Through The Cross
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዕብራዉያን መፅኀፍ የማይታወቀዉ ፀኀፊ ስለ ኢየሱስ እንደ ሊቀ ካህን በግልፅ ፅፏል ፡፡ ትናትና በዕብራዉያን 2 እንዴት በኢየሱስ ሞት በኩል ሞት ከዚህ በኋላ እንዴት እንደማይይዝ አዉርተናል ፤ በሞቱ በኩል ኢየሱስ የሞት ኃይል የነበረዉን ክፉዉን አጠፋው (ዕብ 2፡ 14) ፡፡ ዕብራዉያን 1 እና 2 ኢየሱስ ከመለዓክት እና ከመለዓክት መልዕክት እንደሚበልጥ ይናገራሉ ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ኢየሱስ ከሙሴ እንደሚበልጥ እናያለን ፤ ሙሴ እና ነቢያቶች ስለሚበልጥ ሰዉ እንዳወሩ አስታዉሱ - ስለ ኢየሱስ አዉርተዋል ፡፡ ኮንስታብል የመጀመሪያዎች ስድስት ቁጥሮች ለምን ኢየሱስ ከሙሴ እንደሚበል እንደሚገልፁ ይናገራል ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (3፡ 1-6)፡ ስለ ሐዋሪያነት በምናስብ ጊዜ የእግዚአብሄርን መንግስት በመጠበቅ የሚመለከተዉን ስለ ቀዳሚዉ ስለ ጳዉሎስ እናስባለን ፤ ስለ ሊቀ ካህን በምናስብ ጊዜ ስለ ሰዎች ሲል መስዋዕትን ስላቀረበው እናስባለን፡፡ አሁን ኢየሱስን እንደ ሐዋሪያ እና እንደ ካህን ሁለቱንም እንድናስብ የተጠየቅን እንሆናለን፤ የኔልሰን ማብራሪያ ሰማያዊ ጥሪያችን “ በክርስቶስ ወደ ድነት መጥሪያ/መሰብሰቢያ “ እንደ ሆነ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን እንደሾመዉ እግዚአብሄር ኢየሱስን ሾመው/መረጠው ፡፡ ዘኁ (12፡ 7) ሙሴን በእግዚአብሄር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ተገልፆአል ፤ ሙሴ የእግዚአብሄርን ቤት በመጠበቅ/በመንከባከብ የታመነ አገልጋይ ነበር - መቅደሱን (ተጨባጭ የሆነዉን ህንፃ) ፡፡ ዕብ (2፡ 17) የኢየሱስን ታማኝነት ይገልፃል ፤ ነገር ግን ሙሴ ለአካላዊዉ መቅደስ እንክብካቤ/ጥንቃቄን ሲያደርግ ኢየሱስ “ ለሰዎች ኃጢዓት ይቅርታን በማድረግ “ የታመነ እና ባለ ምህረት ሊቀ ካህን “ ነበር ፤ ሁለቱም ሰዎች በመለኮታዊ ጥሪአቸዉ መለኮታዊ ስራቸዉን ፈፅመዋል ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር እግዚአብሄር ሕዝቡን በመጠበቅ የታመነ እንዲሆን ኢየሱስን እንደ ሾመዉ ያመለክታል ፤ ለመቅደሱ እንዲጠነቀቅ በዚህ በተለዬ ተግባር ላይ ሙሴን ሾመው ፡፡ በ 1ቆሮ (4፡ 2) ጳዉሎስ አማኞችን እግዚአብሄር እንድናደርገዉ በጠራን ነገር ላይ ታማኝ ኃላፊዎች እንድንሆን አሳሶቦአቸዋል ፤ ነገር ግን ኢየሱስ የቤቱ ሰራተኛ/ገንቢ ስለሆነ የብዙ ክብር ባለቤት/የተገባዉ ነው (ቁጥር 3) ፡፡ ሙሴ የታመነ አገልጋኝ ሲሆን (ቁጥር 5) ኢየሱስ ደግሞ በቤቱ ላይ የታመነ ልጅ ነው (ቁጥር 6) ፡፡ እኛ ያ ቤት ነን ! ከዚህ በኋላ ሞት እንደማያዘን፣ ዘላለማዊ ድነት አለን እንዲሁም በዉስጣችን መንፈስ ቅዱስ አለን በሚሉት እዉነቶች የተያዝን ነን (ዕብ 6፡ 19) ፡፡
የዕብረዉያን ፀሀፊ ሰዎስት ተደራሺያንን ይደርሳል ፤ አንዳንዶቹ አማኞች ነበሩ፣ አንዳንዶች ደግሞ በእዉቀታቸዉ ተገናኝተዉ የነበሩ የማያምኑ ሲሆኑ አንዳንዶች ደግሞ በፍፁም ምንም ግንኙነት ያልነበራቸዉ አላማኞች ነበሩ ፡፡ ፀኀፊው ሁሉም እምነታቸዉን በሕጉ ላይ እና በቤተ መቅደሱ መስዋዕቱ ላይ ማስቀመጥ እንደማይችሉ እንዲረዱ ፈለገ ፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ የተቀደደ ቢሆንም አሁንም አይሁዶች መስዋዕታቸዉን እያቀረቡ ነበር ፡፡ ፀኃፊው ሙሴ ጥሩ ሰዉ እንደ ነበር ተስማማ ነገር ግን ነገሮች እንደተቀየሩ አብራራ ፡፡ አሁን ኢየሱስ ከሙሴ ይበልጣል መጋረጃዉም ተቀዷል ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር የክርስቶስ መስቀል ለእኛ የሰጠንን ነገር ያቀርባል፡
- ከመጋረጃዉ ጀርባ መቅደሱ ዉስጠኛ ክፍል መግባትን (ዕብ 6፡ 19)
- የተሻለ ተስፋ (ዕብ 7፡ 19) እና የተሻለ ኪዳን ስላለ (ዕብ 7፡ 22) ወደ እግዚአብሄር መቅረብ እንችላለን
- የተሸለ ተስፋ/ቃል ኪዳን (ዕብ 8፡ 6)
- የተሸለ መስዋዕትን (ዕብ 9፡ 23)
- የተሻለ እና የማይጠፋ ንብረትን (ዕብ10፡ 34)
- በፍፁም የማይጠፋ ነገር - ለእኛ የተሻለ ስፍራን (ዕብ 11፡ 16)
- የሚበልጥ/የተሻለ ትንሳኤን (11፡ 35)
- የሚበልጥ ስጦታን (ዕብ 11፡ 40)
ይህ ዝርዝር ሰዉ ለምን ክርስቶስን ማመን እንዳለበት ስምንት ምክንያቶችን ይሰጣል ፤ ፀኀፊው አንባቢዎቹ በክርስቶስ መስቀል አግኝተዉት የነበረዉን ነገር በሚገባ ተረድተዉት እንደሆነ እየጠየቀ ነበር ፤ ምን እንደ ቀረበልን ካስተዋልን ይህ ህይወት ቀያሪ ነው ፡፡
ዕብራዉያን (3፡ 7-11)፡ የመጀመሪያዉ ማስጠናቀቂያ በዕብራዉያን ዉስጥ ቃሉን ስለ መታዘዝ/ስለ መስማት እና ዞር ስላለማለት/በሌላ ስላለመሳብ ነበር ፤ ሁለተኛዉ ማስጠንቀቂያ የአለማመን እና የጥርጣሬ አደጋ ነበር ፡፡ ፀኃፊው አባቶቻቸዉ ከብዙ አመታት በፊት በምድረበዳ አድርገዉት እንደ ነበረው ልባቸዉን እንዳያደነድኑ አስጠነቀቃቸው ቁጥር 7-10) ፡፡ “ በልባቸው ወደ ተሳሳተ ነገር የሚሚሄዱ “ ድምፁን ችላ በማለት በራሳቸዉ መንገድ የሚጓዙ ይሆናሉ ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገልንን ነገር እና ወደ ህይወት ተመልሶም እንደ መጣ በምናምን ጊዜ በዉስጣችን መንፈስ ቅዱስ ይኖረናል ፤ አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስራ እኛን መምራት ነው (ሮሜ 8፡ 14) ፡፡
መንፈስ ይመራናል ማለት ሲቀድምልን እና ሲመራን ድምፁን መስማት ወይም ድምፁን መለየት አለብን ማለት ነው ፡፡ ለመስማት እምቢ በማለት እና ድምፁን ባለመታዘዝ መንፈሱን ካሳዘነው በልባችን ወደ ተሳሳተ መንገድ እንሄዳለን ፡፡ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ላይ ስላመፁ ለ40 አመታት በምድረበዳ ተንከራተቱ በፍፁምም ተስፋይቱ ምድር አልገቡም (ቁጥር 11) ፤ ከአባቶቻችን ስህተት መማር እንችላለን ፡፡ መንፈስ ቅዱስን በፍፁም ማሳዘን ወይም ዛሬም አማኞችን እንደማይመራ መናገር የለብንም ፡፡
ዕብራዉያን (3፡ 12-14)፡ ማስጠንቀቂያዉ ቀጠለ “ …..ተጠንቀቁ “ (ቁጥር 12) ፡፡ በእግዚአብሄር ካለማመን እና ከመራቅ ይልቅ ሁልጊዜ እርስ በእርስ ልንበረታታ ይገባንል (13) ፤ በእያንዳንዱ ቀን ሰዉን ለማበረታታት የምናስብ/የተዘጋጀን ነን ? እርስ በእርስ በመበረታታት ማንም ከዉስጣችን “ በኃጢዓት መታለል እልከኛ አይሆንም “ (ቁጥር 13) ፡፡
ዕብራዉያን (3፡ 15-19)፡ ማስጠንቀቂያዉ የተደገመ ነው፡ “ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት በማስመረር እንደ ሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ “ (ቁጥር 15) ፡፡ እስራኤላዊያን ስላመፁ ባለማመናቸዉ ምክንያት አልገቡም (ቁጥር 19) ፡፡ የዚህ ምዕራፍ መልዕክት ለምን አስፈላጊ ነው ? ምክንያቱም ኢየሱስ ከሙሴ ስለሚበልጥ ነው ፡፡ ሙሴ መልስ አልነበረም ነገር ግን ኢየሱስ መልስ ነው ፡፡
መደምደሚያ
በመፅኀፉ ዉስጥ የዕብራዉያን ፀሀፊ ያለማቋረጥ ኢየሱስ ካወራዉ ከማንኛዉም ነገር ይበልጣል አለ - ከመለዓክት፣ ከመለዓክት መልዕክት እና ከታላቁ አገልጋይ ከሙሴም እንኳን ይበልጣል አለ ፡፡
Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Hebrews, p. 60; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/hebrews.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Hebrews (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1639.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1843.
MacArthur, p. 1843.
Constable, p. 65.
ጥያቄዎች
-
ዕብ (3፡ 5-6) “ ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረዉ ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበር ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው ፤ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን “ ይላል ፡፡ ሙሴ መጉዞው እስከመጨረሻዉ የጸናዉ እንዴት ነበር (ዘዳ 3፡ 27, 4፡ 21, 32፡ 52) ? እንዴት እስከ መጨረሻው ፀንታችሁ ትቆያላችሁ ?
-
ሙሴ ለመሲሁ እንዴት መንገድን አዘጋጀ (ዘዳ 18፡ 15, 18, 31፡ 2-3) ? እግዚአብሄር ወደ ኢየሱስ መንገድን እንዲጠቁሙ የተጠቀመባቸዉን አንዳንድ የብሉይ ኪዳን ነቢያቶችን ጥቀሱ ፤ ይህን እንዴት አደረጉ ?
-
ልክ እንደ እስራኤላዊያን “ በምድረባ እየተንከራተታችሁ እንደ ነበር “ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር በሆነ ምክንያት ያላ አላማ እንድትንከራተቱ ለምን እንደሚፈቅድ ምን ታስባላችሁ ?
-
ዕብራዉያን 3 ሁለት ጊዜ “ እስከ መጨረሻ ብንፀና “ የሚለዉን ለምን እንደደገመዉ ምን ታስባላችሁ (ዕብ 3፡ 6, 14) ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተመሳሳይ ቃል ታነባላችሁ (ማቴ 24፡ 13, ማር 13፡ 13) ? ለእናንተ ይህ ምን ማለት ነው ?
-
በዕብራዉያን 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 3:13
“But encourage each other daily, while it is still called today, so that none of you is hardened by sin’s deception.”
የዕብራውያን ጸሀፊ ለተደራሲያኑ የኢየሱስ የመስቀል ሞት ያስገኛቸውን በረከቶች አስረግጦ ይነግራቸዋል ፡፡ በዚህ ዓለም አሳቹ አማኞች እንኳ ሳይቀሩ አንድጠራጠሩ ፣ እንድስቱና ከኢየሱስ ፊታቸውን እንድመልሱ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ ስለዚህም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳትሆኑ እርስ በእርሳችሁ ተመካከሩ ፡፡ አስታውሱ ፣ ኢየሱስ ከሙሴ ይልቃል ፡፡ ኢየሱስ የተሻለ ተስፋን ፣ የተሻለ ኪዳንን ፣ የተሻለ መስዋዕትን ፣ የተሻለ እርዳታንና የተሻለ ዘላለማዊ ቤትን ሰጥቷል ፡፡ በምትደፍሩበትና በምትመኩበት በኢየሱስ ዘንድ በሆነው ተስፋ ላይ መጣበቅ አለባችሁ ፡፡
እግዚአብሔር አማኞች በየቀኑ እርስ በእርሳቸው እንድመካከሩ ያዛል ፡፡ እርሱ ልክ እርሱ እንደወደዳችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ እንድትዋደዱ ያዛል ፡፡ ነገር ግን ምናልባት “ እንዴት ነው አንድን ሰው የምመክረው ? “ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል ፡፡ ለመኖር ለመቀጠል ድፍረትን ብርታትን እንድያገኙ አግዟቸው ፡፡ ምናልባት ይህ ምሳ ሰዓት ላይ እነርሱን ማዳመጥ ፣ ለእነርሱ የእግዚአብሔርን ኪዳን ማስታወስ ፣ ከእነርሱ ጋር አብሮ መጸለይ ፣ በእነርሱ ላይ የምትናገሩትን የምክር ቃል እንድሰጣችሁ እግዚአብሔርን መጠየቅ ወይም ደግሞ ከእነርሱ ጋር አብሮ ልብስ ማጠብ ፣ ሳር ማጨድ ወይም ለእነርሱ ምግብን መስጠት ሊሆን ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን የፍቅር ተግባራት በእምነት እርስ በእርሳችሁ እንድትበረታቱ ለማድረግና ደግሞም የስህተትን ትምህርትና በዓለም ያለውን ክፉ መንገድ ለይታችሁ እንድታውቁ እናንተን ለመርዳት ይጠቀምበታል ፡፡ ዛሬ በኢየሱስ ዘንድ በሚገኘው ተስፋ እንድጸና ማንን ነው ልትመክሩ የምትችሉት ?
“ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ ፡፡ “
- ዕብራውያን 3፡13
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ተሰሎንቄ 5:11 — “ ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው ። “
ዕብራውያን 3:6 — “ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን ። “
ዕብራውያን 10:23–25 — “ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ፤ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው ፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ። ”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።