Jesus Is Greater Than The Angels
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ High Priest Hebrews 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ አዲስ የመፅኀፍ ክፍል እንጀምራለን ፡፡ ይህ ጊዜ በአጠቃላይ መልዕክቶች ላይ ነን፣ በአዲስ ኪዳን ስምንት መልዕክቶች በጳዉሎስ ያልተፃፉ ናቸው - ዕብራዉያን፣ ያዕቆብ፣ 1 እና 2 ጴጥሮስ፣ 1, 2 እና 3 ዮሐንስ እና ይሁዳ ፡፡ ከዚህ ክፍል በኋላ ወደ ብሉይ ኪዳን ትንንንሽ ስለ ተነበዩት ነቢያቶች ላይ ተመልሰን እንሄዳለን ከዚያም ራዕይን ለማጥናት ወደ አዲስ ኪዳን እንመለሳለን ፡፡ የዕብራዉያን መፅሀፍት በትክክል የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን ቅልቅል ነው (ማቴ 5፡ 17) ፡፡
በዕብራዉያን መፅኀፍ ለኢየሱስ ቃላችን/ሀረጋችን ሊቀ ቃህኑ የሚል ነው ፡፡ በብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህኑ/ታላቁ ካህን ለሰዉ ለመማለድ በአመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስፍራ የሚገባዉ ነበር ፤ በእግዚአብሄር እና በሰዉ መካከል አስታራቂ ነበር ፡፡ ኢየሱስ በዕብ (4፡ 14) የተገለፀዉ መካከለኛ ሊቀ ካህን ነው (ዕብ 5፡ 10, 10፡ 19-21) ፡፡ በኢየሱስ ስጋ እግዚአብሄርን የማግኘት እድል አለን ፤ ኢየሱስ ብቸኛዉ መቅረቢያ መንገድ ነው (ዮሐ 14፡ 6) ፡፡
የዕብራዉያን ፀኃፊ አይታወቅም ፤ በቀጥታ በአፃፃፉ ዘዴ/ሁኔታ ማንም የአዲስ ኪዳን ፀሃፊ መፅኀፉን የፃፈዉ አይመስልም ፡፡ ከመጀመሪያዉ ርዕሱ “ ለዕብራዉያን “ ነበር ፤ በዕብ (2፡ 3) ፀኃፊው መጀመሪያ የጌታን ንግግርን ከሰሙት ጋር ራሱን (ራሷን) አካትቷል ፤ ያ ንግግር እንደ ፀሀፊ ጳዉሎስን አያካትተዉም ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ተሳትፎበት ነበር ማለት ተገቢ/ትክክል ነው ፡፡
ምናልባትም መፅሀፉ ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ ከመፍረሱ በፊት ከክርስቶስ ሞት (67-69) በኋላ የተፃፈ ነበር ፡፡ ሌሎች የሚታወቁ ቀናቶች ይህ የተፃፈበትን ቀን ለመወሰን ይረዳሉ ፤ በሮም ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ሞት 32 በኋል ተመስርታ ነበር የኢየሩሳልም ሸንጎ/ምክር ቤት ከክርስቶስ ሞት 50 በኋላ ተካሄደ ፡፡ በዕብ (13፡ 23) መሰረት ጢሞቴዎስ ከሮም ከእስር ቤት ተለቆ ነበር መከራም እየሆነ ነበር (ዕብ 12፡ 4) ፡፡ የዕብራዉያን መልዕክት ተቀባዮች ከስደቱ የተነሳ በእምነታቸዉ ፀንተዉ ለመቀመጥ እትግል ላይ ነበሩ ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ ታላላቅ ነቢያቶች ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት የመጀመሪያዉ ቤተ መቅደስ ከመፍረሱ በፊት በቅርብ የተፃፉ ሲሆኑ የዕብራዉያን መፅኀፍ ድግሞ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስከመዉደቁ በፊት የተፃፈ ነበር ፡፡
የዕብራዊያን ትክክለኞቹ ተደራሾች የተሰሩት፡ 1) ከአማኞች፣ 2) በሀሰባቸዉ ወንጌልን አምነዉ የነበሩ አላማኞች እና 3) በወንጌል ተስበዉ የነበሩ ነገር ግን ለክርስቶስ መሰጠትን አድርገዉ ያልነበሩ አላማኞች ነበሩ ፡፡
በመፅኀፉዉስጥአንዱየጋራየሆነዉጭብጥየኢየሱስየበላይነትነው፡
- ኢየሱስ ከመለዓክት የተሸለ/የበለጠ/የላቀ ነው (ዕብ 1፡ 4-14) ፡፡
- የኢየሱስ መልዕክት ከመለዓክት መልዕክት የሚበልጥ/የላቀ ነው (ዕብራዉያን 2) ፡፡
- ኢየሱስ ከሙሴ የሚበልጥ ነው (ዕብራዉያን 3) ፡፡
- ኢየሱስ ከታላቁ ካህን ከአሮን የሚበልጥ/የላቀ ነው (ዕብራዉያን 4) ፡፡
- ኢየሱስ ከመልከፀዲቅ የላቀ/የበለጠ ነው (ዕብራዊያን 5) ፡፡
- ኢየሱስ ከሌዋዊያን ካህናቶች የተሻለ ነው (ዕብራዉያን 7) ፡፡
ትምህርት
ዕብራዉያን (1፡ 1-3)፡ ባለፉት ዘመናት እግዚአብሄር በተለያዬ መንገድ እና ጊዜያት በነቢያት በኩል ተናግሯል (ቁጥር 1) ፤ ያም ከ1,800 አመታት በላይ ነበር ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር “ በራዕይ፣ በምልክት እና በግጥም እና በዝማሬ በሁለቱም በተፃፈ በምሳሌ እንደተናገረና…. ሁልጊዜ የእግዚአብሄር መገለጥ ሕዝቦቹ እንዲያዉቁት ለሚፈለጉት እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ ነገር ግን አሁን (በእነዚህ መጨረሻ ቀናቶች) እግዚአብሄር በልጁ በኩል ይናገራል (ቁጥር 2) ፡፡ በቁጥር 2-3 ፀኀፊዉ ሰባት የኢየሱስን መገለጫዎችን ተጠቅሟል፡
ኢየሱስ “ የእግዚአብሄር የሁሉም ነገር ወራሽ ነው “ ፤ በዚያም ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ቆጥሮታል (ቁጥር 2) ፡፡
እግዚአብሄር “ አለምን/ፍጥረትን በእርሱ ሰራ “ (ቁጥር 2, ዮሐ 1፡ 3, ቆላ 1፡ 16) ፤ ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ፡፡
ኢየሱስ “ የእግዚአብሄር ክብር ነፀብራቅ ነው “ (ቁጥር 3) ፤ ኢየሱስ መገለጥ ነው ፡፡
ኢየሱስ “ የተፈጥሮዉ ትክክለኛ መገለጫ ነው “ (ቁጥር 3, ዮሐ 14፡ 9) ፤ ኢየሱስ አምላክ ነው ፡፡
ኢየሱስ “ ሁሉንም ነገር በስልጣን ቃሉ የሚደግፍ ነው “ (ቁጥር 3, ቆላ 1፡ 7)) ፤ ኢየሱስ ደጋፊ/ የሚያቆም ነው ፡፡
ኢየሱስ “ ለሁሉም ሰው ከኃጢዓት መንፃትን ሰጥቷል “ (ቁጥር 3, ቲቶ 2፡ 14) ፤ ኢየሱስ አዳኝ ነው ፡፡
ኢየሱስ “ በሰማያት በግርማዉ በቀኙ ተቀምጧል “ (ቁጥር 3) ፤ ኢየሱስ የሚበልጥ/የላቀ ጌታ ነው ፡፡
ዕብራዉያን (1፡ 2-14)፡ በቁጥር (4-14) ፀኃፊዉ ኢየሱስን ከመለዓክት ጋር አወዳደረው ፤ ኢየሱስ ከመለዓክት የሚበልጥ ደረጃ እንዳለዉ የተነገረ/የታወጀ ነው ፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሄር እንደ ልጁ የጠራዉ ብቸኛ ነው (ቁጥር 5) ፡፡ እግዚአብሄር መለዓክት ኢየሱስን ይሰግዱለታል/ያመልኩታል አለ (ቁጥር 6) ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ዙፋን የተሰጠው ብቸኛ ነው (ቁጥር 8) ፡፡ መለዓክት ለሌሎች ድነትን የሚሰብኩትን ለመርዳት እንደ መናፍስት የሚያገለግሉ ናቸው (ቁጥር 14) ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ ከማንኛዉም መለዓክት በጣም የሚበልጥ/በጣም የከበረ/በጣም የላቀ ነው ፤ መለዓክት እርሱን ያገለግሉታል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1832.
MacArthur, p. 1832.
MacArthur, p. 1835.
ጥያቄዎች
-
በዕብ (1፡ 1) መሰረት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የተናገረባቸዉ የተለያዩ መንገዶች ምን ነበሩ (ዘኁ 12፡ 6, ኤር 1፡ 9, ሕዝ 17፡ 1-2) ? በእነዚህ በመጨረሻ ቀናት እግዚአብሄር ለእኛ እንዴት ተናገረን ?
-
በዕብራዉያን 1 የሚበልጠዉ ኢየሱስ ማነው (ዕብ 1፡ 1-4) ? እንዴት ነዉ የሚበልጠው ?
-
ከአባቱ ከአብ ጋር መለዓክት በፍፁም ሊኖራቸዉ የማይችለዉ ኢየሱስ ያለዉ የተለዩ አንዳንድ የግንኙነት መገለጫዎች ምንድን ናቸው ? (ዕብ 1፡ 5-13)
-
በዕብ (1፡ 8) ፀኃፊዉ እንደ አምላክ የደረሰው ማንን ነበር ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስራ አምላክነቱ የተጠቀሰ ነው ? (ኤር 23፡ 5-6, ዮሐ 5፡ 18, ቲቶ 2፡ 13, 1ዮሐ 5፡ 20)
-
በዕብ (1፡ 14) እንደ ተጠቀሰዉ የመለዓክት አንዱ ስራ ምንድን ነው ?
-
በዕብራዉያን 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Hebrews 1:3
“The Son is the radiance of God’s glory and the exact expression of His nature, sustaining all things by His powerful word. After making purification for sins,He sat down at the right hand of the Majesty on high.”
እግዚአብሔር ኢየሱስን ሁሉን ወራሽ አደረገው ፡፡ የአለም ምድር ፈጣሪ የሆነው ኢየሱስ በምድር ላይ የሰውን ስጋ የለበሰ የአምላክ አምሳል ሆኖ ኖረ ፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ክብር አያንጸባረቀ በስልጣን ቃሉም ሁሉን ይደግፋል ፡፡ ኢየሱስ እናንተን ከኋጢአታችሁ ለማንጻት ሞተ ፡፡ ከዚያም ከሞት ተነሳ በሰማይም በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ አብዝቶ ከመላዕክቱ ይበልጣል ፡፡
አዎን ! ኢየሱስ ሁሉን አንድ አድርጎ ይዟል ፡፡ እርሱ ሁሉን ነገር በስልጣን ቃሉ አጽንቷል ፡፡ እርሱ ስለ ህይወታችሁ እያንዳንዷን ነገር ያውቃል ፣ የተሸከማችሁትን ሸክም እንኳ ሳይቀር ያውቃል ፡፡ ኢየሱስ እንደ ብርቱ ፣ ኃያል ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ ሆኖ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሳላ እንኳ አሁንም እንድታወሩት ፣ ከእርሱ ጋር አብራችሁ እንድትቀመጡና የልባችሁን አሳብ እንድታካፍሉት ይፈልጋል ፡፡ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጅ ለሆነው ለሚጠብቃችሁ ለኢየሱስ ምስጋናን ስጡ ፡፡ አይኖቻችሁን ጨፍናችሁ በጌታ ላይ ተደገፉ ፡፡ ኢየሱስን በህይወታችሁ ልክ እንደ ማጠበቂያ አድርጋችሁ አስቡት ማለትም ፡- ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ የሚይዝ ፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ እንዳለና ከሁሉም ነገር በላይ እንደሆነ እመኑ ፡፡ አትወድቁም ፡፡ እርሱ ይዟችኋል ፡፡ እርሱ በደስታ ቅባት ይቀባችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ደካማውን ደግሞም የዛለውን ያበረታል ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር ኃያል አምላክ ነውና ! የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ እናንተ በእርሱ አይን ውዶች ናችሁ ፡፡
“ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ “
- ዕብራውያን 1፡3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 54:4 — “ እነሆ ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል ፥ ጌታዬም ለነፍሴ ደጋፊዋ ነው ። “
ቆላስያስ 1:17 — “ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል ። “
ዕብራውያን 1:4 — “ ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።