General Letters Hebrews

Don't Drift Away

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 654 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በዕብራዉያን መፅሀፍት አፃፃፍ ላይ እና እንዲሁም ደግሞ በምዕራፍ 1 ላይ የተመለከትን በት ክፍለ ጊዜ ነበር ፤ ብዙ ነበር ፡፡ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር የዕብራዉያን መፅኀፍትበመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ወሳኝ/የሚበሉ/የበሰሉ ከሆኑት መፅኀፍ ዉስጥ አንዱ መፅኀፍ መሆኑን ነው ፤ ዕብራዉያንን ከብሉይ ኪዳን ጋር እና ኢየሱስ ህጉን ሊያጠፋ ሳይሆን ሊፈፅፍ ከመጣበት ከማቴ (5፡ 17) የሚያስተሳስሩትን ሰባት የብሉይ ኪዳን ንግግሮችን በያዘዉ በምዕራፍ 1 በቁጥር 4-14 እንኳን አላገኘንም ፡፡

ትምህርት

ዕብራዉያን (2፡ 1)፡ ማክአርቱር በዕብራዉያን ዉስጥ ስድስት ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ ፅሁፎችን አስቀምጧል ፡፡ የመጀመሪያው በምዕራፍ 2 የሚገኝ ሲሆንሰዎቹን ስምተዉት ስለ ነበረዉ ነገር የበለጠ ጥኩረት በመስጠት ወደ ሌላ የተሳቡ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል (ቁጥር 1-4) ፡፡ የዕብራዉያን 2 መልዕክት አይናችሁን በጌታ ላይ እንድታደርጉ ነው ፡፡ ሌሎቹ ማስጠንቀቂያዎች በዕብ (3፡ 1- 4፡ 6, 5፡ 11- 6፡ 20, 10፡ 19-39, 12፡ 15-17 እና 12፡ 25-29) ላይ የሚገኙ ናቸው ፡፡

ፀኀፊው ቀድመዉ ሰምተዉት ለነበረዉ ነገር የበለጠ ትኩረት የመስጠት አስፈላጊነትን አብራርቷል ፡፡ እምነት ቃሉን ከመስማት እና ከመታዘዝ ይመጣል ፤ ለእግዚአብሄር ቃል ትኩረትን መስጠት ከእርሱ የተሳብን እንዳንሆን ይጠበቀናል ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ አንዳንዶቻችን በእግዚአብሄር ቃል ላይ ስላልሆንን የተሳብን/ፈቀቅ ያልን መሆናችንን እንኳን አናዉቅም ፤ በእርግጥ አብዛኞቹ አሜሪካዊያን መፅኀፍ ቅዱስ ቢኖራቸዉም አያነቡትም ፡፡ ፀኃፊው “ መሳብ “ የሚለዉን የባህሪይ ቃል ተጠቅሟል ፡፡ ማክአርቱር “ ማስጠንቀቂያው በድነት ወደብ አጠገብ ብቻ ላይ ላለማለፍ የተጠነቀቀ በመሆን ራስን በወንጌል እዉነት ላይ ስለ መጠበቅ ነው ፤ የቀረቡት ትኩረቶች ለእነዚህ በክርስቲያን እምነት ላይ በጣም ከባድ በሆኑት ነገሮች ላይ ይከፈላሉ ፤ አንባቢዎቹ ለግደሌሽነት ባላቸዉ ዝንባሌአቸው ኑሮአቸዉን የጠፋ ለማድረግ አደጋ ላይ ናቸው “ በማለት ይናገራል ፡፡

ሮበርት ሮቢሰን በጆርጅ ዋይትፊልድ ሰባኪነት በኩል ክርስቶስን ወደ ማወቅ በመምጣት “ ወደ በረከቶች ሁሉ ራስ ኑ “ የሚል ግጥምን/ዜማን ፃፈ ፤ ይሁን እንጂ ሮቢሰን ከጌታና መንፈሳዊ ከሆኑ ነገሮች ተሳበ/ዞር አለ ፡፡ በጉዞ ላይ የእርሱን ግጥም እያነበበች የነበረች አንድ ወጣት ሴትን አገኘ ስለግጥሙም ምን እንደሚያስብ ጠየቀችዉ ፤ ማን እንደ ነበርና ከእግዚአብሄር ዞር/ፈቅቅ ብሎ እንደ ነበር አመነ ፤ “ የእግዚአብሄር የምህረት ወንዝ “ አሁንም እየፈሰሰ እንደ ነበርና አሁንም ለእርሱ ምህረት ማግኘት እንደሚችል አሳሰበችዉ ፡፡ በእርሷ ማበረታታት እና በራሱ ቃል ሮቢሰን ወደ እግዚአብሄር በመመለስ መንገዱን ማግየት ይችል ነበር ፤ ሁልጊዜ እግዚአብሄር ከእርሱ ርቀዉ የነበሩትን ምንም ያክል ከእርሱ ቢርቁ ወደ እርሱ የሚመለሱትን ይቀበላቸዋል ፡፡

ዕብራዉያን (2፡ 2-4)፡ “ የሚበልጥ “ የሚለዉ ቋንቋ ወደ ቁጥር (2-3) የተጠቀሰ ነው ፡፡ በመለዓክት ተደርሶ/ተሰጥቶ የነበረዉ መልዕክት አስፈላጊ ከነበርና ሕግ ከመሆኑ እና ለሚጥሰዉ ቅጣትን ከማማጣቱ የተነሳ ሕጋዉ አሰገዳጅ/የጸና ነበር (ዘዳ 33፡ 2) ፤ ነገር ግን ክርስቶስ የድነትን መልዕክት የሰበከ ብቸኛዉ ይሆናል ለማይቀበሉትም ቅጣቱ የበለጠ/የከፋ ይሆናል ፡፡ ማክአርቱር “ ታላቅ/የሚበልጠዉ ስጦታ ላልተቀበሉት ወይም ለማይታዘዙት የሚበልጥ ቅጣት እንዳለው “ ይናገራል ፡፡ (ዕብ 10፡ 29, ሉቃ 12፡ 47) እግዚአብሄርም በምልክት እና ኢየሱስ ባደረጋቸዉ ተዓምራቶች ስለ ኢየሱስ መስክሯል (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር “ በኢየሱስ እና በሐዋሪያቱ የተገለጠው መለኮታዊ ኃይል የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ መለኮታዊ ማረጋገጫዎች እንደነበሩ “ ይናገራል ፡፡

ዕብራዉያን (2፡ 5-9)፡ “ አለም “ የሚለዉ ቃል የሚኖርባትን ምድር ያመለክታል በተጨማሪም ደግሞ የሺዉ አመት አለም ፤ መለዓክት በሺዉ አመት አለም ላይ አይቀመጡ - ኢየሱስ እንጂ (ቁጥር 5) ፡፡ ቁጥር (6-8) ከመዝ (8፡ 4-6) የሆኑናበምድር ላይ እግዚአብሄር ለሰዉ ልጅ ስለሰጠው ተግባር ይናገራሉ - ለጥቂት ጊዜ ከመለዓክት ትንሽ ዝቅ አሳነሳቸው ፤ ይሁን እንጂ ከሰዉ ኃጢዓት የተነሳ እግዚአብሄር እንድናደርግ የተገባንን ሁሉንም ነገር በማድረግ መመላለስ አልቻልንም ፡፡ በቁጥር 9 መሰረት ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ከመለዓክት ትንሽ ዝቅ ተደርጎ ስለ ነበር በመስቀል ሞቱ በኩል “ ለሁሉም ሰዉ ሞትን መቅመስ ቻለ “ ፡፡ ኢየሱስ ለዚያ ጊዜ ራሱን ከመለዓክት በታች አደረገ ፤ ከሞቱም የተነሳ በክብር በመክበር ከፍ አለ (ፊል 2፡ 8-9) ፡፡

ዕብራዉያን (2፡ 10-14)፡ በቁጥር 10 ፀኃፊው በመከራችን ወደ ክብር እንደምንመጣ አብራርቷል - “ የብዙ ክብር ልጆች ነን “ ፡፡ ማክአርቱር “ ያለ ክርስቶስ የሆነ ዉርደት እና መከራ ቤዛነትን ሊኖረዉ አይችልም ፤ ያለ ቤዛነት መክበር ሊኖር እንደማይችል “ ፅፏል ፡፡ የሚያፀድቀዉ ኢየሱስ እና የፀደቁት አማኞች አንድ አባት አላቸው “ ኢየሱስም ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸዉ አያፍርም “ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ይህ ሁሉ ቀላል ነዉ ምክንያቱም ኢየሱስ የድነታችን እና የፅድቃችን ምንጭ ስለሆነ ፡፡

ኢየሱስ እንደ ሊቀ ካህናችን ያገለግላል ፡፡ በቁጥር 13 ፀኃፊው በሞቱ ሰይጣንን ማጥፋት እንዲችል ክርስቶስ በስጋና በደም በኩል ሰዋዊነትን እንዲጋራ እንደ ተላከ ለማብራራት ኢሳ (8፡ 18) ጠቅሷል (ቁጥር 14) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ፡

“ ሰይጣን ሰዎች ኃጢዓት እንዲያደርጉ ይፈትናል ከዚያምበእግዚአብሄር ላይ አምፃችኋል በማለት ይከስሳል (ዘፍጥረት 3, ኢዮብ 1) ፤ ወደ ኃጢዓት በማስገባት ሰይጣን ሰዎችን ስለ ኃጢዓታቸዉ እንዲቀጡ ወደ ሞት ይመራቸዋል (ሮሜ 5፡ 12) ፤ ሰይጣን አሁንም የሚሰራ ነው ነገር ግን በሞት ላይ ኃይሉ ከእርሱ ተወስዷል (1ጴጥ 5፡ 8) ፡፡ የክርስቶስ ሞት የኃጢዓትን ቅጣት ፈፅሞታል…. የሰይጣን ፍርድ በመስቀል ምላሹ የተሰጠ ነበር ነገር ግን ፍርዱ ለሚመጣዉ ጊዜ ተቀምጧል (1ቆሮ 15፡ 54-57, ራዕ 20፡ 10) “ ይገልፃል ፡፡

ድልማድረጉ ቀድሞዉኑ ተሰጥቷል ነገር ግን የሰይጣን ፍርድ እና ቅጣት በኋላ ይመጣል ፡፡

ዕብራዉያን (2፡ 15-18)፡ ቁጥር 15 በክርስቶስ የሆነዉ ድነት ከባርነት ቀንበር እና ከሞት ነፃ እንዳወጣን ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሄርን ለማገልገል በሰዉ መልክ በመዉሰድ ሊቀ ካህናችን ለመሆን መጣ (ቁጥር 16) ፤ እንደ ሰው የሰዉን ልጅ ሁሉ ኃጢዓት በመዉሰድ ዋጋዉን ራሱ ከፈለ (ቁጥር 17) ፡፡ በመከራ ስለተፈተነ በምንፈተን እና በምንቸገር ጊዜ ሊረዳን ይችላል (ቁጥር 18) ፡፡

መደምደሚያ

የባርነትን ቀንበር ክብደትን የምታዉቁት ከሆነ አትጠብቁ - በእምነት ወደ ኢየሱስ ተመለሱ (ሮሜ 5፡ 8, 10፡ 9) ፡፡ ኢየሱስ ስለ እናንተ ሁሉንም ነገር ስለሚረዳ ወደ እርሱ ለመሄድ አትዘግዩ/አትጠብቁ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1839.

  2. MacArthur, p, 1838.

  3. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: Hebrews (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), pp. 282–283.

  4. MacArthur, p. 1838.

  5. MacArthur, pp. 1838–1839.

  6. MacArthur, p. 1840.

  7. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: Hebrews (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), pp. 1638–1639.

ጥያቄዎች

  1. አማኞች የሰሙት ትኩረት ሊሰጡት እና ሊይዙት የሚገባዉ መልዕክት ምንድን ነው (1ቆሮ 15፡ 1-4) ? በዚህ መልዕክት ላይ አጥብቀን መያዝ ያለብን ለምንድን ነው ? (ሮሜ 12፡ 2)
  2. የዚህ ታላቅ ድነት ጅማሮ መቼ ነበር ? እግዚአብሄር ቃሉን ለማረጋገጥ ሌላ ነገር እንዴት አደረገ ?
  3. እግዚአብሄር ለአጭር ጊዜ ኢየሱስን ከመለዓክት ያነሰ ያደረገበት ምክንያት ምን ነበር (ዕብ 2፡ 7-9) ? መጀመሪያ/ቀድሞ እንደ አስተዳዳሪ በምድር ላይ የተቀመጠው ማን ነበር ? (ዘፍ 1፡ 26-28)
  4. ኢየሱስ በመለኮታዊዉ ተፈጥሮዉ ቀድሞዉኑ ፍፁም ነበር ፤ በሰዉ ተፈጥሮዉ እንዴት ፍፁም ሆነ (ፊል 2፡ 8, ዕብ 2፡ 9-10, 5፡ 8-9) ? እንደ አማኝ ለእኛ ጥቅሙ ምን ነበር ? (ዕብ 2፡ 18)
  5. ኢየሱስ በሁሉም መንገድ እኛን የመምሰለ መሆን ለምን አስፈለገው (ዕብ 2፡ 17)? ይህን እዉነት ማወቅ ለእናንተ እንዴት ምቾት ይኖረዋል ?
  6. በዕብራዉያን 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Hebrews 2:18

“For since He Himself was tested and has suffered, He is able to help those who are tested.”

ኢየሱስ ስጋና ደም ሆኖ በወንድሞቹ መካከል ኖረ ፡፡ ኢየሱስ በመከራና በፈተና ተካፈለ ደግሞም በሞትም እንዲሁ ፡፡ ሆኖም ግን የኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ የሞት ኃይል የነበረውን ዲያብሎስን ሻረ ፡፡ ሞት በኢየሱስ አማካኝነት ተሸነፈ ፡፡ በርግጥም ኢየሱስ ለኃጢአት ባሪያ ለነበሩት ነጻነትን አድርጓል ፡፡ ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም ፣ ኢየሱስ ተፈትኖና መከራን ተቀብሎ ስለነበር አሁን ደግሞ እርሱ እናንተን በፈተናችሁ ሊረዳችሁ ይችላል ፡፡ ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነበር ደግሞም እንዲሁ ሩህሩህም ነበር ፡፡

ፈተና እና መከራ ሁሉንም ሰው የሚያጋጥሙ የህይወት ትልቅ አካል ናቸው ፡፡ ሆኖም ግን እናንተ አሁንም በዚህ ዘመን ለሚያጋጥሟችሁ ተግዳሮቶች ፍጹም ዝግጁ አይደላችሁም ፡፡ ኢየሱስን ሰዎች አሾፉበት ፣ ተፉበት እርሱም በአካሉ አሰቃቂ ሞትን ሞተ ፡፡ በርግጥም ኢየሱስ በፈተናና በመከራ ውስጥ ሳላችሁ የሚሰማችሁን ህመም ያውቃል ፡፡ በስሜት ፣ በአካል ወይም በመንፈስ ደረጃ ያለውን ጉዳታችሁን ኢየሱስ ያያል ፣ ሊያግዛችሁም ይችላል ፡፡ ይህን ተስፋ ሰምታችኋልን ? ኢየሱስ ሊረዳችሁ ይችላል ፡፡ አዎን በመከራ ሰዓት እርዳታ ያስፈልጋችኋል ፡፡ ይህንን ብቻችሁን ለማድረግ አልተፈጠራችሁም ፡፡ ኢየሱስ ሊረዳችሁ ይችላል ፡፡ ስለዚህም የእርሱን መልካምነት ለመቀበል እጆቻችሁን ዘርጉ ፤ የእርሱን ተስፋ ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ ፣ መገኘቱም በልባችሁ ይሞላ ዘንድ ልባችሁን ክፈቱ ፡፡ ትዕቢታችሁን ወደ ጎን በሉትና በመከራ ውስጥ ሳላችሁ የእርሱን እርዳታ ተቀበሉ ፡፡ ብቻችሁን አይደላችሁም ፡፡

“ እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና ። “

  • ዕብራውያን 2፡18

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 121:1–2 — “ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ። “

ዕብራውያን 2:14–15 — “ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር ፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው ፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ። “

1ኛ ጴጥሮስ 5:10 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል ። “