡ 11, ማቴ 11፡ 29)
  2. በዕብ (4፡ 12-13) ሀሳባችሁን አንፀባርቁ ፤ ይህ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል ? በህይወታችሁ እንድትቀየሩ የሚመራችሁ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር የሚመለከተዉ እንዴት አይነት አዉቀት ነው ?
  3. ኢየሱስ ከኃጢዓት በቀር በሁሉም ነገር ተፈትኗል ፤ ይህ ለአባቱ ስላለዉ መታዘዝ ምን ይነግራችኋል ? ኃጢዓት እንዳታደርጉ እንዲረዳችሁ ለእግዚአብሄር ፍቃድ በመታዘዝ እንዴት ልትመላለሱ ትችላላችሁ ?
  4. በዕብራዉያን 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hebrews 4:9–11

“Therefore, a Sabbath rest remains for God’s people. For the person who has entered His rest has rested from his own works, just as God did from His. Let us then make every effort to enter that rest, so that no one will fall into the same pattern of disobedience.”

በጌታ እረፉ ደግሞም በእርሱ ዘንድ ያለውን የተነገራችሁን ድነት ተቀበሉ ፡፡ ዘላለማዊ የሆነውን የሰማዩን ተስፋችሁን ስትቀበሉ ፣ ጌታ በጎ ስራ ለመስራትና በምድር ላይ ስኬታማ ለመሆን የምታደርጉትን ጥረት እንድታቆሙ ይነግራችኋል ፡፡ ራሳችሁን ከእንደዚህ አይነቱ ሀላፊነት ነጻ አውጡ ፡፡ በእርሱ ፣ በእርሱም እውነትና ተስፋ እረፉ ፡፡ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ አወቁ ድልም ከእርሱ ዘንድ እንደሆነ እመኑ ፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ፥ ወደ እኔ ኑ ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ። “ ልክ እርሱን ሙሉ በሙሉ ስትቀበሉ ኢየሱስ በዛሬው ህይወታችሁ እረፍትን ይሰጣችኋል ፡፡ ከቃሉም ጋር ጊዜን ስታሳልፉ ፣ ቃሉ ለመንፈሳችሁና ለነፍሳችሁ ህይወትን ይናገር ዘንድ ፍቀድሉት ፡፡

ከእግዚአብሔር የተደበቀ ምንም ነገር የለም ፡፡ እርሱ ያያችኋል ደግሞም እርሱ ብቻ ልባችሁን ይመዝናል ፡፡ እርሱ እናንተ በንስሃ ወደ እርሱ በትክክል እንደተመለሳችሁና እንዳልተመለሳችሁ ያውቃል ፡፡ ስለዚህም ደካማነታችሁን ተቀበሉ ፣ ሸክማችሁን የሚሸከምላችሁ አዳኝ እንደሚያስፈልጋችሁ ደግሞም በራሳችሁ ምንም ልታደርጉ እንደማትችሉ አምናችሁ ተቀበሉ ፡፡ እስኪ እራሳችሁን በአበቦች ማሳ ላይ በጀርባችሁ እንደተኛችሁ አድርጋችሁ ሳሉት ፡፡ በየቀኑ በእግዚአብሔር መልካምነት እረፉ እናም በመጨረሻ በህይወት መጨረሻ ላይ ከአዳኛችሁ ጋር ለዘላለም እንደምታርፉ እመኑ ፡፡ ዛሬ ወደ ጌታ ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእርሱ ፊት ጣሉት ፣ እረፍትንም ታገኛላችሁ ፡፡

“ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል ። ወደ ዕረፍቱ የገባ ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና ። እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ ። “

  • ዕብራውያን 4፡9-11

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 46:10 — “ ዕረፉ ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ ። “

ማቴዎስ 11:28–30 — “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ፥ ወደ እኔ ኑ ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና ። “

ዕብራውያን 4:12–13 — “ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና ፥ የሚሠራም ፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል ፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል ፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም ። “